ቆቦ ኮሙኒኬሽን kobo communication

ቆቦ ኮሙኒኬሽን kobo communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቆቦ ኮሙኒኬሽን kobo communication, Government Organization, ቆቦ, K'obo.

የቆቦ ከተማ አስተዳደር "የእመርታ ቀን" በመስክ ጉብኝት በደመቀ ሁኔታ አከበረ።​ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን ) የቆቦ ከተማ አስተዳደር "የኢትዮጵያ መንሰራራት" በሚል መሪ ቃል ...
06/09/2026

የቆቦ ከተማ አስተዳደር "የእመርታ ቀን" በመስክ ጉብኝት በደመቀ ሁኔታ አከበረ።

​ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን ) የቆቦ ከተማ አስተዳደር "የኢትዮጵያ መንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የተሰናዳውን "የእመርታ ቀን" በግብርና ልማት ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት የተካሄደውን የመስክ ጉብኝት ጨምሮ በታላቅ ድምቀት አክብሯል።

​ የቀኑን መከበር ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው በዚህ የመስክ ምልከታ ላይ የከተማውና የየቀበሌው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣ የፀጥታ አመራርና አባላት ፣የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም ከሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ነዋሪዎችና ጎብኝዎች በጋራ ተሳትፈዋል።

​በጉብኝቱ ወቅት በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች፣ የወቅቱ ሰብል ልማት እንቅስቃሴዎችና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፉ አሰራሮች የተጎበኙ ሲሆን፣ በተለይም በግብርናው ዘርፍ የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ በምግብ ራስን ለመቻል በሚደረገው ሀገራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ጎልቶ ታይቷል።

ዘመናዊ የምርት ማሳደጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም፣ የመስኖ ልማትን በማስፋፋት እና የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የምግብ ዋስትናን በዘላቂነት ማረጋገጥ እንደሚገባ አጽንኦት ተሰጥቶበታል።

​ተሳታፊዎች በበኩላቸው በመስክ ያዩት የምርታማነት እድገትና የልማት እንቅስቃሴ በምግብ ራስን ለመቻል የተያዘውን ግብ ለማሳካት ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጸው፣ በቀጣይም ለአካባቢው አጠቃላይ እድገትና ለወደፊት እመርታ የበኩላቸውን አዎንታዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የቆቦ ከተማ አሰተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት እና የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎችን ገመገመ።​ ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን ) የቆቦ ከተማ አስተዳ...
04/09/2026

የቆቦ ከተማ አሰተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት የ1ኛ ሩብ ዓመት እና የክረምት በጎ ፈቃድ ሥራዎችን ገመገመ።

​ ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን ) የቆቦ ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ከሰሜን ወሎ ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ከመጡ ባለሙያዎች ጋር በመሆን የ2019 ዓ.ም የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሥራዎችን በጋራ ገመገመ።

በከተማው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን ለማደስ እና አዳዲስ ባለሀብቶችን ለመሳብ የተደረጉ ጥረቶች በጥንካሬ የተነሱ ሲሆን፣ የቀረቡ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶችን ለማሻሻል አቅጣጫ ተቀምጧል።

በክረምቱ ወቅት የባለሀብቶችን አቅም በማስተባበር በበጎ ፈቃድ የተከናወኑ የልማት እና የማህበራዊ አገልግሎት ሥራዎች አበረታች ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጻል።

በመጨረሻም ከዞኑ መምሪያ የመጡት ባለሙያዎች በቀረበው ሪፖርት ላይ ገንቢ አስተያየት የሰጡ ሲሆን፣ በቀጣይ ሩብ ዓመት በኢንቨስትመንት ዘርፍ የሚታዩ ማነቆዎችን በመቅረፍ፣ የቁጥጥር እና ድጋፍ ሥርዓቱን በማጠናከር ወደ ሥራ የገቡ የባለሃብቶችን አቅም ለማሳደግ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ ገልፀዋል ።

በቆቦ ከተማ አስተዳደር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመጀመሪያ ምዕራፍ ጥቅል አፈጻጸም ተገመገመ።​​ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )በቆቦ ከተማ አስተዳደር ከዞን በመጡ የክረም...
04/09/2026

በቆቦ ከተማ አስተዳደር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የመጀመሪያ ምዕራፍ ጥቅል አፈጻጸም ተገመገመ።

​ነሃሴ 29/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )በቆቦ ከተማ አስተዳደር ከዞን በመጡ የክረምት በጎ ፍቃድ ቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪዎች በተገኙበት የሁለተኛ ዙር የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ጥቅል አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።

​በአፈፃፀም ግምገማ መድረኩ ላይ የቴክኒክ ኮሚቴ፣የአብይ ኮሚቴ አባላት እና የሴክተሮች ፎካል ፐርሰኖች የተገኙ ሲሆን፣ በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ የተመዘገቡ ስኬቶች እና የታዩ ክፍተቶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

​ የአብይ ኮሚቴ እና የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ፎካል ፐርሰኖች ያደረጉት የተቀናጀ አመራር ለስራው ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ ተገልጿል።በተለይም በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ በአረጋውያንና አቅመ-ደካሞች ቤት እድሳት፣ በደም ልገሳ፣ በትምህርት ድጋፍና በማህበራዊ ልማት ዘርፎች የታቀዱ ስራዎች በስኬት መከናወናቸው ተመልክቷል።

​የህብረተሰብ ተሳትፎ፦ የወጣቶችንና የመላው የቆቦ ከተማ ነዋሪን ንቁ ተሳትፎ አስተባብሮ በመምራት ረገድ ውጤታማ ስራ መሰራቱ አንስተው የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎቱ በበጋውም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል ።

​በመጨረሻም በግምገማው ወቅት የታዩ አዎንታዊ ጎኖችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ያጋጠሙ ክፍተቶችን በመቅረፍ ለቀጣይ ተመሳሳይ ማህበራዊ አገልግሎቶች የተሻለ ዝግጅት ለማድረግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተስጠው መድረኩ ተጠናቋል።

04/09/2026
ተስፋ ለሚሹ ኢትዮጵያ  Hope for the Needy - HN አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት በይፋ ተመሠረተ።​ነሃሴ 28/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )በህፃናት፣ በሴቶች እና በወጣቶ...
03/09/2026

ተስፋ ለሚሹ ኢትዮጵያ Hope for the Needy - HN አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት በይፋ ተመሠረተ።

​ነሃሴ 28/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )በህፃናት፣ በሴቶች እና በወጣቶች ሕይወት ላይ ብሩህ ተስፋን ለመፈንጠቅና ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ያለመ «ተስፋ ለሚሹ ኢትዮጵያ» (Hope for the Needy - HN) የተሰኘ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ምስረታውን በይፋ አከናወነ።

​ድርጅቱ በዋናነት ትኩረቱን አቅመ-ደካሞች እና ድጋፍ የሚሹ ማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የሚያደርግ ሲሆን፤ በተለይም የህፃናትን መሠረታዊ ፍላጎት፣ ትምህርት ማረጋገጥ፤የሴቶችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አቅም በማጎልበት እራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዲደግፉ ማስቻል፤የወጣቶችን ክህሎትና ፈጠራ በማውጣት ለተሻለ ነገ ማዘጋጀትና ብሩህ ተስፋን መፍጠር የሚሉ ዋና ዋና ዓላማዎችን ሰንቆ የተነሳ ነው።

​በምስረታው ስነ-ስርዓት ወቅት የድርጅቱ መስራቾችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፋጡማ ሙሀመድ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ ከልዩ ልዩ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት፣ በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን ህይወት ለመቀየርና በተግባር የተደገፈ ስራዎችን ለማከናወን ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።

በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።​ ነሃሴ 27/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )በቆቦ ከተማ “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት ...
02/09/2026

በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።

​ ነሃሴ 27/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )በቆቦ ከተማ “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን በሚል መሪ ቃል በማዕከል ደረጃ ከጠቅላላ የንግዱ ማህበረሰብ ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ።

​በምክክር መድረኩ ላይ የከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች እና የንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮች የተገኙ ሲሆን፣ በወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ሁኔታዎች እንዲሁም በከተማዋ ዘላቂ ሰላም እና ልማት ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

​በውይይቱ ወቅት እንደተገለፀው፣ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ማስከበር ለንግድ እንቅስቃሴው መቃናት፣ ለኢኮኖሚ መረጋጋት እና ለህብረተሰቡ እንግልት መቀነስ ዋና መሰረት በመሆኑም የንግዱ ማህበረሰብ የሰላም ባለቤት መሆን እንዳለበት ተገልጿል ።

ለንግዱ ማህበረሰብ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን፣ ምርት መሸሸግን እና የዋጋ ጭማሪን በመከላከል ገበያው እንዲረጋጋ በማድረግ፤​ልማትን በማፋጠን በከተማዋ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎችና ማህበራዊ አገልግሎቶች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

በመጨረሻም የንግዱ ማህበረሰብ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ሰላም ለንግድ ስራቸው ህልውና ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው ህገ-ወጥነትን በመታገልና ከአመራሩ ጋር በቀጣይ በመቀናጀት የአካባቢውን ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በቆቦ ከተማ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ያለመ የህዝብ የውይይት መድረክ ተካሄደ።​ ነሃሴ 26/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )በቆቦ ከተማ አስተዳደር “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ...
01/09/2026

በቆቦ ከተማ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ያለመ የህዝብ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

​ ነሃሴ 26/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )በቆቦ ከተማ አስተዳደር “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ የሰላምና የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከሴቶች እና ወጣቶች ጋር በማዕከል ደረጃ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

​ በመድረኩ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ዘላቂ ለማድረግ በሚቻሉባቸው መንገዶች፣ የወጣቶች እና ሴቶች አደረጃጀቶች ባላቸው ሚና እንዲሁም የደህንነት ስጋቶችን በጋራ በመመከት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ወጣቶች እና ሴቶች የአካባቢያቸውን ሰላም በመጠበቅ፣ ዘላቂ የልማት ስራዎችን በማፋጠን እና የፀጥታ ስጋቶችን ቀድሞ በመከላከል ረገድ ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን እንዳለባቸው ተመላክቷል።

ያለ ሰላም ልማት፡ ያለ ልማት ደግሞ ዘላቂ ሰላም ሊኖር ስለማይችል ህብረተሰቡ ከመንግስት ጋር በመቀናጀት ለአካባቢው መረጋጋት በጋራ እንዲሰራም ጥሪ ቀርቧል።

​ተሳታፊዎቹም በአካባቢያቸው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍንና የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉና የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

በቆቦ ከተማ  አስተዳድር ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የሰላምና ፀጥታ ውይይት ተካሄደ።​ነሃሴ 26/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )በቆቦ ከተማ “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አ...
01/09/2026

በቆቦ ከተማ አስተዳድር ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የሰላምና ፀጥታ ውይይት ተካሄደ።

​ነሃሴ 26/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )በቆቦ ከተማ “ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!” በሚል መሪ ቃል በክላስተር ደረጃ ከመንግስት ሰራተኞች ጋር በወቅታዊ የሰላም እና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

​መድረኩ የመንግስት ሰራተኛው የአካባቢውን ሰላም በማስከበር፣ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች በመመለስ እና አገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍ ረገድ ያላቸውን የጎላ ሚና ለማጠናከር ያለመ ነው።

የመንግስት ሰራተኞች ህዝቡን በቅንነት በማገልገል፣ የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ እና ህዝባዊ ወገንተኝነትን በማሳየት ረገድ የአንበሳውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው ተገልጿል።

የህዝቡን እንግልት የሚቀንሱ ቀልጣፋ አሰራሮችን በመዘርጋት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መፍታት ለዘላቂ ሰላምና ልማት መረጋገጥ መሰረት መሆኑ ተጠቅሷል።

​በመጨረሻም የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የተጣለባቸውን ህዝባዊ ኃላፊነት በብቃት በመወጣት፣ የከተማዋን ሰላም ለማስከበር እና የልማት ስራዎችን ለማፋጠን በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

የቆቦ ከተማ አስተዳደር የከተማ ክላስተር ተቋማት የበጀት ዓመቱን የሁለት ወር የሥራ አፈጻጸም ገመገሙ።​ቆቦ ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም  (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )የቆቦ ከተማ አስተዳደር የከተማ ክላስ...
31/08/2026

የቆቦ ከተማ አስተዳደር የከተማ ክላስተር ተቋማት የበጀት ዓመቱን የሁለት ወር የሥራ አፈጻጸም ገመገሙ።

​ቆቦ ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )የቆቦ ከተማ አስተዳደር የከተማ ክላስተር ተቋማት ከዞን ከተመደቡ አስተባባሪዎች ጋር በመሆን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹን ሁለት ወራት (ሐምሌ እና ነሐሴ) የሥራ አፈጻጸም የገመገሙበት የምክክር መድረክ አካሄዱ።

​ የቆቦ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ እና የክላስተሩ አስተባባሪ አቶ ተሾመ ፈንታው እንደገለፁት በሁለቱ ወራት ውስጥ የታቀዱ ዋና ዋና ልማታዊ እና አስተዳደራዊ ተግባራት አፈጻጸም ያቀረበ ሲሆን፣ በተለይም የከተማ ኮሪደር ልማት፣ የሕዝብ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የሰራ ፈላጊ ምዝገባናየስራ ዕድል ፈጠራ፣የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና የውስጥ ገቢ አሰባሰብ ላይ የተከናወኑ አበይት ሥራዎች በጥንካሬና በክፍተት ተለይተው ተገምግመዋል።

​ከዞን የመጡት አስተባባሪዎች በበኩላቸው በሁለቱ ወራት የተመዘገቡ መልካም አፈጻጸሞችን በማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን ደግሞ በሚቀጥሉት ወራት በዕቅድ በመምራትና በቅንጅት በመስራት ፈጣን ውጤት ማምጣት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የከተማ ክላስተር ተቋማት እርስ በእርሳቸው ተቀናጅተው በመስራትና ውጤታማ ተግባራትን በማከናወን የበጀት አመቱን እቅድ ለማሳካት ያለው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ ገልጸዋል ።

​በመጨረሻም የከተማ ክላስተር ተቋማት አመራሮች የታዩ ክፍተቶችን በማስተካከል፣ የሕዝቡን የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች በወቅቱ ለመመለስ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

ሆፕ ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ (HN)ተስፋ ለሚሹኢትዮጵያ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።​ነሃሴ 24/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )ሆፕ ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ (Hop...
30/08/2026

ሆፕ ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ (HN)ተስፋ ለሚሹኢትዮጵያ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ነሃሴ 24/2018 ዓ.ም (ቆቦ ኮሙኒኬሽን )ሆፕ ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ (Hope for the Needy - HN) የተሰኘው ሀገር በቀል የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅት፣ አዲስ የትምህርት ዘመን መጀመርን ምክንያት በማድረግ ለሴቶች ህወፃናት እና ወጣቶች ብሩህ ተስፋ ለመፍጠር ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ እና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

​ድርጅቱ ባከናወነው የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ እርሳስ፣ገንዘብ እና ሌሎች አስፈላጊ የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ለተማሪዎቹ ተደርጓል ።

ሆፕ ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ (HN) መስራች እና ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ወ/ሪት ፋጡማ ሙሀመድ እንደገለጹት ሆፕ ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ (HN) ወደፊትም ማህበረሰብ አቀፍ ድጋፎችን በማጠናከር ለወጣቶችና ህጻናት ብሩህ ተስፋ ለመፍጠር የሚሰራውን በጎ ስራ አጠናክሮ ይቀጥላል።

​ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎችና ወላጆች በበኩላቸው የተደረገላቸው ድጋፍ በትክክለኛው ጊዜ ደራሽና ትልቅ እፎይታ የፈጠረ መሆኑን ገልጸው ለድርጅቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

Address

ቆቦ
K'obo

Telephone

+251333340389

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቆቦ ኮሙኒኬሽን kobo communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share