03/09/2026
በጃጁራ ከተማ አስተዳደር ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም ተገመገመ
ጃጁራ፦ ነሐሴ 28/12/2018 ዓ/ም (የጃጁራ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን )
በጃጁራ ከተማ አስተዳደር ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም የእስከ አሁን ሥራዎች አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት መደረጉ ተገለፀ ።
መድረኩን የጃጁራ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ለይኩን ሱልዶሎና የከተማ አስተዳደሩ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ክባሞ አባይነህ በጋራ መርተዋል ።
ለውይይት መነሻ የሚሆን የገቢ አሰባሰብ ፣ የንግድ ምዝገባና እድሳት ፣ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ የግብርና ፣ የሠላምና ፀጥታ ሥራዎች ፣ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሥራዎች እና የፓርቲ ሥራዎች አፈፃፀም ሪፖርት በጃጁራ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኤልያስ ሀንድሶ በኩል ቀርቧል ።
የቀረበውን የአፈፃፀም ሪፖርት መነሻ በማድረግ አመራር ፑሉ በስፋት ውይይት በማድረግ የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና ድክመቶችን በማረም በሁሉም ዘርፍ ውጤት ለማስመዝገብ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል ።
በመድረኩ የከተማ አስተዳደሩ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትና አመራር ፑሉ ተገኝተዋል ።