Hossana City Administration Communication affairs Office Media

Hossana City Administration Communication affairs Office Media Giving constructive ideas about the city

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት  የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮ...
02/09/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ፕሮጀክቶችን ተመለከቱ

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም

ወጣቶቹ በክልሉ በነበራቸው ቆይታ ግንባታቸው በስድስት ወራት ብቻ የተጠናቀቁ የልማት ፕሮጀክቶችን ተመልክተዋል።

የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት፣የመሰብሰቢያ አዳራሽ እና ቤተ መንግስት ወጣቶቹ ከተመለከቷቸው የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ወሰን ተሻጋሪ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ልኡካን ቡድን በክልሉ ልዩ ልዩ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እያከናወነ ይገኛል።

ዘገበው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነዉ ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ስራ ዕቅድ ክንውን አፈፃፀምና የ2019 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ላይ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል ።የዕለቱ ...
02/09/2026

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት ስራ ዕቅድ ክንውን አፈፃፀምና የ2019 ዓ.ም መሪ ዕቅድ ላይ የምክክር መድረክ እያካሄደ ይገኛል ።

የዕለቱ ዕቅድ ክንውን አፈፃፀምና ሪፖርት በጽ/ቤቱ የልማት ዕቅድ አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ተገኔ ሰዶሮ አማካይነት እየቀረበ ይገኛል ።

"አንድነት ለፅዳት፤ትጋት ለአገልግሎት ፤ወሳኔ ለልማት!!"በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው መድረክ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት ስራ ዕቅድ ክንውን አፈፃፀምና የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግም ተገልጿል ።

በመድረኩም የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ፣የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ፋንታሁን ሊረንሶ፣የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደጉ ከባሞ እንድሁም የከተማው ስራ አስፈፃሚዎች

የዞን፣የከተማና የቀ በሌ የመንግስትና የፓርቲ የስራ ሀላፊዎች፣የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።
ጌታቸው ደስታ
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም

አቶ ማቴዎስ አኒዮ የሀድያ ዞን አስፈጻሚ አካላትን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቀረቡ በሆሳዕና ከተማ መካሄድ የጀመረው የሀድያ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 14ኛ...
01/09/2026

አቶ ማቴዎስ አኒዮ የሀድያ ዞን አስፈጻሚ አካላትን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቀረቡ

በሆሳዕና ከተማ መካሄድ የጀመረው የሀድያ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 14ኛ የሥራ ዘመን፣ 27ኛ መደበኛ ጉባኤ በሁለተኛ ቀን ውሎው ቀጥሎ እያካሄደ ይገኛል።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም

በጉባኤው የሀድያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ የዞኑን መንግስት አስፈጻሚ አካላት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ አኒዮ ካቀረቡት ሪፖርት መካከል ዋና ዋናዎቹ፦

✅ በግብርና ዘርፍ፦ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተደረገው ጥረት 156 ሺህ 502 ሄክታር መሬት በዋና ዋና ሰብሎች በዘር በመሸፈን 7 ሚሊዮን 533 ሺህ 898 ኩንታል ምርት መሰብሰብ ተችሏል። በተጨማሪም 128 ሺህ 577 ነጥብ 5 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ተሰራጭቷል።

✅ በኢንቨስትመንት ዘርፍ፦ 2 ሺህ 35 ሄክታር መሬት በምዕራብ ሶሮ፣ በግቤ፣ በምስራቅ ባዳዋቾ፣ በአነሌሞ እና በጎምቦራ ወረዳዎች እንዲሁም በጊምቢቹና በቦኖሻ ከተማ አስተዳደሮች ለኢንዱስትሪ የሚሆን መሬት ለባለሀብቶች ቀርቧል።

✅ በከተሞች ልማት፦ ከተሞችን ጽዱ፣ ምቹና ለኢንቨስትመንት ሳቢ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ተከናውነዋል። ለአብነትም በሆሳዕና ከተማ እየተሰራ ባለው 35.5 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት ለወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ተጨባጭ ለውጥ መታየቱ ተጠቅሷል።

✅ በትምህርት ዘርፍ፦ በበጀት ዓመቱ በክልል ደረጃ ከተሰጠው ትኩረት ጋር ተያይዞ በዞኑ የተሻለ ውጤት የተመዘገበ ሲሆን፤ በ6ኛ ክፍል ከፈተና የተቀመጡ ተማሪዎች 79.4 ከመቶ፣ ከ8ኛ ክፍል ደግሞ 96.7 ከመቶ የሚሆኑት 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ውጤት በማስመዝገብ ወደ ቀጣይ ክፍል ተሸጋግረዋል።

✅ በጤና እና መሠረተ ልማት፦ የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሁሉም መዋቅሮች "አንድ ፕሮጀክት ለአንድ ወረዳ" መርህ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፤ በእናቶችና ሕፃናት ጤና አጠባበቅ ላይም በትኩረት ተሰርቷል።

✅ በገቢና የኑሮ ውድነት፦ የዞኑን የገቢ አማራጮች አሟጦ ለመጠቀም የተሰራ ሲሆን፤ የኑሮ ውድነትን ለማቃለል በከተሞች የሰንበት ገበያ ቦታዎችን የማስፋት ሥራ ተከናውኗል።

✅ በበጎ ፈቃድና የሥራ ዕድል ፈጠራ፦ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተከናወኑ ተግባራት ከመንግሥት ይወጣ የነበረውን 66 ሚሊዮን 533 ሺህ 761 ብር በላይ ማዳን ተችሏል። በተጨማሪም ከ129 ሺህ በላይ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ተለይተው ከ45 ሺህ በላይ ለሚሆኑት በቋሚነትና በጊዜያዊነት የሥራ ዕድል ተፈጥሯል።

✅ በሰላምና ፀጥታ፦ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ከ3 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጥቷል።

በመጨረሻም ዋና አስተዳዳሪው በዞኑ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች የሀሰት ዜናዎችን እና የጥላቻ ንግግሮችን የሚያሰራጩ አካላት መበራከታቸው በልማትና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መሆኑን በመጠቆም፣ ምክር ቤቱ አቅጣጫ እንዲያስቀምጥ ጠይቀዋል።
ዘገባው የዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው

ምክር ቤቶች የአስፈጻሚ አካላትን አፈጻጸም በመከታተልና በመገምገም የህዝብ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የማድረግ ሚናቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀድያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ...
01/09/2026

ምክር ቤቶች የአስፈጻሚ አካላትን አፈጻጸም በመከታተልና በመገምገም የህዝብ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ የማድረግ ሚናቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የሀድያ ዞን ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ እቴነሽ ሙሉጌታ ገለፁ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም

አፈ-ጉባኤዋ ይህንን ያሉት ዛሬ በሆሳዕና ከተማ መካሄድ በጀመረው የሀድያ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር፣ 14ኛ የሥራ ዘመን 27ኛ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ነው።

ወ/ሮ እቴነሽ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት፤ ምክር ቤቶች የአስፈጻሚ አካላትን የሥራ እንቅስቃሴ በመከታተልና በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን ያጠናክራሉ፤ አፈጻጸማቸው ደካማ የሆኑ አሰራሮች ደግሞ እንዲታረሙ አቅጣጫ ይሰጣሉ።

አክለውም የመንግስትና የህዝብ ሀብት በአግባቡ ለልማት መዋሉን ማረጋገጥና የህዝብ ሰላምና ፀጥታ እንዲሰፍን ማድረግ የምክር ቤቶች ዋነኛ ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።

በዞኑ በዜጋ ተኮር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተለያዩ ገቢዎችን በመሰብሰብ የበርካታ አቅመ-ደካሞች ቤቶች መገንባታቸውን የጠቀሱት አፈ-ጉባኤዋ፤ በሌላ በኩል የሊች ጎጎ አዳሪ የልህቀት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ያስመዘገበው ከፍተኛ ውጤት በዞኑ በትምህርት ዘርፍ የታየውን አበረታች ለውጥ የሚያስረዳ መሆኑን ገልጸዋል።

የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በገቢ አሰባሰብ ረገድ የታየው አበረታች እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም አሳስበዋል።

በመጨረሻም ምክር ቤቱ የሀድያ ዞን 4ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 26ኛ መደበኛ ጉባኤ አጠቃላይ አፈፃፀምን በጥልቀት መርምሮ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
ዘገባው የዞን ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነዉ

በሆሳዕና ከተማ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገው እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ የአመራር አካላት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ ።የሆሳዕና ከተማ የአመራር ፑል የማዕከላዊ ኢትዮጵ...
01/09/2026

በሆሳዕና ከተማ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገው እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ የአመራር አካላት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገለፀ ።

የሆሳዕና ከተማ የአመራር ፑል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የኢንስፔክሽን ቡድን አባላት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የስካሁን ዕቅድ አፈፃፀም ያደረጉት የመስክ ምልከታ ግብረ መልስ ተከትሎ የውይይት መድረክ አካሂደዋል ።
የውይይት መድረኩ የመሩት የሆሳዕና ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሊረንሶ እንደገለጹት በከተማው ከተረጅነት ወደ ምርታማነት በስካሁን አፈፃፀም በጉድለት የታዩ ተግባራት ፈጥኖ በማረም ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ተረጂነት ለመቀነስ የተያዘው ግብ ማሳካት ከአመራሩ ይጠበቃል ።

አክለውም ከተረጅነት ወደ ምርታማነት የተያዘው ግብ ለማሳካት ከዛሬ ጀምሮ በቀበሌ ደረጃ የንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው መንቀሳቀስ እንደሚጠበቅባቸውም ኃላፊው አሳስበዋል ።

የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በከተማው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በስካሁን ዕቅድ አፈፃፀም ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ የታዩ ጉድለቶች በማረም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

በመድረኩ ላይ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀዲያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት የ2019 ዓ.ም ዕቅድ ማስፈፀሚያ አቅጣጫ እና የንቅናቄ ከተማዊ ሰነድ በከተማው የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ በአቶ ተመስገን ወርቁ እና የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትአዋጅ ቁጥር 1389/2017 የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ በከተማው ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ በአቶ ተካልኝ አቦ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።

በመጨረሻም በከተማው ከጳጉሜ -1 እስከ ከጳጉሜ -5 በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ኦረንቴሽን በመስጠት የውይይት መድረኩ ተጠናቋል ።
በነስሩ ባደዢ

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም

ለትክክለኛ መረጃ ከታች ሊኩን በመጫን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ያገኙናል ።
Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063559671902&mibextid=ZbWKwL
Telegram
https://t.me/hossanacommunicatin
Twitter
https://x.com/gov_city86471?t=_HpdGUXInnC_gtHHDh_yRw&s=09

Tiktok
http://tiktok.com/.city.govt
YouTube ሀ
https://youtube.com/?si=ps9RX4IRgOpxjF_D
Instagram
https://www.instagram.com/hossanacity?igsh=aTBiY2JwdTlzN3Vl
WhatsApp
https://chat.whatsapp.com/GoZK5IRGk1B5gxAqHqnFeU

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል የኢንስፔክሽን ቡድን አባላት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት  የስካሁን ዕቅድ አፈፃፀም በሆሳዕና ከተማ ያደረጉት ምልከታ ግብረ መልስ ለከተማው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት...
31/08/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል የኢንስፔክሽን ቡድን አባላት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የስካሁን ዕቅድ አፈፃፀም በሆሳዕና ከተማ ያደረጉት ምልከታ ግብረ መልስ ለከተማው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት አብይ ኮሚቴ አቀረቡ ።

በመድረኩ ላይ የኢንስፔክሽን ቡድኑ አባላት ወ/ሮ አምሪያ ሲራጅ እና አቶ ተስፋዬ ኤርሰዶ ፣የሆሳዕና ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሊረንሶ እና የአብይ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል ።

የኢንስፔክሽን ቡድኑ አባላት የተግባር አፈፃፀም በቀበሌ ደረጃ ምልከታ ያደረጉ ሲሆን በአፈፃፀም የታዩ ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል እና በጉድለት የታዩ አፈፃፀሞች ፈጥኖ በማረም ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ተረጂነት ለመቀነስ የተያዘው ግብ ለማሳካት ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊቀሳቀሱ እንደሚገባም አሳስበዋል ።

የሆሳዕና ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን ሊረንሶ እንደገለጹት በከተማ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገው እንቅስቃሴ የእስካሁን አፈፃፀም ወደ ውጤት ለማሸጋገር የኢንስፔክሽን ቡድኑ አባላት ምልከታና ግብረመልስ አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሽጉጤ በበኩላቸው የኢንስፔክሽን ቡድኑ አባላት ግብረ መልስ ተቀብሎ በጉድለት የታዩ አፈፃፀሞች ፈጥኖ በማረም በከተማው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት የሚደረገው እንቅስቃሴ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል።
በነስሩ ባደዢ

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም

ለትክክለኛ መረጃ ከታች ሊኩን በመጫን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ያገኙናል ።
Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063559671902&mibextid=ZbWKwL
Telegram
https://t.me/hossanacommunicatin
Twitter
https://x.com/gov_city86471?t=_HpdGUXInnC_gtHHDh_yRw&s=09

Tiktok
http://tiktok.com/.city.govt
YouTube ሀ
https://youtube.com/?si=ps9RX4IRgOpxjF_D
Instagram
https://www.instagram.com/hossanacity?igsh=aTBiY2JwdTlzN3Vl
WhatsApp
https://chat.whatsapp.com/GoZK5IRGk1B5gxAqHqnFeU

የሀድያ ዞን ምክር ቤት 27ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከነሐሴ 26 እስከ 27/2018 ዓ.ም ያካሂዳል።።።ሆሳዕና፣ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (ሀድያ ዞን ኮሙኒኬሽን)።።።የሀድያ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ...
31/08/2026

የሀድያ ዞን ምክር ቤት 27ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከነሐሴ 26 እስከ 27/2018 ዓ.ም ያካሂዳል

።።።ሆሳዕና፣ ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም (ሀድያ ዞን ኮሙኒኬሽን)።።።

የሀድያ ዞን ምክር ቤት 4ኛ ዙር 14ኛ የሥራ ዘመን 27ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከነሐሴ 26 እስከ 27 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚያካሂድ የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ እቴነሽ ሙሉጌታ አስታወቁ።

ዋና አፈ ጉባኤዋ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ ምክር ቤቱ በሁለት ተከታታይ ቀናት ቆይታው በሚቀርቡለት ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ላይ በጥልቀት ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል።

ምክር ቤቱ በጉባኤው በሚከተሉት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ይመክራል፦

👉የ4ኛ ዙር 13ኛ የሥራ ዘመን 26ኛ መደበኛ ጉባኤ እና የ7ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ቃለ ጉባኤዎችን መርምሮ ማፅደቅ፤

👉የአስፈፃሚ መስሪያ ቤቶችን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እንዲሁም በልማትና መልካም አስተዳደር ረገድ በተከናወኑ ተግባራት ላይ በጥልቀት መወያየት፤

👉የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅዶችና አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቶ ማፅደቅ፤

👉የሀድያ ዞን ምክር ቤትን የ2018 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድና በጀት መርምሮ ማፅደቅ፤

👉የዞኑን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መርምሮ ማፅደቅ፤

👉የዞኑን የ2019 አጠቃላይ በጀት መርምሮ ማፅደቅ።

ለዚሁ መደበኛ ጉባኤ ዝግጅቶች በሙሉ መጠናቀቃቸውን ዋና አፈ ጉባኤዋ ክብርት ወ/ሮ እቴነሽ ሙሉጌታ አረጋግጠዋል።

ምንጭ የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ከክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የካፍ ‘ዲ’ ላይሰንስ (CAF D License) ...
31/08/2026

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ከክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆየው የካፍ ‘ዲ’ ላይሰንስ (CAF D License) የአሰልጣኝነት ስልጠና እየተካሄደ ይገኛል።

​በስልጠናው መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ረዳት ተጠሪና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ፍሰሓ ታደሰ እንደገለፁት፣ የካፍ ‘ዲ’ ላይሰንስ የአሰልጣኞች ስልጠና በዓይነቱ ልዩና በከተማው ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀ ነው።

​አክለውም ስልጠናው ስፖርታዊ ዲስፕሊን ተላብሰው በዕውቀት፣ በክህሎት፣ በታክቲክና በቴክኒክ የበቁ አሰልጣኞችን ለማፍራት የሚረዳ በመሆኑ ሰልጣኞች በቁርጠኝነትና በቅንጅት መከታተል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አቶ ፍሰሓ አያይዘውም «ይህ ስልጠና የነገ የካፍ ሲኒየር ኢንስትራክተሮች የምትሆኑበት መንገድ ጅማሮ በመሆኑ፣ ከሁነቱ በሚገኘው ዕውቀትና ክህሎት የከተማችንን እግር ኳስ ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ያለው ፋይዳ ከፍተኛ ነው» ብለዋል።

​የሀዲያ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ክብሩ ዮሐንስ በበኩላቸው በዘርፉ በርካታ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በተለይም በታዳጊ ወጣቶች ልማት ላይ ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆናቸውን በመጠቆም፣ ስልጠናው በዞኑ የሚታየውን የእግር ኳስ አሰልጣኞች እጥረት ይቀርፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

​የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኪበሞ ሰለሞን በበኩላቸው፣ ስልጠናው የእግር ኳስ መሠረታዊ ቴክኒክና የማስተማር ክህሎትን የሚፈጥር እንዲሁም መሠረታዊ የአሰልጣኝነት ዕውቀትን የሚያስጨብጥ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ኪበሞ አክለውም ስልጠናው በስፖርቱ ዘርፍ ለሀገርና ለአህጉር የሚተርፉ ስፖርተኞችን ለማፍራት ከፍተኛ ወሳኝነት እንዳለው በመግለፅ፣ ሰልጣኞች ስፖርታዊ ስብዕናን በመላበስ መከታተል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

​የአሰልጣኝነት ስልጠናው በክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የካፍ ሲኒየር ኢንስትራክተር አቶ ዓለምባንተ ማሞ እየተሰጠ ይገኛል።
#በአየለ ደልከሶ
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም

ለትክክለኛ መረጃ ከታች ሊኩን በመጫን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ያገኙናል ።
Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063559671902&mibextid=ZbWKwL
Telegram
https://t.me/hossanacommunicatin
Twitter
https://x.com/gov_city86471?t=_HpdGUXInnC_gtHHDh_yRw&s=09

Tiktok
http://tiktok.com/.city.govt
YouTube ሀ
https://youtube.com/?si=ps9RX4IRgOpxjF_D
Instagram
https://www.instagram.com/hossanacity?igsh=aTBiY2JwdTlzN3Vl
WhatsApp
https://chat.whatsapp.com/GoZK5IRGk1B5gxAqHqnF

የቦቢቾ ቀበሌ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት< እናት ጤና ሲኖራት ህፃናት በፅዱ አካባቢ ሲያድጉ ህብረተሰባችን ብሩህ ተስፋ ይኖረዋል > በሚል መርህ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ...
31/08/2026

የቦቢቾ ቀበሌ አስተዳደር ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት< እናት ጤና ሲኖራት ህፃናት በፅዱ አካባቢ ሲያድጉ ህብረተሰባችን ብሩህ ተስፋ ይኖረዋል > በሚል መርህ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት አካል የሆነው የፅዳት ዘመቻ አካሄደ ።

በፕሮግራሙ ላይ በሆሳዕና ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ታደሰ፣ የከተማው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ስንታየሁ ምህርከ፣የቦቢቾ ቀበሌ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ደሳለኝ፣ የቦቢቾ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በረከት ታገሰ፣የሴቶች ልማት ህብረት አባላት እና የሴቶች አደረጃጀቶች ተሳታፊ ሆነዋል ።

የቦቢቾ ቀበሌ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ካሰች ደሳለኝ እንደገለጹት የአካባቢያችን ንጽሕና በመጠበቅ እናቶች ህፃናት ከተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች መታደግ እንደሚችል በመጠቆም የፅዳት ዘመቻው የአንድ ቀን ሥራ ብቻ ሳይ የአኗኗር ዘይቤያችን የመጀመሪያው ተግባር ሊሆን ይገባል ።

የቦቢቾ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ በረከት ታገሰ በፅዳት ዘመቻው የተሳተፉ እናቶች በማመስገን በቀበሌው የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት ተግባራት በሁሉም መስክ ተጠናክሮ መቀጠሉን ተናግረዋል ።

የከተማው ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ስንታየሁ ምህርከ በበኩላቸው የግልና የአካባቢያችን ንጽሕና በመጠበቅ ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የሴቶች ሚና ቀላል ግምት የሚሰጠው አለመሆኑን ገልፀው ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በማገዝ የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ለማሳካት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።

በሆሳዕና ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ በረከት ታደሰ ባስተላለፉት መልዕክት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት በአንድ ወቅት ተፈፅመው የሚያበቁ አለመሆናቸውን በመግለፅ የፅዳት ዘመቻና ድጋፍ የሚሹ ወገኖች መርዳት ባህል ለማድረግ ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል ።
በነስሩ ባደዢ

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም

ለትክክለኛ መረጃ ከታች ሊኩን በመጫን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ያገኙናል ።
Facebook
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063559671902&mibextid=ZbWKwL
Telegram
https://t.me/hossanacommunicatin
Twitter
https://x.com/gov_city86471?t=_HpdGUXInnC_gtHHDh_yRw&s=09

Tiktok
http://tiktok.com/.city.govt
YouTube ሀ
https://youtube.com/?si=ps9RX4IRgOpxjF_D
Instagram
https://www.instagram.com/hossanacity?igsh=aTBiY2JwdTlzN3Vl
WhatsApp
https://chat.whatsapp.com/GoZK5IRGk1B5gxAqHqnFeU

በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከተማ አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ፕሮግራም የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ "ያሆዴን" ምክንያት በማድረግ ተካሄደ ።"ፅዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ እናስተላልፍ"በሚል መሪ ቃል የተ...
31/08/2026

በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ከተማ አቀፍ የጽዳት ዘመቻ ፕሮግራም የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ "ያሆዴን" ምክንያት በማድረግ ተካሄደ ።

"ፅዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ እናስተላልፍ"በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የፅዳት ዘመቻው በከተሞች ተጠናክሮ መቀጠሉም ተገልጿል ።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት የሀዲያ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መመሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ አናሞ እንደገለፁት የሀዲያ ብሔር ዘመን መለወጫ "ያሆዴን" ምክንያት በማድረግ በርካታ የውጭና የውስጥ እንግዶች በዓሉን ለማክበር ወደ ከተማው ስለሚመጡ ከፅዳት ዘመቻ ባሻገር ሁሉ አቀፍ ዝግጅቶችም ከወዲሁ መጀመራቸውን ገልጸዋል ።

ፅዳትን ባህል በማድረግ አከባቢያችንና ከተማችንን በየጊዜው በማጽዳትና በማስዋብ ለነዋሪዎችና ለቱሪዝም እንቅስቃሴ ምቹ ፣ውብ፣ሳቢና ማራኪ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል ።

የሀዲያ ዞን ደንና አከባቢ ጥበቃ መመሪያ ኃላፊ አቶ ሰላሙ ደመቀ በበኩላቸው ከተማን ማስዋብ የአንድ ግለሰብ ወይም ተቋም ተግባር ብቻ አለመሆኑን በመግለፅ የሁሉም አካላት የጋራ ቅንጅትና ትብብር ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል ።

በተጨማሪም በከተማው በሁሉም አቅጣጫ የተተከሉ አረንጓዴ አሻራ ችግኞችን በዘላቂነት መጠበቅና መንከባከብ እንደሚገባም አክላው ገልጸዋል ።

የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ማዘጋጀት ቤታዊ የመሠረተ ልማት ማስፈፀም አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊና ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አብነት አባቢያ በዕለቱ በሰጡት አስተያየት "ፅዱ ኢትዮጵያን ለትውልድ እናስተላልፍ"በሚል መሪ ቃል የተጀመረው የከተማ የፅዳት ዘመቻ በሁሉም ቀበሌያት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል ።

የፅዳት ዘመቻ የአንድ ወቅት ተግባር ብቻ ባለመሆኑ ከተማዋን የማስዋብና ለእንግዶችና ነዋሪዎች ምቹ የማድረግ ስራ የዘውትር ተግባር ሆኖ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል ።

በዕለቱም የዞንና ፣የከተማ የመንግስትና የፓርቲ የስራ ሀላፊዎች ፣ወጣቶችና የተለያዩ የከተማው ህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል ።

ጌታቸው ደስታ
የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነሐሴ 25/2018 ዓ.ም

Address

Hossana

Telephone

+251465550930

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Hossana City Administration Communication affairs Office Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share