12/06/2026
ቀን 05/10/2018ዓ.ም(ጌጃ)
በሀዲያ ዞን አመካ ወረዳ በአረንጓዴ ዐሻራ 4.79 ሚሊየን ችግኞች ይተከላሉ፤
በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐግርብ 4.79 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ዝግጅት እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡
የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ጡምዶዕሎ፣ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግርብ ከ4.79 ሚሊየን በላይ ችግኝ ለመትከል ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ ኢኒሼቲቭ በስፋት እየተሰራ ነው ያሉት ኃላፊው፤ በወረዳው በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከሚተከሉ ችግኞች መካከል ከ50% በላይ ፍራፍሬ ነው ብለዋል፡፡
በበልግ ወቅትም ችግኝ መተከሉን አስታውሰው፤ ቀሪው ደግሞ ሀምሌ ላይ በክረምት የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር እንደሚተከል ገልጸዋል፡፡
አመካ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት!