የገ/ጉ/ወ/ወረዳ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Kokir
  • የገ/ጉ/ወ/ወረዳ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወረዳ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት Governmental institution at Central Erhiopia-Guraghe Zone- G/G/W/W/- Mehal Amba.

It is governmental organization at SNNP,Guraghe zone,Gedebano Gutazer Wolene Woreda,Mehal Amba town.

06/09/2026
ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ምጉራጌ በንግድ ብቻ ሳይሆን በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ በርትቶና ፀንቶ በመስራት ውጤታማ መሆን እንደሚችል ዳግም ስላሳያችሁ እናመሰግናለን:-አቶ ሸምሱ አማን ፨፨፨፨፨///፨...
06/09/2026

ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ም
ጉራጌ በንግድ ብቻ ሳይሆን በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ በርትቶና ፀንቶ በመስራት ውጤታማ መሆን እንደሚችል ዳግም ስላሳያችሁ እናመሰግናለን:-አቶ ሸምሱ አማን
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በኢትዮጵያ ETFC በተዘጋጀው ውድድር አሸናፊ የሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒና ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሀመድ መኪ ጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሀል አምባ ከተማ በዛሬው እለት ደማቅ አቀባበል ተደረጎላቸዋል።

የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን እንዳሉት ኢትዮጵያም ሆነ ዞናችን ከዚህ ቀደም በአትሌቲክስ ስፖርት ዘርፍ ብቻ ይታወቁ እንደነበር አንስተው፤ አሁን ላይ መንግስት የፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም ወጣቶች ሀገሪቷ በቦክስ ስፖርትን እንድትታወቅ እያደረጉ ነው ብለዋል።

ጉራጌ በንግድ ብቻ ሳይሆን በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ በርትቶና ፀንቶ በመስራት ውጤታማ መሆን እንደሚችል ዳግም ስላሳያችሁ እናመሰግናለን ሲሉም ተናግረዋል።
ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒና ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሀመድ መኪ በቦክስ የስፖርት ውድድር እያሳዩት ያለው ድንቅ ብቃት አድንቀዋል።

የጉራጌ ዞን የብዙ ስፖርተኞች መፍለቂያ ነው ያሉት አቶ ሸምሱ መሰል ስፖርተኞች የሀገራችን ወጣቶች ከተለያዩ ሱሶች እንዲወጡና ጊዜያቸውን አልባሌ ቦታ እንዳያሳልፉ አርአያ ከመሆን ባለፈ ስፖርት ላይ እንዲያዘወትሩና ለነጋቸውን ትልቅ ተስፋ እንዲሰንቁ እንደሚያደርጋቸውም ገልጸዋል።

ከዚህም ባሻገር የሀገር ኩራት የሆኑ ተተኪ ስፖርተኞች ለማፍራት በዘርፉ የተሰማሩትን ተገቢውን እውቅናና ክብር መስጠት እንደሚገባ አቶ ሸምሱ አስገንዝበዋል።

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን በበኩላቸው ስፖርት ነጠላ ትርክት በማስቀረት የጋራ ትርክትን ከመገንባት ባለፈ ለአንድነት፣ ለትብብር፣ ለሰላምና ለሀገር ግንባታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም ገልጸዋል።

ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሀመድ መኪና አትሌት ረቢቅ ሳኒ ወረዳው ያፈራቸው ስፖርተኞች መሆናቸው ጠቁመው፤ እነዚህ ስፖርተኞች የሀገራቸውን ባንድራ በተለያዩ በአፍሪካና በአለም ሀገራት ከፍ ማድረግ ችለዋል ብለዋል።

ወጣቱ በስፖርቱ ዘርፍ እንዲሳተፉ በማድረግ በቀጣይ የወጣቱን እጣ ፋንታ ልንታደግ ይገባል ያሉት አቶ ሚፍታ ለዚህም በወረዳው የወጣት ማሰልጠኛ ተቋማት ማብዛት ላይ ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ግሎባል ቴኳንዶ ፌደሬሽን መስራችና ፕሬዝዳንት ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሀመድ መኪ እንዳሉት ዞኑ በአለም፣ በአፍሪካና በሀገር ደረጃ ታዋቂ ስፖርተኞችን በማፍራት ማበርከቷንም አንስተዋል።
ወጣቶች ጊዜያቸውን በመልካም ነገር በማዋል በስፖርት ዘርፍ መሰማራት እንዳለባቸው መክረው ከዚህም ባለፈ የወረዳው ልማት ለማረጋገጥ በአንድነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በETFC 02 በተዘጋጀው ውድድር አሸናፊ ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒ ወጣቶች ነገአቸውን የተሻለ ለማድረግ በስፖርቱ ዘርፍ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው መክረው የወረዳው አስተዳደር ላደረገላቸው አቀባበልም አመስግነዋል።

ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ምበወረዳው በ2018 የምርት ዘመን በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላሉ:- አቶ አብድረሂም ርዳ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘ...
06/09/2026

ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ም
በወረዳው በ2018 የምርት ዘመን በግብርናው ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላሉ:- አቶ አብድረሂም ርዳ
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ጳጉሜ 1 "የእምርታ ቀንን" በማስመልከት በግብርና ልማት የተሰሩ ስራዎች ምልከታ ተካሂዷል።

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አብድረሂም ርዳ እንዳሉት በወረዳው 5ቱንም የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ስያሜዎች እንደሚከበሩ አንስተዋል።
በዛሬው እለት ጳጉሜ 1 የእምርታ ቀን በማስመልከት በወረዳው በ2018 ዓ.ም በግብርና ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች ምልከታ ማድረጋቸውን ጠቁመዋል።

አክለውም በወረዳው በግብርና ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማራው የHLS አበባ እርሻ ልማት መጎብኘቱን ገልጸዋል።
በግብርና ልማት ዘርፍ በተጠናቀቀው በጀት አመት በወረዳው ትላልቅ ስኬቶች እንደተመዘገበ አንስተው፤ ከዚህም ባለፈ የፓርቲው ኢንሼቲቭ በተገቢው በመተግበሩ አርሶ አደሩ ምርት ከራሳቸው አልፎ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እንደ አብድረሂም ገለጻ በወረዳው ከዚህ ቀደም ታርሰው የማይታወቁ 5 ሺህ ሄክታር መሬት በማረስ በሰብል መሸፈን እንደተቻለም ገልጸዋል።
በ2018 በጀት ዓመት በግብርናው ልማት ዘርፍ የአርሶ አደሩን ህይወት ለመቀየር በዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶችን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመላክተዋል።

የወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከድር መርጋ በበኩላቸው፥ በወረዳው በ2018 የምርት ዘመን 20 ሺህ 518 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 17 ሺህ 812 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈን መቻሉን ገልጸዋል።

በመኸር ከለማው ማሳ ከ1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም አመላክተዋል።
የዘንድሮ ማሳ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር 5 ሺህ 6 ሄክታር መሬት በላይ እድገት እንዳለውም አስረድተዋል።
በወረዳው በመኸር ከለማው ማሳ ውስጥ ስንዴ፣ ጤፍና ገብስ በሰፊው በክላስተር መልማቱንም አንስተው፤ ይህም በወረዳው በክላስተር የማልማት ዘዴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል ብለዋል።

በመስክ ምልከታውም የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን፣ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ፕላን ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ዘይነብ ወራቄ ጨምሮ የወረዳው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ምየገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቡም መሀመድ መኪ እና በኢትዮጵያ ETFC የተዘጋጀው ውድድር አሸናፊ የሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒ ...
06/09/2026

ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቡም መሀመድ መኪ እና በኢትዮጵያ ETFC የተዘጋጀው ውድድር አሸናፊ የሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒ የወረዳችን ተወላጅ ጀግኖቻችን በዛሬው እለት በመሀል አምባ ከተማ ደማቅ አቀባበል አደረገላቸው።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር በኢትዮጵያ ETFC በተዘጋጀው ውድድር አሸናፊ ለሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒና ለኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሀመድ መኪ ለእያንዳቸው 3 መቶ ሺህ ብር አበርክቶላቸዋል።

የፕሮግራሙን ዝርዝር መረጃ ይዘን እንመለሳለን!!!

ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "የእምርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ ወረዳዊ የግብርና ልማት ስራ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨በጉብኝቱም ...
06/09/2026

ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ "የእምርታ ቀን" ምክንያት በማድረግ ወረዳዊ የግብርና ልማት ስራ የመስክ ጉብኝት ተካሂዷል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉብኝቱም በወረዳው HLS አበባ ልማት እና በክላስተር የለማ የሰብል ልማት የግብርና ስራዎች ምልከታ ተካሂዷል።

በጉብኝቱ ላይ የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊና የወረዳው ደጋፊ አመራር አቶ ሸምሱ አማን ፣የወረዳው አስተባባሪ አካላት ፣የወረዳው አመራሮች ተገኝተዋል።

06/09/2026

የዛሬ አቀባበል ላይ ረቢቅ ሳኒ መልእክት

ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ምበጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የእምርታ ቀን በማስመልከት የወረዳው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በETFC ውድድር አሸናፊ የሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒና ኢንተር...
06/09/2026

ጳጉሜ 01/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የእምርታ ቀን በማስመልከት የወረዳው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ በETFC ውድድር አሸናፊ የሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒና ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሀመድ ጨምሮ ሌሎችም በተገኙበት የHLS አበባ እርሻ ልማት ጎብኝተዋል።

ስፖርተኞቹም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሀልአምባ ከተማ ሲደርሱም በህዝቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ወረዳው በግብርና ዘርፍ ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው።

በኢትዮጵያ ETFC በተዘጋጀው ውድድር አሸናፊ የሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒና ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሀመድ መኪ መሀል አምባ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው።

በሙአይ ታይ ስፖርት ውድድር አሸናፊ የሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒና ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቦም መሀመድ መኪ ጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ መሀል አምባ ከተማ ሲደርሱ በወረዳው የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ስፖርተኞች፣ አድናቂዎቻቸውና ደጋፊዎቻቸው ደማቅ አቀባበል እያደረጉላቸው ነው።

ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒ በETFC ሀገሩን ወክሎ በታሪካዊው አድዋ ሙዚየም በተካሄደው የሙይታይ ፍልሚያ የደቡብ ሱዳን ተጋጣሚውን ስካይን በማሸነፍ አስደናቂ ብቃቱን ማሳየቱ ይታወሳል።

በፕሮግራሙም የጉራጌ ዞን የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ አማን፣ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚፍታ ሁሴን ጨምሮ የወረዳው የስራ ኃላዎች፣ የአካባቢዎ ነዋሪዎችና ሌሎችም ተገኝተዋል።

ነሐሴ 30/2018 ዓ/ምአጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከጉራጌ ዞን ሰ/ማ/ጉ/መምሪያ ጋር በመቀናጀት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ከ550 ...
05/09/2026

ነሐሴ 30/2018 ዓ/ም
አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከጉራጌ ዞን ሰ/ማ/ጉ/መምሪያ ጋር በመቀናጀት በወረዳ ውስጥ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች ከ550 ሺህ ብር የሚያወጣ ዊልቸር ድጋፍ አደረገ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገ/ጉ/ወ/ወ/ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት ከጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ጋር በመተባበር አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ግብረ-ሰናይ ድርጅት አማካኝነት 5 የአዋቂዎች ዊልቸር 4 የአዋቂ ክራንች ድጋፍ ተደረገ።

የወረዳው ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃይደር ዝይን እንዳሉት አጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ግብረ ሰናይ ድርጅት 5 የአዋቂዎች ዊልቸር ከ550 ሺህ ብር በላይ የሚወጣ
ድጋፍ መድረጉን ገልጸዋል።
የጀርባ ችግር ላለባቸው፣ ራሳቸውን መቆጣጠር ለማይችሉና ውስንነት ላለባቸው አዋቂዎች የሚሆን ዊልቸር ድጋፍ መደረጉን አስታወቀዋል።

አቶ ሃይደር አክለውም የዊልቸሩ ድጋፍ አካል ጉዳተኞች ራሳቸውን ችለው እንዲቀመጡ፣ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ጊዜያቸውን በአግባቡ እንዲያሳልፉ እንዲሁም ጎረቤቶቻቸው ሄደው እንዲዝናኑና እንዲሳተፉ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል።

በመጨረሻም አቶ ሃይደር ድጋፉን ላደረገው ለአጋፔ ሞቢሊቲ ኢትዮጵያ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ለጉራጌ ዞን ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ እና ለወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ላደረገው የትራንስፖርት ድጋፍ በራሳቸውና በተቋማቸው ስም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅረበው ይህን መሰል ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ላይ ልዩ ተሸላሚ በመሆን የዋንጫና ሰርተፍኬት ተበረከተለት።፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨የጉራጌ ዞን ...
05/09/2026

የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ላይ ልዩ ተሸላሚ በመሆን የዋንጫና ሰርተፍኬት ተበረከተለት።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ የ2018 በጀት አመት ማጠቃለያ ሴክቶሪያል ጉባኤ "አንድነት ለጽዳት፣ ትጋት ለአገልግሎት፣ ውሳኔ ለልማት" በሚል መሪ ቃል የምክክር መድረክ በወልቂጤ ከተማ ባካሄደበት ወቅት የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ፅ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ላይ ልዩ ተሸላሚ በመሆን የዋንጫና ሰርተፍኬት ተበርክቷለታል።

በኢትዮጵያ ETFC የተዘጋጀው ውድድር አሸናፊ የሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒ እና የኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቡም መሀመድ መኪ የወረዳችን ተወላጅ ጀግኖቻችን በነገው እለት በመሀል አምባ ከተማ...
05/09/2026

በኢትዮጵያ ETFC የተዘጋጀው ውድድር አሸናፊ የሆነው ቦክሰኛ ረቢቅ ሳኒ እና የኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ሳቡም መሀመድ መኪ የወረዳችን ተወላጅ ጀግኖቻችን በነገው እለት በመሀል አምባ ከተማ የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር አማካኝነት ደማቅ አቀባበል ያደረግላቸዋል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ አስተዳደር ያዘጋጀው የወረዳችን ተወላጅ ጀግኖቻችን አቀባበል እና የማበረታቻ ፕሮግራም በነገው እለት በመሀል አምባ ከተማ በከተማው ወጣቶችና ነዋሪዎች
በዳማቁ አቀባበል የሚደረግላቸው ይሆናል።

Address

Kokir

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 09:00 - 17:00
Wednesday 09:00 - 17:00
Thursday 09:00 - 17:00
Friday 09:00 - 17:00
Saturday 09:00 - 17:00
Sunday 09:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የገ/ጉ/ወ/ወረዳ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የገ/ጉ/ወ/ወረዳ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት:

Shortcuts

Share