Gedebano Gutazer Welene W Science and Information Technology - SIT Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Kokir
  • Gedebano Gutazer Welene W Science and Information Technology - SIT Office

Gedebano Gutazer Welene W Science and Information  Technology - SIT Office ICT -mean information communication technology that deal about how to comunicat, transreceiving info from person to person and technology

25/01/2026
25/01/2026
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሆሳዕና የሚገኘውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ጉብኝት  የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር በከፊል
15/01/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሆሳዕና የሚገኘውን የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን ጉብኝት የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር በከፊል

08/11/2025
29/05/2025
20/05/2025
ምንጭ INSAዋይ   እንዳይጠለፍ እና ለመረጃ ጥቃት እንዳያጋልጠን በምን መልኩ መከላከል እንችላለን? ባለንበት የዲጂታል ዘመን በተለይም በከተሞች አካባቢ ከቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር በተያያዘ  ...
07/04/2025

ምንጭ INSAዋይ እንዳይጠለፍ እና ለመረጃ ጥቃት እንዳያጋልጠን በምን መልኩ መከላከል እንችላለን?

ባለንበት የዲጂታል ዘመን በተለይም በከተሞች አካባቢ ከቴክኖሎጂ መስፋፋት ጋር በተያያዘ የዋይ ፋይ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ተበራክቷል፡፡ ብዙ ጊዜ ለቤት ዉስጥ አገልግሎትም ሆነ ለመስሪያ ቤት ያስገጠምነዉ ዋይፋይ እኛ ያሰብነዉን አገልግሎት እየሰጠን ከሆነ ስለ ደህንነቱ ብዙም ግድ አይሰጠንም፡፡ ነገር ግን ይሄ ተግባር ፍፁም ስህተት የሆነና ብዙ ችግሮችን ሊያስከትል የሚችል ጎጂ ልምድ ነው፡፡

ለምንጠቀማቸው ዋይፋዮቻችን ተገቢውን የደህንነት ስርዓት ተግባራዊ የማናደርግ ከሆነ የሳይበር ወንጀለኞች አውታረ-መረቡን /networks/ በመጠቀም ምስጢራዊ መረጃዎችን መመንተፍ እና ዋይፋዩን በሚገባው ፍጥነት እንዳንጠቀም አገልግሎቱን ሊያስተጓጉሉብን ይችላሉ፡፡

በመሆኑም ከአገልግሎት መስተጓጎል እና ከመረጃ መዝባሪዎች ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጮች ተግባራዊ ማድረግ ይመከራል፡፡

• ጠንካራ የይለፍ ቃል /password/ ይጠቀሙ
የዋይፋይ ራውተሮች ሲመረቱ ነባሪ መጠቀሚያ ስም /default username/ እና ምስጢራዊ የይለፍ-ቃል ይኖራቸዋል። የራዉተሩ አምራች ከታወቀ እነዚህን የዲፎልት መጠቀሚያ ስሞችን እና ምስጢራዊ የይለፍ-ቃላትን ለመገመት በጣም ቀላል ነው፡፡ በመሆኑም የግል ዋይፋዮቻችን ደህንነት ለማረጋገጥ ጠንካራ የይለፍ-ቃሎችን መጠቀም ይገባል፡፡

• የበይነ-መረብ አገልግሎት መስጫ መለያ ይቀይሩ /SSID/
እያንዳንዱ ራውተር ከነባሪ መጠቀሚያ ስም ማለትም “ነባሪ” /default/ ጋር ስለሚመጣ የአውታረ መረባችንን አገልግሎት መስጫ መለያ ስም /SSID/ መለወጥ ያስፈልጋል። ይህንን በራውተራችን ገመድ አልባ መሰረታዊ ቅንብር ገጽ /wireless basic setting page/ በመሄድ መጠሪያውን በመለወጥ የዋይፋያችንን ተገማችነት በማስቀረት ለጥቃት እንዳንጋለጥ ማድረግ እንችላለን፡፡

• አውታረ-መረባችንን መመስጠር
የዋይፋይ ራውተራችን ከመረጃ ጠለፋ እና የአገልግሎት መስተጓጎል ለመከላከል የአውታረ-መረብ ምስጠራን መተግበር አስፈላጊ ነዉ፡፡

• ሎጊንግ መፍቀድ (Enable Logging)
ሎጊንግ አማራጭን ስንፈቅድ (Enable) የዋይፋይ ኔትዎርካችንን እንዳይጠለፍ ለማድረግ ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ ነዉ፡፡ በዋይፋይ ራውተራችን ውስጥ ያለው የመለያ ባህሪ ሁሉንም የአይፒ አድራሻ ይመዘግባል፡፡ እንዲሁም ሁሉንም የግንኙነት ሙከራዎች ዝርዝር ይሰጣል። ምንም እንኳን ይህን ተግባራዊ ማድረግ ዋይፋያችንን ከጠላፊዎች የማይጠብቅ ቢሆንም ማንኛውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ለመከታተል ይረዳናል፡፡ ይህንን ስርዓት "Enable" ማድረግ ይገባናል፡፡

• የዋይፋይ ሲግናል ማስተካከል
የዋይፋይ ሲግናላችን ጠንካራ እና በአጭር የቆዳ ስፋት ብቻ የምንጠቀም ከሆነ የዋይፋዩን ሲግናል አቅም መቀነስ ይኖርብናል፡፡ ይህን ለማድረግ የራውተራችንን ሞድ 802.11n ወይም 802.11b ምትክ 802.11g መጠቀም ይመከራል፡፡

• የራውተራችንን ፈርምዌር ማዘመን
ራውተራችን ፈርምዌር /Firmware/ የሚባል ሶፍትዌር አለው፡፡ ፈርምዌር ጊዜው ያለፈበት እና በወቅቱ ያልዘመነ ከሆነ ለአንዳንድ የደህንነት ሰጋቶች የተጋለጠ መሆኑ አይቀርም፡፡ ምንም እንኳ የዘመናዊ ራውተሮች ፈርምዌር በራሳቸው የሚያዘምኑ ቢሆንም እርግጠኛ ለመሆን በየጊዜው መዘመናቸውን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡

• የራውተራችን ፋየርዋል ማንቃት መጠቀም
የራውተራችንን ፋየርዎል/firewall/ ተግባራዊ ማድረግ ወይም ማንቃት ይኖርብናል፡፡ ይህን በማድረጋችን ሊከሰት ከሚችል ተጨባጭ የሳይበር

Address

Kokir

Telephone

+251918823328

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gedebano Gutazer Welene W Science and Information Technology - SIT Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gedebano Gutazer Welene W Science and Information Technology - SIT Office:

Share