ኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት - K/Z/S/Z/Woreda Education Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Konso
  • ኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት - K/Z/S/Z/Woreda Education Office

ኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት - K/Z/S/Z/Woreda Education Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት - K/Z/S/Z/Woreda Education Office, Government Organization, Konso.

መስከረም 30/2015 ዓም------------------------------ከመስከረም 30/2015 ዓም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመላ ሀገሪቱ እየተሠጠ በሚገኝበት ዕለት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ...
10/10/2022

መስከረም 30/2015 ዓም
------------------------------
ከመስከረም 30/2015 ዓም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በመላ ሀገሪቱ እየተሠጠ በሚገኝበት ዕለት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው አደጋ የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ትምህርት ቢሮ ማዘኑን ገለጸ፡፡
------------------------------------------------------
በዛሬው ዕለት ጠዋት በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዉን ዋናውን ግቢ እና የቴክኖሎጂ ካምፓስን የሚያገኛኘው ድልድይ በመፍረሱ ምክንያት ድልድዩን ሲሻገሩ በነበሩ ተማሪዎች ላይ በደረሰዉ ጉዳት ማዘኑን የትምህርት ሚኒስቴር በይፋዊ ማኅበራዊ ገጹ ላይ አስፍሯል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አክሎም ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በሀዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ እንደሚገኝና የተከሰተውን ሁኔታ መላዉ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ እና የትምህርት ሚኒስቴር ግብረ ሀይል በቅርበት እየተከታተለ በመሆኑ ወላጆች እንዳይደናገጡ አሳውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ አያይዞም ጉዳት የደረሰባቸዉ ተማሪዎች በቀጣይ በሚሰጠዉ ፈተና የሚፈተኑ መሆኑን በመግለጽ ሌሎች ተማሪዎች በአጋጣሚዉ ሳይረበሹ ተረጋግተዉ እንዲፈተኑ አሳስቧል፡፡

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግሥት ትምህርት ቢሮም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በደረሰው ጉዳት ለተጎዱ አካላት ሀዘኑን እየገለጸ ቢሮው በክልሉ ውስጥ ለሚገኙ ተፈታኝ ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራን፣ የትምህርት አካላት እና መላው ማኅበረሰብ ከሀሰተኛ መረጃዎች በመጠበቅ በየአካባቢያቸው የሚሰጠውን ፈተና በስኬት ለማጠናቀቅ እንዲቻል ትብብር እንዲያደርጉ ያሳስባል፡፡

መረጃው፦ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት

10/10/2022
መስከረም 26/2015 ዓ/ም--------------------------------''በወንድማማችነታችን በጽኑ መሰረት ላይ እንዲሆን እንደጋገፋለን!!"                  አቶ ዳዊት ገበየ...
06/10/2022

መስከረም 26/2015 ዓ/ም
--------------------------------
''በወንድማማችነታችን በጽኑ መሰረት ላይ እንዲሆን እንደጋገፋለን!!"

አቶ ዳዊት ገበየሁ
(የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ)

የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ጂንካ ዩኒቨርስቲ ለሚሄዱ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች አቀባበል አደረጉ።
___________

ዋና አስተዳዳሪው እንኳን ደህና መጣችሁ! በማለት የሚትሄዱለት አላማ የስኬትና ውጤት እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ ብለዋል።

"ኮንሶ ፍቅር ነው፣ ኮንሶ ታታሪ ህዝብ ነው! ኮንሶ እንግዳ ተቀባይ በመሆኑ ስንቀበላችሁ በደስታ ነው ብለዋል ዋና አስተዳደሰሪው አቶ ዳዊት ገበዬሁ።

ወደ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመፈተን የሚሄዱ የደራሼ ልዩ ወረዳ ተማሪዎች በኮንሶ ዞን ካራት ከተማ ሲደርሱ፣ዋና አስተዳደሩ፣ አመራሮች እና ታታሪው የኮንሶ ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አቶ ዳዊት ገበየሁ ለተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ!፣ በፈተናው በርትታችሁ ሀገራችሁን እንደሚታኮሩ ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉም ምክራቸውን ለግሰዋል።

አቶ ዳዊት ጨምረው በጉዞአችው ሁሉ መልካም ጊዜ እንዲሆንላቸው ልባዊ ምኞታቸውን ገልጸዋል።

መረጃው
የኮንሶ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉ/መምሪያ

መስከረም 23/2015 ዓ.ም------------------------------የዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት መደረጉ  ተገለፀ።-------...
03/10/2022

መስከረም 23/2015 ዓ.ም
------------------------------
የዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለፀ።
----------------------------------------------------------
የደቡብ ክልል ፖሊስ የዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ያለ ምንም የፀጥታ ችግር በሰላም እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ማድረጉን ገልጿል።

መንግስት ብቁና የተሻለ ትውልድ ለመቅረፅ በማሰብ የዘንድሮዉ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከወትሮዉ በተለየ በዩንቨርሲቲዎች የሚሰጥ በመሆኑ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተናዉ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ የተለየ ትኩረት ተሰጥቶ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ተግባር መግባቱ የደቡብ ክልል ፖሊስ አስታዉቋል።

በደቡብ ክልል በሚገኙና የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሚሰጥባቸዉ ሁሉም ዩንቨርስቲዎች ፈተናው ከማንኛውም የፀጥታ ችግር ነፃ ሆኖ ተፈታኞች ያለምንም ስጋት ተረጋግተው መፈተን እንዲችሉና ፈተናዉን የማጓጓዙ ሂደት እንከን እንዳይገጥመዉ ተገቢዉ ጥበቃና ፍተሻ በማድረግ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ኃይሉ የተሰጠዉ ተልእኮና ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንደሚገባዉ የክልሉ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎች ለፈተና ሲቀርቡ ስለት ያላቸውን ብረቶችንና ጠንካራ ፕላስቲኮች፣ አደንዛዥ ዕፅ፣ ጫት፣ ሲጋራ፣ የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም እንዲሁም የሃኪም ማዘዣ የሌለው መድሃኒት ሽሮፕም ሆነ ታብሌት፣ የህክምና መስጫ መርፌ፣ የአንገት ሀብል፣ የጸጉር ጌጥ፤ የጆሮ ጌጥ፤ የጣት ቀለበት፤ የእጅ አንባር አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት እንዲሁም ተንቀሳቃሽ ስልክ፤ አይ-ፓድ፤ ታብሌት፤ ላፕቶፕ፤ ስማርት ሰአት ፤ ማጂክ ብዕር (እስኪሪቢቶ)፤ ማጂክ ኮት(ጃኬት)፤ የግል ፍላሽ ዲስክ፤ ሲዲ፤ ሚሞሪ፤ ሚሞሪ ሪደር፤ ኦ-ተጂ ኮንቨርተርና ፎቶ የሚያነሱ እና ድምፅ የሚቀርፁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዞ መገኘት ለተፈታኞች የተከለከሉ ተግባራት በመሆናቸውን ሁሉም ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር የተጣለዉ ክልከላ አክብረዉ እንዲገኙ ኮሚሽኑ አሳስቧል።

መረጃው፦ የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን

መስከረም 21/2015 ዓ/ም--------------//---------------ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል። -----------------...
01/10/2022

መስከረም 21/2015 ዓ/ም
--------------//---------------
ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የዘንድሮውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል።
-------------------------------------------------
የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ ይታወቃል።

ለዚህም ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ዩኒቨርሲቲዎች የተለያዩ ሀላፊነቶች የተጣለባቸው በመሆኑ በርካታ ስራዎችን እያከናወኑ ይገኛሉ።

ጂንካ ዩኒቨርሲቲም የተጣለበትን ሀላፊነት ለመወጣት በፕሬዚዳንቱ የሚመራ ግብረሃይል በማደራጀት አስፈላጊ ግብአቶችን የማሟላትና የሰው ሀይል የማደራጀት ስራዎችን ማጠናቀቁን ተገልጿል።

ብሄራዊ ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ የተማሪዎች መኝታ ክፍሎች ዝግጅት ፣ የምግብ ግብአቶች አቅርቦት፣ የፈተና አዳራሾች ዝግጅትና ሌሎች አገልግሎቶችን ለመስጠት በትኩረት እየተሰራ እንደሆነም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ኩሴ ጉዲሼ ገልፀዋል።

ተፈታኝ ተማሪዎችም ያለምንም ስጋትና ጭንቀት ፈተናቸውን እንዲፈተኑና የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውን አስደሳች ለማድረግ ሁለንተናዊ ዝግጅት መደረጉንም ተመላክቷል።

*እውቀት ለለውጥ*

መረጃው፦ ከጅንካ ዩንቨርሲቲ

መስከረም 20/2015 ዓ/ም----------------//---------------በኮንሶ ዞን ለምትገኙ ሁሉም የማህበራዊ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለምትወስዱ ተማሪዎች በቀን 27/0...
30/09/2022

መስከረም 20/2015 ዓ/ም
----------------//---------------
በኮንሶ ዞን ለምትገኙ ሁሉም የማህበራዊ ሣይንስ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለምትወስዱ ተማሪዎች በቀን 27/01/2015 ዓ/ም ከዚህ በታች የተለጠፈው ኘሮግራም መሰረት በተባለው ሰዓት እንድትገኙ የዞኑ ትምህርት መምሪያ አጥብቆ ያሳስባል፡፡

መስከረም 20/2015 ዓ/ም  --------------//--------------የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤታማ እንዲሆን የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚናቸውን በተገቢው  ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡--...
30/09/2022

መስከረም 20/2015 ዓ/ም
--------------//--------------
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤታማ እንዲሆን የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚናቸውን በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
---------------------------------------------------------------
የ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች እና ሚድያዎች ሚናቸውን በተገቢው ሊወጡ እንደሚገባ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ፒኤችዲ) ገልጸዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር በተለያዩ ወቅታዊ የዘርፉ ጉዳዮች ላይ ምክክር አካሂዷል፡፡

መድረኩ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና፣ የተማሪዎች ምዝገባ የምገባ እና በጦርነት የተጎዱ ትምህርት ቤቶች በሚመለከቱ ርዕሰ ጉዳዮች ተግባቦት ላይ ያተኮረ ነው ።

ከ12ኛ ክፍል ፈተና በተመለከተ ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲዎቹ ፈተናውን ለመፈተን ሲመጡ ማድረግ ያለባቸውንና የሌለባቸውን የተከለከሉ ጉዳዮች እና አጠቃላይ ዝግጅቶችን በሚመለከት ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር እሸቱ ከበደ የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በውጤታማነት እንዲጠናቀቀቅ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ለሚድያዎች ትክክለኛውን መረጃ ለህበረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል፤

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ተማሪዎች ሳይረበሹ ፈተናቸውን እንዲወስዱ በማድረግ ረገድ የህዝብ ግንኙነት እና ሚድያዎችን ጨምሮ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

በተጨማሪ ተማሪዎች ኩረጃን በመጠየፍ የራሳቸውን ብቻ መስራት እንደሚገባቸው የግንዘቤ ማስጨበጥ ስራ ከወዲሁ መስራት ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡

ሀገር አቀፍ ፈተናዎች አገልግሎት የ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች ለመስጠት የሚያስችለውን የቅድመ ዝግጅት ስራ ማጠናቀቁ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

Address

Konso

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ት/ቤቶች ጽ/ቤት - K/Z/S/Z/Woreda Education Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share