Benatsemay woreda Government Communication Affairs Office

Benatsemay woreda Government Communication Affairs Office Government communication affairs office

የበና ፀማይ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ለጤና ጣቢያ ኃላፊዎች የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ተጠሪዎች እና የጽ/ቤት ባለሙያዎች የወረዳ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ላይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንም ተገለፀ...
03/09/2026

የበና ፀማይ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ለጤና ጣቢያ ኃላፊዎች የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ተጠሪዎች እና የጽ/ቤት ባለሙያዎች የወረዳ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ላይ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑንም ተገለፀ

✅ነሐሴ፦28/2018 ዓ.ም (በፀወመኮአ)
ቀይ አፈር
========================
✍️ስልጠናውም በወረዳው ጤና ጽ/ቤት ለጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ፣ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ተጠሪዎች እና የጽ/ቤት ባለሙያዎች የወረዳ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች ስልጠና እንዲሁም ወቅታዊ የወባና ስርዓተ ምግብ አለመመጣጠን ክስተት አስተዳደር ውይይት እየተደረገ መሆኑን ተገለፀ።

✍️ስልጠናውም በዘርፉ የወረዳ ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎች እና በቀጣዮ በ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎች በወረዳው ውስጥ ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች ከAMREF እና JSI MIHR የ4ኛ ሩብ አመት ግብረ መልስ እና የወባና የምግብ እጥረት ልየታና ህክምናን አጠናክሮ ከመስራት አኳያ ያለውን ወቅታዊ ሂደቶች ላይ ያተኩራል ተብሏል ።

✍️ይኸውም ስልጠና የደቡብ ኦሞ ዞን ጤና መምሪያ ባለሙያ በሆኑት በአቶ አልዲ ኦይታ እና ዋሲሁን ጌታሁን በጋራ በመሆን ለተከታታይ ለሁለት ቀናት እንደምሰጥ ተገልጿል።

✍️በወረዳ ደርጃ ተግባራት በብቃትና በስፋት ማስፈፀምና መፈፀም እንዲቻል በማህበረሰቡ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ከማድርግ ኢፍትሃዊነት እና ጥራት ባለው መልኩ ለማህበረሰቡ ከማዳረስ አኳያ ጠንከር ያለ አቅጣጫ ከመሆኑ አንጻር ከጤና ጣቢያ አንስቶ እስከ ጤና ኬላ ደረጃ በቼክሊስት መሰረት በትኩረት እንደሚሰራና ግብረ መልስ ተጠናክሮ የሚቀርብ መሆኑን ጭምር የበና ፀማይ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሴ ኦይታ አሳውቀዋል ።

👉የመረጃ ምንጭ የበና ፀማይ ጤ/ጽ/ቤት ነው

በደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ የ2018 ዓ,ም  የክረምት ወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት መዝጊያና የበጋ በጎ ተግባር ማብሰሪያ በጎልድያ ቀበሌ መድረክ ተካሄደ ።ጎልድያ፣ነሐሴ 28/2018 ...
03/09/2026

በደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ የ2018 ዓ,ም የክረምት ወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት መዝጊያና የበጋ በጎ ተግባር ማብሰሪያ በጎልድያ ቀበሌ መድረክ ተካሄደ ።

ጎልድያ፣ነሐሴ 28/2018 ዓም(በፀወመኮ)
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፤፤፣፣፣፣፣፤፤፤፣፣፣፣፣፣፣፣፣
በደቡብ ኦሞ ዞን በና ፀማይ ወረዳ የ2018 ዓ,ም የክረምት ወጣቶች በጎ ፍቃድ አገልግሎት መዝጊያና የበጋ በጎ ተግባር ማብሰሪያ በጎልድያ ቀበሌ መድረክ ተካሄዷል ።

የበና ፀማይ ወረዳ ዋና አሰተዳደር አቶ ዮሐንስ ጋርሾ በመድረክ ላይ ተገኝተው የተናገሩት መልዕክት የጎልድያ ቀበሌ በ2018 ዓ/ም የወረዳው መንግሥት በክረምት በጎ ተግባር የሰጠውን ተልዕኮ በግንባር ቀዳሚነት በመጨረስ የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገበ ቀበሌ መሆኑን ክቡር ዋና አሰተዳደር ተናግሯል ።

አያይዘውም የክረምት በጎ ተግባር በዚህ የሚያልቅ ሳይሆን አሁንም በበጋው በጎ ተግባር ላይም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በንግግራቸው ገልፀዋል ።

የጎልድያ ቀበሌ የወጣቶች ክረምት በጎ ተግባር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የጎልድያ ቀበሌ ደጋፍ አቶ ዮሐንስ ዱባሌ አቅርቧል ።

በማስቀጠል የጎልድያ ቀበሌ የወጣቶች ክረምት በጎ ተግባር ላይ የተሻለ ተሳትፎ ላደረጉት የቀበሌው አመራር እና የቀበሌው ወጣቶች የበና ፀማይ ወረዳ ዋና አስተዳደሪና የወረዳው ብልፅግና ፖርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግሥት ዋና ተጠሪ፣ እንድሁም የመንግስት ረዳት ተጠሪዎች አማካኝት የእውቅና ሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቷል ።

በስተመጨረሻም ላይ ለአቅመ ደካማ አረጋዊያኖች የቀለብ እህል ፣ ስጋጃ፣ ብጃማ እንድሁም ለአቅመ ደካማ ቤተሰብ ልጆች የመማሪያ ደብተር ስጦታ ተበርክቷል ።

በበና ፀማይ ወረዳ በዋለው የቀይ አፈር ገበያ በእንስሳት ሽያጭ ተመጣጣኝ ግብይት መካሄዱን በቁም የእንስሳት የተሰማሩ የንግዱ ማህበረሰብ ገለፁ✅ነሐሴ ፦28/2018ዓ.ም(በፀወመኮአ)=======...
03/09/2026

በበና ፀማይ ወረዳ በዋለው የቀይ አፈር ገበያ በእንስሳት ሽያጭ ተመጣጣኝ ግብይት መካሄዱን በቁም የእንስሳት የተሰማሩ የንግዱ ማህበረሰብ ገለፁ

✅ነሐሴ ፦28/2018ዓ.ም(በፀወመኮአ)
===========================
በበና ፀማይ ወረዳ በዋለው የቀይ አፈር ገበያ በእንስሳት ሽያጭ ተመጣጣኝ ግብይት መካሄዱን በቁም የእንስሳት የተሰማሩ የንግዱ ማህበረሰብ ገለፁ።

የወረዳው ማዕከል በሆነችው ቀይ አፈር ከተማ በዋለው የሐሙስ ገበያ በቁም እንስሳት የደለቡ ሰንጋ በሬዎች የሽያጭ ዋጋ መቃኘት የተቻለ ስሆን ከፍተኛው ዋጋም 150,000 ብር መካከለኛውም እሰከ 115,000 መሸጡን እንዲሁም በየደረጃው የዋጋ ቅናሽ መኖሩን አመላክተዋል ።

03/09/2026
"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪቃል  በበና ፀማይ ወረዳ ቃቆ ከተማ ለወ/ሮ አርድ ዶርኮ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ቤት ግንባታ ለማስጀመር ላውች አካሄደ።ቃቆ፣ነሐሴ 28/2018 ...
03/09/2026

"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪቃል
በበና ፀማይ ወረዳ ቃቆ ከተማ ለወ/ሮ አርድ ዶርኮ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ቤት ግንባታ ለማስጀመር ላውች አካሄደ።

ቃቆ፣ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም(በፀወመኮ)
=========+++++++=========

"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪቃል በበና ፀማይ ወረዳ ቃቆ ከተማ ለወ/ሮ አርድ ዶርኮ የቤት ግንባታ ለማስጀመር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ላውች አካሄደዋል።

የበና ፀማይ ወረዳ ዋና አሰተዳደር ክቡር አቶ ዮሐንስ ጋርሾ በስፍራው ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ስሆን ለክቡር እንግዶች እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ የ2018ዓ,ም የክረምት በጎ ተግባር በዘርፍ ብዙ ስራዎች እየተሰራ እንዳለና በቃቆ ከተማ የአንድ አቅመ ደካማ አረጋዊያን ቤት ተገንብቶ አልቆ ርክክብ በተደረገበት ማግስት ተጨማሪ ለላ በክልሉ ጤና ቢሮ በኩል የአንድን አቅመ ደካማ አረጋዊ ቤት ለመስራት ላውንች መደረጉ ልዩ እንደሚያደርግ ገልፀው ፦

የዕለቱ ክብር እንግዳ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ መና ሞክርያን ንግግር እንድያደረጉ ጋብዘዋል ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ም/ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ መና ሞክርያ በንግግራቸው እንደገለፁት መንግስታችን ሰው ተኮር መንግሥት ከመሆኑ ባሻገር በተለይ ለአቅመ ደካማዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ እንዳለው በንግግራቸው ገልፀዋል ።

አክሎም አቶ መና ዛሬ ላውንች የምናደርገው የቤቱ ግንባታው 3.ነጥብ ሚልዮን ብር ወጪ እንደሚደርስ ተናግሮ ሁለት ወር ውስጥ የቤቱ ግንባታው ተጠናቆ ርክክብ እንደሚደረግ በንግግራቸው አክሏል ።

ወ/ሮ አርድ ዶርኮ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ቤትዋን ለመገንባት የጀመረውን ዕቅድ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቅርበዋል ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና የቢሮ ባለሙያዎች የበና ፀማይ ወረዳ ዋና አሰተዳደር የበና ፀማይ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ የቃቆ ከተማ ማዘጋጃ ስራ አስኪያጅና የዘርፍ ኃላፊዎች እንድሁም የቃቆ ከተማ ማህበረሰቦች በስፍራው ተገኝተዋል ።

ዘገባው ፦የበና ፀማይ ወረዳ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ነው ።

በበና ፀማይ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018ዓ.ም አመታዊ የቦርድ መድርክ ማጠቃልያ ሪፖርት  ተካሄደ ✅ነሐሴ ፦27/2018ዓ.ም (በፀወመኮአ)                     ቀይ አፈር=======...
02/09/2026

በበና ፀማይ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018ዓ.ም አመታዊ የቦርድ መድርክ ማጠቃልያ ሪፖርት ተካሄደ

✅ነሐሴ ፦27/2018ዓ.ም (በፀወመኮአ)
ቀይ አፈር
==========================
በበና ፀማይ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2018ዓ.ም አመታዊ የቦርድ መድርክ ማጠቃልያ ሪፖርት ተካሄደ።

የ2018 ዓ.ም አመታዊ ቦርድ መድርክ ማጠቃልያ ሪፖርት የበና ፀማይ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና የቦርድ ሰብሳቢ በሆኑት በክቡር አቶ ዮሐንስ ጋርሾ መሪነት መካሄድም ተችሏል ።

በወረዳው በ6ቱም ጤና ክላስተር በተካሄደውም የቦርድ ውይይት መሠረት በዛሬውም ዕለትም የቦርድ መድርክ ማጠቃልያ ሪፖርት በወረዳው ጤና ጽ/ቤት በአቶ ሙሴ ኦይታ መቅርብ ችሏል ።

ይኸውም ጠንካራ ጎኖች በሰለጠነ ባለሙያ የታገዘ የወልድ አገልግሎት አፈጻጸም የተሻለ መሆኑ ፣የክትባት አገልግሎት ከሽፋን በላይ አፈፃፀም መምጣቱን የተከበሩ አቶ ዮሐንስ ጋርሾ አስቀምጠዋል ።

የመድሃኒት አቅርቦት ጋር በተያያዘ የተሻለ መሆኑንና የማቆያ እናቶች እንክብካቤ በጀት ተመድቦ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ እንዲሁም የውስጥ ገቢ ከእቅድ በላይ መሰብሰቡ መቻሉን እና በጀት አመቱን የውባ ወረርሽኝ ያሳለፈን ቢሆንም የተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ ከወትሮው መሻሻሉ የሚበረታታ ነው ሲሉ የወረዳው አስተዳደሪ ገልጸዋል ።

ከሪፖረት አንጸር ዋና ዋና በድክመት የታዮት ጉዳዬች በልዬነት የመንግሥት የወባ መድሀኒት ቁጥጥር ላይ በዲስፔንሰሪ ክፍል የBin card አለመጠቀም ፋርማሲ ባለሙያዎች የመከታተል ክፈተት መኖሩ ለብልሹ ስራዎች የሚያጋልጥ መሆኑንም ተቀምጧል።

በ24 ሰዓት ውስጥ የወልድ መቆጣጠሪያ አገልግሎት ዝቅተኛ እንደሆነና የነፍሰጡር እናቶች የተሟላ የእርግዝና ምርመራ ከመስጠት አኳያ ከግብዓት አቅርቦት አንፃር ክፍተቶች መኖሩ አመላክተዋል ።

ከ5 ዓመት በታች የህጻናት የእድገት ክትትልና የምግብ እጥረት ልይታ ስራ አንፃርም ዝቅተኛ መሆኑ የተገለፀ ስሆን የእናቶች ማቆያ ቁሳቁስ አለማሟላት፣ የላብራቶሪ ምርመራ አከባቢ የቆይታ ጊዜ አለመለጠፍ እንዲሁም የሰራተኛ ደንብ ልብስ አለማሰፋት የታዩ ጉድለቶች መሆኑን ተገልጿል።

የ6ቱም ጤና ጣቢያ ኃላፊዎች በጤና ጣቢያ በየሳምንቱ የመገመምገምና የሃይጅንና ሳንቴሽን ክፍተቶችን የማየት ስራ በልዩነት እንዲቆጣጠሩ እና ክትትል እንዲያደርጉ በጥብቅ አቅጣጫ ተቀምጧል።

በወረዳ ደርጃ የሚፈቱት የተለያዩ ጥያቄዎች በትኩረት ከሚታይ አንዱም የዲውቲ ጉዳይ መሆኑን ያስቀመጡት ስሆን ይኸውም ከዚህ ወር ደሞዝ በኃላ 2017ዓ.ም ክፍያ ይፈፀማል ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል ።

ሌሎች ችግሮችን በህደት የሚፈቱት ጉዳዮች ቦርዱ በቀጣይ ውይይቶች የሚያይ መሆኑን ከመድረኩም ተገልጾ የቦርድ መድረክ ማጠቃለያውም ተቋጭቷል።

የክረምት ወራት በጎ አድራጎትን ምክንያት በማድረግ የበና ፀማይ ወረዳ ማ/ሴ/ጉ/ጽ/ቤት ቃቆ ጤና ጣቢያ ማቆያ ላሉ እናቶች ማዕድ ማጋራት መረሃ ግብር ተካሄደ ።     ቃቆ፦  ነሐሴ 27/201...
02/09/2026

የክረምት ወራት በጎ አድራጎትን ምክንያት በማድረግ የበና ፀማይ ወረዳ ማ/ሴ/ጉ/ጽ/ቤት ቃቆ ጤና ጣቢያ ማቆያ ላሉ እናቶች ማዕድ ማጋራት መረሃ ግብር ተካሄደ ።

ቃቆ፦ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም(በፀወ)

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የበና ፀማይ ወረዳ ዋና አስተዳደር ክቡር አቶ ዮሐንስ ጋርሾ እንደተናገሩት ማዕድ ማጋራት አብሮ የመብላት የመተሳሰብ የመደጋገፍና የወንድማማችነት እሴታችንን የሚያጠናክር ሆኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል ብለዋል።

አያይዘውም ፓርቲያችን ብልፅግና ሰው ተኮር እንደመሆኑ ማዕድ ማጋራት የአብሮነት የመረዳዳትና የመተሳሰብን እሴት የሚያጎላ ተግባር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የበና ፀማይ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፍ ወ/ሮ አዛለች ጎይትያር በበኩላቸው እንደተናገሩት በተለያዩ ጊዜያት የምናደርገው የማዕድ ማጋራት የመረዳዳት ባህላችንን እንዲሁም ህብረ ብሄራዊ ወንድማማችነት/እህትማማችነት አጉልቶ የሚያሳይ በመሆኑ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ያለውን በማካፈል ሊያጠናክረው ይገባል ብለዋል።

የማዕድ ማጋራት ተግባር በጤና ጣቢያው ማቆያ ውስጥ ያሉ እናቶችና ህፃናትን እንክብካቤ ለማጠናከር፣ የማህበረሰቡን የወገንተኝነት እና የበጎ ፈቃደኝነት ባህል ለማሳደግ እና ለእናቶችና ህፃናት ምቹ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ሁኔታ መፍጠር ያለመ መሆኑ የበና ፀማይ ወረዳ ማ/ጉ/ጽ/ቤት ኃላፍ ወ/ሮ አርሜ አይኬ ገልፀዋል።

አክለውም የበጎ አገልግሎት በጤና ተቋሙ የአካባቢ ንጽህናንና የአገልግሎት ምቹነትን ለማሻሻል ያለመ ሲሆን፣ ተግባሩ የማህበረሰብ ተሳትፎንና የመተጋገዝ ባህልን ለማጠናከር አስተዋጽኦ አለው።

በበና ፀማይ ወረዳ የ2018 ዓ.ም ክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእስከአሁን ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ  ቀይ አፈር፦ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም(በፀወመኮአ)በበና ፀማይ ወረዳ የ...
02/09/2026

በበና ፀማይ ወረዳ የ2018 ዓ.ም ክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የእስከአሁን ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

ቀይ አፈር፦ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም(በፀወመኮአ)

በበና ፀማይ ወረዳ የ2018 ዓ.ም የክረምት ወራት ወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት በወረዳዉ እየተከናወነ የሚገኝ ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ አካሂዷል ።

መድረኩ እስካሁን የተከናወኑ ሥራዎችን በመገምገም፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት እና ቀጣይ የአፈፃፀም አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ተካሂዷል።

እስካሁን የተገኙ ውጤቶች መነሻ በማድረግ የታዩ ክፍተቶችን በመለየት ለቀጣይ ጊዜ የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በትኩረት መሥራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።

በተለይም የትምህርት ሥራው የሁሉም አካላት ቀጣይነት ያለው ትብብርና ተሳትፎ የሚፈልግ በመሆኑ፣ የተማሪዎች ምዝገባን በማጠናቀቅ እና ትምህርት ቤቶችን ሙሉ በሙሉ በማዘጋጀት የትምህርት ዘመኑን በተሳካ ሁኔታ መጀመር እንደሚገባ ተገልጿል።

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት አፈፃፀም በማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችና ድክመቶችን ለይቶ ተጨባጭ ሰው ተኮር በጎ አገልግሎት በማስቀጠልና በሁሉም መስኮች ማህበራዊ ተፅዕኖን ለማምጣት በቁርጠኝነት መሰራት እንዳለበት ተገልጿል።

በአንዳንድ መዋቅሮች የታየው የአፈፃፀሞች ጉድለቶችን ፈጣን የማሻሻያ እርምጃ የሚፈልጉ ሲሆን ተለይተው እንዲሻሻሉ በሪፖርት ግምገማዉ ተስተውሏል ።

በተያያዘ ለሁሉም መዋቅሮች ግብሬ መለስ በመስጠት ሪፖርቶች ከተገመገሙና ወቅቱ የጠበቀ የተግባር አፈፃፀም በመረጃ አስደግፎ ለሚመለከተው ማድረስ ለቀጣይ ተሞክሮ መሆኑን ተመላክቷል።

የዘንድሮው ክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በትምህርት፣ በጤና፣ በማህበራዊ ድጋፍ፣ በግብርና እና ሌሎች የልማት ዘርፎችን ጨምሮ የተለያዩ የትኩረት መስኮችን በማካተት የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እና የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማጠናከር ለአካባቢው ልማትና ለማህበራዊ አንድነት ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን በሪፖርቱ ዳስሰዋል።

Address

ቀይ አፈር
Jinka

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Benatsemay woreda Government Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share