Kombolcha Customs Branch -ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ ቤት

Kombolcha Customs Branch -ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ ቤት በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

 #የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ዋና ዋና ስልጣንና ተግባራት
05/08/2026

#የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ዋና ዋና ስልጣንና ተግባራት

03/08/2026
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ሀገራዊ መርሃ ግብር ላይ በነቃ ተሳትፎ አሻራቸውን አኖሩ፡፡(ሐምሌ 27 ቀን 2018፤ ኮምቦልቻ ጉምሩክ)የኢትዮጵያ ...
03/08/2026

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሠራተኞች በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል ሀገራዊ መርሃ ግብር ላይ በነቃ ተሳትፎ አሻራቸውን አኖሩ፡፡

(ሐምሌ 27 ቀን 2018፤ ኮምቦልቻ ጉምሩክ)

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በዛሬው ዕለት “ተስፋን እንትከል!” በሚል መሪ መልዕክት በተካሄደው የሀገራዊ የአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞች የመትከል መርሃ ግብር ላይ በነቃ ተሳትፎ አሻራቸውን አኖረዋል።

የተከላ መርሃ ግብሩ በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ቦርከና ክፍለ ከተማ፣ መጠኔ ቀበሌ በሚገኘው የመንጠራ ተፋሰስ የተካሄደ ሲሆን፤ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ አመራሮችና ሠራተኞች ከኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች ጋር በመሆን በጋራ ችግኞችን ተክለዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰማን ዳውድ ባስተላለፉት መልዕክት፤ “እኛ የኢትዮጵያ ተምሳሌት እንደመሆናችን መጠን በአንድነት መንፈስና በጋራ ሀገራችንን በማልማት፣ የተጣለብንን ታሪካዊ ኃላፊነት መወጣት ይኖርብናል” ብለዋል።

ይኸው የጋራና የልህቀት መንፈስ በ2019 በጀት ዓመት የተሰጣቸውን ተቋማዊና ሀገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ ለመወጣት ትልቅ መነቃቃት እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

በተጨማሪም የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ አመራርና ሠራተኞች ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በየዓመቱ ችግኝ ሲተክሉበት በቆዩበት የኮምቦልቻ ኢኮኖሚ ዞን ቅጥር ግቢ በመገኘት የተተከሉ ችግኞችን የልማት እድገት ተዟዙረው ጎብኝተዋል፤ በዕለቱም በኢኮኖሚ ዞኑ ቅጥር ግቢ ተጨማሪ ችግኞችን ተክለዋል።

የኮምቦልቻ ኢኮኖሚ ዞን ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ ሰይድ በበኩላቸው፤ የኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ለአካባቢው አረንጓዴ ልማት ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

አያይዘውም በቅጥር ግቢው ውስጥ አድገው ለውበትና ለጥ ጥላ የበቁትን ችግኞች በማሳያነት በማስጎብኘት፣ “ተተክለው አያድጉም” የሚለውን የተሳሳተ ማህበረሰባዊ አመለካከት በተግባር ማፍረስ መቻሉን ገልጸዋል።

ተቋምን በልህቀት፤ ገቢን በስኬት!
በደንበኞች ትምህርት ቡድን

ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ላስመዘገበው የላቀ ተቋማዊ አፈፃፀም እውቅና ተበረከተለት።(ሐምሌ 24 ቀን 2018፤ ኮምቦልቻ ጉምሩክ)የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በላቀ የደንበ...
31/07/2026

ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ላስመዘገበው የላቀ ተቋማዊ አፈፃፀም እውቅና ተበረከተለት።

(ሐምሌ 24 ቀን 2018፤ ኮምቦልቻ ጉምሩክ)

የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በላቀ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በፈጠረው አስደናቂ መነቃቃትና ውጤታማነት ተመራጭነቱ እጅግ በማደጉ፤ በ2018 በጀት ዓመት ላስመዘገበው የላቀ ተቋማዊ አፈፃፀም እውቅና ተሰጥቶታል።

ይህ እውቅና የተሰጠው በቢሾፍቱ ከተማ በተካሄደው የገቢዎች ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ በክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ እና በክቡር ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ (ዶ/ር) እጅ ነው።

የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስኬታማነት የመጣው አመራሩና ሠራተኛው ለላቀ የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት በሰጡት ልዩ ትኩረት ነው።

በዚህም የተነሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጊዜው እጅግ ተመራጭ እየሆነ በመምጣቱ፤ ታማኝ የሆኑ የክቡራን ደንበኞቻችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ሊጨምር ችሏል።

ለዚህ ታላቅ ዕውቅና መሠረት ለሆኑት ክቡራን ደንበኞቻችን፣ አመራርና ሠራተኞች፣ እንዲሁም አጋር አካላት "እንኳን ደስ ያላችሁ!" እንላለን።

አሁንም ይህንን የላቀ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎታችንን መሰረት በማድረግ ነባር ደንበኞቻችን ከእኛ ጋር ያላቸውን አጋርነት አጠናክረው እንዲቀጥሉ፤ አዳዲስ ደንበኞችም ወደዚሁ ተመራጭ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤታችን በመምጣት የላቀ አገልግሎታችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት እንጋብዛለን።

ፎቶ፦ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት

ተቋምን በልህቀት፤ ገቢን በስኬት!

በደንበኞች ትምህርት ቡድን

 #የጨረታ ማስታወቂያ
31/07/2026

#የጨረታ ማስታወቂያ

ከ704 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ   # # #  # # #  # # #  # # #  # # #  # # #  # # #  # # #  # # # ...
31/07/2026

ከ704 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
# # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # # #
(ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ሀምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም )

የጉምሩክ ኮሚሽን ከሀምሌ 16 እስከ ሀምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 661.1 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 43.3 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 704.4 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አዳዲስ እና ልባሽ ጨርቆች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ እቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የቁም እንስሳት ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ ማዕድናት እና የውጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር አዋሽ፣ አዲስ አበባ ኤርፖርት እና ጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 261 ሚሊዮን፣ 111 ሚሊዮን እና 90 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በጥቆማ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 34 ተጠርጣሪዎች እና 14 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን በዚህ የህግ ማስከበር ስራ ላይ ለተሳተፉ የኮሚሽኑ ሰራተኞች እና አመራሮች፣ የክልልና የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ለመላው ህዝባችን ምስጋናውን ያደርሳል፡፡

የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ጉምሩክ ኮሚሽን ብቻ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ ባለመሆኑ ሁሉም ባላድርሻ አካላትና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽንን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ecczena
በድረ ገጽ፦ www.ecc.gov.et
በቴሌግራም፦ https://t.me/EthiopianCustomsCommission

 #የጉምሩክ አስተላላፊ ጥፋቶችና አስተዳደራዊ ቅጣት
31/07/2026

#የጉምሩክ አስተላላፊ ጥፋቶችና አስተዳደራዊ ቅጣት

 #ስነ ስርዓት የያዘ አስተሳሰብ እና ተግባር #ከስነ ምግባር መከታተያ ቡድን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ
30/07/2026

#ስነ ስርዓት የያዘ አስተሳሰብ እና ተግባር
#ከስነ ምግባር መከታተያ ቡድን ጋር በመተባበር የተዘጋጀ

Address

Ethiopia Kombolcha City
Kembolcha
251

Telephone

+251335512352

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kombolcha Customs Branch -ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Kombolcha Customs Branch -ኮምቦልቻ ጉምሩክ ቅ/ጽ ቤት:

Shortcuts

Share