24/05/2023
በጅማ ቅ/ፅ/ቤት ለአዲስ የጉምሩክ ባለሙያዎች በሃኒ ላንድ ሆቴል አቀባበል ተደረገ
===================
ላለፉት ሶስት ወራት ፖሊሳዊ ስልጠና እና የጉምሩክ አዋጅ፣ መመሪያዎችና ደንቦችን እንዲሁም የአካል ብቃት ስልጠና በደቡብ ፖሊስ ይርለም ከተማ ሙሉ ስልጠና ወስደው ወደ ቅ/ፅ/ቤት ለተመደቡ ሠራተኞች በሃኒ ላንድ
ሆቴል አቀባበል ተደረገ።
በአቀባበል ስነ ስርዓቱ የቅ/ቤቱ ከቡድን አስተባባሪ በላይ ያሉ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ መርጋ ቶለራ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ።
የቅ/ጽ/ቤቱ የህግ ተገዥነት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ጀምበሬ ምትኩም በተልእኮዎች ዙሪያ አጠቃላይ ስለ ቅ/ጽ/ቤቱ፣ ስለ እያንዳንዱ ጣቢያዎች ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ገቢና ወጪ ኮንትሮባንድን አስመልክቶ ያለውን ሁኔታ አስረድተዋል ።
በተጨማሪም የቅርንጫፉ የኢንተለጀንስ እና ኮንቶሮባንድ ስራ ህደት አቶ ሀይሉ ታምሩ አዲስ ባለሙያዎች በጣቢያ አሰራር ማኑዋል ዙርያ ስልጠና በመስጠት ለሰልጣኞቹ የተሰጣቸው ኃላፊነት ከፍተኛ በመሆኑ ህዝብና መንግስት የሰጣቸውን አደራ በላቀ ሁኔታ እንዲወጡ አስረድተዋል ።
በመጨረሻም አዳዲስ ባለሙያዎች እንድሁም ከቡድን በላይ ያሉ አመራሮች እና ዘርፎች ባሉበት በቅ/ጽቤቱ የትውውቅ ፕሮግራም በተዘጋጀት የእራት ግብዣ በመታደም ተጠናቋል።
የልህቀት ዓመት!!
Year of Excellence !!!