02/09/2026
የሁምቦ ወረዳ የምክር ቤት የኦዲት ግኝት ዕዳ አስመላሽ ግብረ -ኃይል የ2018 ዓ/ም የአፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ ዉይይት አደረጉ።
ሁምቦ ፦ነሐሴ 17- 2018 ዓ/ም የምክር ቤት የኦዲት ግኝት ዕዳ አስመላሽ ግብረ -ኃይል የ2018 ዓ/ም የእስካሁኑ
አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ዙሪያ ዉይይት አደረጉ።
በመድረኩ የምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ ተስፋዬ ጋንአሞ በቀጣይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ትኩረት በመስጠት የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዶችና የኦዲት ግኝቶችን ለማሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት መረባረብ አለበት በማለት አቅጣጫ አስቀምጧል።
በመቀጠልም እስካሁን የተመለሱ ኦዲት ገንዘብ ላይ ውይይት በማድረግ በሂደቱ ላይ ባጋጠሙ ችግሮች ላይ የጋራ መግባባትን በመፈጠር በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም እንድኖር ሁሉም መረባረብ አለበት ተብሏል።
በግምገማ መድረኩ የወረዳ ዋና አፈጉባኤ ፣ም/አፈጉባኤ ፣የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፈ፣የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፈ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።