South Omo Zone Public Service & Human Resource Department

South Omo Zone Public Service & Human Resource Department Public service & Human Resource activities

የደቡብ ኦሞ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ በሳላማጎ ወረዳ  በሁሉም ሰክተር መሥሪያ ቤቶች የተሠራ የኢንስፔክሽን ሥራ ግብረ መልስ  አቀረበ።  ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።...
09/02/2026

የደቡብ ኦሞ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ በሳላማጎ ወረዳ በሁሉም ሰክተር መሥሪያ ቤቶች የተሠራ የኢንስፔክሽን ሥራ ግብረ መልስ አቀረበ።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ቀን 02/06/2018 ዓ/ም
ዲመካ
የደቡብ ኦሞ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ የኢንስፔክሽን ቲም በሳላማጎ ወረዳ በሁሉም ሰክተር መሥሪያ ቤቶች የተሠራ የሰው ሀብት ሥራ አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ ሥራውን አስመልክቶ በወረዳው ለባለድረሻ አካላት ግብረ-መልስ የቀረበ ሲሆን በኢንስፔክሽን ሥራው የተደሰቱት ባለድርሻ አካላት ለበርካታ ዓመታት የህዝብን ሀብት አለአግባብ ስባክን የነበረውን ማስቆም መቻል እንዳለበት በመግለፅ አለአግባብ የባከነውን የመንግስት ሀብት ማስመለስ የሁሉም ባለድርሻ አካላት ሪብርብ የሚያስፈልግ መሆኑን እና በብልሹ አሰራር ላይ የተሳተፉ አካላት ላይ የተወሰደው አስተዳደራዊ እርምጃ የሚደገፍ መሆኑን በመግለፅ ውይይቱ ተጠናቋል።

08/02/2026
26/12/2025
የደቡብ ኦሞ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ የሰው ሀብት ሥራ አፈፃፀም መመሪያ፣ ደንቦች እና ሰርኩላሮች አተገባበር አንፃር በሳላማጎ ወረዳ በሁሉም መንግስት መ/ቤቶች የተቀናጀ ኢንስፔክሽን ሥራ ተ...
22/12/2025

የደቡብ ኦሞ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ የሰው ሀብት ሥራ አፈፃፀም መመሪያ፣ ደንቦች እና ሰርኩላሮች አተገባበር አንፃር በሳላማጎ ወረዳ በሁሉም መንግስት መ/ቤቶች የተቀናጀ ኢንስፔክሽን ሥራ ተጀመረ።
ቀን 13/04/2017 ዓ/ም
ዲመካ
የደቡብ ኦሞ ዞን ሲቪል ሰርቪስ መምሪያ የሰው ሀብት ሥራ አፈፃፀም መመሪያ፣ ደንቦች እና ሰርኩላሮች አተገባበር አንፃር በሳላማጎ ወረዳ በሁሉም መንግስት መ/ቤቶች የተቀናጀ ኢንስፔክሽን ሥራ ለማከናወን ከሁሉም ሰክተር መ/ቤቶች ለተወጣጡ የተቋም ኃላፊዎችና ሰው ሀብት ሥራ አመራር ባለሙያዎች የኢንስፔክሽን ሥራ ቅድመ ሁኔታ አጭር ኦረንቴሽን በመስጠት ሥራው ተጀምሯል።

15/11/2025
🫵የማርበርግ ቫይረስ በዋነኛነት ወደ ሰዎች የሚተላለፈው በበሽታው ከተያዙ እንስሳት የሰውነት ፈሳሽ ጋር በመገናኘት ሲሆን በተለይም  የሌሊት ወፍ ሲሆን እነዚህም እንደ ተፈጥሯዊ የቫይረሱ አስተ...
14/11/2025

🫵የማርበርግ ቫይረስ በዋነኛነት ወደ ሰዎች የሚተላለፈው በበሽታው ከተያዙ እንስሳት የሰውነት ፈሳሽ ጋር በመገናኘት ሲሆን በተለይም የሌሊት ወፍ ሲሆን እነዚህም እንደ ተፈጥሯዊ የቫይረሱ አስተናጋጅ ተደርገው ይወሰዳሉ። ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፉ እንደ ደም፣ ምራቅ፣ ላብ፣ ማስታወክ ወይም ሌሎች ፈሳሾች ካሉ የሰውነት ፈሳሾች ጋር በቀጥታ በመገናኘት ሊከሰት ይችላል።
በተጨማሪም በቫይረሱ ​​የተያዙ የሟቾችን አስከሬን በመያዝ ወይም በማዘጋጀት በተለይም በመቃብር ወቅት ስርጭቱ ሊከሰት ይችላል። ትክክለኛ የኢንፌክሽን መቆጣጠሪያ እርምጃዎች ካልተከተሉ የጤና እንክብካቤ ሰራተኞች ለአደጋ ሊጋለጡ ይችላሉ።
👉የመከላከያ እርምጃዎች በበሽታው ሊያዙ ከሚችሉ እንስሳት ጋር ንክኪን ማስወገድ፣ ንፅህናን መጠበቅ እና በበሽታው የተያዙ ሰዎችን በሚንከባከቡበት ጊዜ የመከላከያ መሳሪያዎችን መጠቀምን ያጠቃልላል።
በአሁኑ ጊዜ የማርበርግ ቫይረስ በመተንፈሻ አካላት ወይም በአይሮሶልዝድ( aerosol) ቅንጣቶች ሊተላለፍ እንደሚችል የሚያሳይ ምንም መረጃ የለም።
👉የማርበርግ ቫይረስ በዋነኛነት የሚተላለፈው በበሽታው ከተያዙ ግለሰቦች ወይም እንስሳት የሰውነት ፈሳሽ ጋር በቀጥታ በመገናኘት ሲሆን ይህም እንደ ደም፣ ምራቅ፣ ማስታወክ ወይም ሌሎች ፈሳሾች ባሉበት ነው።

14/11/2025

በወቅታዊ የጤና ጉዳይ የተሰጠ መረጃ

11/11/2025

‎በክልሉ አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ የመስከረም እና ጥቅምት ወር ውዝፍ ክፍያ ነገ ኅዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ይከፈላል :- አቶ ተፈሪ አባተ

ህዳር 1/2018 ዓ.ም

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ የመስከረም እና ጥቅምት ወር ውዝፍ ክፍያ ነገ ኅዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚከፈል የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አስታወቀ።

‎በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ እንደሀገር ከመስከረም ወር 2018 ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገውን አዲሱ የመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

‎አቶ ተፈሪ በሰጡት መግለጫ በክልሉ አዲሱ የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ መክፈል የሚያስችል ሀብት ከኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ መተላለፉን አስታውቀዋል።

‎እንደሀገር መንግስት የመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉን የገለጹት አቶ ተፈሪ፥ ይህንኑ በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል።

‎ቢሮው በክልሉ ሥር የሚገኙ መዋቅሮች አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ ለመፈፀም የሚያግዙ መረጃዎችን አጣርተው እንዲያደረሱ ሲጠባበቅ መቆየቱንም ገልጸዋል።

‎በክልሉ ሥር ከሚገኙ 12 ዞኖች እና 3 ሪጆዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች በአሁኑ ሰዓት ሁሉም መረጃዎች ተደራጅተው መምጣቱን ያስታወቁት አቶ ተፈሪ፥ የመስከረም እና የጥቅምት ወር አዲሱ ጭማሪ ደመወዝ እንዲከፈል ለባንክ መላኩን ገልጸዋል።

‎በክልሉ ስር የሚገኙ ሁሉም ዞኖችና ሪጆዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደር መዋቅሮች ነገ ኅዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ድረስ ገንዘቡን ከባንክ ማገኘት የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

‎በመሆኑም ሁሉም መዋቅሮች የመንግስት ሠራተኞች ውዝፍ ክፍያውን በሁለት ቀናት ውስጥ በመፈፀም ለክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሪፖርት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

‎በክልሉ የልዩ ስኬል ደመወዝ ተከፋዮች የዐቃቤ ህግ ፤ ዳኞች እና ገቢዎች በተመለከተ እና የበረሀ አበል ክፍያ የሚፈፀምባቸው መዋቅሮች በአዲስ መልክ ተሰልቶ የሚደርስ ስለመሆኑ አቶ ተፈሪ አስረድተዋል።

‎ከኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር የተላለፈው ሃብት መዋቅሮች ባላቸዉ የሰዉ ሃይል ስሌት መሠረት የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ባስተላለፈው መረጃ መነሻ በማድረግ የተላከ መሆኑን የገለጹት አቶ ተፈሪ፥ ለተፈፃምነቱ በየደረጃው ያለው አመራር በጥብቅ ድስፕሊን እንዲመራ አሳስበዋል።

05/11/2025

‎አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ ይደረጋል -የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ

‎ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም

‎በክልሉ አዲሱ የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ በተያዘው ጊዜ ለመፈፀም ከወረዳ አስከ ክልል ካለው መዋቅር ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተጠቁሟል።

‎በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የወላይታ ሶዶ ክላስተር ማዕከል ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደፋሩ ፣መንግስት የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ አድርጎ ለመንግስት ሠራተኞች የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉን ጠቁመዋል።

‎ይህንኑ በክልሉ ተግባራዊ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ተስፋዬ፣ ክፍያውን ለመፈፀም የሚያግዙ መረጃዎች በክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በመግባት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

‎የኑሮ ማሻሻያ ቋሚ፣ መደበኛና ጊዜያዊ የመንግስት ሰራተኞችን እንደሚያካትት ገልፀው ፣ክፍያው በተያዘው ጊዜ ለመፈፀም ከወረዳ አስከ ክልል ካለው መዋቀር ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

‎አሁን ላይ በታችኛው መዋቀሮች አልፎ አልፎ የመረጃዎች ክፍተቶች ስለመኖራቸው የገለፁት አቶ ተስፋዬ ፣ይህም በአጭር ጊዜ ተሟልተው ለክልል ፋይናንስ ገቢ ሆኖ ክፍያ ይፈፀማል ብለዋል።

‎በተወሰኑ በታችኛው መዋቀሮች ደመወዝንና ደረጃን በትክክል የሚገልጹ የመረጃ ክፍተቶች እንደ ችግር መታየቱን ጠቁመው ፣ይህንኑ የማጥራት ስራ እየተፋጠነ ስለመሆኑ አስረድተዋል።

‎የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ አዲሱን የኑሮ ማሻሻያ የደመወዝ ጭማሪ ክፍያ በተያዘው ጊዜ ለመፈፀም በቅንጅት እየሰራ መሆኑን የገለፁት አቶ ተስፋዬ ፤ ማህበረሰቡ በሀሰተኛ ማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ መረጃዎች ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።

26/10/2025
03/10/2025

Address

South Omo Zone
Jinka
125987PU

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when South Omo Zone Public Service & Human Resource Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share