30/03/2026
የሶማሊ ክልል ስያሜና ባንድራን ከመገንጠል ጋር ምን አገናኛቸው?
አቶ ሙስጠፌ መሀመድ በ2010 ዓ.ም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ከተሾሙ በኋላ፣ በሶማሊ ክልል ውስጥ ህገ መንግስታዊ የሆኑ ጉዳዮችን በህጋዊ መንገድ ብቻ እንዲመለሱ ማድረግ ከጎረቤት ክልሎች የሕውሓት ጉዳይ አሰፈጻምዋች የፊጠሩትን ግጭቶች መፈታት መቻሉ ክልሉን ከነበረበት የፖለቲካ ቀውስ አውጥተው ወደ መረጋጋት ያሸጋገሩት ናቸው።
በክልሉ ትኩረት ከተሰጣቸው ሪፎርሞች መካከልም የፖለቲካ ፥የፍትህ እና የፀጥታ ዘርፍ እና የማህበራዊ ጉዳዬች ይገኙበታል።
በዚህም መሰረት ቀደም ሲል በነበረው የነ አብዲ ኢሌይ አንባገነን ስርዓትና በሕውሓት እኔ አውቅልሃለሁ ፓለቲካ ከቀለም ጀምሮ ሁሉም ነገር እኛን መምሰል አለበት በሚል በክልሉ በዘፈቀደ ከህገ መንግሥቱ ወጪ በመሆን በክልሉን ህገ መንግስቱ ሰፍሮ የሚገኘውን መጠሪያ ስያሜ ና ክልላዊ ባንድራ መቀየር ይገኙበታል።
ህገ መንግስት ላይ ሰፍሮ የሚገኘውን "የክልሉ ሰንደቅ ዓላማ ከላይ አረንጓዴ፤ ከመሃል ነጭ፤ ከታች ቀይ ፤ በስተግራ በኩል ባለሦስት መዓዘን ውሃ ሰማያዊ መደብ መሃል ላይ ባለ አምስት ጫፍ ነጭ ኮኮብ ይኖረዋል"የሚል ሲሆን ሀገር አፍራሹና የቀድሞው ስርዓት ህገመንግስቱን ወደ ጎን በመተው በኢሕገ_መንግታዊ አካሄድ የህብረተሰቡን ባሕል እና ሰነልቦና ያላገናዘበ ትርጉም የለሽ በሆነ መንገድ የክልሉን ሰንደቅ አላማና ስያሜ ቀይሯል።
በመሆኑም በአቶ ሙስጠፌ መሀመድ የሚመራው የሶማሌ ክልል መንግስት በህገመንግስቱ የሰፈረውን ክልላዊ ባንዲራ ዳግም ህገ መንግስቱን መሰረት ባደረገ መልኩ ስራ ላይ እንዲውል አድርጓል።
ዛሬ ላይ እንደ ሀገርም ሆነ ክልል ያመጣውን ታዓምራዊ ለውጥ ማየት የተሳነው አፍራሹ ቡድን የክልሉ ስያሜና ባንድራ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ውሳኔ የተቀየረ አድርጎ መሰረተ ቢስ ፕሮፖጋንዳ መስተጋባቱን ቀጥሏል።
የሶማሌ ክልል ህዝብና መንግስት የመገንጠል ፖለቲካን ነው የሚያራምዱት በሚል ያለፈበት የማጠልሸት ተግባራቸው የተሰማሩት የከፋፋይ ፖለቲካ አራማጆቹ የህወሓት ቡድኖች በሶማሌ ክልል ያቀዱት የመገንጠል ፖለቲካ ባለመስራቱ ዛሬ ላይ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጎን በመቆም ያፈጀ ያረጀ የመገንጠል ፖለቲካን ለማራመድ ሲሞክሩ እየተመለከትን ነው።
በአሁኑ ወቅት የክልሉ መንግስት እና የክልሉ አመራር ለዚህ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ቦታ ሳይሰጡ ትኩረታቸውን ልማት እና ልማት ላይ ብቻ በማድረግ የሚሰራ አመራር መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።