Oromo Special Zone High Court

Oromo Special Zone High Court It is An Official Page Where We Communicate the Work of the Court to The Public.

30/08/2026
30/08/2026
የኦሮሞ ብሔ/ብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የአንድ ዓመት የስራ አፈጻጸም።በከፍተኛ ፍ/ቤት በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የመዝገብ አፈጻጸም ሁኔታዎች ፡-በከፍተኛ ፍ/ቤት በወንጀል ...
28/08/2026

የኦሮሞ ብሔ/ብ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የአንድ ዓመት የስራ አፈጻጸም።

በከፍተኛ ፍ/ቤት በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ
የመዝገብ አፈጻጸም ሁኔታዎች ፡-

በከፍተኛ ፍ/ቤት በወንጀል ጉዳይ:-
• ከባለፈው የተላለፈ መዝገብ 146
• አዲስ የቀረበ 448
• ከመዝገብ ቤት የተንቀሳቀሰ 14
• ድምር አቅርቦት 608
• ክንዉን 452

በወረዳ ፍ/ቤቶች በወንጀል ጉዳይ፡-
• ከባለፈው የተላለፈ መዝገብ 151
• አዲስ የቀረበ 2,438
• ከመዝገብ ቤት የተንቀሳቀሰ 11
• ድምር አቅርቦት 2,600
• ክንዉን 2,476

በከፍተኛ ፍ/ቤት በፍታብሔር ጉዳይ፡-
• ከባለፈው የተላለፈ መዝገብ 131
• አዲስ የቀረበ 356
• ከመዝገብ ቤት የተንቀሳቀሰ 49
• ድምር አቅርቦት 536
• ክንዉን 425

በወረዳ ፍ/ቤቶች በፍታብሔር ጉዳይ፡-
• ከባለፈው የተላለፈ መዝገብ 677
• አዲስ የቀረበ 5,142
• ከመዝገብ ቤት የተንቀሳቀሰ 210
• ድምር አቅርቦት 6,029
• ክንዉን 5546

በከፍተኛ ፍረድ ቤት በወንጀልና ፍታብሔር ጉዳይ፡-
• ድምር አቅርቦት 1,144
• ክንዉን 877
• ክንዉን ከአቅርቦት 76.6%
• በቀጠሮ የተላለፈ 267

በወረዳ ፍ/ቤቶች በወንጀልና ፍታብሔር ጉዳይ፡-
• ድምር አቅርቦት 8,629
• ክንዉን 8,022
• ክንዉን ከአቅርቦት 92.97%
• በቀጠሮ የተላለፈ 607

ቅድሚያ ተሰጥቷቸዉ የተስተናገዱ ባለጉዳዮች
በከፍተኛ ፍርድ ቤት፡-
• አካል ጉዳተኛ፡ - ወንድ-20፤ሴት-10 ድምር-30
• አረጋዊን፡- ወንድ-671፤ሴት-249 ድምር-965
• ሴቶችና ህጻናት ፡- 304

በወረዳ ፍ/ቤቶች ፡-
• አካል ጉዳተኛ ፡-ወንድ-64፤ሴት-44 ድምር-105
• አረጋዊን ፡- ወንድ-514 ፤ ሴት 562 ድምር 1076
• ሴቶችና ህጻናት ፡- 1,701

ከዳኝነት የተሰበሰበ ገንዘብ
በከፍተኛ ፍርድ ቤት:-
• ከመቀጫ 103,800
• ከዳኝነት 1,594,250.68
• በድሀነት በነጻየታዩ 85,000

በወረዳ ፍ/ቤቶች ፡-
• ከመቀጫ 654,100
• ከዳኝነት 4,046,276.95
• በድሀነት በነጻ የታዩ 623,500

የትኩረት አቅጣጫዎች:-

1. የዉሳኔ ጥራትን ማምጣት።
2. በእድሜ ቆይታ ያላቸዉን መዝገቦች በአጭር ጊዜ ዉስጥ ዉሳኔ እንዲያገኙ መስራት።
3. የባህላዊ ፍርድ ቤትን በማቋቋም ፍርድ ቤት መር የእርቅና ድርድር ስርአርን በመዘርጋት በስምምነት ወይም በእርቅ መዝገቦችን ከፍ ለማድረግ በቀጣይ በየደረጃዉ የሚገኙ ፍርድ ቤቶች አንድ ዳኛ እራሱን ችሎ በእርቅ የሚታዩ ጉዳዮችን ብቻ እንዲመራ በማድረግ የህብረተሰቡን ችግሮች የመፍታት ባህል ያለዉ በመሆኑ በቀጣይ ይህ ተግባር ተጠናክሮ የሚቀጠረል ይሆናል።
4. የህዝብ የምክክር መድረክ ማካሄድ ከህዝብ የሚነሱ አስተያየቶችን እንደ ግብዓት በመጠቀም የማስተካከያ እርምጃ መዉሰድ።
5. የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ ተገልጋዩ ህብረተሰብ በአገልግሎት አሰጣጡ ምንያህል ረክቷል የሚለዉን መረጃ መሰብሰብ ናቸዉ።

24/08/2026
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የድጋፍና ክትትል ልኡካን ቡድን በኦሮሞ ብሄ/ብ ዞን  የፍርድ ቤቶች የስራ ጉብኝ አደረጉ።ከሚሴ:ነሐሴ 16/2018 ዓ/ም (የኦሮሞ ብሄ/ብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ...
22/08/2026

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የድጋፍና ክትትል ልኡካን ቡድን በኦሮሞ ብሄ/ብ ዞን የፍርድ ቤቶች የስራ ጉብኝ አደረጉ።

ከሚሴ:ነሐሴ 16/2018 ዓ/ም (የኦሮሞ ብሄ/ብ
ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት)

የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የድጋፍና ክትትል ልኡካን ቡድን በኦሮሞ ብሄ/ብ ዞን በከፍተኛ ፍርድ ቤት፣በደዋ ጨፋ ወረዳ ፍርድ ቤት እና በባቲ ወረዳ ፍርድ የፍርድ ቤቶች የስራ ጉብኝ አድርገዋል።

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የክሉን ፍርድ ቤቶች አሰራር ለማሻሻልና ለማዘመን በርካታ ስራዎችን እያከናወነ መቆየቱ እሙን ነዉ።ከነዚህም ዉዝጥ በዲጂታላይዜሺን:በሰው ሀይል አቅም ግንባታ: ለዳኝነት ነጻነት መረጋገጥ :ምቹ የስራ ከባቢ ከመፍጠር :የባህል ፍርድ ቤቶችን ማቋቋም ፣ ዘመናዊ የዳኝነት አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ለአብ ይጠቀሳሉ።

የአብመ ጠቅላይ ፍ/ቤት አማካሪ አቶ ቢኒያም ዩሀንስ እንደተናገሩት"ይህም የፍርድ ቤቶች የስራ ጉብኝት የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ ቤቶች ያለባቸዉን ክፍተቶች በመለየት ክፍተቶቻቸዉን ለመሙላትና ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ነዉ።"ብለዋል።

የልኡካን ቡድኑበየቀበሌዎች የተቋቋሙትን የባህል ፍርድ ቤት ማዕከላትን ተዘዋዉረዉ በመጎብኘት የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር ዉይይት አድርገዋል።በመቀጠል በፍርድ ቤቶች በመገኘት በፍርድ ጉ ቤቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በመጨረሻም ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶ እናከማናጅመንት አባላቶች ረዘም ያለ ዉይት እርገዋል።

የኦሮሞ ብሄ/ብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳት ክቡር አቶ አሊ ሙመድ ".ይህ ዉይይት የአሰራር ክተቶቻሽን በደንብ እንድንፈትሽና ለቀጣይ እንዳንደግማቸዉ እና በትኩረት እንድንሰራ አቅም የሚሰጠን ነዉ"በማለት የልኡካን ቡድቡ ያደረገዉን የስራ ጉብኝት አመስግነዋል።

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድጋፍና ክትትል ልኡካን ቡድን በኦሮሞ ብሄ/ብ ዞን በደዋ ጨፋ ፍርድ ቤትየስራ ጉብኝን አደረጉ።ከሚሴ:ነሐሴ 16/2018 ዓ/ም (የኦሮሞ ብሄ/ብ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ...
22/08/2026

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድጋፍና ክትትል ልኡካን ቡድን በኦሮሞ ብሄ/ብ ዞን በደዋ ጨፋ ፍርድ ቤት
የስራ ጉብኝን አደረጉ።

ከሚሴ:ነሐሴ 16/2018 ዓ/ም (የኦሮሞ ብሄ/ብ
ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት)

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ድጋፍና ክትትል ልኡካን ቡድን በኦሮሞ ብሄ/ብ ዞን በከሚሴ ከተማ በሚገኘዉ በደዋ ጨፋ ፍርድ ቤት የስራ ጉብኝን አደረጉ።

የልኡካን ቡድኑ በከሚሴ ከተማ በየቀበሌዎች የተቋቋሙትን የባህል ፍርድ ቤት ማዕከላትን በመጎብኘት የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር ዉይይት አድርገዋል።

የልኡካን ቡድኑ በመቀጠል በደዋ ጨፋ ፍርድ ፍርድ ቤት በመገኘት በፍርድ ቤቱ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተዘጋጀዉ የፍርድ ቤት ስራዎች መመዘኛ ቼክሊስት መሰረት ከፍርድ ቤቱ የማናጅመንት አባላት የገመገመ ሲሆን ይህም የስራ ጉብኝትም የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍርድ ቤቶች ያለባቸዉን ክፍተቶች በመለየት ክፍተቶቻቸዉን ለመሙላትና ድጋፍ ለማድረግ ያለመ ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል።

Address

Kemise

Opening Hours

Monday 09:00 - 17:00
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00

Telephone

+251335540249

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Oromo Special Zone High Court posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share