03/09/2026
✍️ "ከኤልኒኖ ተፅዕኖ በፊት ክትባትን በማጠናከር የእንስሳት ጤናን እንጠብቅ" በሚል መሪ ቃል ወረዳዊ የእንስሳት ክትባት ዘመቻ በቃይሳ ቀበሌ በይፋ ተጀመረ ።
✅✅ ነሐሴ፦ 28/2018 ዓ.ም
#ዲመካ
✍️ በደቡብ ኦሞ ዞን የሐመር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከVSF Germany ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር "ከኢልኒኖ ተጽዕኖ በፊት ክትባትን በማጠናከር የእንስሳትን ጤና እንጠብቅ" በሚል መሪ ቃል የእንስሳት ክትባት ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል።
✍️ የሐመር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ዛንጋ ኛይታ እንዳሉት እየተካሄደ የሚገኘው የክትባት ዘመቻ በእንስሳቱ ላይ ሊከሰት የሚችለውን በሽታ ቀድሞ ለመከላከል አቅም ያለው መሆኑን በመጠቆም አርብቶአደሩ ያለማስቀረት እንስሳቶቻቸውን ማስከተብ እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
✍️ የክትባቱ ፋይዳ አባሰንጋን ቀድሞ መከላከል የሚያስችል መሆኑን የተናገሩት ዶ/ር ዛንጋ በሽታው ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ ማስከተብ እንዳለበት በማሳሰብ ሊከስት የሚችለውን ኤልኒኖ ለማቋቋም ወሳኝ ነው ብለዋል ።
✍️ የሚሰጠው ክትባት በወረዳው ሁሉም ቀበሌያት (31) እንዲሁም በዲመካ ከተማ አስተዳደር ስር ባሉት አራት(4) ቀበሊያትን ጨምሮ እንደሚካሄድ ዶ/ር ዛንጋ አብራርተዋል።
✍️ በአሁን ሰአት እየተሰጡ ያሉት ክትባት አይነት እና ዶዝ(Dose) አንትራክስ (Anthrax).......... 60,000 Dose፣ Bovine Pastuerellosis (B.P).........50,000 Dose፣ Lumpy Skin Disease(LSD)..........62,000 Dose፣ New Castle Disease Vaccine (ፈንግል)...........5000 Dose አጠቃላይ ድምር(Total Doses):177,000 ዶዝ(Doses ) መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።
✍️ የህክምና ባለሙያዎች እያንዳንዱን ተከታትሎ ክትባት አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸውም ኃላፊው አሳስበዋል።
✍️ የሐመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ጋርሾ እንዳሉት የኤልኒኖ ክስተትን ተከትሎ የእንስሳት በሽታዎች የመከሰት ዕድል ሊገጥም እንደሚችል ያነሱ ሲሆን የዘርፉ ባለሙያዎች ክትባቱን በመስጠት አርብቶ አደሮች ደግሞ እንስሳትን በማስከተብ የድርሻውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
✍️ በማስጀመሪያው መርሃግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሐመር ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ እና ረዳት የመንግስት ተጠሪ የሆኑት አቶ በሱፍቃድ ጎይቲ እንዳሉት የእንስሳት ጤናን መጠበቅ የዘርፉን ምርታማነት በማሳደግ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንደሚያስችል ተናግረዋል።
✍️ ክትባቱን በይፋ ያስጀመሩት የደቡብ ኦሞ ዞን ግብርና መምሪያ ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ምላርገው አዲሱ እንዳሉት አንድም ከብት እንዳይሞት ዕቅድ በመያዝ በሁሉም የዞናችን መዋቅሮች ክትባት ማስጀመራቸውን በመግለፅ ክትባቱ አባሰንጋ የሚባለውን በከብቶች ላይ የሚከሰተውን ገዳይ በሽታ ለመከላከል የሚያስችል ነው ብለዋል ።
✍️ አንድም ከብት ህክምና አገልግሎት ሳያገኝ መቅረት እንደሌለበት አፅንኦት የሰጡት አቶ ምላርገው የአየር ንብረት ለውጥና የኢልኒኖ ተጽዕኖ መቋቋም የሚችል አቅም መገንባት አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል ።
✍️ የመምሪያ ኃላፊው አክለውም እደተናገሩት የዕንስሳቱን ጤና በተጠናከረ ሁኔታ ለመጠበቅ ወረዳው በበጀት አስደግፎ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ብር በመያዙ የሐመር ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ የሆኑትን አቶ ሳሙኤል ጋርሾን ከልብ በማመስገን ሌሎች ወረዳዎች ከዚህ ሊማሩ ይገባል በማለት የሚሰጡ የመድሃኒት ዶዞች በበጀት በማስደገፍ ትኩረት በተሰጠባቸው መዋቅሮች ላይ እንደሚደረግ አቶ ምላርጋቸው ተናግረዋል።
✍️ ዘመቻው ከዛሬው ዕለት ተጀምሮ በሁሉም ቀበሌያት ክትባት መጀመሩንና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኃላፊው አፅንኦት ሰጥተዋል።
✍️ በስተመጨረሻም ይህ የክትባት ዘመቻ እንዲሳካ በሎጂስቲክ ድጋፍ እያደረገ የሚገኘውን VSF Germany ግብረሰናይ ድርጅትን ዋና አስተዳዳሪው ከልብ አመስግነዋል።
✍️ በክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መረሃ ግብሩ ላይም የደቡብ ኦሞ ዞን ፊት አመራሮች፣ የሐመር ወረዳ እና የዲመካ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የሐመር ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ ኃላፊዎች፣ የዞን እና የወረዳ ግብርና ጽ/ቤት እንስሳት ጤና ዘርፍ ባለሙያዎች ተገኝተዋል ።