በሀዲያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Hossana
  • በሀዲያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት

በሀዲያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ ብልጽግና  ፓርቲ ጽ/ቤት አንሌሞ ወረዳ ብልጽግና ፓርት /ቅ/ ጽ/ቤት

13/09/2026
13/09/2026
በሀዲያ ዞን በአንሌሞ ወረዳ የ2019 ዓ.ም የያሆዴ በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ውይይት መድረክ ተካሄደፎንቆ:-መስከረም 2/2019( የአንሌሞ ወረዳ ብ/ፓ/ኮሙኒኬሺን)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ...
12/09/2026

በሀዲያ ዞን በአንሌሞ ወረዳ የ2019 ዓ.ም የያሆዴ በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ውይይት መድረክ ተካሄደ

ፎንቆ:-መስከረም 2/2019( የአንሌሞ ወረዳ ብ/ፓ/ኮሙኒኬሺን)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክል በሀድያ ዞን በአንሌሞ ወረዳ በአጫሞ ከተማ በአቶ ታመነ ተፈራ በራፍ የ2019 ዓ.ም. ወረዳዊ የሀድያ ዘመን መለወጫ ያሆዴ በዓል አከባበር የቅድመ ዝግጅት ውይይት መድረክ ተካሂዷል።

የያሆዴ በዓሉን የሀዲያን ባህልና እሴት በሚያጎለ መልኩ ለማክበር የአከባቢው የባህል ሽማግሌዎች፣የወረዳው አስተባባሪ አካላት፣ የአጫሞ ክላስተር ቀበሌያት አመራሮችና የአከባቢው ተወላጅ የወረዳ አመራሮች እንድሁም የባ/ቱ/ጽ/ቤት ኃላፊና ባለሙያዎች በተገኙበት በዓሉን በተሻለና በደመቀ ሁኔታ ለማክበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎ በመግባባት ተጠናቋል።

የአንሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሓንስ አበጋ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉፎንቆ:-ጳጉሜ 5/2018 (የአንሌሞ ወረዳ ብ/ፓ/ኮሙኒኬሺ...
10/09/2026

የአንሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሓንስ አበጋ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ፎንቆ:-ጳጉሜ 5/2018 (የአንሌሞ ወረዳ ብ/ፓ/ኮሙኒኬሺን)

የአንሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሓንስ አበጋ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመትን በማስመልከት ለአንሌሞ ወረዳ ህዝብ፣ በውጭ ሀገራት ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ዋና አስተዳዳሪው በመልዕክታቸው፥ አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ሕልም፣ አዲስ ጉልበትና አዲስ ስኬት የሚጀምርበት ወቅት ነው በማለት፣ 2019 ዓ.ም. ለሁሉም የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የተስፋና የብልፅግና ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።

በአንሌሞ ወረዳ የሚኖሩ ነዋሪዎችና በሥራ፣ በትምህርትና በተለያዩ ምክንያቶች በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የወረዳውተወላጆች በወረዳው ልማትና ዕድገት ሥራ ላይ አሻራቸውን እንዲያኖሩ ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል።

አቶ ዮሓንስ አዲሱ ዓመት በግልና በጋራ የተሻለ የምንሠራበት፣ ያሉንን ችግሮች በውይይትና በትብብር የምንፈታበት፣ ሰላማችንን የምናጠናክርበትና ልማታችንን የምናፋጥንበት ዓመት እንዲሆን ተመኝተዋል።

በመጨረሻም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለወዳጆቿ በሙሉ “እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም፣ በጤናና በደስታ አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት፣ የልማትና የብልፅግና ዓመት ይሁንላችሁ!” በማለት አቶ ዮሓንስ መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

!

አቶ ዮሓንስ አበጋ
የአንሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ
#መልካምአድስ ዓመት!!!

በአንሌሞ ወረዳ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ ''ያሆዴ'' በዓል አከባበርን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር  መድረክ አካሄደበዓሉ ከዞን አከባበር ቀን አስቀድሞ በሉም ቀበሌያት እ...
10/09/2026

በአንሌሞ ወረዳ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ ''ያሆዴ'' በዓል አከባበርን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

በዓሉ ከዞን አከባበር ቀን አስቀድሞ በሉም ቀበሌያት እንደሚከበርም በዕለቱ ተገልጿል።

ፎንቆ:- ጳጉሜ 05/2018 ዓ.ም(የአንሌሞ ወረዳ ብ/ፓ/ኮሙኒኬሽን )

በአንሌሞ ወረዳ የሀድያ ዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል አከባበርን አስመልክቶ የወረዳ አመራር ፑል፣ የቀበሌ ዋና አስተዳዳሪዎችና ሥራ አስኪያጆች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

የአንሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሓንስ አበጋ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት ሀሳብ እንደገለፁት ፣በዓሉ የሀዲያ ብሔር የማንነቱ መገለጫ መሆኑን አንስተው በዓሉ ከየትኛውም ሃይማኖት ጋር የማይገናኝና ከአሮጌው ዓመት ወደ አድሱ ዓመት ያሸጋገረውን ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት የምሥጋና በዓል በመሆኑ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ መከበር እንዳለበት ገልጸዋል።

የአንሌሞ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱኔ በበኩላቸው "ያሆዴ" ከባህላዊ ይዘት በተጨማሪ ሕዝባዊ ትስስርና ኣንድነት ከመፍጠር አንጻር የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ሁሉም የድርሻውን ልወጣ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የወረዳው ባ/ቱ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደጉ ስላሴ በዓሉ የማህበረሰቡ ቱባ ባህል እንደመሆኑ መጠን ለቀጣይ ትውልድ ሳይበረዝ ለማሸጋገር የግንዛቤ ሥራዎች ተጠናክሮ መሠራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የበዓሉ አከባር ከዝግጅት ምዕራፍ አንስቶ በደመቀና ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት እንደለበት አንስተው በተነሱ ሃሳቦች ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሮ መድረኩ ተጠናቋል።

በመድረኩ የወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዮሓንስ አበጋን ጨምሮ ሁሉም አስተባባሪ አካላት፣ የወረዳ አመራር ፑል፣ የቀበሌ ዋና አስተዳዳሪዎችና ሥራአስኪያጆች ተገኝተዋል።

10/09/2026
09/09/2026
09/09/2026
በአንሌሞ ወረዳ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ ''ያሆዴ'' በዓል አከባበር ዝግጅት ዙሪያ የበዓሉ አብይ ኮሜቴ የውይይት መድረክ አካሄደበዓሉ በጊዜያዊነት መስከረም 07/2019 ዓ/ም ልከበር እ...
09/09/2026

በአንሌሞ ወረዳ የሀዲያ ብሔር የዘመን መለወጫ ''ያሆዴ'' በዓል አከባበር ዝግጅት ዙሪያ የበዓሉ አብይ ኮሜቴ የውይይት መድረክ አካሄደ

በዓሉ በጊዜያዊነት መስከረም 07/2019 ዓ/ም ልከበር እንደሚችል ኮሚቴው አስታውቋል ።

ፎንቆ:- ጳጉሜ 04/2018 ዓ.ም(የአንሌሞ ወረዳ ብ/ፓ/ኮሙኒኬሽን )

የአንሌሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የበዓሉ አብይ ኮሜቴ ሰብሳቢ አቶ ዮሓንስ አበጋ ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት ሀሳብ እንደገለፁት ፣በዓሉ የሀዲያ ብሔር የማንነቱ መገለጫ በመሆኑ አጠቃላይ ማህበረሰቡ በበዓሉ ባህላዊ ይዘቱን ጠብቆ በድምቀት በአደባባይ ጎልቶ የሚታይበትና የሚተዋወቅበት በመሆኑ ትኩረት እንደሚሰጥ አንስተዋል ።

በዓሉ የማህበረሰቡ ቱባ ባህል እንደመሆኑ መጠን በዓሉ ሕዝባዊ መሠረት እንዲኖረው የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚሠራም አቶ ዮሓንስ አንስተዋል ።

አያይዘውም ፣ በተለይ በበዓል አከባበር ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችና ውጥረቶችን አስቀድመው በመፍታት በዓሉ በተሳካ መልኩ እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ዝርዝር ስራዎችን በመለየት በየዘርፉ ተልዕኮ የተሰጣቸው የኮሚቴ አባላትም ኃላፊነታቸውን በተገቢው ሁኔታ መወጣት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የአንሌሞ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዱኔ በበኩላቸው "ያሆዴ" ከባህላዊ ይዘት በተጨማሪ ሕዝባዊ ትስስርና ኣንድነት ከመፍጠር አንጻር የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ከበዓሉ አከባበር ጋር ተያይዞ የሚነሱ ያልተገቡ አስተሳሰቦችን የሚያርሙ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎችን በትኩረት መስራት እንዳለበትም ተናግረዋል።

የኮሜቴው አባላት በሰጡት አስተያየት የበዓሉ አከባር ከዝግጅት ምዕራፍ አንስቶ በቅንጅት በመሥራት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲከበር ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንደለበት ተናግረዋል።

በመጨረሻም በተነሱ ሃሳቦች ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሮ ቀጣይ የስራ ስምሪት ተሰጥቷል ።

Address

ፎንቆ ከተማ
Hossana

Telephone

+462630091

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሀዲያ ዞን የአንሌሞ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share