Kelala wereda revenue office -ከላላ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Kelela
  • Kelala wereda revenue office -ከላላ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት

Kelala wereda revenue office -ከላላ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ይህ page ስለ ግብር እና ታክስ እንድሁም ሌሎች ጉዳዮች የሚዳሰሱ

01/08/2023

ከላላ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ.ም ያለው አፈፃፀም
የገቢ አይነት እቅድ ክንውን አፈፃፀም
ቀጥታ ታክስ ..........63945569....60471455.80....94.57%
ቀጥታ ያልሆነ ታክስ..3738324.....2754950.73 .....73.69%
ታክስ ያልሆነ ገቢ ...5855947 .....5390605.31.......92.05%
ድምር ...............73539840..... 68617011.84 ...93.31%

 #ለወረዳችን ደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮች በሙሉ የ2014 የግብር መክፈያ ግዜያችሁ ሳያልቅ እንድትከፍሉ
30/08/2022

#ለወረዳችን ደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮች በሙሉ የ2014 የግብር መክፈያ ግዜያችሁ ሳያልቅ እንድትከፍሉ

ጊዜው ቢዘገይም መላካችሁ ጥሩ ነው::   "
30/06/2022

ጊዜው ቢዘገይም መላካችሁ ጥሩ ነው::
"

በ2014 ዓ.ም የግብር ዘመን በወረራ ተይዘው የነበሩ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የደረጃ "ሐ" ግብር ታክስ አከፋፈልን ይመለከታል

 ! 🎉🎊🎈 !👏 👏 👏  /ቤትAchieved 100% yearly plan!
29/05/2022

! 🎉🎊🎈
!
👏 👏 👏
/ቤት
Achieved 100% yearly plan!

አንዳንድ አትሌቶቻችን በአለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድር ላይ ተጠልፈው ከወደቁ በኃላ

በመነሳት የአሸናፊነት ድል እንዳሳዩን ሁሉ የደቡብ ወሎ ከተሞችም ከትህነግ ወረራ አገግመው የገቢ አሰባሰብ ድል እያሰሙን ነው።

እንኳን ደስ አላችሁ!

በደቡብ ወሎ ዞን አስ/ር የከለላ ከተማ አስተደደር የዕቅዱን ብር 16,923,635.19 ወይም 100.055 በመቶ መሠብሠብ እንደሚቻል አሳይተውናል።

ውድድሩ ከሯል በቀጣይ አስራ ሁለት ቀናት ብዙ ተአምር እንደምናይ እርግጠኛ ሁነናል

በርቱልን
ክብረት ማህሙድ ምክትል ቢሮ ሃላፊ

11/03/2022

ሠንጠረዥ “ሐ”
ከንግድ ሥራ በሚገኝ ገቢ ላይ ግብርን ስለመጣል
ገቢ ግብር አዋጅ 240/2008 ዓ.ም ከአንቀፅ 18 እስከ 24
በንግድ ስራ ገቢ ላይ ግብርን ስለመጣል

1. በግብር ዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ያለው ሰው በእያንዳንዱ የግብር ዓመት የንግድ ሥራ ገቢ ግብር ይከፍላል።
2. አንድ ግብር ከፋይ በአንድ የግብር ዓመት የሚከፍለው የንግድ ሥራ ገቢ ግብር የሚሰላው ከዚህ በታች በተጠቀሱ ምጣኔዎች በግብር ከፋዩ የግብር ዓመት ግብር የሚከፈልበት ገቢ ላይ ተፈፃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ነው።

በንግድ ሥራ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ ምጣኔዎች
1. በድርጅት ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው የንግድ ሥራ ገቢ የግብር መጣኔ ሰላሳ በመቶ (30%) ነው።
2. በግለሰቦች ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑ የንግድ ሥራ ገቢ ምጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
3. ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ግብር የሚከፍሉት በዚህ ሥር በተመለከቱት ምጣኔዎች መሠረት ይሆናል።
4. "ጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ" የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ቴክኒክ ሙያና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ለማቋቋም በወጣው የመስተዳድር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 205/2003 ዓ.ም የተሰጠውን ትርጉም ይይዛል።

ግብር የሚከፈልበት የንግድ ሥራ ገቢ
1. የአንድ ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት ዓመታዊ የንግድ ሥራ ገቢ ነው የሚባለው ከንግድ ሥራ ከተገኝ ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀዱት ወጪዎች ተቀናሽ ከተደረጉ በኋላ የሚገኘው የገቢ መጠን ነው።
2. የአንድ ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት የግብር ዓመቱ ገቢ የሚወሰነው ግብር ከፋዩ በፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች መሠረት በሚያዘጋጀው የትርፍና ኪሳራ ወይም ገቢ መግለጫ ላይ በመመስረት ይሆናል።

የንግድ ሥራ ገቢ
1. የዚህ አዋጅ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፤ በአንድ የግብር ዓመት የአንድ የንግድ ሥራ ገቢ ግብር ከፋይ የንግድ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-
ሀ/ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢን ሳይጨምር ግብር ከፋዩ ዕቃዎችን በማስተላለፍ እንዲሁም አገልግሎቶችን በመስጠት የሚያገኘውን የገንዘብ መጠን ጨምሮ (በግብር ዓመቱ ከንግድ ሥራ ያገኘው ጠቅላላ ገንዘብ መጠን፣)
ለ/ ለንግድ የሚውል ዕቃን ሳይጨምር በግብር ዓመቱ የንግድ ስራ ሀብትን በማስተላለፍ የሚገኝ የገንዘብ መጠን፤
ሐ/ ለግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩ ገቢ ተደርጎ የሚወሰድ ሌላ ማንኛውም የገንዘብ መጠን፣
2. ከንግድ ሥራ የሚገኝ ገቢ ከገቢ ግብር ነፃ የተደረገን ገቢ አይጨምርም።
3. በንግድ ሥራ ገቢ ውስጥ የሚካተተው የንግድ ስራ ሀብትን በማስተላለፍ የሚገኝ ገቢ ከንግድ ሥራ ሀብቱ የመዝገብ ዋጋ በላይ የሆነው የንግድ ሥራ ሀብቱ በሚተላለፍበት ጊዜ ከተላለፈው ሀብት የተገኘው ገቢ ነው።
4. አንድ የንግድ ስራ ሀብት ግብር የሚከፈልበት ከሆነ፡-
ሀ/ በንግድ ስራ ገቢ ውስጥ የሚካተተውን የንግድ ስራ ሀብትን በማስተላለፍ የሚገኘውን ገቢ ለንግድ ስራው ሀብት የተደረገው ወጪ ከንግድ ስራው ሀብት የተጣራ የመዝገብ ዋጋ የሚበልጠው የገንዘብ መጠን ሲሆን፣
ለ/ ከወጪው በላይ በሚገኘው ጥቅም ላይ ግብር ይከፈልበታል።

ተቀናሽ የሚደረጉ ወጪዎች
1. በግብር ዓመቱ የግብር ከፋዩን ግብር የሚከፈልበት ገቢ ለመወሰን በተቀናሽ የሚያዙት ወጪዎች የሚከተሉትን ይጨምራሉ፡-
ሀ/ በንግድ ስራው ገቢው ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማግኘት፣ ለንግዱ ዋስትና ለመስጠትና የንግድ ስራውን ለማስቀጠል በግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ ውስጥ የተደረጉ አስፈላጊ የሆኑ ወጪዎች፣
ለ/ በፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች በተመለከተው መሠረት የተሠላ በግብር ዓመቱ በግብር ከፋዩ ለተሸጠ የንግድ ዕቃ የወጣ ወጪ፣
ሐ/ የንግድ ሥራ ገቢን ለማግኘት ሥራ ላይ የዋሉ ዋጋቸው የሚቀንስ ሀብቶች እና ግዙፋዊ ሀልዎት ለሌላቸው የንግድ ሀብቶች በግብር ዓመቱ የሚታሰበው ጠቅላላ የእርጅና ቅናሽ፣
መ/ ግብር ከፋዩ የንግድ ዕቃን ሳይጨምር በግብር ዘመኑ የንግድ ሥራ ሀብትን ሲያስተላልፍ የሚገጥመው ኪሳራ፣
ሠ/ ለግብር ዘመኑ ለግብር ከፋዩ በተቀናሽነት የሚፈቀድ ሌላ ማናቸውም ወጪ፣
2. ግብር የሚከፈልበት ሃብት ዋጋው የሚቀንስ ሀብት ካልሆነ በስተቀር፣ ግብር የሚከፈልበት ሃብት በሚተላለፍበት ጊዜ ለሚደርስ ኪሳራ የዚህ አዋጅ አንቀጽ 56 ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) (መ) ግን ተፈጻሚ አይሆንም።
3. ለዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 (መ) አፈጻፀም፤ የንግድ ሀብትን በማስተላለፍ የሚደርስ ኪሳራ የሚባለው ሀብቱ በተሸጠበት ጊዜ የሀብቱ የተጣራ የመዝገብ ዋጋ ሀብቱ ከተላለፈበት ዋጋ በሚበልጠው የገንዘብ መጠን ልክ ነው።

የወለድ ወጪ
1. ግብር ከፋዩ የወሰደውን ብድር ወይም ሌላ ዕዳ ወይም ያደረገውን ስምምነት የንግድ ሥራ ገቢውን ለማግኘት ተግባር ያዋለው እስከሆነ ድረስ ከዚህ ጋር በተያያዘ የተከፈለው ወለድ የግብር ከፋዩ የግብር ዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚወሰንበት ጊዜ እንደ ወጪ ይያዝለታል።
2. ለሚከተሉት ወጪዎች ተቀናሽ አይፈቀድም፡
ሀ/ ወለዱ በብሔራዊ ባንክ እና በንግድ ባንኮች መካከል በተደረገ ብድር ከሚታሰብ የወለድ ምጣኔ 2% የሚበልጥ ከሆነ በተቀናሽ አይያዝም፤ ነገር ግን ወለዱ፡-
1/ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ለተሰጠው የፋይናንስ ተቋም ወይም
2/ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ሰዎች ብድር እንዲሰጥ ለተፈቀደለት የውጭ ሀገር ባንክ የተከፈለ ወይም የሚከፈል ከሆነ በተቀናሽ ይያዛል።
ለ/ የወለዱ ገቢ ግንኙነት ባለው ሰው የሠንጠረዥ “መ “ ገቢ ውስጥ ካልተካተተ በስተቀር፣ አንድ ግብር ከፋይ በኢትዮጵያ ነዋሪ ለሆነ ግንኙነት ላለው ሰው የከፈለው ወይም የሚከፍለው ወለድ፣

ለበጎ አድራጎት ዓላማ የሚደረጉ ስጦታዎች
1. የግብር ከፋዩ ግብር የሚከፈልበት የግብር ዓመቱ ገቢ በሚወሰንበት ጊዜ ግብር ከፋዩ ያደረገው ስጦታ ተቀናሽ የሚደረገው ስጦታው ለሚከተሉት የተደረገ ሲሆን ነው፡-
ሀ/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) ለተመለከተው የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት ወይም የኢትዮጵያ ማኅበር፣ ወይም
ለ/ መንግሥት ባደረገው ጥሪ መሠረት ለልማት፣ የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስከበር፣ ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ አደጋ ወይም ወረርሽኝ ለመከላከል ወይም ለተመሳሳይ ጥሪዎች ምላሽ ለመስጠት የተደረገ ከሆነ፣ ነው።
2. ለግብር ከፋዩ የሚፈቀደው ጠቅላላ ተቀናሸ ከግብር ከፋዩ ግብር ከሚከፈልበት የግብር ዓመቱ ገቢ 10% (አሥር በመቶ) መብለጥ የለበትም።
3. ለዚህ አንቀጽ አፈጻጸም “የኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት” ወይም “የኢትዮጵያ ማኅበር” በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 የተሰጠው ትርጉም ይኖረዋል፡፡

09/03/2022

ሠንጠረዥ "ለ" ከቤት ኪራይ የሚገኝ ገቢ
በቤት ኪራይ ገቢ ላይ ግብር ስለመጣል በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 240/2008 ዓ.ም አንቀፅ 13 እሰከ 17

1. ቤት በማከራየት ገቢ የሚያገኝ ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ 14 በተመለከተው ምጣኔ ወይም ምጣኔዎች መሠረት በእያንዳንዱ የግብር ዓመት የቤት ኪራይ ገቢ ግብር ይከፍላል።

2. በግብር ዓመቱ አንድ ግብር ከፋይ ከቤት ኪራይ በሚያገኘው ገቢ ላይ የሚከፈለው ግብር በዚህ አዋጅ አንቀጽ 14 ሥር የተመለከቱትን ምጣኔዎች ግብር በሚከፈልበት ዓመታዊ ገቢ ላይ ተፈፃሚ በማድረግ ይሰላል፡፡

3. ይህ ሠንጠረዥ በዚህ አዋጅ አንቀጽ 55 መሠረት የኪራይ ገቢ ግብር ለሚከፈልበት ገቢ ተፈጻሚነት አይኖረውም።
የኪራይ ገቢ ግብር ምጣኔዎች

1. በድርጅቶች የኪራይ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚ ሆነው የግብር ምጣኔ 30 በመቶ ነው፡፡
2. በግለሰቦች የኪራይ ገቢ ላይ ተፈጻሚ የሚሆኑት ምጣኔዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
ግብር የሚከፈልበት የኪራይ ገቢ

1. የአንድ ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት የግብር ዓመቱ የኪራይ ገቢ ነው የሚባለው ግብር ከፋዩ በግብር ዓመቱ ውስጥ ቤት በማከራየት ካገኘው ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢ ላይ ለግብር ከፋዩ የተፈቀደው ጠቅላላ ወጪ ተቀናሽ ተደርጎ የሚቀረው ገቢ ነው፡፡
2. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) እና (4) እንደተጠበቁ ሆነው፣ አንድ ግብር ከፋይ በግብር ዓመቱ ቤት በማከራየት የሚያገኘው ጠቅላላ ገቢ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-

ሀ/ የኪራይ ዋጋ ጭማሪን ወይም ተመሳሳይ ክፍያዎችን ጨምሮ፣ በኪራይ ውሉ መሠረት ግብር ከፋዩ በዓመቱ የሚያገኘው ማናቸውም የገንዘብ መጠን፣
ለ/ በኪራይ ውሉ መሠረት ተከራዩ አከራዩን በመወከል በግብር ዓመቱ ለሌሎች የሚከፍላቸው ክፍያዎች፤

ሐ/ ግብር ከፋዩ ጉዳቱን ለማስተካከል ያልተጠቀመበት እና በቤቱ ላይ ለሚደርሰው ጉዳት ማስተካከያ ይሆን ዘንድ የያዘው እና በግብር ዓመቱ ለግብር ከፋዩ ገቢ የተደረገው ማንኛውም ቦንድ፣ ዋስትና ወይም ተመሳሳይ የገንዘብ መጠን፤
መ/ ለግብር ከፋዩ ከሚከፈለው ኪራይ በተጨማሪ በኪራዩ ውል መሠረት ተከራዩ ራሱ ለቤቱ እድሳት ወይም ማሻሻያ የሚያወጣው የገንዘብ መጠን፤

3. ግብር ከፋዩ ቤቱን ያከራየው ከዕቃዎች ጋር በሚሆንበት ጊዜ፣ ያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከዕቃዎቹ የተገኘውን የኪራይ ገቢም ያጠቃልላል፡፡

4. ግብር ከፋዩ ቤት በማከራየት የሚያገኘው ጠቅላላ ገቢ ከገቢ ግብር ነጻ የሆነን ገቢ አይጨምርም፡፡

5. በአንድ የግብር ዓመት የሂሳብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ የሌለበት ግብር ከፋይ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ የሚከተሉት ወጭዎች በተቀናሽ ይያዛሉ፡

ሀ/ ታክስን ሳይጨምር ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩ ለመንግሥት ወይም ለከተማ አስተዳደር በግብር ዓመቱ ውስጥ የከፈላቸው ክፍያዎች፣
ለ/ ለቤቶች፣ ለቤት ዕቃና መሣሪያ ማደሻ፣መጠገኛና ለእርጅና መተኪያ የሚሆን ከቤት፣ ከቤት ዕቃ እና ከመሳሪያ ኪራይ ከሚገኘው ጠቅላላ ገንዘብ ላይ ሃምሳ በመቶ፣

6. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 ድንጋጌ በማናቸውም ምክንያት በዚህ አዋጅ መሠረት የሂሣብ መዝገብ የመያዝ ግዴታ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ተፈፃሚ ሊሆን አይችልም፡፡
7. የሂሳብ መዝገብ የሚይዝ ግብር ከፋይ የዓመቱ ግብር የሚከፈልበት ገቢ በሚሰላበት ጊዜ ገቢውን ለማግኘት የወጣና በታክስ ከፋዩ የተከፈለ ወጪ ተቀናሽ የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም ወጪ የሚከተሉትን ይጨምራል፡-

ሀ/ ቤቱ ያረፈበት መሬት ኪራይ፣
ለ/ የጥገና ወጭ፣
ሐ/ የቤቱ፣ የቤት ዕቃዎችና የመሣሪያዎች የእርጅና ቅናሽ፣
መ/ ወለድና የመድን አረቦን፣
ሠ/ ታክስን ሳይጨምር ለመሬቱ ወይም ከተከራየው ቤት ጋር በተገናኘ ግብር ከፋዩ ለመንግሥት ወይም ለከተማ አስተዳደር የከፈላቸው ክፍያዎች፣

የተከራይ አከራዮች
1. የተከራይ አከራይ በግብር ዓመቱ ያገኘው ግብር የሚከፈልበት ገቢ ነው የሚባለው የተከራይ አከራዩ በግብር ዓመቱ ከተቀበለው ጠቅላላ የኪራይ ገቢ ላይ ለዋናው አከራይ የሚከፍለው ኪራይ እንዲሁም ገቢውን ለማግኘት ያወጣቸው ሌሎች አስፈላጊ ወጪዎች ከተቀነሰ በኋላ የሚቀረው የገንዘብ መጠን ነው።

2. ተከራይ የተከራየውን ቤት መልሶ እንዲያከራይ የሚፈቅድ የቤት ባለቤት ተከራዩ ግብሩን ሳይከፍል ቢቀር ስለእርሱ ሆኖ ግብሩን የመክፈል ኃላፊነት ይኖርበታል።
የሚከራይ አዲስ ቤትን ስለማሳወቅ

1. ለኪራይ የሚሰራ ቤት ተሰርቶ እንዳለቀ ወይም ቤቱ እንደተከራየ፣ ከሁለቱ በሚቀድመው ጊዜ የቤቱ ባለቤትና የቤቱ ሥራ ተቋራጭ የቤቱ ግንባታ የተጠናቀቀ ወይም የተከራየ መሆኑን ከቤቱ ኪራይ በሚገኘው ገቢ ላይ የሚፈለገውን ግብር መክፈል ያለበትን ሰው ስም፣ አድራሻና የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር፣ ቤቱ ለሚገኝበት የቀበሌ አስተዳደር ወይም የአካባቢ አስተዳደር ማስታወቅ አለባቸው፡፡

2. የቀበሌው አስተዳደር እና የአካባቢው አስተዳደር በማስታወቂያው መሠረት የተገኘውን መረጃ ለባለሥልጣኑ መግለጽ አለባቸው።

09/03/2022
12/02/2022

የቀን ገቢ ግምት ለማጥናት ………. // ……. ከግብር ከፋይ የሚጠበቅ ግዴታ

 ለመረጃ ሰብሳቢ ባለሙያዎች ትክክለኛ የንግድ እንቅስቃሴያቸውን የሚገልጽ መረጃ መስጠት፣
 የቀን ገቢ ግምት አማካይ የግብይት መጠን ከፍተኛ መካካለኛ እና ዝቅተኛ ሲጠየቁ መሥጠት፣
 ድርጅቱ አንድ ቦታ ብቻ መሆኑንና አለመሆኑን ማሳወቅ ወይም መጋዘኑ የሚገኝበትን ቦታ ማሳወቅ፣
 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር መስጠት /ማሳየት/፣
 የንግድ አይነት አድራሻ የባለቤትነት ማረጋገጫ ማቅረብ ወይም የንግድ ፍቃድ፣
 ስራ የጀመሩበትን ጊዜ ማሳወቅ፣
 ግብር ከፋዩ የሚሠጣቸውን መረጃዎች አውቆና ተገንዝቦ የመሥጠት እና
 ለሚሠጠው መረጃ ትክክለኛነት ማረጋገጫ ሲያስፈልግ ያረጋግጣል።

06/10/2021

ስለ ሒሳብ መዝገብ ምንነት እና ጠቀሜታ ዙሪያ የተዘጋጀ

Address

Kelela

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kelala wereda revenue office -ከላላ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share