07/09/2026
በደቡብ ኣሪ ወረዳ የኤልኒኖን ተፅዕኖ ለመቋቋም “ኤልኒኖን በመስኖ ውሃ አማራጮች እንጠቀም” በሚል መሪ ቃል ሰፊ የመስኖ ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ነሐሴ 2018 ዓ/ም
ጋዘር
የደቡብ አሪ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ደይዳቆ በዞኑ በጨለጎድ ቀበሌ በኦምበት መስኖ ላይ በተለያዩ ሰብሎች 5 ሄክታር መሬት እየለማ ያለበትን ሁኔታ በቦታው ተገኝተው ተመልክተዋል።
በወረዳው የኤልኒኖን ተፅዕኖ ለመቋቋም በውሃ አማራጮች ለማልማት የታቀደው አጠቃላይ የመሄር ዕቅድ፦14,857.5 ሄክታር መሬት መሆኑን የገለጹት አቶ አሸናፊ ደይዳቆ፦ዕቅዱን ለማሳካት በተለያዩ የውሃ አማራጮች የታገዘ ሰፊ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በዚህም መሠረት፦
* በዘመናዊ መስኖ ፦9,817.1 ሄክታር
* በሞተር ፓምፕ ፦1,982.6 ሄክታር
* በምንጭ ፦1,230.23 ሄክታር
* በወንዝ፦1,111.6 ሄክታር እንዲሁም
* በእጅ ጉድጓድ፦716.02 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን አብራርተዋል።
ወረዳዋ እጅግ ለም መሬት ያላት ከመሆኑም በላይ ወደ ታች ጥቂት ሜትሮች ብቻ ሲቆፈር ውሃ ማግኘት ብርቅ ያልሆነባት ምድር መሆኗን ኃላፊው ጠቁመዋል።
በመጨረሻም የውድ የወረዳው ማህበረሰብ አባላት ተረጅነትንና የተረጅነት አስተሳሰብን በጋራ በመታገል፣ በአሁኑ ወቅት የገጠመውን አስከፊውን የኤልኒኖ እና የላኒኖ ተፅዕኖ በትብብርና የባለሙያዎችን የግብርና ምክር ሐሳብ ተግባራዊ በማድረግ ማሸነፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል። ለዚህም ስኬት ሁሉም የአካባቢው ማህበረሰብ አባል የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አቶ አሸናፊ ደይዳቆ ጥሪ አቅርበዋል።
#ደኣወመኮ