Central Ethiopia Regional State - Office Of The President

Central Ethiopia Regional State - Office Of The President This is the official Central Ethiopia RS Office of the president page where you can get recent info.

በዛሬዉ ዕለት ክቡር ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የተካሄደዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ ድባብ በምስል፦
31/08/2026

በዛሬዉ ዕለት ክቡር ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የተካሄደዉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ ድባብ በምስል፦

የሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ ስኬት እና የአዲሱ ዓመት ተስፋ ኢትዮጵያ ያለመግባባት ምዕራፏን ዘግታ በጠረጴዛ ዙሪያ ተነጋግራ ተግባብታለች፡፡ በዚህም በታሪኳ አዲስ ምዕራፍ በመክፈት፣ ልዩነቶችን እ...
31/08/2026

የሀገራዊ ምክክሩ ታሪካዊ ስኬት እና የአዲሱ ዓመት ተስፋ

ኢትዮጵያ ያለመግባባት ምዕራፏን ዘግታ በጠረጴዛ ዙሪያ ተነጋግራ ተግባብታለች፡፡ በዚህም በታሪኳ አዲስ ምዕራፍ በመክፈት፣ ልዩነቶችን እና አለመግባባቶችን በጥይት ሳይሆን፣ በውይይት እንዲሁም በመደማመጥ ባህል መፍታት እንደምትችል በማረጋገጥ ልጆቿ ለሀገራቸው በጋራ በመቆም ታሪካዊ ድል አስመዝግበዋል።

አዲስ ዓመት በደጅ በቆመበት በዚህ ወቅት፣ በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ የተዘራው የመግባባት ዘር ለአዲሱ ዘመን ትልቅ የምስራች ሆኗል። የሚመጣውን አዲሱ ዓመት ከቀድሞዎቹ ለየት የሚያደርገው፣ ሀገራዊ ምክክሩ የዘመናት ቅራኔዎችንና የፖለቲካ ጥያቄዎችን በመፍታት የመግባባት መሠረት መጣሉ ላይ ነው።

ዘመን ቅየራ የጊዜ ሰሌዳ መቀየር ብቻ ሳይሆን፣ የትናንትን ተሞክሮ በመገምገም የተፈጠሩ ክፍተቶችን በማረምና ለነገ የተሻለ ተስፋ በመገንባት ወደ አዲስ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ነው።

ለዘመናት በልዩነት፣ በአለመግባባትና በግጭት የተፈተነችው ኢትዮጵያ ከጥላቻ በላይ ፍቅርን፣ ከበቀል በላይ ይቅርታን፣ ከጦርነት በላይ ንግግርን በመምረጥ የጋራ ችግሮቿን በጋራ ለመፍታት የምክክርን መንገድ መርጣ በስኬት አጠናቅቃለች።

የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው በስኬት መጠናቀቁም ለዚህ ሂደት አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። የኢትዮጵያ ልጆች "ችግሬ ከችግርህ አይበልጥም" በሚል እሳቤ፣ የተለያዩ ምንጮች ወደ አንድ ባሕር እንደሚፈሱ ሁሉ፣ የተለያዩ ድምፆችን ወደ አንድ ሀገራዊ መግባባት በማምጣት የጋራ ድል አስመዝግበዋል።

ይህ ሰፊ ሀገራዊ የውይይት መድረክ ማኅበራዊ ትስስርን ለማጠናከርና የፖለቲካ ከባቢውን ለማረጋጋት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡ የወጣቶች እና የሴቶች ተሳትፎ በሁሉም ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲሰፋ መደረጉም ለነገው ትውልድ ትልቅ ተስፋን ፈጥሯል።

ከማኅበረሰቡ እውቀትና ተሞክሮ በመነሳት የተደረጉ ውይይቶች፣ የፖሊሲ እና የልማት አቅጣጫዎች የሕዝቡን ፍላጎት በቀጥታ አንጸባርቀዋል፡፡ የምክክር ሂደቱ ከጉባኤው መጠናቀቅ ጋር የሚያበቃ ሳይሆን፣ በቀጣይ የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ በተግባር መቀጠል የሚገባው የሀገራዊ መግባባት መሠረት ነው።

ይህም የፖለቲካ ተቋማትን ማጠናከር፣ የዜጎችን እምነት ማሳደግ፣ የልዩነት አያያዝን ማሻሻልና በጋራ የሀገር ጉዳይ ላይ የመሥራት ባህልን ማዳበር የሚያስችል ሀገራዊ ካፒታል ይሆናል።

ሀገር ለማስቀጠል የሚያስፈልገው ድል በኃይል ብቻ የሚገኝ ሳይሆን፣ በመደማመጥ፣ በመከባበርና በሰከነ ውይይት የሚገነባ መሆኑን የምክክሩ ሂደት ያሳያል።

በዚህ አውድ 2019 ዓ.ም ለኢትዮጵያውያን አዲስ ዓመት ብቻ ሳይሆን፣ በምክክር የተጣለውን መሠረት ወደ ተግባር የሚቀይሩበት አዲስ የተስፋ ምዕራፍ ነው።

ኢትዮጵያውያን አዲሱን ዓመት የሚያከብሩት ቀን በመቀየር ብቻ ሳይሆን የትናንት ቁስሎችን በመፈወስ፣ የዛሬን ልዩነቶች በመወያየት እና የነገን የጋራ ተስፋ በመገንባት እንዲሁም የአስተሳሰብ፣ የመግባባትና የጋራ የሀገር ግንባታ አዲስ ምዕራፍን በመክፈት ነው።

ከኢትዮጵያ ጥቅም ጋር ተቃርኖ ያላቸውን አካላትን ሴራ ማክሸፍ ተገቢ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ሆሳዕና፣ነሐሴ 25/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል"ዘላቂ ሰላማችን ...
31/08/2026

ከኢትዮጵያ ጥቅም ጋር ተቃርኖ ያላቸውን አካላትን ሴራ ማክሸፍ ተገቢ ነው:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና፣ነሐሴ 25/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
"ዘላቂ ሰላማችን ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ ሲካሄድ የነበረው የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ ተጠናቋል

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ ጸጥታ ምክር ቤት ሰብሳቢ እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የሰላም ማዕከል የሆኑ መንደር ቀበሌ እና ወረዳዎችን መፍጠር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ሂደት የጸጥታ እና የአጋዥ አካላትን ሚና ማጠናከር እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

ህግ ማስከበር እና ከአጎራባች ክልሎች ጋር በትብብር መስራት በዘላቂ ሰላም ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚያስችልም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ከኢትዮጵያ ጥቅም ጋር ተቃርኖ ያላቸውን አካላትን ሴራ ማክሸፍ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።

እነዚህ አካላት የታጠቁ ኃይሎችን ወደ ክልሉ በማስገባት ቀጠናውን የትርምስ ማዕከል ለማድረግ እየሰሩ ስለመሆኑም አውስተዋል።

የስራ ባህል ለውጥ በማድረግ ድህነትን ማሸነፍ አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የወጣቶችን ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የክልሉ መንግስት ለወጣቶች የስራ እድል እየፈጠረ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህም በየ አመቱ እድገት ማሳየቱን በአብነት ጠቅሰዋል።

ብልሹና አሰራር እና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማስቀረት በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ወደ ስራ ማስገባቱን ጠቁመዋል።

በ2019 በጀት ዓመት በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ማዕከላትን ተደራሽነት ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የንግድ ቁጥጥርን በማጠናከር የኑሮ ውድነቱን ማስተካከል ተገቢ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

የሰንበት ገበያዎችን በማስፋፋት ሳምንቱን ሙሉ ግብይት እንዲካሄድባቸው መስራት ተገቢ መሆኑን ጠቁመዋል።

የጸጥታ ምክር ቤቱ በክልሉ በአንዳንድ አካባቢዎች ያጋጠሙ የጸጥታ ችግሮችን በመፍታት ሂደት የላቀ ድርሻ እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጋራ ትብብር እና ጥረት ያሻል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ሆሳዕና፣ነሐሴ 25/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል"ዘላቂ ሰላማችን ለሁለንተናዊ ብልጽግ...
31/08/2026

ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጋራ ትብብር እና ጥረት ያሻል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና፣ነሐሴ 25/2018፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል
"ዘላቂ ሰላማችን ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የክልሉ ጸጥታ ምክር ቤት ሰብሳቢ እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉባኤው እንደገለጹት የሰላም ዋጋ የሚታወቀው ሰላም ሲጎድል ብቻ ነው ብለዋል።

ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የጋራ ትብብር ያሻል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የበርካታ ተዋናዮችን ተሳትፎም ይጠይቃል ሲሉም ጠቁመዋል።

ማህበረሰቡ ቤቱን አካባቢውን፣ጎረቤቱን መጠበቅ ይኖርበታል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የዚህ ድምር ውጤት በዘላቂ ሰላም ላይ የጎላ ሚና እንዳለውም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላከክተዋል።

የጸጥታ ኃይሉ የማህበረሰቡን አቅም የማስተባበር፣የማቀናጀት ቀዬ፣መንደር፣ ቀበሌዎች እና ወረዳዎች በሰላም ውለው እንዲያድሩ መትጋት ይኖርበታል ብለዋል።

አንዳንድ ሀገሮች ተፈጥሮ በሚያደርስባቸው የሰላም ችግሮች ተጎጂ ሲሆኑ ተመልክተናል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በኛ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ በሰው ሰራሽ የሰላም መደፍረስ ምክንያት የሚያጋጥመንን ችግር ለመፍታት የተቀናጀ ጥረት ይጠይቃል ሲሉም አስረድተዋል።

ሚዲያዎች በሰላም ስራ ላይ የሚኖራቸው አበርክቶ ከፍተኛ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

አሁን ባለዉ ነባራዊ ሁኔታ በእያንዳንዱ ሰው የእጅ መዳፍ ስር ሚዲያ አለ ያያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ከሁሉም በላይ ትኩረቱ በዘላቂ ሰላም ላይ ሊሆን እንደሚገባም ጠቅሰዋል።

ለቤተሰብ ብልጽግና መረጋገጥ ሰላም የሚኖረው ድርሻ መሰረታዊ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ለዚህም የሁሉንም አካላት ቁርጠኝነት እንደሚጠይቅም አብራርተዋል።

በየአካባቢው ለሰላም መደፍረስ መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ጉባኤተኛው በስፋት ሊመክርባቸው ይገባል ብለዋል።

በየደረጃው የሚገኙ ምክር ቤቶች በዘላቂ ሰላም ላይ ሊሰሩ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

ክልሉ ከተመሰረተ ወዲህ የማምሸት ምጣኔ እየጨመረ መጥቷል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቅሰዋል።

ህግ በማስከበር ስራ ላይ ምክር ቤቱ በዝርዝር መወያየት ይኖርበታል ሲሉም አብራርተዋል።

የመንግስት ዋነኛ ሚና ህግ ማስከበር ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ህግ እንዲከበር የሚፈልግ የማህበረሰብ ክፍል ሲኖር በሌላ በኩል ደግሞ ህግ እንዲከበር ፍላጎት የሌለው አካል መኖሩን ጠቁመዋል።

ይህንን በማስታረቅ የህዝቡን ሰላም ማረጋገጥ አብይ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሰላም የሚጀምረው ከቤት፣ከጎረቤት፣ከአካባቢ መነሻነት ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

በሀገሪቱ ወደ 4ሺ የሚጠጉ የኢትዮጵያ ልጆች በ8 ዋና ዋና አጀንዳዎች 400 ንኡሳን አጀንዳዎች ላይ በመምከር 99በመቶ ምክረ ሀሳብ ማቅረባቸውን በአብነት ጠቅሰዋል።

ይህን ምክረ ሀሳብ በመንቀፍ የሚዲያ ዘመቻ የሚያካሄዱ አካላት እንደነበሩም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ የሚያጋጥሟትን ተግዳሮቶች በጽናት እና በድል አድራጊነት እየተሻገረች ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

ከጠብመንጃ ወደ ጠረጴዛ ውይይት ሀገራዊ ምክክር እና የመደመር መንግሥት የመግባባት ዴሞክራሲ ታሪካዊ ድልሀገር የሚገነባው እንዲሁም ዘላቂ ሰላም እና የተረጋጋ ዴሞክራሲ የሚረጋገጠው ዜጎች ያለስ...
31/08/2026

ከጠብመንጃ ወደ ጠረጴዛ ውይይት ሀገራዊ ምክክር እና የመደመር መንግሥት የመግባባት ዴሞክራሲ ታሪካዊ ድል

ሀገር የሚገነባው እንዲሁም ዘላቂ ሰላም እና የተረጋጋ ዴሞክራሲ የሚረጋገጠው ዜጎች ያለስጋት በነጻነት ተወያይተው፣ ልዩነቶቻቸውን አክብረው በሚፈጥሩት ጠንካራ የጋራ መግባባት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ሂደት ስኬት የመደመር መንግሥት አንግቦት የተነሳውን የመግባባት ዴሞክራሲ ፍልስፍና በተግባር ያረጋገጠ ታሪካዊ ክስተት ነው።

የመደመር አስተሳሰብ አንዱ እና ዋነኛው ምሰሶ ሀገራዊ ጉዳዮችን በኃይል ወይም በጥቂት ወገኖች ድርድር ሳይሆን በጋራ መግባባት እና በሰለጠነ ውይይት መፍታት በመሆኑ፣ ይህ መርህ በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት እውን ሆኖ ታይቷል።

የሀገር አስተማማኝ መሠረት የሚጣለው በዜጎች ንቁ ተሳትፎ በመሆኑ፣ ዜጎች ስለ ሀገራቸው ያለፈ ታሪክ፣ የአሁኑ ፈተና እና የመጪው ጊዜ ራዕይ በነጻነት የመምከር እና የመወያየት መብታቸው ሲጠበቅ የባለቤትነት ስሜት የሚፈጠር ሲሆን፣ ሕጎችና የወደፊት አቅጣጫዎች በሕዝብ የጋራ ውሳኔ ሲቃኙ የሁሉም ብሔር፣ ሃይማኖትና ጾታ ድምፅ በእኩልነት ተሰምቶ የመገለል ስሜት ይወገዳል።

ኃይል የሚያስገኘው ጊዜያዊ ስምምነት ዘላቂ ሰላም ማምጣት ስለማይችል፣ በውይይት የሚገነባ መግባባት ቂምና ቁስሎችን በመካስ፣ በሕዝቦች መካከል መተማመንን በመፍጠር ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ባህልን ያዳብራል።

ኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቁ ስልታዊ እና መዋቅራዊ ልዩነቶች፣ የፖለቲካ አለመግባባቶች እንዲሁም የታሪክ ትርክት ክፍተቶች ያሏት ሀገር እንደመሆኗ፣ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተጣጣጡ ድምፆችና ሐሳቦች የሚደመጡበት ሰፊ ሜዳ በመፍጠር በሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያዎች፣ በሀገራዊ ምልክቶች፣ በፌዴራሊዝም ቅርጽ እና በታሪክ ትርክቶች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር መንገድ ከፍቷል።

ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት በየደረጃው ባከናወናቸው መድረኮች እንዲሁም በመጨረሻው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከየአካባቢው ከተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች ጋር ያካሄደው ውይይት፣ ከጠብመንጃ ይልቅ ውይይት፣ ከውግዘት ይልቅ ማዳመጥ የሚነግስበትን አዲስ የፖለቲካ ባህል በማስረጽ ረገድ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማይታወቅ እጅግ ግዙፍ ሀገራዊ ድል አስመዝግቧል።

ሀገርን ማቅናት እና አስተማማኝ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት በአንድ ጀምበር የሚፈጸም ባይሆንም፣ ትክክለኛው መንገድ ግን በዜጎች ነፃ ውይይት የሚገኝ የጋራ መግባባት እንደሆነ የመደመር አስተሳሰብ ያስተምራል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ያስመዘገበው ውጤት የመደመር መንግሥት የተከተለው የመግባባት ዴሞክራሲ ፍልስፍና ፍሬ ማፍራቱን በተግባር ያረጋገጠ ሲሆን፣ የፖለቲካ ኃይሎች፣ የሲቪክ ማኅበራት እና ሙሉው ሕዝብ ሂደቱን በጥቅል ባለቤትነት ተረክበው ለተግባራዊነቱ ሲቆሙ በውይይት የተገነባች፣ ሰላምና ፍትሕ የሰፈነባት ጽኑ ኢትዮጵያ እውን መሆኗ አይቀሬ ነው።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ነው ሆሳዕና፣ነሐሴ 25/2018 "ዘላቂ ሰላማችን ለሁለንተናዊ ብ...
31/08/2026

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ነው

ሆሳዕና፣ነሐሴ 25/2018 "ዘላቂ ሰላማችን ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ካሳ በጉባኤው ባደረጉት ንግግር እንዳስታወቁት
ኢትዮጵያ ስለወደፊቱ ሁለንተናዊ መፃኢ እድል ከዜጎቿ ጋር በመከረችበት ማግስት ስለ ክልላችን ዘላቂ ሰላምና ደህንነት ለመመካከር መሰብሰባችን ጉባኤውን በእይነቱም በይዘቱም የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።

ሠላምና ፀጥታ የልማት፤ የዲሞክራሲ ግንባታ፣ የአኗኗር፣ የደህንነት፣የጤና፣ የፍቅር፣ የእድገት፣ የነጻነት የአብሮነት፣ የወንድማማችነትና የመከባበር ማረጋገጫ ብቸኛው መንገድ ነው ሲሉም ኃላፊው አብራርተዋል፡፡

ሠላም ባልተረጋገጠበት ማምረት፣ መነገድ፣ መማር፣ በነጻነት ማምለክ ፈጽሞ የማይታሰብ ነው ያሉት አቶ ተመስገን
የአንድን ማህበረሰብ ወይም ሀገርሁለንተናዊ ሠላም መገንባት ለምርጫ የሚቀርብ ጉዳይ አይደለም ብለዋል።

ሰላምን መጠበቅ፣ ማስጠበቅ፣ ማስከበር፣ መንከባከብ፣ ማጠናከርና ማጽናት ለመንግስት ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑን ኃላፊው በንግግራቸው አመላክተዋል።

ሁሉም ዜጋ በኃላፊነት፣ በተጠያቂነትና በባለቤትነት የሚወጣው የማይቋረጥ ተከታታይ ተግባር ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

ሠላም በተቋማት ጥምረትና በተቋማዊነት ውስጥ ሊፈጸም የሚገባ እሳቤ መሆኑን አቶ ተመስገን አስታውቀዋል።

ሰላም በግለሰብ፣በቤተሰብ፣በማህበረሰብና ተቋማት መካከል ከዚያም አልፎ ሀገራትንና አህጉሮችን የሚያካትት ድንበርና ወሰን የማይገድበው አጀንዳ ስለመሆኑም አስታውቀዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ሰላምን ቀዳሚ አጀንዳው በማድረግ የህዝቦችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ የተለያዩ ሳይንሳዊ አሰራሮችን በመዘርጋት እየሰራ ነው ብለዋል።

የሰላም ተምሳሌት የሆነች ክልል ለመገንባት በተሰራው ስራ የ24 ሰዓት ነጻ እንቅስቃሴ የማረጋገጥ አላማ በማሳካት ላይ እንገኛለን ሲሉም አብራርተዋል።

ከእነዚህ ሳይንሳዊ አሰራሮች የሰላምና ፀጥታ ማረጋገጫ መሳሪያዎች ተብለው ከሚጠቀሱት አደረጃጀቶች ውስጥ የጸጥታው ምክር ቤት የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ ስለመሆኑም ኃላፊው ጠቅሰዋል።

ምክር ቤቱ ከክልል እስከ ቀበሌ በ1319 ምክር ቤቶች እና በ118ሺ927 የምክር ቤት አባላት እንዲደራጅ መደረጉን አቶ ተመስገን አስታውቀዋል።

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀመረ (ሆሳዕና፣ነሐሴ 25/2018) "ዘላቂ ሰላማችን ለሁለንተናዊ ...
31/08/2026

ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ መካሄድ ጀመረ

(ሆሳዕና፣ነሐሴ 25/2018) "ዘላቂ ሰላማችን ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"በሚል መሪ ሀሳብ በሆሳዕና ከተማ የጸጥታ ምክር ቤት ጉባኤ እየተካሄደ ነው

በመድረኩ በክልሉ ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ ረገድ በተከናወኑ ተግባራት ላይ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተዋሳኝ አካባቢዎች የጋራ ጥምረት የፀጥታ ኮማንድ ፖስት  የኮማንድ ፖስቱን የእሰከ አሁን አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል...
30/08/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተዋሳኝ አካባቢዎች የጋራ ጥምረት የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የኮማንድ ፖስቱን የእሰከ አሁን አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል ፤በቀጣይ ጊዜ ጠቋሚ ዕቅድ ላይም ተወያይቷል

ሆሳዕና፣ ነሐሴ 24 2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ ( ዶ/ር) በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተዋሳኝ አካባቢዎች የጋራ ጥምረት የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የተዋሳኝ አካባቢዎች ጥመረት ኮማንድ ፖስትን የእሰከ አሁን አፈፃፀም ሪፖርት ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ገምግሟል ፤በቀጣይ ጊዜያት ጠቋሚ ዕቅድ ላይም ተወያይቷል።

በመድረኩ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተመስገን ካሳ፣ የጥመረት ኮማንድ ፖስቱን የእሰከ አሁን አፈፃፀም ሪፖርት እና የቀጣይ ጊዜ ጠቋሚ ዕቅድ አቅርበዋል፤ ዝርዝር ውይይትም ተደርጎበታል።
ዘላቂ ሠላምን ማስፈን ፣ የህዝቦችን አንድነት እና ትስስር ማጎልበት በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ የተጀመረዉን የቅንጅት ሥራ አጠናከሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸዉ አግባቦች ላይ ዉይይት ከመካሔዱም በላይ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችም ተለይተዉ መቀመጣቸው ተገልጿል ።

በዉይይት መድረኩ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሰት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሰት ፖሊስ ኮሚሽን፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና በሁለቱ ክልሎች ተዋሳኝ ዞኖች እና ወረዳዎች አመራሮች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ሰላም ለአፍሪካ፡ የሀገራዊ ምክክር ስኬት አህጉራዊ ትርፍነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጠናቀቀው ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የኢትዮጵያ ሰላም ለጠቅላላው የአፍሪካ አህ...
30/08/2026

የኢትዮጵያ ሰላም ለአፍሪካ፡ የሀገራዊ ምክክር ስኬት አህጉራዊ ትርፍ

ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጠናቀቀው ታሪካዊው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የኢትዮጵያ ሰላም ለጠቅላላው የአፍሪካ አህጉር የሚተርፍ መሆኑን በተግባር ያስመሰከረ ታላቅ ክስተት ነው።

ይህ ጉባኤ ዜጎችን ከመሠረቱ ያሳተፈ፣ ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ የዳያስፖራ አባላትን ጨምሮ 4 ሺህ ተወካዮችን በማሰባሰብ የተከናወነ ሁሉን አቀፍ እና አሳታፊ ሂደት ነበር።

በዚህ ታሪካዊ ውይይት የውጭ ኃይሎች ቀጥተኛ ጣልቃ ገብነት ሳይኖር በራስ አቅም እና በሕዝብ ንቁ ተሳትፎ የጸና የሰላም መሠረት መጣሉ፣ "የኢትዮጵያ ሰላም የአፍሪካ ሰላም ነው" የሚለውን ጥልቅ ጂኦፖለቲካዊ እውነት በግልጽ አሳይቷል።

የምክክሩ ስኬት በአፍሪካ ቀንድም ሆነ በመላው አህጉር ላይ ቀጥተኛ አዎንታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድር በመሆኑ፣ ሂደቱ ለአፍሪካውያን አዲስ ተስፋን ፈንጥቋል።

ከዚህም ባለፈ ማኅበራዊ ትሥሥርን በማጠናከር የመጪውን ትውልድ ሥነ-ልቦና በጎ አቅጣጫ የሚያስይዝ ትልቅ ማዕቀፍ ፈጥሯል።

በምክክር ጉባኤው ማጠቃለያ ላይ የታደሙት የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት እና በአፍሪካ ኅብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ እንዲሁም የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ፣ ይህ ሀገራዊ ስኬት ለአፍሪካ ያለውን ወሳኝ ድርሻ አስምረውበታል።

ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ ሰላም የማይከፋፈል ባሕርይ እንዳለው ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያ በረጅም ጊዜ ዝግጅት እና ጥልቀት ባለው ውይይት የፈጠረችው መረጋጋት ለአጠቃላይ የአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ዕድገት እና የጋራ ብልጽግና ዋና ሞተር እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

አሁሩ ኬንያታ በበኩላቸው የሺህዎችን ድምፅ በአንድ መድረክ ማሰባሰብን “ከፍተኛ የሀገር ፍቅር ተግባር” ሲሉ ያወደሱ ሲሆን፣ የኢትዮጵያውያን ሰላም ለቀጣናው ደኅንነት መሠረታዊ ቅድመ-ሁኔታ መሆኑን አብራርተዋል።

እነዚህ አንጋፋ መሪዎች ለሐሳባቸው ማረጋገጫ አድርገው ያነሡት የኢትዮጵያን ታሪካዊ ድሎችን ነው። የዓድዋ ድል አፍሪካውያን ቅኝ አገዛዝን በራሳቸው ጽናት በማሸነፍ ነጻነታቸውን ማስከበር እንደሚችሉ ያሳየበት ታሪካዊ ክስተት እንደነበር ሁሉ፣ ሀገራዊ ምክክሩም አፍሪካውያን የውስጥ ፖለቲካዊ ውዝግቦቻቸውን በራሳቸው ጥበብ መፍታት እንደሚችሉ ማረጋገጫ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም በዩኔስኮ የማይጨበጥ የዓለም ባህላዊ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው የኦሮሞ ሕዝብ ሀገር በቀል የገዳ ሥርዓት በውይይት እና በጋራ መግባባት ውሳኔ የመስጠት ዕሴቱ ለዘመናዊ የዴሞክራሲ ሂደት እና ለሰላም ግንባታ ትልቅ አህጉራዊ አርዓያ መሆኑ በጉባኤው ተስተጋብቷል።

አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫ እና የፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መዲና መሆኗ ደግሞ በኢትዮጵያ የሚገነባው ሰላም መላውን አህጉር የማነቃቃት አቅም እንዳለው ያረጋግጣል።

በምክክር የሚፈጠረው ሀገራዊ መግባባት መዋቅራዊ ጸጥታን ያጠናክራል። ይህ መረጋጋት በተራው በአፍሪካ ቀንድ የሚታየውን ሕገ-ወጥ ፍልሰት፣ የድንበር ተሸጋሪ ሽብርተኝነት እና የጦር መሣሪያ ዝውውር በመቀነስ የቀጣናውን የጸጥታ መዋቅር አስተማማኝ ያደርገዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን ኢትዮጵያ በጠንካራ ብሔራዊ መግባባት ላይ ስትቆም፣ እንደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ያሉ ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶቿን በሙሉ አቅም በመጠቀም ለአፍሪካ ቀንድ የኤሌክትሪክ ኃይል ትሥሥር፣ ለድንበር ተሸጋሪ ንግድ እና ለጋራ የኢኮኖሚ ውህደት መንገድ ትከፍታለች።

ሀገራዊ ምክክሩ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ የተደረጉ ሰፊ ውይይቶችን በማጠናቀቅ 400 መሠረታዊ የውሳኔ ሐሳቦችን ማቅረቡ ለወደፊት የፖሊሲ እና የሕግ ማሻሻያ ግልጽ ካርታ አስቀምጧል።

ምክክሩ የጉዞው ማጠቃለያ ሳይሆን የረጅም ጊዜ የእርቅ እና የመደጋገፍ ሂደት መጀመሪያ ነው።

በመሆኑም በሂደቱ የሚገኘው ሀገራዊ መግባባት ለኢትዮጵያ ዘላቂ ዕድገት መሠረት ከመሆኑም በላይ፣ ለአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት እና ለአጠቃላይ አህጉሪቱ የጋራ ብልጽግና ታላቅ የማፋጠኛ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።

ከጥገኝነት ወደ አምራችነት፦ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እመርታ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ስኬቶችየአንዲት ሀገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የረጅም ጊዜ ዕድገት የሚረጋገጠው ከውጭ ጥገኝነ...
30/08/2026

ከጥገኝነት ወደ አምራችነት፦ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ እመርታ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ስኬቶች

የአንዲት ሀገር የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የረጅም ጊዜ ዕድገት የሚረጋገጠው ከውጭ ጥገኝነት ተላቅቃ የራሷን ፍላጎት በራሷ ማምረት ስትችል ነው።

የመደመር መንግሥት ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ የጀመራቸው “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል ሀገራዊ ንቅናቄ እና በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ ግብር፣ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን በማነቃቃት አስደናቂ ለውጦችን ማምጣት ጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው የሰጡት ማብራሪያ፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአፈጻጸም ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት፣ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ከውጭ ጥገኝነት በመላቀቅ የሀገር ውስጥ አቅምን ወደ መገንባት በተኪ ምርት የተሳካ ሽግግር እያደረገ ይገኛል።

የማምረት አቅም ማደግ እና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ሚና

ለረጅም ጊዜ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከነበራቸው የማምረት አቅም ከግማሽ በታች (በአማካይ 47 በመቶ) ብቻ ሲጠቀሙ ቆይተዋል። ይህ ዝቅተኛ አፈጻጸም በኃይል አቅርቦት መቆራረጥ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት እና በጥሬ ዕቃ አቅርቦት ችግሮች የተተበተበ ነበር።

ሆኖም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምክር ቤቱ እንዳብራሩት፣ አሁን ላይ አጠቃላይ የማኑፋክቸሪንግ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ሊል ችሏል።

የዚህ ከፍተኛ ለውጥ ዋነኛ ሞተር በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እየተመራ ያለው የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በተለያዩ ምክንያቶች ተዘግተው የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፋብሪካዎች ወደ ሥራ እንዲመለሱ በማድረግ፣ እንዲሁም የአምራቾችን የፋይናንስ እና የመሠረተ ልማት ማነቆዎች በመፍታት ምርታማነትን በእጅጉ አነቃቅቷል።

➡ የኢንዱስትሪ ፓርኮች መስፋፋት እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ፖሊሲ ሌላኛው የትኩረት አቅጣጫ ምቹ የኢንቨስትመንት መሠረተ ልማት ማቅረብ ነው። እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ ነባር ከሆኑት የኮምቦልቻ፣ የመቐለ እና የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በተጨማሪ ዐሥር አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን መገንባት ተችሏል።

የእነዚህ ፓርኮች መስፋፋት የሀገር ውስጥ አቅምን ከማጎልበት ባለፈ፣ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነውን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት (FDI) ወደ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ለመሳብ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

የውጭ ኢንቨስተሮች ቴክኖሎጂን ወደ ሀገር ውስጥ እንዲያመጡ እና የዕውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ።

➡ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት፦ የ5 ቢሊዮን ዶላር ስኬት

ለዘመናት የኢትዮጵያን ማክሮ ኢኮኖሚ ሲፈታተን የነበረው ዋነኛ ችግር፣ የውጭ ምንዛሬ እጥረት እና በገቢ ምርቶች ላይ ያለ ከፍተኛ ጥገኝነት ነበር።

ይህንን ለመቀልበስ "የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት" ስትራቴጂ በተጠናከረ መልኩ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

ሲሚንቶ፣ ብረት፣ ብርጭቆ እና ሴራሚክስን የመሳሰሉ ከባድ እና ወሳኝ የግንባታ/የኢንዱስትሪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ብቻ ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ የውጭ ምንዛሬ ማዳን ተችሏል።

መንግሥት ቀደም ሲል በብዙ ቢሊዮን ዶላር ወደ ሀገር ውስጥ ይገቡ የነበሩ ምርቶችን በሒደት በሀገር ውስጥ ምርት የመተካት ፖሊሲውን በተግባር እያረጋገጠ ይገኛል።

በግብርናው (በተለይም በስንዴ ምርት) የተገኘው የገቢ ምርትን የመተካት ስኬት ወደ ኢንዱስትሪው ዘርፍም በተጨባጭ ተሸጋግሯል።

➡ የተቀናጀ የዘርፎች ዕድገት

የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ መነቃቃት በሌሎች ተያያዥ ዘርፎች ላይም አዎንታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። የኢንዱስትሪ ዕድገት ብቻውን ሊመጣ አይችልም፤ ኃይል እና የጥሬ ዕቃ ግብዓት ይፈልጋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዘርፉ እያስመዘገበ ባለው ፈጣን ዕድገት ምክንያት፦ በማዕድን ዘርፍ 24 በመቶ፣ በማኑፋክቸሪንግ 20.3 በመቶ፣ እና በኢነርጂ ዘርፍ 23 በመቶ ጭማሪ መታየቱን አብራርተዋል። እነዚህ ሦስቱ ዘርፎች (ማዕድን፣ ኢንዱስትሪ እና ኢነርጂ) እርስ በርስ በመመጋገባቸው የመጣ "የተቀናጀ ዕድገት" (Synergy) መሆኑን ያሳያል።

➡ የወደፊቱ አቅጣጫ እና ራዕይ

የተገኙት ስኬቶች የጉዞው ጅማሮ እንጂ ማቆሚያ አይደሉም። ይህንን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ በመጪው ዓመት ግልጽ ዒላማዎች ተቀምጠዋል። እነዚህም፦

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ብቻ የ12.7 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ እና ከኢንዱስትሪ ምርቶች ኤክስፖርት (ወጪ ንግድ) የ1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ሲሆኑ ለስኬቱም በትኩረት እየተሠራ ይገኛል።

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ዘርፍ እውነተኛ ዕምርታ እያሳየ ነው። “ኢትዮጵያ ታምርት” በሚለው ብሔራዊ ንቅናቄ በመመራት፣ የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ወደ 67 በመቶ ማሳደግ ተችሏል።

አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመክፈት ኢንቨስትመንትን መሳብ እና ቁልፍ የገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት 5 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሉም ሀገራችን ከሸማችነት ወጥታ ጠንካራ እና ራሷን የቻለች አምራች ኢኮኖሚ ወደ መገንባት የተጨበጠ ዕርምጃ መጀመሯን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።

ራዕዩ ግቡን ሲመታም፣ የኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የብልጽግናዋ ዋነኛ የጀርባ አጥንት መሆኑ አይቀርም።

Address

Hossana

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Regional State - Office Of The President posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share