Raya Kobo Communication Office

Raya Kobo Communication Office ​"የራያ ቆቦ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን፤ የዘወልድ፣ መዛርድ፣ ክፍሎና ስንየ አባቶች የሰላም እና የአንድነት አሻራ ባለቤት። የወረዳችንን የልማት ስራዎች፣ ወቅታዊ መረጃዎች እና የአንድነት እሴቶች እዚህ ይከታተሉ!"

በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ። 🇪🇹🇪🇹በኢትዮጵያ ባለፋት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የላቀ ውጤት መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር...
06/09/2026

በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ። 🇪🇹

🇪🇹በኢትዮጵያ ባለፋት ዓመታት በግብርናው ዘርፍ የላቀ ውጤት መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛው ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ በሰጡት ማብራሪያ መግለጻቸው የሚታወስ ነው።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተውም :-

📌 ባለፉት አምሥት ዓመታት አጠቃላይ የግብርና ምርት ከ44 ሚሊዮን ቶን ወደ 150 ሚሊዮን ቶን አድጓል። በዚህም ከ3 እጥፍ በላይ የምርት ዕድገት አምጥቷል።

📌 የደን ሽፋን ከ17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ አድጓል። ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኝ በመትከል 12 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር መሬት እንዲያገግምም ተደርጓል።

📌 በ2018 በጀት ዓመት 29 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ኩንታል ምርትም ተሠብሥቧል።

👉 ቡናን ለውጭ ገበያ በማቅረብ በአንድ ዓመት ብቻ 3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማግኘት ተችሏል። ይህም የ17 ዓመታት የቡና ምርት ገቢን በአንድ ዓመት ማሳካት የተቻለበት ታሪካዊ ስኬት ኾኗል።

👉 ቀደም ሲል ስንዴን ከውጭ በማስገባት በርካታ ዶላር ታወጣ የነበረውን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከሀገር ውስጥ ፍጆታ አልፎ ወደ ውጭ እየላከች የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ጀምራለች።🌾

📌 በድርቅ የሚታወቁት አካባቢዎች ምርታማ እየኾኑ ነው። ታርሰው የማያውቁ ሥፍራዎች በግብርና ልማት ተሸንፈዋል። ታይቶ የማይታወቅ ምርትም እየሰጡ ነው።

📌 የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረው የሌማት ቱርፋት መርሐ ግብር አስገራሚ ውጤት ተገኝቶበታል።

👉 የዶሮ ስጋ ምርት ከ8 ሺህ ቶን ወደ 190 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። ይህም የ296 በመቶ ጭማሪ እንዳለ ያሳያል።

👉 የአቮካዶ፣ ሙዝ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ እና ሌሎችንም የፍራፍሬ አይነቶች በስፋት በማምረት ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ኾኗል። ለአብነትም በአቮካዶ ምርት በአፍሪካ ሁለተኛዋ ለውጭ ገበያ የምታቀርብ ሀገር መኾን ችላለች።

📊 ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ እያስመዘገበች ያለው ተጨባጭ ለውጥ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት የማረጋገጥ ግስጋሴዋን እንድታስቀጥል የሚያስችላት ስለመኾኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጻቸው አይዘነጋም።

#አሚኮ

06/09/2026
ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ እመርታና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዋና ምሰሶ መሆኑ ተገለፀ ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ራያ ቆቦ ኮሙኒኬሽን)የጳጉሜ 1 የእመርታ ቀንን በማስመልከት የራያ ቆቦ ወረዳ ኢንዱስትሪና ...
06/09/2026

ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ እመርታና የሥራ ዕድል ፈጠራ ዋና ምሰሶ መሆኑ ተገለፀ

ጳጉሜ 1/2018 ዓ.ም (ራያ ቆቦ ኮሙኒኬሽን)
የጳጉሜ 1 የእመርታ ቀንን በማስመልከት የራያ ቆቦ ወረዳ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ በማምረት ላይ ያሉና በግንባታ ላይ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የመስክ ጉብኝት አካሂዷል።

የወረዳው ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደጀን ስለሺ እንደገለጹት፣ በጉብኝቱ በአሁኑ ወቅት ምርት ላይ የሚገኘው ጎሊና ዱቄት ፋብሪካ እንዲሁም በግንባታ ላይ ያሉት ቤዛዊት ሞላ ዱቄት ፋብሪካ፣ ንጉስ ከበደ አትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ እና በ240 ሚሊዮን ብር ካፒታል እየተገነባ ያለው ራያ ውሃ ፋብሪካ ተጎብኝተዋል።

በግንባታ ላይ ያሉት ኢንዱስትሪዎች ወደ ሙሉ ምርት ሲገቡ ለ180 ዜጎች ቋሚ እና ለ140 ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ተገልጿል።

ይህም በወረዳው የኢንዱስትሪ ልማትን ከማፋጠን ባሻገር ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠር የኢኮኖሚ እመርታን እንደሚያጎለብት ተጠቁሟል።

ባለሀብቶቹ በበኩላቸው ፕሮጀክቶቻቸውን በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ ለማጠናቀቅ ተግተው እየሰሩ መሆኑን ገልጸው፣ ነገር ግን ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮችና የነዳጅ እጥረት ለግንባታ ሥራቸው ፈተና መሆኑን አስረድተዋል።

#ጳጉሜ1

06/09/2026
ጳጉሜ 1 – የእመርታ ቀን በመስክ ጉብኝት ተከበረ ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ም (ራያ ቆቦ ኮሙኒኬሽን)የራያ ቆቦ ወረዳ ጳጉሜ 1 “የእመርታ ቀንን” በወረዳው እየተከናወኑ ያሉ የግብርናና የኢንዱስ...
06/09/2026

ጳጉሜ 1 – የእመርታ ቀን በመስክ ጉብኝት ተከበረ

ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ም (ራያ ቆቦ ኮሙኒኬሽን)
የራያ ቆቦ ወረዳ ጳጉሜ 1 “የእመርታ ቀንን” በወረዳው እየተከናወኑ ያሉ የግብርናና የኢንዱስትሪ ልማቶችን ለማበረታታት በተደረገ የመስክ ጉብኝት አክብሯል።

በጉብኝቱ የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊና የወረዳው አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ሲሳይ አማረ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌታቸው አማረ ተገኝተው እንደገለጹት፣ የጳጉሜ 1 የእመርታ ቀን በአንድ ዓመት ውስጥ የተመዘገቡ የልማት ውጤቶችን የምንገመግምበት፣ ለቀጣይ የተሻለ ሥራም የምንነሳሳበት ቀን መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም በግብርና ምርታማነት፣ በችግኝ ልማት፣ በፍራፍሬና አትክልት እሴት ጭማሪ እንዲሁም በአካባቢው ኢንዱስትሪ ልማት የተጀመሩ ሥራዎች የወረዳውን ኢኮኖሚ ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል።

በመስክ ጉብኝቱም የግብርና ችግኝ ጣቢያዎች፣ በክላስተር እየለሙ ያሉ የማንጎ ማሳዎች፣ የጎሊና ዱቄት ፋብሪካ፣ በግንባታ ላይ ያሉ የዱቄት ፋብሪካዎች እና የአትክልትና ፍራፍሬ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ተጎብኝተዋል።

በመጨረሻም አመራሮቹ የተጀመሩ ልማቶች በጥራትና በተያዘላቸው ጊዜ መጠናቀቅ እንዳለባቸው ገልጸው፣ የወረዳውን የእመርታ ጉዞ በተጠናከረ ትብብር ለማስቀጠል ጥሪ አቅርበዋል።

በራያ ቆቦ ወረዳ የጳጉሜ ቀናትን አከባበር በተመለከተ ከወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ ።      ጳጉሜ 01/2018 (ራያ ቆቦ ኮሙኒኬሽን) በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የጳጉሜ ቀ...
06/09/2026

በራያ ቆቦ ወረዳ የጳጉሜ ቀናትን አከባበር በተመለከተ ከወረዳ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሄደ ።

ጳጉሜ 01/2018 (ራያ ቆቦ ኮሙኒኬሽን)
በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የጳጉሜ ቀናት አከባበርን በተመለከተ ከወረዳ አመራሮች ጋር የወይይት መድረክ ተካሂዷል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የራያ ቆቦ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊና የአስተዳዳሪ ተወካይ አቶ ሲሳይ አማረ እና የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጌታቸው አማረ የጳጉሜ ቀን አከባበር በተመለከተ ሰፋ ያለ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ፤ ሁሉም አመራር ያገባኛል እና በኃላፊነት ስሜት አምስቱን የጳጉሜ ቀናት በንቃት እንዲከበሩ መከታተል እና ማስተባበር እንዳለባቸው በአጽንኦት አሳሰበዋል ።

እያንዳንዱ የጳጉሜ ቀናት አከባበር የራሳቸው የሆነ ስያሜ እንዳላቸው እና ስያሜዎች በዝርዝር ቀርበዋል።
ጳጉሜ 1 የእምርታ ቀን
ጳጉሜ 2 የማንሰራራት ቀን
ጳጉሜ 3 የጽናት ቀን
ጳጉሜ 4 የህብር ቀን
ጳጉሜ 5 የነገ ቀን ሁነው ተሰይመዋል።

አዲሱን ዓመት በአዲስ ተስፋና በአዲስ ራዕይ!ጳጉሜን 1 — የእመርታ ቀንጳጉሜን፤ የአሮጌው ዓመት መደምደሚያ፣ የአዲሱ ዓመት መነሻ ነው። አዲሱን ዓመት በአዲስ ተስፋና በአዲስ ራዕይ እንቀበላለ...
06/09/2026

አዲሱን ዓመት በአዲስ ተስፋና በአዲስ ራዕይ!

ጳጉሜን 1 — የእመርታ ቀን

ጳጉሜን፤ የአሮጌው ዓመት መደምደሚያ፣ የአዲሱ ዓመት መነሻ ነው። አዲሱን ዓመት በአዲስ ተስፋና በአዲስ ራዕይ እንቀበላለን።

በፈጠራና በፍጥነት በታጀበው ሀገራዊ ሪፎርም፣ ኢትዮጵያ ከአዝጋሚ ዕድገት ወደ እመርታዊ ለውጥ እየተሸጋገረች ትገኛለች።

ይህ እመርታም በተጨባጭ ውጤቶች ተገልጧል፡፡ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ወደ ሥራ በመግባቱ በተፈጠረው መነቃቃት፣ የኮሪደር ልማቶች፣ በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ እውን የሆኑ ፕሮጀክቶችና የፈጠሯቸው አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎች የዚህ እመርታ መገለጫዎች ናቸው።

በስንዴ አብዮትና በሌማት ትሩፋት በግብርናው፣ በትምህርትና ሥልጠና እና በጤና ዘርፎች የተመዘገቡ ውጤቶችም የዚህ እመርታ ተጨባጭ ማሳያዎች ናቸው።

በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በዲጂታላይዜሽን አዳዲስ አቅሞችን እየገነባን፣ በኢንዱስትሪ ምርትና ምርተማነትን እያሳደግን፣ በቱሪዝም ያለንን ሀብት ወደ ዕድል እየቀየርን፣ በቴክኖሎጂና ፈጠራ አዳዲስ የዕድገት አድማሶችን መክፈት ችለናል፡፡

ይህን እምራተዊ ለውጥ ቀጣይነት ማረጋገጥ የሚችለው የሰው ሀይላችን ነው፡፡ ስለሆነም ገበያ መር በሆነው የክህሎት ልማት እና ክህሎት መር የሆነውን የሥራ ዕድል ፈጠራ አጠናክሮ በማስቀጠል እንዲሁም ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነቱን በማጠናከር በመስኩ የተመዘጉቡ ውጤቶችን በማላቅና የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ርብርቡ በአዲሱ ዓመትም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

መልካም የእመርታ ቀን!

የእመርታ_ ቀን - ጳጉሜን አንድ ነገን ተልሞ ለትውልድ መቅረጽ የመደመር መንግሥት መገለጫው ሆኗል።የመደመር መንግሥት ለትውልድ የሚሻገር አገራዊ ወረት እያኖረ፤ በተጨባጭ ውጤቶችም እየተገለጸ ...
06/09/2026

የእመርታ_ ቀን - ጳጉሜን አንድ

ነገን ተልሞ ለትውልድ መቅረጽ የመደመር መንግሥት መገለጫው ሆኗል።

የመደመር መንግሥት ለትውልድ የሚሻገር አገራዊ ወረት እያኖረ፤ በተጨባጭ ውጤቶችም እየተገለጸ ቀጥሏል። ባለፉት የለውጥ ዓመታት ከባንዳ እስከ ባዳ በቅንጅት የተወረወሩበትን እያንዳንዷን ጠጠር በጥበብና በጽናት እየለቀመ የአገር ግንባታ ጡብ አድርጓቸዋል፤ ከጸኑ ፈተናዎች የሰሉ ዕድሎች ተፈልቅቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ “ኢትዮጵያዊ ጽናት እና አርቆ አስተዋይነት የታየበት” ሲሉ ያረጋገጡት እና መንግሥት ይፋ ያደረጋቸው የጉባ ብስራቶች የሀገራችን እምቅ አቅም በተግባር የሚገለጥባቸው ግዙፍ ማሳያዎች ናቸው። ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚፈጀው ይህ ማዕቀፍ የኢትዮጵያን የነገ ዕጣ ፈንታ በሰፊው የሚቀይር ታሪካዊ የጋራ ስኬት ነው።

ለመደመር መንግሥት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የብልጽግናው ዋና መለኪያ ነው። የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ መጀመሩ የአርሶ አደራችንን ምርታማነት በብዙ እጥፍ ያሳድጋል። እንደ ሀገርም በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላርን እናተርፍበታለን።

በአፍሪካ ግዙፉ የሆነው አዲሱ የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ግንባታም እውን እየሆነ ነው። ይህ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን የአህጉሪቱ ዋንኛ የሎጂስቲክስ፣ የንግድ እና የዲፕሎማሲ መገናኛ በማድረግ የጂኦ-ኢኮኖሚ አቅማችንን ወደ ታላቅ ከፍታ ያሸጋግረዋል። ብዙዎች በሀገራቸው እውን እንዲሆን የሚመኙትን ይህን ታላቅ ፕሮጀክት ኢትዮጵያውያን በጽናት ጀምረነዋል፤ እንፈጽመዋለን።

የመደመር መንግሥት የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የነገው ትውልድ ዕድል የሚቀየር ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን በአጽኖት ተልሟል። የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ያለ ኢነርጂ ሉዓላዊነት የሚታሰብ አይደለም። ለዚህም ነው መንግሥት የኢነርጂ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የኢኮኖሚ ነጻነታችን ማዕዘን ድንጋይ ነው በሚል ስትራቴጂያዊ ትኩረት የሰጠው።

ከታላቁ የህዳሴ ግድባችን ቀጥሎ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት የሆነው የመጀመሪያው የጋዝ ፋብሪካችን ተመርቋል፤ ሁለተኛውም እየተገነባ ነው። የነዚህና ሌሎች በሂደት ላይ ያሉ ግዙፍ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች መጠናቀቅ እና ሥራ መጀመር ከውጭ የሚገባውን የኢነርጂ ፍላጎት በማሟላት ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ ያስቀራል፤ ለኢንዱስትሪ ዘርፉ ማበብም ጽኑ መሠረት ይጥላል።

የልማት እውነተኛ ልክ የዜጎች ክብርና ማኅበራዊ ፍትህ መረጋገጥ ነው። መንግሥት ለዚህ አብላጫ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል። በመላው ሀገሪቱ የሚከናወነው የ1.5 ሚሊዮን ቤቶች ግንባታ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ተጀምሯል። ፕሮጀክቱ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሚሊዮኖችን የቤት ባለቤት ያደርጋል። የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ማኅበራዊ ፍትህን ያረጋግጣል።

መደመር ማለት አብሮ ማደግ እና ሀብትን መጋራት ማለት ነው። እነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ለሚሊዮን ወጣቶች ቀጥተኛ እና ቀጥተኛ ያልሆኑ የሥራ ዕድሎችን ይፈጥራሉ። በዚህ ረገድ ገና ከጅምሩ ውጤቶች መመዝገብ ጀምረዋል።

የመደመር መንግሥት ለትውልድ የሚያሻግረው ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ነው። አዲሱን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ፤ ነገን ዛሬ ተልሞ ለትውልድ መቅረጽ የመደመር መንግሥት ልዩ መገለጫ ሆኗል። ወገባችንን አስረን፣ መቀነታችንን አጥብቀን በላባችን ወዝ የምናኖራቸው ወረቶች ለነገው ትውልድ የሚቀሩ የብልጽግና ውርስ ይሆናሉ። በላባችን ጥረት ኢትዮጵያን በጸና መሠረት ላይ እናቆማለን።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Address

+251914802280
K'obo
NONE

Telephone

+251333340269

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Raya Kobo Communication Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Raya Kobo Communication Office:

Shortcuts

Share