Commercial bank of ethiopia-yem branch

Commercial bank of ethiopia-yem branch commercial bank of ethiopia

26/05/2026

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ ቀዳሚው ተወዳጅ የፋይናንስ ተቋም ተብሎ ተመረጠ
***************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ ቀዳሚው ተወዳጅ የፋይናንስ ተቋም ተብሎ መመረጡን ብራንድ አፍሪካ (Brand Africa) ይፋ አድርጓል።

ተቋሙ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የእንኳን ደስ አለዎት ይፋዊ ደብዳቤ ልኳል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ ቀዳሚው እጅግ ተወዳጅ የፋይናንስ አገልግሎት ብራንድ (Most Admired Financial Services Brand) በመሆን መመረጡን ተቋሙ በላከው ደብዳቤ ማሳወቁን ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አሳውቋል፡፡

ዓመታዊው የ"Africa's Best Brands" የሽልማት ስነ-ስርዓት ትላንት ግንቦት 17 ቀን 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን ተቋሙ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክቱን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ልኳል፡፡

ብራንድ አፍሪካ ጥናቱን ያካሄደው ከአፍሪካ ቢዝነስ መጽሔት እና ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) ጋር በመተባበር ሲሆን፣ በ30 የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ከ85% በላይ የሚሆነውን የአህጉሪቱን ህዝብ እና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሸፈነ ጥናት መሆኑም ተገልጿል። በጥናቱ ውጤት መሰረት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሸማቾች ዘንድ ያለውን ጠንካራ ተቀባይነት ፣ የህዝብ እምነት እና የፋይናንስ መሪነት ለሽልማት እንዳበቃው ተገልጿል።

Address

Jimma Road
Jimma

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Commercial bank of ethiopia-yem branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share