Awi Administrative Zone Revenue Department /አዊ አስተዳደር ዞን ገቢዎች መምሪያ/

  • Home
  • Ethiopia
  • Injibara
  • Awi Administrative Zone Revenue Department /አዊ አስተዳደር ዞን ገቢዎች መምሪያ/

Awi Administrative Zone Revenue Department /አዊ አስተዳደር ዞን ገቢዎች መምሪያ/ ይህ የአዊ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ፌስቡክ ገጽ ነዉ

12/05/2026

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ገቢዎች መምሪያ በቀን 04/09/2018 ዓ.ም ከወረዳ እና ከተማ አስ ገቢ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ ስራ ሂደት አስተባባሪዎች፣ ዞን ሙያተኞች እንዲሁም አጋር አካላት ጋር የ9 ወራት እቅድ አፈፃፀም በእንጅባራ ከተማ በብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አዳራሽ እየገመገመ ይገኛል። በተጨማሪም በቀን ገቢ ጥናት ዙሪያ ስልጠና የሚሰጥ ይሆናል። መድረኩ በዉጤታማነት እንደሚጠናቅ ይጠበቃል። መድረኩ እንደቀጠለ ይገኛል።

07/02/2026
03/02/2026

ባለፉት ወራት 45 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰበሰበ

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት እስከ ጥር 22/2018 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 45 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የቢሮው የግብር ትምህርትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ታዘባቸው ጣሴ ገለጹ፡፡

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ የክልሉ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ በመሰብሰብ የክልሉ ህዝብ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ ለማሰጠት በርትቶ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 ዓ.ም ከመደበኛ እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ በድምሩ 100 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ እስከ ጥር 22/2018 ዓ.ም ከመደበኛ ገቢ 40 ነጥብ 2 እና ከከተማ አገልግሎት ገቢ 5 ነጥብ 4 በድምሩ 45 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወይም የእቅዱን 45.6 በመቶ መሰብሰብ እንደቻለ ተናግረዋል፡፡

የተሰበሰበው ገቢ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተሰበሰበው ገቢ አኳያ ሲነፃፀር 15 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር እድገት እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ሰሜን ሽዋ ዞን ገቢዎች መምሪያ፣ ወልቃይት ጠገዴ ሴቲት ሁመራ ገቢዎች መምሪያ፣ወልዲያ ከተማ ገቢዎች መምሪያ፣ማዕከላዊ ጎንደር ገቢዎች መምሪያ፣ኦሮሞ ብሔረሰብ ገቢዎች መምሪያ፣ አዊ ብሔረሰብ ገቢዎች መምሪያ እና ደብረ ብርሃን ከተማ ገቢዎች መምሪያ በቅደም ተከተላቸው የእቅዳቸውን ከ50.6 እስከ 47.04 በመቶ ባለው ውስጥ በመፈፀም በተሻለ አፈፃፀም ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ ገቢዎች መምሪያ፣ ደሴ ከተማ እና ሰሜን ጎንደር ገቢዎች መምሪያ ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ የሚያሻቸው በአፈፃፀም በጣም ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዞኖች እንደሆኑ አብራርተዋል።

ቢሮው የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ዘመናዊ ለማድረግ የኤሌክትሮኒክ ታክስ አስተዳደር ስርዓት (ኢ-ታስ) የተሰኘ ሲስተም በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስለምቶ እየተገበረ ሲሆን በክልሉ ካሉ 257 የታክስ ማዕከላት ውስጥ 225 ሲስተሙን መጠቀም መጀመራቸውን ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በ2018 የታቀደው የገቢ እቅድ በስኬት እንዲሳካ ቢሮው የገቢ እቅዱን ለከፍተኛ አመራሩ፣ ለአጋርና ባለድርሻ አካላት እና ከገቢ ተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ተደጋጋሚ መድረክ ተፈጥሮ የእቅዱ ባለቤት እንዲሆኑ የማድረግ ስራ መሰራቱን ተናረዋል፡፡

በአጠቃላይ ውጤቱ በጥንካሬ የሚገለፅ ቢሆንም ግን አሁንም በቀጣይ የደረሰኝ አቆራረጥ ላይ ብዙ ስራ መስራት እንዳለበት ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፡- ሲሳይ አስማማው
ፎቶ፡- ማስተዋል ሁነኛው

አስተያየት እና ጥያቄ ቢኖርዎ ከዚህ ገፅ በተጨማሪ እነዚህን አድራሻዎች ይጠቀሙ
በፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/AmraNews
https://www.facebook.com/profile.
በቴሌግራም:- Amhara Region revenue bureau
በዩትዩብ:- https://www.youtube.com/ ገቢያችን
እንዲሁም አስተያየትና ጥቆማ በ 9504 ይደውሉ
መደበኛ ስልክ ቁጥሮች 058 220 57 49/ 09 47

27/11/2025

ለሚመለከተው ሁሉ
ገቢ ለመሰብሰብ በሚል ምክኒያት የተዘረጉ ኬላዎች የተነሱ መሆኑን እናሳውቃለን።

Address

Injibara

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awi Administrative Zone Revenue Department /አዊ አስተዳደር ዞን ገቢዎች መምሪያ/ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share