Oromo Zone Labour and Training.

Oromo Zone Labour and Training. ለኢንዱስትሪ ልማት አሰተማማኝና ሰፊ መሰረት ያለው በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለኢንዱስትሪው ማብቃትና ማፍራት ነው።

በከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ «በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ» በሚል መሪ ቃል ለአቅመ-ደካሞች የማዕድ ማጋራት ድጋፍ ተደረገ​ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም (ከሚሴ)​የአካባቢውን ማህበረሰብ ሁለገብ ተጠቃሚነ...
31/07/2026

በከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ «በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ» በሚል መሪ ቃል ለአቅመ-ደካሞች የማዕድ ማጋራት ድጋፍ ተደረገ

​ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም (ከሚሴ)

​የአካባቢውን ማህበረሰብ ሁለገብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ በጎ አድራጎታዊ እንቅስቃሴዎች አካል የሆነው እና የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን መርሃ-ግብር መነሻ ያደረገው የማዕድ ማጋራት መድረክ በከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አዘጋጅነት በ04 ቀበሌ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ተካሄደ።

​በእለቱ ከተከናወኑት አበይት ተግባራት መካከል ለተመረጡ 20 አቅመ-ደካሞችና ድጋፍ ለሚሹ የቤተሰብ አባላት የምግብ ቁሳቁስና የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል። በዚህም መሰረት ለተጠቃሚዎቹ በነፍስ-ወከፍ ዘይት፣ ዱቄት፣ 10 ደርዘን ደብተር እና ሁለት ፓኬት እስክርቢቶ ድጋፍ ተደርጓል።

​በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኮሌጁ ምክትል ዲን እና የትምህርት ስልጠና ኃላፊ አቶ አሸናፊ አበራ እንደገለጹት፤ አነስተኛ ገቢ ያላቸውንና የዕለት ከዕለት ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን ማደገፍ ተቋማዊና ማህበራዊ ኃላፊነት በመሆኑ የተጀመሩ አዎንታዊ ጥረቶች ይበልጥ ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል። አክለውም የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የማህበራዊ ትስስርንና የመረዳዳት እሴትን ለማጠናከር የሚጫወተው ሚና የጎላ መሆኑን ጠቁመው፣ «የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ የህሊና እርካታን ከማስገኘቱም በላይ ከህብረተሰባችን ታሪካዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጋር በጥብቅ የተሳሰረ አኩሪ ተግባር ነው» ብለዋል።

​ኮሌጁ በተለያዩ የክረምትና የበጋ ወራት የሚያከናውናቸውን ማህበራዊ አገልግሎቶች አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያመለከቱት ኃላፊው፣ የዛሬው ድጋፍም የዚሁ ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን አብራርተዋል።

​የድጋፉ ተጠቃሚዎች በሰጡት አስተያየት የተደረገላቸው ድጋፍ ከጠበቁት በላይና በወቅቱ የደረሰላቸው መሆኑን በመግለጽ ለኮሌጁ አባላት የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አክለውም የተደረገላቸው አዎንታዊ ምላሽ ወደፊት እነሱም ቢሆኑ ባላቸው አቅም ልክ ለሌሎች ድጋፍ የሚሹ ወገኖች እጃቸውን እንዲዘረጉ ትልቅ የህይወት ትምህርትና መነሳሳትን እንደፈጠረላቸው አብራርተዋል።

25/07/2026
በዛሬው የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ  የምረቃ ፕሮግራም ኮሌጁ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተመራቂዎችን ሲሸልም ተመራቂዎችም ታታሪ አሰልጣኛቸውን ሸልመዋል።በዛሬው ዕለት በተካሄደው ደማቅ የምረቃ ስነ...
25/07/2026

በዛሬው የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የምረቃ ፕሮግራም ኮሌጁ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተመራቂዎችን ሲሸልም ተመራቂዎችም ታታሪ አሰልጣኛቸውን ሸልመዋል።

በዛሬው ዕለት በተካሄደው ደማቅ የምረቃ ስነ-ስርዓት፣ የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ የነገ ሀገር ተረካቢ ተመራቂዎች የመልካም ስራቸው አክሊል የሆነውን የላቀ እውቅና እና ሽልማት አበርክቶላቸዋል። 🏆✨

​ይህ በደስታና በስሜት የተሞላው በዓል በዚሁ አላበቃም፤ ተመራቂ ተማሪዎችም ሌሊት ከቀን ሳይታክቱ፣ እውቀታቸውንና ልባቸውን ሰጥተው ለዚህ ማዕረግ ያበቋቸውን ታታሪና ባለሙያ አሰልጣኛቸውን በክብርና በፍቅር ሽልማት አበርክተውላቸዋል።

​"ጥራት ያለው እውቀትና ክህሎት ለወደፊቱ ስኬታችን መሰረት ነው!"

25/07/2026

Big shout out to my newest top fans! Seid Endris Seid, Alex Yazea, Abdu Oumer, Seid Ahmed Aea

የከሚሴ ከተማ አስተዳደርና የኮሌጁ ቦርድ አመራሮች የተቀናጀ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ​የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ከኮሌጁ ቦርድ አመራሮች ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀውን ...
25/07/2026

የከሚሴ ከተማ አስተዳደርና የኮሌጁ ቦርድ አመራሮች የተቀናጀ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

​የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች ከኮሌጁ ቦርድ አመራሮች ጋር በመቀናጀት የተዘጋጀውን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በስኬት አከናውነዋል።

​ይህ መርሃ ግብር በአካባቢው አረንጓዴ ልማትን ለማስፋፋት፣ የስነ-ምህዳር ሚዛንን ለመጠበቅ እና የትምህርት ተቋማቱን ቅጽር ግቢ ለትምህርትና ምርምር ምቹ ለማድረግ የተከናወነ ሁነቶች አካል ነው።

​የመርሃ ግብሩ ዋና ዋና ዓላማዎችና ትኩረቶች፡

​ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ፡ በአካባቢው ላይ የሚታየውን የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ለመቀነስ እና የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል የሚያስችል እቅድ።

​የተቋማት አጋርነት፡ በከተማ አስተዳደሩ እና በትምህርት ተቋማት መካከል ያለውን ሁለገብ ትብብርና ህዝባዊ አጋርነት ማጠናከር።

​አረንጓዴ ግቢ፡ ለተማሪዎችና ለሰራተኞች ሳቢ፣ ጸጥተኛ እና ለአእምሮ እረፍት ምቹ የሆነ አረንጓዴ አካባቢን መፍጠር።

​በዕለቱ የተተከሉት ችግኞች በቀጣይነት አስፈላጊው እንክብካቤና ጥበቃ እንደሚደረግላቸው የአመራር አካላቱ ገልጸዋል።

አቶ ተስፋዬ ታደሰ፡ የክህሎት ልማትና የተግባር ትስስር አቀጣጣይ ዲናሞ​በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት የትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ታደሰ፤ በከተ...
25/07/2026

አቶ ተስፋዬ ታደሰ፡ የክህሎት ልማትና የተግባር ትስስር አቀጣጣይ ዲናሞ

​በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የስራና ክህሎት ጽህፈት ቤት የትምህርትና ስልጠና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ታደሰ፤ በከተማው ወጣቶችና አምራች ኃይሎች ዘንድ ተግባራዊ የክህሎት ሽግግር እንዲፋጠን የማይተካ ሚና በመጫወት ላይ የሚገኙ ቁርጠኛ መሪ ናቸው።

​አቶ ተስፋዬ የከተማ አስተዳደሩን አጠቃላይ የስራ እድል ፈጠራ ጥረት ከከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች ጋር በብቃት በማስተሰረር እንደ ጠንካራ የመገናኛ ድልድይ ሆነው ያገለግላሉ። የወጣቶችን ህይወት በክህሎት ለመቀየር ባላቸው ያልተጠበቀ ትጋት፣ ቀጣይነት ያለው የስልጠና እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ያደረጉ እውነተኛ የስራ አቀጣጣይ «ዲናሞ» ናቸው።

በርታ ተስፊሽሽሽሽሽሽ----------

         (2000-2018)የከሚሴ ቴክኒክና ሙያ (ፖሊ ቴክኒክ) ኮሌጅ ከ2000 እስከ 2018 ዓ.ም ባሉት ዓመታት (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) በዞኑና በወረዳው ማህበረሰብ ዘንድ የሰለጠ...
25/07/2026


(2000-2018)

የከሚሴ ቴክኒክና ሙያ (ፖሊ ቴክኒክ) ኮሌጅ ከ2000 እስከ 2018 ዓ.ም ባሉት ዓመታት (እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር) በዞኑና በወረዳው ማህበረሰብ ዘንድ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራትና የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቷል።

​በእነዚህ ዓመታት ውስጥ ኮሌጁ ያከናወናቸውን ዋና ዋና ተግባራት በሚከተሉት ዋና ዋና ዘርፎች ከፍለን ማየት እንችላለን፡

​1. የሰው ኃይል ስልጠና እና ልማት (Training & Human Resource Development)

​መደበኛ ስልጠና፡ በደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 (Level 1–5) በቴክኒክና ሙያ ዘርፎች (በኮንስትራክሽን፣ በአውቶሞቲቭ፣ በኢንዱስትሪ ኤሌክትሪሲቲ፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በጨርቃ ጨርቅና ስፌት፣ በብረታ ብረት ወዘተ) በአስርሺዎች የሚቆጠሩ ሰልጣኞችን አሰልጥኖ ማስመረቅ።

​አጭር ጊዜ ስልጠና፡ ለስራ አጦች፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የስራ እድል ፈጠራን ታላመደ መልኩ በአጭር ጊዜ ሙያዊ ስልጠናዎች ክህሎት ማስጨበጥ።

​የተጠቃሚዎች ብቃት ማረጋገጫ (CoC)፡ ሰልጣኞች በየደረጃቸው የብቃት ምዘና ተመዝነው ስራ ላይ እንዲሰማሩ የማብቃት ተግባር።

​2. የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንተርፕራይዞች ድጋፍ (Technology Transfer & MSE Support)

​አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማፈልቅና ማሻሻል፡ ለአካባቢው አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች፣ ለገበሬዎችና ለነጋዴዎች ምርታማነትን የሚጨምሩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን (ለምሳሌ፡ የግብርና ማቀባበያ መሳሪያዎች፣ የብረታ ብረትና እንጨት ስራ ቴክኖሎጂዎች) በማሻሻል ማሸጋገር።

​የኢንተርፕራይዝ ልማት ድጋፍ፡ ለአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት የሙያ፣ የክህሎትና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ስራዎቻቸውን እንዲያጠናክሩ ማገዝ።

​3. ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር የተደረጉ የስራ ግንኙነቶች (Community Services)

​የህዝብ ተቋማትን ጥገና፡ በአካባቢው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎችና የመንግስት መሪያ ቤቶች ያሉ የኤሌክትሪክ፣ የመኪናና የኮምፒውተር ጥገናዎችን በልምድና በስልጠና መልክ ማከናወን።

​የስራ እድል ፈጠራ ትስስር፡ ከተለያዩ የዞንና የወረዳ የመንግስት አካላት (ከስራና ክህሎት ጽ/ቤት ጋር) በመተባበር የሰለጠኑ ወጣቶች በቀጥታ ወደ ስራ የሚገቡበትን መንገድ ማመቻቸት።

​4. የተቋም ግንባታና አቅም ማሳደግ (Capacity Building)

​የአሰልጣኞች አቅም ማሳደግ፡ የኮሌጁን አሰልጣኞች (Instructors) የትምህርት ደረጃና የሙያ ብቃት ማሳደግ።

​የአውደ ጥናት (Workshop) ማደራጀት፡ ዘመናዊ ማሽኖችንና የስልጠና ቁሳቁሶችን በማሟላት የስልጠናውን ጥራት የማሳደግ ስራ አከናውኗል።

Koollejjiin Polîteknikii Kamisei Barattoota 100 Ol Leenjise Baredina Guddaan Eebbisiise​Adoolessa 18/2018 A.L.I | Kamise...
25/07/2026

Koollejjiin Polîteknikii Kamisei Barattoota 100 Ol Leenjise Baredina Guddaan Eebbisiise

​Adoolessa 18/2018 A.L.I | Kamise

​Koollejjiin Polîteknikii Kamisei bara leenjii 2018tti gosa barnoota ogummaa dhaloota keessoo fi teeknoolojii irratti xiyyeeffataniin leenjisee kan xumursiise leenjitoota ga'umsa fi dorgomaa ta'an 100 ol Adoolessa 18, bara 2018 A.L.I ulfina fi baredina guddaan eebbisiiseera.

​Piroogiraamni eebbaa kun seenaa Koollejjicha keessatti yoo 13ffaaf kan geggeeffame yoo ta'u, piroogiraama kanaan misooma oomisha qonnaatiin 11, akkasumas misoomsa weebii fi daataabeesiitiin 90, walumaagalatti eebbifamtoota 101 eebbisiiseera.

​Sirna eebbaa seenaqabeessa kana irratti qondaaltotni hojii mootummaa olaanoo Godinaa fi Bulchiinsa Magaalaa, hooggantoonni dhaabbatichaa, leengistoonni, eebbifamtoonni fi maatiin isaanii kan irratti argaman yoo ta'u, haala oo'aan kabajameera.

​Gama mootummaa fi dhaabbatichaatiin keessummoota kabajaa ta'anii kan argaman:

​Obbo Muktaar Gezahagñ — Deenii Muudamaa Koolleejjii Polîteknikii Kamisei

​Obbo Ashenafii Aberra — Iggita Deenii Damee Barnoota fi Leenjii Koolleejjii Polîteknikii Kamisei

​Obbo Sayid Indris Sayid — Iggita Hoogganaa Qajeelcha Hojii fi Dandeettii Bulchiinsa Sablammii Oromoo

​Obbo Mahammad Alii — Hoogganaa Waajjira Damee Paartii Badhaadhina Magaalaa Kamisei

​Obbo Arabuu Alii — Itti Aanaa Kantiibaa Magaalaa Kamisei fi Hoogganaa Waajjira Hojii fi Dandeettii, akkasumas hooggantoonni dhaabbilee michuu fi keessummoonni biroo argamaniiru.

​Keessummoonni kabajaa sirna eebbaa kana irratti argaman akka ibsanitti; eebbifamtoonni beekumsa ogummaa fi gochaa argaataniin fayyadamuudhaan uumamsa hojii, damee industrii fi maanufaakchariingii irratti hirmaachuun diinagdee naannoo fi biyyaa guddisuu keessatti shoora isaanii isa olaanaa akka ba'atan dhaamaniiru.

የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 የሥልጠና ዘመን ያሰለጠናቸውን ከ100 በላይ ሰልጣኞች በታላቅ ድምቀት አስመረቀ
​ሀምሌ 18/2018 ዓ.ም | ከሚሴ
​የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 የሥልጠና ዘመን በሀገር በቀልና በቴክኖሎጂ ተኮር የሙያ መስኮች አሰልጥኖ ያበቃቸውን ከ100 በላይ ብቁና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን ሀምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በታላቅ ድምቀትና ማዕረግ አስመርቋል።

ይህ የምረቃ መርሃ ግብር በኮሌጁ የምረቃ ታሪክ ለ13ኛ ጊዜ ሲሆን በዚሁ መርሃ ግብር በሠብል ልማት 11 እንድሁም በዌብ ደቨሎፕመንትና ዳታ ቤዝ 90 በድምሩ 101 ምሩቃን አስመረቀ።
​በዚህ ታሪካዊ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የተቋሙ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ ተመራቂዎችና ወላጆች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
​በመንግሥትና በተቋሙ በኩል በክብር እንግድነት የተገኙት፡
​አቶ ሙክታር ገዛሀኝ — የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን
​አቶ አሸናፊ አበራ — የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ም/ዲን
​አቶ ሰይድ እንድሪስ ሰይድ — የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መመሪያ ም/ኃላፊ
​አቶ መሐመድ አሊ — የከሚሴ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
​አቶ አረቡ አሊ — የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ እና ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ እንድሁም የአጋር ተቋማት አመራሮችና እንግዶች ቸገኝተዋል::
​በምረቃው መርሃ-ግብር ላይ የተገኙት የክብር እንግዶች እንደገለጹት፤ ተመራቂዎች በቀሰሙት የክህሎትና የተግባር እውቀት በመጠቀም በሥራ ፈጠራ፣ በኢንዱስትሪና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ በመሰማራት የአካባቢውንና የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት በማሳደግ ረገድ የበኩላቸውን የጎላ ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።

Kemise Polytechnic College Graduation Ceremony July 18/2018...The graduation process is already accomplished.
25/07/2026

Kemise Polytechnic College Graduation Ceremony
July 18/2018...

The graduation process is already accomplished.

 :‎​የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ላሰለጠናቸው ሰልጣኞች የ2018 ዓ.ም የምረቃ ፕሮግራሙን ነገ ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ ...
24/07/2026

:

‎​የከሚሴ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ላሰለጠናቸው ሰልጣኞች የ2018 ዓ.ም የምረቃ ፕሮግራሙን ነገ ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የተመራቂ ቤተሰቦችና ወዳጆች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ያካሂዳል።
‎​📍 የፕሮግራሙ ዝርዝር መረጃ
‎​📅 ቀን፡ ነገ ሐምሌ 18/2018 ዓ.ም
‎​⏰ ሠዓት፡ ከጧቱ 3:00 ጀምሮ
‎​ቦታ፡ በኮሌጁ ግቢ

‎🌟 የፕሮግራሙ ዋና ዋና ክፍሎች
‎​የክብረ እንግዶች አቀባበልና መግቢያ
‎​የኮሌጁ አመራር የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትና የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት
‎​የዞንና ከተማ አስተዳደር አመራሮች ንግግር
‎​የዋንጫ፣ የሜዳሊያና የልዩ ልዩ ሽልማቶች ሥነ-ሥርዓት
‎​የምስክር ወረቀት (ዲፕሎማ) አሰጣጥና የቃል ኪዳን ሥነ-ሥርዓት
‎​ለተመራቂዎች በሙሉ፡
‎እንኳን ለዚህ ታላቅ የሙያ ስኬት ማዕረግ በሰላም አደረሳችሁ! ለሀገራችን ልማትና እድገት የድርሻችሁን የምታበረክቱበት ብቁ ባለሙያዎች እንድትሆኑ ይመኛል::

Address

ኦሮሞ ዞን ስራና ስልጠና መምሪያ
Kemissie

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Oromo Zone Labour and Training. posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Oromo Zone Labour and Training.:

Shortcuts

Share