Injibara Communication

Injibara Communication Injibara communication

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር  ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ተሸላሚ ሁኗል ።ቡድን ከሁሉም ዞኖች ጋር ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣት የዋንጫና የምስክ...
04/09/2026

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን በ2018 በጀት ዓመት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ተሸላሚ ሁኗል ።

ቡድን ከሁሉም ዞኖች ጋር ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣት የዋንጫና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ መሆን ችሏል ።

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ማዕድን  መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ በተካሄደው የሥራ አፈጻጸም ምዘና 3ኛ ደረጃን በመያዝ  የዕውቅና ስርቲፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።
04/09/2026

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ማዕድን መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ በተካሄደው የሥራ አፈጻጸም ምዘና 3ኛ ደረጃን በመያዝ የዕውቅና ስርቲፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።

ፓራዳይዝ አካዳሚ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች የደብተር ድጋፍ አደረገ።በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው ፓራዳይዝ አካዳሚ ት/ቤት የትምህርት አቅምን ለመደገፍ እና ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስች...
03/09/2026

ፓራዳይዝ አካዳሚ ትምህርት ቤት ለተማሪዎች የደብተር ድጋፍ አደረገ።
በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው ፓራዳይዝ አካዳሚ ት/ቤት የትምህርት አቅምን ለመደገፍ እና ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት የሚያስችል አብነት የሚሆን ተግባር አከናወነ። ትምህርት ቤቱ በ2019 በጀት ዓመት በካፒታል አቅም ውስንነት ምክንያት የመማሪያ ቁሳቁሶችን ሙሉ በሙሉ ማሟላት ለቸገራቸው ተማሪዎች ድጋፍ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ትምህርት ቤቱ ለተማሪዎች የሚሆን ጠቅላላ 10 ደርዘን ደብተሮችን በመለገስ ተማሪዎች ያለምንም ስጋት በትምህርታቸው ላይ እንዲያተኩሩ እገዛ አድርጓል።
ይህ በጎ ፈቃድና ማህበራዊ ኃላፊነት የተሞላበት ተግባር ችግር ውስጥ ያሉ ተማሪዎችን እርስ በእርስ በመረዳዳት እና በመደጋገፍ የአገር ተረካቢ ትውልድን ለማፍራት ሰፊ አስተዋጽኦ እንዳለው ተገልጿል። ፓራዳይዝ አካዳሚ ት/ቤት በቀጣይነትም መሰል የድጋፍ እና የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

የእንጅባራ ከተማና የቀበሌ ም/ቤቶች የዕቅድ አፈፃፀምና የትውውቅ መድረክ ተካሄደ።እንጅባራ፡ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም (የእንጅባራ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን)የእንጅባራ ከተማ ም/ቤት እና...
03/09/2026

የእንጅባራ ከተማና የቀበሌ ም/ቤቶች የዕቅድ አፈፃፀምና የትውውቅ መድረክ ተካሄደ።
እንጅባራ፡ ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም (የእንጅባራ ከተማ መንግስት ኮሙኒኬሽን)
የእንጅባራ ከተማ ም/ቤት እና የቀበሌ ም/ቤት የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ከባለድርሻ አካላት ጋር የመተዋወቂያ መድረክ በከፍተኛ ድምቀትና ተሳትፎ ተካሄዷል።

በመድረክ ላይ የተገኙት የእንጅባራ ከተማ ም/ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፍቅሬ በፈቃዱ እንደተናገሩት፣ ባለፈው በጀት ዓመት ህዝብን ማዕከል ባደረጉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

አፈ ጉባኤዋ አክለውም በቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመትም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የከተማዋን ሁለተናዊ ዕድገት ለማፋጠን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚከናወኑ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከተማዋ በፈጣን ዕድገት ጎዳና ላይ የምትገኝ መሆኗን ያነሱት የከተማዋ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፍቅሬ በፈቃዱ፣ ባለፉት ዓመታት በመሠረተ ልማት፣ በግብርና ስራዎች፣ እንዲሁም በወጣቶችና ማህበራዊ አገልግሎቶች ዘርፎች የታዩት ለውጦች የሚበረታቱ መሆናቸውን አንስተዋል።

አፈ ጉባኤዋ ባሰመሩበት አቅጣጫ መሠረት፣ በ2019 በጀት ዓመት የከተማውን ገጽታ ከፍ የሚያደርጉ የልማት ስራዎችን ማስፋፋት፣ የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ፍትሃዊነትን ማረጋገጥ፣ እንዲሁም የህብረተሰቡን ተሳትፎ በባለቤትነት መንፈስ ማጠናከር የትኩረት ማዕከል እንደሚሆኑ አመላክተዋል።

ይህ ሁሉ ጥረት ተቀናጅቶ የእንጅባራ ከተማን ሁለንተናዊ ብልጽግና እውን ለማድረግ የተጀመረው ጉዞ በቁርጠኛ መንፈስ እንዲቀጥል ከተማ አስተዳደሩ እና ህብረተሰቡ በትብብር እየሠሩ ይገኛልም ብለዋል።
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላትም በቀረቡት እቅዶች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ የበኩላቸውን አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ በቀጣይ ዓመት ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች አጋርነታቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።

አሱሪቴ በዓል በደማቅ ሁነት በእንጅባራ ከተማ ተጀመረ!የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ኢ/ር ማስተዋል ፈንቴ የዘንድሮውን የአሱሪቴ በዓል በድምቀት...
03/09/2026

አሱሪቴ በዓል በደማቅ ሁነት በእንጅባራ ከተማ ተጀመረ!
የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ኢ/ር ማስተዋል ፈንቴ የዘንድሮውን የአሱሪቴ በዓል በድምቀትና በደማቅ ሁነት ዛሬ በይፋ ከፈቱ።

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ከነሐሴ 28 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚከበረውን ታሪካዊና ባህላዊ የአሱሪቴ በዓል ዛሬ በይፋ ጀምሯል።

የእንጅባራ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ኢ/ር ማስተዋል ፈንቴ በበዓሉ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፤ አሱሪቴ የህዝብን አብሮነት፣ ፍቅርና ማህበራዊ ትስስር የሚያጠናክር ታላቅ እሴት ነው ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም ለሶስት ቀናት በሚቆዩትና በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች፣ የኪነ-ጥበብ ስራዎችና ውይይቶች በሚታጀቡት የበዓል ቀናት በርካታ የባህል ባለሙያዎች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች በስፍራው በመገኘት በዓሉን በባለቤትነት ሊያደምቁት እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር መንገድ፣ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ በተካሄደው የሥራ አፈጻጸም ምዘና 3ኛ ደረጃን በመያዝ  የዕውቅና ስርቲፊኬት ተሸላሚ ሆኗ...
03/09/2026

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር መንገድ፣ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ በተካሄደው የሥራ አፈጻጸም ምዘና 3ኛ ደረጃን በመያዝ የዕውቅና ስርቲፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የገቢዎች መምሪያ በበጀት ዓመቱ አፈፃፀም 1ኛ ወጣ።የላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት አስደናቂ ውጤት አስመዘገበ! የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት...
02/09/2026

የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የገቢዎች መምሪያ በበጀት ዓመቱ አፈፃፀም 1ኛ ወጣ።
የላቀ ብቃትና ቁርጠኝነት አስደናቂ ውጤት አስመዘገበ! የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር የገቢዎች መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ከተወዳደሩት ዞኖች መካከል ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣት የድል አክሊልን ተቀዳጅቷል።

የዚህ ታላቅ ስኬት ባለቤት የሆኑት የመምሪያው ኃላፊ አቶ ፈጠነ ጥላሁን ሽልማቱን በተቀበሉበት ወቅት ያስተላለፉት መልእክት የጋራ ትጋትን የሚያንፀባርቅ ነው። ኃላፊው «ለተገኘው የላቀ ውጤት በየደረጃው ያለው የሥራ አመራር፣ መላው ባለሙያዎች እንዲሁም አጋር አካላት ያደረጉት አስተዋጽኦ የላቀና አርአያነት ያለው ነው» ብለዋል፤ ላደረጉት አስተዋጽኦም ከልብ የመነጨ እንኳን ደስ አላችሁ! መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

🏆 ልዩ ተሸላሚ​በአደጋ ሥጋት ቅነሳ ተግባራት—በተለይም በክልሉ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ በማቋቋምና በተያያዥ በጎ ሥራዎች የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱት የአዊ ብሔረሰብ አስተ...
02/09/2026

🏆 ልዩ ተሸላሚ

​በአደጋ ሥጋት ቅነሳ ተግባራት—በተለይም በክልሉ በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ በማቋቋምና በተያያዥ በጎ ሥራዎች የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱት የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሠርክዓለም አያሌው የመርሐ ግብሩ ልዩ ተሸላሚ በመሆን የእውቅና የምስክር ወረቀትና ማበረታቻ ተበርክቶላቸዋል። 👏✨

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙ ከክልሉ አጠቃላይ ዞኖች ጋር ተወዳድሮ ሁለተኛ (2ኛ) በመውጣት የላፕ...
02/09/2026

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን በ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸሙ ከክልሉ አጠቃላይ ዞኖች ጋር ተወዳድሮ ሁለተኛ (2ኛ) በመውጣት የላፕቶፕ እና የክብር ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል።
ጠንካራ ተቋማዊ ግንባታን ከመገንባት ጀምሮ ሐቀኝነትን፣ ቁርጠኝነትን እና መልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ የተደረገው ጥረት ፍሬ አፍርቶ ዛሬም ለብሄረሰብ አስተዳድራችን ስም ከፍተኛ ክብርን አጎናጽፎናል።
ይህ ድል የጋራ ትጋት፣ የቁርጠኝነት እና የየዕለት ልፋት ውጤት ነው። ለተከበሩ የኮሚሽኑ አመራሮች፣ አባላት እና መድረኩን ለዚህ ላበቁ ባለድርሻ አካላት ሁሉ፦ እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ በተካሄደው የሥራ አፈጻጸም ምዘና 1ኛ ደረጃን በመያዝ ዘመናዊ ላፕቶፕና  ስርቲፊኬት...
02/09/2026

የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የ በ2018 በጀት ዓመት በክልል ደረጃ በተካሄደው የሥራ አፈጻጸም ምዘና 1ኛ ደረጃን በመያዝ ዘመናዊ ላፕቶፕና ስርቲፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።

Address

Awi Zone Injibara
Injibara

Telephone

+251582270279

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Injibara Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share