Aari Zone Government Communication Affairs

Aari Zone Government Communication Affairs ይኸ የኣሪ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ነው።
(2)

የሰሜን አሪ ወረዳና የገሊላ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብን የጤና ችግር የሚያቃልል ዘመናዊ አምቡላንስ ተበረከተ!ሐምሌ 30/2018ዓም ጂንካየአሪ ዞን ጤና መምሪያ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ...
06/08/2026

የሰሜን አሪ ወረዳና የገሊላ ከተማ አስተዳደር ማህበረሰብን የጤና ችግር የሚያቃልል ዘመናዊ አምቡላንስ ተበረከተ!

ሐምሌ 30/2018ዓም ጂንካ
የአሪ ዞን ጤና መምሪያ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የተበረከተለትንና ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበትን እጅግ ዘመናዊ አምቡላንስ ለሰሜን አሪ ወረዳ አስረክቧል።

ይህ አምቡላንስ የማህበረሰቡን የጤና መሠረተ ልማት ለማሟላትና በተለይም የእናቶችና ህፃናትን ጤና ለመጠበቅ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገልጿል።

የአምቡላንስ ርክክቡ በተደረገበት ወቅት የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን፣ ተሽከርካሪው ወረዳው ላይ ሲደርስም የወረዳው አመራሮችና የአካባቢው ማህበረሰብ ደማቅ አቀባበል አድርገውለታል።

በቁልፍ ርክክብ መርሃ ግብሩ ላይ የአሪ ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ሼቺ፣ የዋና አስተዳዳሪ አማካሪ አቶ አማረ ጌታሁን፣ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች እና የጤና መምሪያ የማናጅመንት አባላት በክብር ተገኝተዋል።

የሰሜን አሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጎሳዬ ጉሳር ወረዳው ካለው ርቀት፣ የመሠረተ ልማት ችግርና የተሽከርካሪ እጥረት አኳያ የወረዳውን ማህበረሰብ ችግር አይተው ቅድሚያ ስለሰጡ በወረዳውና በገሊላ ከተማ አስተዳደር ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የአሪ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በድሉ ባጊማሶ አምቡላንሱ የተሰጠው ወረዳው ካለው የህዝብ ብዛትና ርቀት አንፃር የአገልግሎት እጥረቱን ታሳቢ በማድረግ መሆኑን ገልጸዋል።

ተሽከርካሪው ከሌሎች በአሠራሩ የተለየና ከፍተኛ ወጪ የወጣበት በመሆኑ ለረጅም ዓመታት እንዲያገለግል በጥንቃቄ መያዝ እንዳለበትም አሳስበዋል።

የአሪ ዞን ሽግግር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ስመኝ ተስፋዬም የዞኑ አስተዳደር ለሰሜን አሪና ለገሊላ ከተማ ቅድሚያ በመስጠቱ አድንቀዋል። አምቡላንሱ በጥቃቅን ምክንያት ሳይበላሽና ሳይቆም፣ በተለይም ለእናቶችና ለህፃናት ህይወት ማዳኛ በአግባቡ በጥንቃቄ እንዲያገለግል መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሰሜን አሪ ወረዳ ጤና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ ጥላዬ ለማህበረሰቡ ጤና፣ በተለይም ለእናቶችና ህፃናት ጥበቃ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ የዞኑን ጤና መምሪያና የዞኑን አስተዳደር በላቀ ሁኔታ አመስግነዋል።

ኣዞመኮአ

እንኳን ደስ አለን
03/08/2026

እንኳን ደስ አለን

እንኳን ደስ አለን! - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
**************

ቃሏን አክባሪዋ ኢትዮጵያ በአንድ ጀምበር 805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል አዲስ ደማቅ ክብረ ወሰን አስመዘገበች።

ኢትዮጵያ ዛሬ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅዳ 805.3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል ታላቁን ሀገራዊ ዕቅድ በላቀ ስኬትና በታላቅ ድምቀት ማሳካቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ አደረጉ።

ይህ ታሪካዊ ድል የዛሬው ዕለት ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለተከታታይ ስምንት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ያቀደችውን ግብ ያለምንም መጓደል በተግባር እያሳካች መሆኗን በድጋሚ ያረጋገጠ ነው።

“ከተረጅነት ወደ ምርታማነት እና የክረምት በጎ ተግባር እንቅስቃሴ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ”  ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ጂንካበአሪ ዞን “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” የሚደረገውን ሽግግር ለማ...
03/08/2026

“ከተረጅነት ወደ ምርታማነት እና የክረምት በጎ ተግባር እንቅስቃሴ አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ”

ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ጂንካ
በአሪ ዞን “ከተረጅነት ወደ ምርታማነት” የሚደረገውን ሽግግር ለማፋጠንና የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራትን የሚገመግም የጋራ መድረክ በጂንካ ከተማ ተካሂዷል።

በግምገማ መድረኩ ላይ ከክልል የመጡ ደጋፊ አመራሮች፣ የዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ እና የክረምት በጎ ተግባር አብይና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በጋራ ተሳትፈዋል።

በመድረኩ ላይ የቀረበው ሪፖርት እንደሚያመላክተው፤ ወጣቶችን፣ ሴቶችን እና የተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማትን በስፋት በማንቀሳቀስ በግብርናው ዘርፍ ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸው ተገልጿል።

በተለይም ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ብሎም በወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት አማካኝነት በክረምት ወራት የተከናወኑ የማህበረሰብ አቀፍ የበጎ አድራጎት ሥራዎች አፈፃፀም ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በዚህ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ላይ አቶ ሣጌ ሻምባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የዲሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ፣ አቶ ግዳልቅ አልቅሚ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣ ወ/ሮ ወይኒቱ ገደላ የክልሉ አደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ከፍተኛ ባለሙያ እንዲሁም የዞኑ የአብይና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በንቃት ተሳትፈውበታል።

ተሳታፊዎቹ የቀረቡትን ሪፖርቶች መነሻ በማድረግ በጥንካሬና በድክመት የታዩ ተግባራትን በመለየትና በቀጣይም ሥራዎቹን ይበልጥ በማጠናከር የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

03/08/2026
03/08/2026
"በአንድ ጀምበር አሻራ በማኖር የምንተክላቸው ችግኞች ተፈጥሮንና የአየር ንብረትን ከመጠበቅ ባለፈ፣ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት መሰረት ናቸው" የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ...
03/08/2026

"በአንድ ጀምበር አሻራ በማኖር የምንተክላቸው ችግኞች ተፈጥሮንና የአየር ንብረትን ከመጠበቅ ባለፈ፣ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት መሰረት ናቸው" የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ

የኣሪ ዞን የ2018 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በደቡብ አሪ ወረዳ ጎመር ቀበሌ በይፋ ተጀመረ!

(ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም፣ ጂንካ)
በአሪ ዞን በደቡብ አሪ ወረዳ ጎመር ቀበሌ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ.ም አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ ዞናዊ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በይፋ ተጀምሯል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል።

በመርሀጎብሩም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ "በአንድ ጀምበር አሻራ በማኖር የምንተክላቸው ችግኞች ተፈጥሮንና የአየር ንብረትን ከመጠበቅ ባለፈ፣ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት መሰረት በመሆናቸው እያንዳንዱ የማህበረሰብ ክፍል ችግኞችን በኃላፊነት የመትከልና የመንከባከብ ግዴታ አለበት ብለዋል ።

የአሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ "አቶ አብርሃም አታ "የምንተክላቸው ችግኞች የተሻለ አካባቢን ለቀጣዩ ትውልድ ለማውረስ፣ ነገን ብሩህ ለማድረግና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ሰፊ ጠቀሜታ አላቸው።

ኃላፊው አክለውም በዘንድሮው መርሃ ግብር በዞን ደረጃ ከ4.9 ሚሊዮን በላይ ችግኞች እንደሚተከሉ ገልጸው፣ ትኩረቱም ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን ለኢኮኖሚ መሰረት በሆኑ የችግኝ አይነቶች ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ ገብሬ ባይስማይ የደቡብ አሪ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በዛሬው መርሃ ግብር በወረዳው ብቻ 1.6 ሚሊዮን ችግኝ እንደሚተከል አሳውቀዋል። ማህበረሰቡ ችግኞችን ተክሎ መተው ሳይሆን ቀጣይነት ያለው እንክብካቤ ሊያደርግላቸው እንደሚገባም አሳስበዋል።

የአሪ ዞን አመራሮች እንደገለጹት፣ የሚተከሉ ችግኞች የአፈርን ለምነት በመጠበቅ ምርታማነትን በመጨመር ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ስላላቸው፣ ለችግኞቹ እንክብካቤ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል።

በአሁኑ ሰዓት በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች የችግኝ ተከላው በደመቀ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል።

አዞመኮአ

የ2018 ዓ.ም አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሐ ግብር ...
03/08/2026

የ2018 ዓ.ም አረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በይፋ ተጀምሯል

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሐ ግብር በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።

በአንድ ጀምበር 800 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ታሪካዊ መርሐ ግብር ዛሬ መጀመሩን አስመልክቶ ሚኒስትሯ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ አረንጓዴ ዐሻራችንን ይዘን ወደ መሬት የምንወርድበት ትልቅ ምክንያት የደረቀች የነጠፈች የተጎዳች ምድር ስላለችን ነው፡፡

ዛሬ 800 ሚሊየን አረንጓዴ ችግኞች ወደ መሬት ዝቅ ብለው መሬትን ይዳስሳሉ፤ መሬትም ቃሏን የምታጸናበትንና የተቀበለችውን መልሳ በእጥፍ መስጠት እንደምትችል የምታሳይበት ልዩ ቀን ነው ብለዋል።

በዘንድሮው ክረምት 8 ቢሊየን ችግኞችን እንተክላለን ብለን እቅድ ይዘናል ብለው የምንተክለው በሃሳብ እና በተግባር አንድነት ሲሉ ተናግረዋል።

በተግባርና በሃሳብ የምንሄድበት ትልቁ መንነሻ ደግሞ የመደመር መንግሥት ኑ በአንድነት የተጎሳቆለች እና የነጠፈችውን ምድራችንን እናክማት በሚል ሃሳብ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

800 ሚሊየን ችግኞች፣ በተግባር እና በሐሳብ አንድነት በመደመር ዕሳቤ እናሳካለንም ነው ያሉት፡፡
የፌመኮአ

ቀደም ሲል አገልግሎት እየሰጡ ያቋረጡ የዉሃ ተቋማት በVSF ጀርመን ዳግም እድሳትና በሶላር ሲስተም የተቀየሩ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ተቋማት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍ ሆኑ።       ሐምሌ 26/...
02/08/2026

ቀደም ሲል አገልግሎት እየሰጡ ያቋረጡ የዉሃ ተቋማት በVSF ጀርመን ዳግም እድሳትና በሶላር ሲስተም የተቀየሩ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ተቋማት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍ ሆኑ።

ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም
በVSF ጀርመን በተሰኘው ግብረሰናይ ድርጅት በጨለጎድ ፣በሽሽር እና ሴንጋል ቀበሌያት ቀደም ሲል ተገኝብቶ አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ንፁህ መጠጥ ዉሃ ተቋማት በVSF ጀርመን ዳግም ታድሶ ወደ ሶላር ሲስተም የተቀየሩ ንፁህ የመጠጥ ዉሃ ተቋማት ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረገ።

የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሃም አታ በዞኑ የሚታየዉን የንፁህ መጠጥ ዉሃ ችግር ለመፍታት ቪ ኤስ ኤፍ ጀርመን ያደረገውን የተግባር እንቅስቃሴ አመስግነዋል ።

በቀጣይም ከመንግስት ጎን በመሆን አሁንም በዞኑ የሚታየዉን የንፁህ መጠጥ ዉሃ በመገንባት እንድያግዙ ጥሪ አቅርበዋል ።ህብረተሰቡም ተጠግኘዉ ወደ አገልገሎት የገቡ የዉሃ ተቋማት በባለቤትነት ጠብቀው እንዲገለገሉበት አሳስበዋል ።

የኣሪ ዞን ዉሃና ኢነርጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ግዛቸዉ በላይ ቪ ኤስ ኤፍ ጀርመን በዞኑ በሁለት ወረዳዎች በመንግሥት መድረስ ያልተቻሉ የንፁህ የጠጥ ውሀ አገልግሎት ክፍተት ከመሙላት አኳያ የተሻለ ስራ መስራታቸዉን አመስግነዋል ።

የVSF ጀርመን ድርጅት ዋና አስተባባሪ አቶ ሐጅ አማን ድርጅቱ በኣሪ ዞን በባካ ዳዉላ ኣሪ እና በደቡብ ኣሪ ወረዳዎች በግብርናና በዉሃ ዘርፍ እየሰሩ እንዳሉ አንስተዉ እስከአሁን በደቡብ ኣሪ ወረዳ 64 ሚሊየን ብር የፈጀ ፕሮጀክቶችን መስራታቸውን ገልጸዋል ።

በግብርና ዘርፍ በሶላር የሚሰራ መስኖ በጨለጎድ ቀበሌ እየሠሩ እንዳለና በሽሽር የእንስሳት መኖ ዝግጅት ላይ 50 አርሶ አደሩን በማሰልጠን ያደራጁ ሆኖ በቅርቡ የመኖ መከትከቻ ማሽን ተገዝቶ እንደሚቀርብ ተናግረዋል ። ለስራቸዉ መሳካት ድጋፍና ትብብር ያደረጉ በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላትን አመስግነዋል ።

በድርጅቱ የዉሃ መሃንዲስ የሆኑ አቶ ሀገሬ በለጠ በሶስቱም ቀበሌ በዲዚል ጀነሬተር ይሰሩ የነበሩና በተለያየ የቴክኒክ ችግር አገልግሎት ያቋረጡ መሆኑን በመጥቀስ ዳግም ወደ አገልግሎት እንድገቡ በሶላር እና በዲዚል ጀኔሬተር እንድሰሩ መቻላቸውን ገልፀዋል ። ተጨማሪ የማስፋፊያ ስራ የተሰራ መሆኑን በመግለጽ እያንዳንዱ የዉሃ ተቋማት ከ3000 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አብራርተዋል ።

የዞን ዉሃና ኢነርጂ መምሪያ የዋንጫና የሴርትፊከት ስጦታዎች ለፕሮጀክቱ አበርክቷል ።
በፕሮግራሙ የኣሪ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅ/ ጽ/ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አፈዶ ወርቁ እና ሌሎች የዞኑ ፊት አመራሮች ፣ የመምሪያ ኃላፊዎች እና የወረዳ አመራሮች ተገኝተዋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደጋፊ አመራር ከዞን የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አስፈፃሚ ኮማንድ ፖስት ጋር በጋራ በመሆን የወረዳዎችን የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ ግምገማና ምልከታ አካሄደ።ሐምሌ፦25...
01/08/2026

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደጋፊ አመራር ከዞን የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር አስፈፃሚ ኮማንድ ፖስት ጋር በጋራ በመሆን የወረዳዎችን የዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ ግምገማና ምልከታ አካሄደ።

ሐምሌ፦25/2018ዓ/ም
ኣሪ ዞን/ጂንካ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ም/ኃላፊ የሆኑት የተከበሩ አቶ ግዳልቅ አልቅሚ እንዳሉት በሀገር አቀፍ ደረጃ በሐምሌ 27/2018ዓ/ም የሚደረገዉን የአረንጓዴ አሻራ ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ ማጠቃለያ ግምገማ የቦታ ዝግጅት ምልከታን ጨምሮ በተደራጁ ግብረሃይሎች በጥብቅ ዲሲፕሊን እየተመራ እንደሆነም ገልፀዋል።

ስምሪት የወሰዱ አመራሮችም የቦታ ዝግጅት፣የችግኝ ሥርጭትና የተሳታፊ አካላት ጥምርታን በጥንቃቄ በማደራጀት የቅስቀሳና ሕብረተሰብን የማነቃቃት ሥራዎችን በልዩ ንቅናቄ እና ትኩረት በመስራት ይኸንን ሀገራዊ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።

በኣሪ ዞን ለሐምሌ 27ቱ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር የተደረጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የመስክ ምልከታ ተካሄደሐምሌ 25/2018ዓም : ጂንካከመምሪያው የፌስቡክ ገፅ ባገኘነው መረጃ መሰረት በመ...
01/08/2026

በኣሪ ዞን ለሐምሌ 27ቱ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር የተደረጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የመስክ ምልከታ ተካሄደ

ሐምሌ 25/2018ዓም : ጂንካ
ከመምሪያው የፌስቡክ ገፅ ባገኘነው መረጃ መሰረት በመጪው ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም የሚካሄደውን ታላቅ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር ውጤታማ ለማድረግ በዞኑ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለመገምገም የሚያስችል የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።

በዚህ የመስክ ምልከታና የክትትል ሥራ ላይ የኣሪ ዞን የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አፌዶ ወርቁ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ከአስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ጋር በጋራ በመሆን ተገኝተዋል።

ኃላፊዎቹ በዞኑ በተመረጡ የችግኝ ጣቢያዎች እና የተከላ ቦታዎች ላይ በመዘዋወር የተከናወኑትን የአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ የጉድጓድ መቆፈር እንዲሁም የችግኝ ዝግጅት ሥራዎችን በአካል ተመልክተዋል።

በምልከታው ወቅት ለአካባቢው ሥነ-ምህዳር ተስማሚ የሆኑና የኢኮኖሚ ጥቅም ሊያስገኙ የሚችሉ የችግኝ ዓይነቶች መዘጋጀታቸው የተረጋገጠ ሲሆን፣ ሕብረተሰቡ በነቂስ ወጥቶ አሻራውን እንዲያኖር ጥሪ ቀርቧል።

Address

Jinka

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aari Zone Government Communication Affairs posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share