Visit Hadiya

Visit  Hadiya የሀዲያ የባህል እና የቱሩዝም ማስታዋዎቅ ትክክል ገፅ ነው ቱሩዝም ለሀገር እድገት

ያሆዴ — የሀዲያ ሕዝብ የአዲስ ዘመን፣ የምስጋናና የተስፋ በዓል የሀዲያ ሕዝብ በረጅም የታሪክ ጉዞው ያዳበረው ጽኑ ማንነት፣ ቋንቋ፣ እምነትና ባህላዊ አኗኗር መገለጫ ከሆኑት ድንቅ ቅርሶች መ...
03/09/2026

ያሆዴ — የሀዲያ ሕዝብ የአዲስ ዘመን፣ የምስጋናና የተስፋ በዓል

የሀዲያ ሕዝብ በረጅም የታሪክ ጉዞው ያዳበረው ጽኑ ማንነት፣ ቋንቋ፣ እምነትና ባህላዊ አኗኗር መገለጫ ከሆኑት ድንቅ ቅርሶች መካከል የያሆዴ በዓል አንዱና ዋነኛው ነው።

የስያሜው ምስጢርና ትርጉም

“ያሆዴ” የሚለው ስያሜ በበዓሉ ወቅት ከሚሰማው “ያሆሆሆ” የሚለው የዜማ ቅላጼ እና “ኤዴ” ከሚለው ጥምር ቃል የተገኘ መሆኑ ይነገራል።

“ኤዴ” ማገናኘት፣ ማጣመርና ማያያዝ የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን፣ ይህም በዓሉ ማህበረሰቡን ከአዲስ ልምላሜ፣ ከተስፋ፣ ከሰላምና ከብርሃን ጋር የሚያስተሳስር ድልድይ መሆኑን ያመለክታል።

የዘመን ስሌትና የተፈጥሮ ምልክቶች

የሀዲያ አባቶች ያለ ዘመናዊ የሳይንስ መሳሪያ የተፈጥሮን ምልክቶች በመመልከት የዘመን መለወጫን ያሰሉ ነበር። የከዋክብትን ጉዞ፣ የጨረቃን ዑደት፣ የንፋስን አቅጣጫ፣ የወፎችን ዝማሬና የወንዞችን ሙላት በመመርመር የአዲሱን ዘመን መምጣት ያረጋግጡ ነበር።

በተጨማሪም ወደ ጥበብ አዋቂዎቹ Hiraagaano / ህራጋኖ በመሄድ የአዲሱን ዓመት ብስራት ያረጋግጣሉ።

Aganchi Yabaraakko — የጨረቃዋ መፈንጠቅ

የክረምቱን ድቅድቅ ጨለማ ገፋ በወርቃማ ድምቀት ብቅ ስትል፣ ሕዝቡ በአንድ ድምፅ፦

“ጨረቃዋ ፈነጠቀች!”

በማለት በደስታ ይቀበላታል።

ዘራሮዕ-ፊታ

ማንም ሳይዘራው፣ በሰው ሰራሽ መስኖም ሆነ በበጋ ዝናብ ሳይበቅል፣ ያሆዴ ሲደርስ ወቅቱን ጠብቆ የሚፈነዳው ይህ ብርቅዬ አበባ የአዲስ ዘመን መባቻ ዋነኛ ማብሰሪያ ነው። አባቶችም ለተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ይጠቀሙበታል።

የበዓሉ ድምቀትና ማህበራዊ እሴት

ያሆዴ የሰው ልጆች ብቻ ሳይሆኑ የተፈጥሮ ፍጥረታትም የሚታደሱበት የደስታና የተስፋ ወቅት ነው።

የእንስሳት ደስታ፦
ለወራት በጥበቃ ታሽጎ የቆየው ኩቱራ (Kutura) ለምለም የግጦሽ መሬት ሲከፈት፣ ከብቶች በነፃነት ይቦርቁበታል።

የማዕድና የህብረት ፌሽታ፦
ባህላዊ ምግቦችና መጠጦች ተዘጋጅተው፣ ዘመድ አዝማድና ጎረቤት በአንድነት ይቋደሳሉ።

ዕርቅና ጋብቻ፦
ያሆዴ ከጨለማ ወደ ብርሃን የመሸጋገሪያ ወቅት ብቻ ሳይሆን፣ የተጣላ የሚታረቅበት፣ የተራራቀ የሚገናኝበት እና ለትዳር የበቁ ወጣቶች የሚተጫጩበት ማህበራዊ መድረክ ነው።

ያሆዴ የአዲስ መጀመሪያ ምልክት ነው።
ያለፈውን በምስጋና ተቀብሎ፣ የወደፊቱን በተስፋ የሚመለከትበት፤ ቤተሰብ የሚቀራረብበት፣ ሰላም የሚሰፍንበትና ማንነት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍበት ታላቅ ባህላዊ ቅርስ ነው።

የቀደምት አባቶች በጥልቅ ጥበብና ማስተዋል የቀመሩትን ይህን የአዲስ ዘመን፣ የምስጋናና የተስፋ በዓል ማንነቱን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው።

✍️ ናኒ ከሆሳዕና

#ያሆዴ #ሀዲያ #የኢትዮጵያባህል #የባህልቅርስ #የአዲስዘመን ​

Visit hadiyaHadiya zone Government CommunicationH Visit Ethiopia Tours Media
05/12/2025

Visit hadiya
Hadiya zone Government CommunicationH
Visit Ethiopia Tours Media

Visit  Hadiya Hadiya zone Government CommunicationVisit Ethiopia Tours Media
02/12/2025

Visit Hadiya
Hadiya zone Government Communication
Visit Ethiopia Tours Media

 ሆሳዕና Visit  Hadiya   ,,🇪🇹🇪🇹
29/11/2025


ሆሳዕና
Visit Hadiya
,,🇪🇹🇪🇹

 ሆሳዕና Visit  Hadiya
29/11/2025


ሆሳዕና
Visit Hadiya

Great Ethiopian RunThe 25th Great Ethiopian Run shines today as Africa’s most iconic road race.More than a race, it is a...
23/11/2025

Great Ethiopian Run

The 25th Great Ethiopian Run shines today as Africa’s most iconic road race.

More than a race, it is a symbol of togetherness and the vibrant spirit Ethiopia is known for.

Cheers to 25 years of greatness.
Happy 25th Anniversary to an African Icon!

Visitethiopia.et
Ethiopia Land of Origins

Visit  Hadiya
23/11/2025

Visit Hadiya

Visit  Hadiya   HOSSANA AT A GLANCEHossana Entertainmentሆሳዕና ከተማ/Hossana city
23/11/2025

Visit Hadiya


HOSSANA AT A GLANCE
Hossana Entertainment
ሆሳዕና ከተማ/Hossana city

Address

01
Hossana
2023

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Hadiya posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share