Kombolcha City Administration Department Of Revenue

Kombolcha City Administration Department Of Revenue This pages Kombolcha City Administration Department Of Revenue official page

20/08/2026
ደረሰኝ በመስጠት እና በመቀበል ህጋዊነታችንን እናረጋግጥ!!
18/08/2026

ደረሰኝ በመስጠት እና በመቀበል ህጋዊነታችንን እናረጋግጥ!!

18/08/2026

ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

18/08/2026

ነሐሴ 08/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ለክቡራን የክልላችን ግብር ከፋዮችአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት እንዲሰበሰብ በክልላችን ም/ቤት ከፀደቀለት የገቢ ዕቅድ ውስጥ ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስቦ የ:ቅዱን ...
13/08/2026

ለክቡራን የክልላችን ግብር ከፋዮች
አማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት እንዲሰበሰብ በክልላችን ም/ቤት ከፀደቀለት የገቢ ዕቅድ ውስጥ ከ93 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰብስቦ የ:ቅዱን 92.66% በማሣካት የክልሉ ተማቋት ያቀዱትን እቅድ እንዲያሣካ የፋይናንስ ምንጭ በመሆን ስኬታማ ውጤት አስመዝግቧል።
በገጠር እና በከተሞቻችን እየተከናወነ የሚገኙት የኮሪደር ልማቶች፣ አዳዲስ የትምህርት ተቋማት ግንባታዎች፣ ዘመናዊ የጤና ጣቢያዎች፣ እንዲሁም የመንገድና የድልድይ ግንባታዎች እርሰዎ የከፈሉት ታክስ ለልማት መዋሉን የሚያሣይ ህያው ምስክሮች ናቸው።
ለዚህ የጋራ ዋና መሠረቱ ለክልላችን እድገት በመቆም ግብር የመክፈል ኃላፊነት በታማኝነት የተወጣችሁት እና እናንተው ታማኝ ግብር ከፋዮቻችንና የክልላችን የልማት አጋሮች ሁሉን አቀፍ ጥረት ነው።
በአሁኑ ወቅት በ2019 በጀት ዓመት ከክልላችንን የሚመጥን እና የህዝባችንን የመልማት ፍላጐት የሚያረካ የ166 ቢሊየን ብር የገቢ ግብ ሰንቀን እየሰራን እንገኛለን።
ይህ ግብ እውን የሚሆነው በጋራ ጥረታችንና በመተማመን ላይ የተመሠረተ የግብር አከፋፈል ስርዓት ሲረጋገጥ ነው።
በአንዳንድ አካባቢዎች በግብር አሰባሰብ ሂደት ላይ የሚስተዋሉ የግብር ጭማሪ ቅሬታዎች ሊኖሩ ይችላሉ።
በግብር ውሣኔ፣ ስርጭትና አሰባሰብ ላይ የሚታዩ ችግሮች በውይይትና በምክክር እንዲሁም በተዘረጋው የቅሬታ ይግባኝ ስርዓት በየደረጃው ባለው አደረጃጀት እየፈታን መጥተናል፡፡ በቀጣይም በዚሁ ስርዓት የሚፈታ ይሆናል።
ስለሆነም ግብር ለሀገር ግንባታ እርስዎ የሚከፍሉት ታክስ የራስዎ፣ ቤተሰብ እና የህዝብዎ የነገ ተስፋ ነው።
ዛሬ የምንገነባው ትምህርት፣ የግብርና ልማት፣ የምናደራጀው የጤና፣ የመንገድ እና ድልድይ ግንባታ የምንዘረጋው የኮሪደር ልማት ለቀጣይ ትውልድ የምናወርሰው ቅርስ ነው።
ስለዚህ ዛሬ ላይ ሆነን ነገን የምንገነባው በሚከፈለው ግብር ነውና ለስኬታማነቱ አሻራችንን እናሣርፋለን።
የጋራ መድረክ በአወሣሰኑ፣ በአሰባሰቡና ወደ ልማት አዋዋሉ ላይ በተለያዩ አደረጃጀቶች በሚፈጠሩ መድረኮች በጋራ እየተነጋገርን ምክክር እያደረግን ችግሮቻችን በዘላቂነት እንፍታ።
የሚሰበሰበው ገቢ በደጅዎ አካባቢ፣ የሚፈቱ ልማትን የሚያወጣ ወሣኝ የልማት ፋይናንስ ነውና ሁላችንም ልማት እንዲመጣ እንዲሁም እንደምንጠይቀሁ ሁሉ ለገቢ አሰባሰቡ የዜግነት ድርሻችንን እንወጣ።
ለጋራ መድረክ የክልላችን ልማት በሁሉም አቅጣጫ እንዲሰፋና በየደረጃው ያለው የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ እንዲሆን የክልላችን ኢኮኖሚ ያመነጨውን ገቢ በአግባቡ መሰብሰብ ይገባል።
እንደ ክልል በራስ የገቢ ምንጭ ወጫችንን ለመሸፈን ግባችንን ለማሣካት ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።
ዘላቂነት ያለው የሀገር ግንባታና ብልጽግና የሚረጋገጠው ከጥፋተኝነት የተላቀቀ ገቢ ማመንጨት ሲቻል ነው፡፡ እያንዳንዱ ተጠቃሚ የሚሆንበት ልማት የሚመጣው በራሱ በሚመነጭና በራስ በሚሰበሰብ ገቢ ነው።
ለዚህም ሁሉም የዜግነት ድርሻውንና ግዴተውን ሊወጣ ይገባል።
መንገሻ ፈንታሁን (ዶ/ር) . . . የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ

13/08/2026

"እኛ የምንሰበስበው ገቢ የመላው ክልላችን ተቋማት ወደ ፊት የመራመጃ አቅም እና የእድገታችን ህያው የልብ ምት ነው።" መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)

👨‍💻:- ሲሳይ አስማማው

አስተያየት እና ጥያቄ ቢኖርዎ ከዚህ ገፅ በተጨማሪ እነዚህን አድራሻዎች ይጠቀሙ

በፌስቡክ ገፅ
https://www.facebook.com/AmraNews
https://www.facebook.com/profile.

በቴሌግራም:- Amhara Region revenue bureau

በዩትዩብ:- https://www.youtube.com/ ገቢያችን
Website:- https://www.abor.gov.et/

እንዲሁም አስተያየትና ጥቆማ በ 9504 ይደውሉ
መደበኛ ስልክ ቁጥሮች 058 220 57 49/ 09 47

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በ2019 በጀት አመት ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ፡፡መምሪያው የ2018 በጀት አመት  አፈጻጸም  ግምገማ እና የ2019 በ...
12/08/2026

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ በ2019 በጀት አመት ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ማቀዱን ገለጸ፡፡

መምሪያው የ2018 በጀት አመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2019 በጀት አመት እቅድ ትውውቅ ከጠቅላላ ሰራተኞች ጋር አድርጓል፡።
በ2018 በጀት አመት የተከናወኑ ቁልፍ እና አበይት ተግባራት የነበረውን አአፈጻጸም በጥንካሬና በድክመት ተለይተው ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የመምሪያው ሃላፊ አቶ ሙሀመድ ሰይድ በ2019 በጀት አመት ከመደበኛ ገቢ 3, 174, 666, 069 ብር ከከተማ አገልግሎት ገቢ 1, 944, 499, 811 ብር በ አጠቃላይ ከመደበኛ እና አገልግሎት ገቢ 5, 119, 165, 880 ብር ገቢ ለመሰብሰብ መታቀዱን ተናግረዋል፡፡

ሃላፊው አክለውም የ2019 በጀት አመት እቅድ በውጤታማነት ለማሳካት ሁሉም የገቢ ተቋም አመራርና ሰራተኞች በእውቀትና ክህሎት ላይ በመመስረት ስራዎችን በባለቤትነት ስሜት በብቃት መፈጸም እና መልካም ስነ-ምግባርን ተላብሶ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የመምሪያው ምክትል ሃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም አሊ በበኩላቸው የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር የገቢ አማራጮችን በማስፋት እና የኛን ጥረት የሚጠይቁ ገቢዎችን ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
ነሀሴ 6/2018 ዓ.ም
የግብር ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ዋና የስራ ሂደት
የኮምቦልቻ ከተማ አሰተዳደር ገቢዎች መምሪያ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ላይክ እና ሸር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
በፌስቡክ
https://www.facebook.com/kombolcha.revenue1
በቴሌግራም
https://t.me/komblcharevenue

08/08/2026

የጥንቃቄ መልዕክት
የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙሀመድ ሰይድ ስምና ፎቶ በመጠቀም ፌክ የቴሌግራም አካውንት በመክፈት የተለያዩ የህብረተሰብ /የንግዱን ማህበረሰብ/ ለማጭበርበር እየሞከሩ ነው ፡፡ ስለሆነም በአቶ ሙሀመድ ሰይድ አማካኝነት የሚጠቀምበት የቴሌግራም አካውንት የሌለ መሆኑን እና የሚላከው መልዕክት የሳቸው አለመሆኑን በመረዳት ጥንቃቄ እንድታደርጉ ስንል መልእክታችን እናስተላልፋለን፡፡

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ከፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር ኮምቦልቻ ቅርጫፍ ጋር ቅንጅታዊ ስራዎችን በሚጠይቁ ተግባሮች ላይ በጋራ ለመስራት ውይይት አደርጓል ።በውይይቱ ከመምሪያና...
06/08/2026

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ ከፌዴራል ገቢዎች ሚኒስቴር ኮምቦልቻ ቅርጫፍ ጋር ቅንጅታዊ ስራዎችን በሚጠይቁ ተግባሮች ላይ በጋራ ለመስራት ውይይት አደርጓል ።

በውይይቱ ከመምሪያና ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ የተውጣጡ አመራሮች እና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን በ2018 በጀት አመት የነበረውን ቅንጅታዊ አሰራር በጥንካሬና በድክመት በመገምገም በ2019 በጀት አመት የገቢ አሰባሰብ ስርአቱ የተሻለ እንዲሆን የጋራና ቅንጅታዊ ስራዎችን የሚጠይቁ ተግባሮችን በመለየት በጋራ ለመስራት ለሚመለከታቸው አካላት የእቅድ ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።

ሀምሌ 30/2018 ዓ.ም
የግብር ትምህርትና ኮሙኒኬሽን ዋና የስራ ሂደት
የኮምቦልቻ ከተማ አሰተዳደር ገቢዎች መምሪያ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ላይክ እና ሸር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
በፌስቡክ https://www.facebook.com/kombolcha.revenue1
በቴሌግራም https://t.me/komblcharevenue

Address

Administration Building
Kembolcha

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00

Telephone

+251930026582

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kombolcha City Administration Department Of Revenue posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share