07/09/2026
በክልሉ የገጠር መንገድ ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ማድረግ ይገባል ተባለ፡፡
(ሆሳዕና፣ ጳጉሜ 2/2018) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮግራም የስትሪንግ ኮሚቴ የውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የፕሮግራሙ የ2018 ዓ/ም አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ዝግጅት ተገምግሞ ፀድቋል፡፡
በሪፖርቱ እንደተገለጸው ፕሮግራሙ በአምስት ዓመት ውስጥ በመንገድ ግንባታ፣ ጥገና፣ በተንጠልጣይ ድልድይ ሥራ በፕሮግራሙ በታቀፉ ስምንት ወረዳዎች የሚኖሩ ከ680 ሺህ በላይ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ለማድረግ ከ33 ሺህ በላይ ዜጎችም የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ ወደሥራ ተገብቷል፡፡
በውይይት መድረኩ የስትሪንግ ኮሚቴው አባላት፣ በፕሮግራሙ የተቀረጹ ፕሮጀክቶች የእስካሁን አፈጻጸም የተሻለ መሆኑን ገልጸው ውጤታማነቱን ለማጎልበት እንዲሁም ቀጣይነትና ተከታታይነትን ለማረጋገጥ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡
በፕሮጀክቶቹ አፈጻጸም ሂደት የክልሉን ፀጋዎች በተገቢው መጠቀም በመቻሉ ወጪ በመቀነስ ጥራት ማሳደግ መቻሉም በሪፖርቱ ተገልጿል፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር መሀመድ ኑሪዬ እንደተናገሩት ፕሮግራሙ በገጠር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ መሻሻል ጉልህ አስታጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል፡፡
ከግምገማ መድረኩ የተገኙ ግብዓቶችን የቀጣይ ዕቅድና ትግበራ አካል በማድረግ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት ይሠራል ሲሉም በአጽንኦት ተናግረዋል፡፡
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩርን በበኩላቸው እንደገለጹት ፕሮግራሙ በገጠር የግብርና፣ የትምህርት፣ የጤና ሥርዓትን በማሻሻልና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የተቀናጀ የገጠር ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡
በፕሮግራሙ ዓላማ፣ ዕቅድና ማስፈጸሚያ ስልቶች ላይ ግንዛቤ መፍጠርና የህብረተሰብ ባለቤትነትን መረጋገጥ እንዲሁም ውጤት ተኮር የሀብት አጠቃቀም ሥርዓት በቀጣይ በትኩረት ሊሠራ ይገባል ብለዋል፡፡
በአሳምነው ተከተል
የቢሮውን ተጨማሪ መረጃዎች ለማግኘት ‼️
📌 በዌብሳይት https://www.cergcab.et/
📌በቴሌግራም https://t.me/CERGCAB
📌 በፌስቡክ https://www.facebook.com/profile.php?id=100070605291100&mibextid=ZbWKwL
📌 በቲውተር https://twitter.com/CabCerg2678
📌 በቲክቶክ tiktok.com/
📌 በዩቲዩብ https://youtube.com/...
📌 በኢንስታግራም https://www.instagram.com/cergcab/profilecard/?igsh=MWNseXBlaW05dnM3MA==
አማራጮችን ይጠቀሙ!
ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን! See less