Konso Zone Government Communication

Konso Zone Government Communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Konso Zone Government Communication, Government Organization, Main Road, Konso.

This is the official digital facebook portal of the Konso Zone Government Communication Service, dedicated to providing timely, accurate, and transparent updates on local governance, development projects, and public affairs.

የTAT  ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ኢንቨስትመንትና የTATI የግብርና አገልግሎቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መኖ ማቀነባበሪያ ሥራቸውን በአዲስ መልክ እያጠናከሩ መሆኑ ተገለጸካራት፣ ነሐሴ...
03/09/2026

የTAT ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ኢንቨስትመንትና የTATI የግብርና አገልግሎቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መኖ ማቀነባበሪያ ሥራቸውን በአዲስ መልክ እያጠናከሩ መሆኑ ተገለጸ

ካራት፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

በኮንሶ ዞን ካራት ዙሪያ ወረዳ፣ አርካሌ ዳራ ቀበሌ የዶሮ እርባታ ኢንቨስትመንት ሥራ የተሰማራው የTAT ዶሮ እርባታ ማኅበር እና በካራት ከተማ የተቋቋመው የTATI የግብርና አገልግሎቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መኖ ማቀነባበሪያ ማኅበር ሥራቸውን በአዲስ መልክ እያጠናከሩ መሆኑ ተገለጸ።

የማኅበሩ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተወካይና የማኅበራዊ ሚዲያ ባለሙያ አቶ ኩሻቦ ኩሲያ እንደገለጹት፣ ማኅበሩ ለኮንሶና አካባቢው አርሶ አደሮች ጥራት ያለው የእንስሳት መኖ በማቅረብ የዶሮ ምርትንና የአርሶ አደሮችን ገቢ ማሳደግን ዋና ዓላማው አድርጎ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።

የTAT ዶሮ እርባታ ማኅበር በቂና ጥራት ያለው የእንስሳት መኖ ለአካባቢው አምራቾች ለማቅረብ በካራት ከተማ የTATI የግብርና አገልግሎቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መኖ ማቀነባበሪያ አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ማስገባቱንም አቶ ኩሻቦ ገልጸዋል።

በመኖ ማቀነባበሪያውም ለዶሮዎች ብቻ ሳይሆን ለወተት ላሞች፣ ለሰንጋና ለበሬዎች፣ ለጫጩቶች እንዲሁም ለእንቁላል ጣይ ፣ለታዳጊ ዶሮዎች የሚያገለግሉ የመኖ ዓይነቶችን እያዘጋጀ መሆኑን ተገልጸው ፣ ምርቶቹንም ከአካባቢው ባለፈ ለአጎራባች አምራቾች ወይም ዞኖች ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑ ታውቋል።

አብዛኛዎቹ የመኖ ግብዓቶች ከእህል የሚገኙ ሲሆን፣ በተለይም በቆሎና ማሽላ እንደሚጠቀሙ ፣ እንዲሁም የመኖውን ጥራትና የንጥረ ነገር ሚዛን ለማስጠበቅ እንደ ዳይካልሲየም ፎስፌት (Dicalcium Phosphate) ፣ ኒዉትረሽ ፕርምክስ(Neturation premix) እና እንድሁም ሞላሰስ(Molasses) ከተቀነባበረ ዉጪ ማቅረብ እንደምቻል እና ሌሎች ግብዓቶችንም እያዘጋጁ መሆኑ ተጠቁሟል።

ተቋሙ በኃይል አቅርቦት እጥረት ሥራው እንዳይስተጓጎል ሁለት የማጫጫ/ማፈልፈያ ማሽኖችን ከቻይና በቅርቡ ማስገባቱንም አቶ ኩሻቦ ገልጸው ፣ እነዚህ ማሽኖች በአንድ ወር ውስጥ ከ24,800 በላይ ጫጩቶችን የመፈልፈል አቅም እንዳላቸው በመግለፅ ፣ ከዚህ ባለፈም ለጫጩቶች መድኃኒትና ክትባት ማቀዝቀዣ የሚያገለግል ፍሪጅ መገጠሙን ገልጸዋል።

ተቋሙ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 12 ሠራተኞችን ያሰማራ ሲሆን፣ ሥራውን ሙሉ በሙሉ ሲጀምር ከ24 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር እንደሚችል አቶ ኩሻቦ ገልጸዋል።

በዚህም የTAT ዘመናዊ የዶሮ እርባታ ኢንቨስትመንትንና የTATI የግብርና አገልግሎቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መኖ ማቀነባበሪያ ማኅበራት የዶሮና የእንስሳት ምርትን ከማሳደግ ባለፈ፣ የአርሶ አደሮችን ገቢ ለማሳደግና የአካባቢውን የእንስሳት መኖ አቅርቦት ለማጠናከር የሚያግዙ ሥራዎችን እያከናወኑ መሆኑ ተገልጿል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ ዞን በዲራሼ ወረዳ "ሠላም ለሁሉም ሁሉም ለሠላም" በሚል መሪ ቃል ታላቂ  የዕርቀ ሠላም የማጠቃለያ ኮንፍራንስ ተካሂዷልካራት፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም (ኮንሶ...
03/09/2026

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋርዱላ ዞን በዲራሼ ወረዳ "ሠላም ለሁሉም ሁሉም ለሠላም" በሚል መሪ ቃል ታላቂ የዕርቀ ሠላም የማጠቃለያ ኮንፍራንስ ተካሂዷል

ካራት፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

በወረዳው በኦርጊሌ ቀበሌ ማዕከል ላይ በተካሄደው በዚሁ ታላቂ መርሃ - ግብር ላይ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፌ - ጉባኤ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ በዞኑ በሠላም ጉዳይ ላይ ስር ነቀል የሆነ ለውጥ እንድመጣ ሁሉም ቂን ልቦናን ተላብሶ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዳለበት ገልጸዋል።

ክልሉን የሠላም፣ የመቻቻል እና የብልፅግና ተምሳሌት ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝም አፌ - ጉባኤው ጠቅሰዋል።

ክልሉ በሠላም ጉዳይ ላይ በየደረጃቸው የጀመራቸው ተግባራትን ከየትኛውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ እንደሚያስቀጥልም ጠቁመዋል።

ክቡር ዋና አፌ - ጉባኤው በዞኑ ለዛሬው በአከባቢው አንፃራዊ ሠላም መስፈን ከክልል ጀምሮ ትልቅ ዋጋ ለከፈሉ አካላት ያላቸውን ትልቅ ክብር፣ ዕውቅናና አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አበነዘር ተረፈ በበኩላቸው የአከባቢው ሠላም እንድፀና ሁሉም ሰው አለያይ ከሆኑት ትርክቶች በመራቅ ለሠላም ዙሪያ ላይ የጀመረውን ዜብ የመቆምእሳበውን አጠናክሮ ማስቀጠል እንዳለበት ጠይቀዋል።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ፍሰሀ ጋርደው ሠላም ከሁሉ በላይ ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን በማመላከት ዛሬ ላይ በአከባቢው የጠብ፣ የጥላቻ እና የመናቆር መንፈስ ተቀርፎ ሁሉም ወደ በመተቃቀፍ ዕርቅ መፈፀሙ ከምንም በላይ ትልቅ ነገር እና የአከባቢው ገጽታ የሚገነባ መሆኑን አብራርተዋል።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ግንኙነት ኪታሞ በዚህን ወቅት ቀደም ሲል በአከባቢው ተከስተው የነበሩ ግጭቶቾ ህዝቡ ያልተገባ ዋጋ እንድከፍል እና ትልቅ የስነ ልቦና እና ቁሳዊ ክሳራዎችን እንድያልፍ ማድረግ መቻሉን አብራርተዋል።

ለግጭቶች መከሰት መንስኤ እየሆነ ያለው የተፈጥሮ ሀብቶች አጠቃቀም
ዙሪያ የሚስተዋሉ ችግሮች ሠላማዊ በሆነ መንገድ እልባት ላይ መድረስ እንድችሉ በልዩ ትኩረት መሰራቱንና በመሰራት ላይ እንዳለም ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

ቀደም ሲል በህዝቡ መካከል ተዘርተው የነበሩ የጥላቻ እና የተዛቡ ትርክቶች ህዝቡ እንድለያይ ምክንያት ሆኗል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ዛሬ ላይ ሁሉም የሠላም ጉዳይ ያገበኛል ብሎ በመነሳሳቱ ቀድሞ የነበሩ የአንድነትና የአብሮነት እሴቶችን ተመልሰው እንድጠገኑ ህዝቡ የጋራ ተግባቦቶችን በመፍጠሩ እነኝህን መልሶ መጠገን መቻሉንም ዋና አስተዳዳሪው በገለፃቸው አክለዋል።

ከአጎራባች ዞኖች ተሳታፊ የነበሩት የኧሌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሐርሻሎ አርካሌ እና የኮንሶ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ምክትል አፌ - ጉባኤ የሆኑት አቶ ገረመው አያኖ በየበኩላቸው ዛሬ በአከባቢው የተካሄደው ይህ ታላቂ ዕርቅ የመጨረሻ መቋጫ መሆን አለበት ብለዋል።

በአከባቢው የሚስተዋሉ ግጭቶች ማህበረሰቡን እንደማይወክል አበክረው የገለጹት አካላቱ አጎራባች ዞኖች የጀመሩትን የጋራ የሠላም ትስስርን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እንደዚሁ አመላክተዋል።

በኮንፍራንሱ ላይም የተጋጩ ሰዎች በይፋ በአደባባይ ላይ በመውጣት በፀፀት የይቅርታ እና የምህረት መርሃ - ግብሮችን አከናውነዋል።

በመጨረሻም ዕርቁ እንድፀና ባለ12 ነጥብ የአቋም መግለጫዎችን በማውጣት የዕለቱ መርሃ - ግብር በኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ፊፃሜውን ማግኘቴ ችሏል።
"ሠላም ለሁሉም ሁሉም ለሠላም"

የሠገን ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ሽግግር ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደካራት፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)የኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ሽግ...
03/09/2026

የሠገን ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ሽግግር ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ

ካራት፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

የኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ሽግግር ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል።

በጉባኤው ለምክር ቤቱ ቀርበው ከጸደቁ አጀንዳዎች መካከል የ8ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ፣ የ2018 ዓ.ም የምክር ቤቱ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የ2019 ዓ.ም የምክር ቤቱ ዕቅድ፣ የ2018 ዓ.ም የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ።

እንድሁም የ2019 ዓ.ም የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች ዕቅድ፣ የ2018 ዓ.ም የወረዳ ፍርድ ቤት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት፣ የ2019 ዓ.ም የወረዳ ፍርድ ቤት ዕቅድ እና የ2019 ዓ.ም ረቂቅ በጀት ይገኙበታል።

በጉባኤው የወረዳውን የግብርና አፈጻጸም በተመለከተም፣ በ2018 ዓ.ም የበልግ ምርት ወቅት በወረዳው 749,728.68 ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉ ተገልጿል።

በመጨረሻም የሠገን ዙሪያ ወረዳ ሕዝብ ሽግግር ምክር ቤት 7ኛ የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ፣ በ2019 ዓ.ም ረቂቅ አዋጅ ቁጥር 10 መሠረት 237,966,266 ብር (ሁለት መቶ ሠላሳ ሰባት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ ስድስት ብር) የ2019 ዓ.ም ዓመታዊ በጀት በምክር ቤቱ አባላት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

የርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መልዕክትካራት፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን) የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ወደ ተሟላ ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነት ለመሸጋገር የ...
03/09/2026

የርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ መልዕክት

ካራት፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ ወደ ተሟላ ሀገራዊ ክብርና ሉዓላዊነት ለመሸጋገር የተያዘው ሀገራዊ እና ክልላዊ ግብ፤ የሉዓላዊነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ከሰው ልጅ ህይወት ጋር የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ፤ በየደረጃው ያለው አመራር በክልሉ ለዚሁ ግብ ስኬት በመከናወን ላይ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ከተለምዷዊ አሰራሮች ወጣ ባለ መልኩ ብዝኃ ታታሪነትንና የተሟላ የአመራር ብቃትን ተላብሶ፤ በከፍተኛ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት በመምራት እና ሕዝባዊ ተሳትፎን ባረጋገጠ መልኩ በማስፈፀም በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ ከግብ ለማድረስ ከምን ጊዜውም በላይ የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ ይገባዋል፡፡

ለዚህ የሕዝባችንን ድንቅ የመተሳሰብና የመደጋገፍ እሴቶች በአግባቡ ተጠቅሞ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች፡- መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፤ የልማት ማህበራትና ድርጅቶች፤ የኃይማኖት ተቋማት፤ መንግስት ሠራተኛውንና የንግዱን ህብረተሰብ፤ አርሶና አርብቶ አደሩን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በንቅናቄ በማሳተፍ ተግባራትን በጠንካራ ተቋማዊ ማዕቀፍ አልቆ በመፈፀምና በማስፈፀም ለውጤት ማብቃት ያስፈልጋል፡፡

ለተሻለ ነገ ዛሬን በኅብረት እንትጋ!!
ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር

ለተማሪዎች ዉጤታማነት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በጥናትና ምርምር በመለየት ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ  ካራት፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒ...
03/09/2026

ለተማሪዎች ዉጤታማነት ማነቆ የሆኑ ችግሮችን በጥናትና ምርምር በመለየት ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ የምክክር መድረክ ተካሄደ

ካራት፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ/ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

ከትምህርት ስብራቶች አንዱ የሆነውን የተማሪዎች ውጤታማነት ችግር ለመቅረፍ፤ በጥናት የተደገፈ የመፍትሄ ሀሳብ ለማመንጨት ያለመ የክልሉ ትምህርት ቢሮ እና የአቅም ግንባታና ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በክልሉ የሚገኙ ዩንቨርሲቲዎችን እና የመምህራን ማ/ኮሌጆች ያሳተፈ የጋራ የምክክር መድረክ በወላይታ ሶዶ ከተማ ተካሂዷል።

ውይይቱ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በክልሉ እንደ ሀገር ያጋጠመን የትምህርት ስብራት ችግር ለመፍታት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን በማሳደግ የተማሪዎች ውጤታማነትን ለማረጋገጥ በመደረግ ላይ ያለው ተከታታይ ጥረት አካል በጥናት ላይ የተመሰረት መፍትሄ ለማበጀት ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት የተካደ ነው፡፡

በውይይቱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዮት ደምሴ፤ መንግስት እንደ ሀገር ያጋጠመን የትምህርት ስብራት ለመጠገን የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን ጨምሮ የተለያዩ ሪፎርሞችን በማድረግ መሻሻሎችን በማሳያት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በትምህርት ስራው ላይ ክፍተት መኖሩን የተማሪዎች የማጠቃለያ የፈተና ውጤት ማሳያ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው፤ ባለፉት ጊዜያት በተካሄዱ የ6ኛ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ክልላዊና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የተማሪዎች ውጤት መሻሻሎች ቢኖሩትም በሚጠበቀው ልክ ባለመሆኑ ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችል የጥናት እና ምርምር ስራ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አብራርተዋል።

አክለው ከታችኛው ዕርከን ጀምሮ በትምህርት ላይ የሚስተዋሉ ህፀፆችን በመለየት እና በጥናትና ምርምር ላይ የተመሰረተ የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ ችግሩን በዘላቂነት መቅረፍ ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ አጥኚ ቡድን መቋቋሙንም አስረድተዋል።

ጥናቱን በክልሉ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎችና የክልሉ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲውት ተመራማሪዎች በጋራ የሚያደርጉት ሲሆን፤ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ትምህርት ቢሮ በጋራ አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ የሚያደርጉ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪና የአማካሪዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ቦሻ ቦንቤ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የክልሉ መንግስት የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የጥናት ቡድን ተቋቁሞ ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣታ መታቀዱን ተናግረዋል።

የጥናቱ ዋና ዓላማ የተማሪዎች ክልላዊና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች የዉጤታማነት ተግዳሮቶችን በመለየት፣ የትምህርት ጥራትን እና የተማሪዎችን አፈፃፀም ለማሻሻል የሚያስችሉ ተግባራዊ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ልዩ አማካሪው አጥኚ ቡድኑ ችግሩን ሳይንሳዊ በሆነ አግባብ አሳታፊ እና አካታች የጥናት መንገዶችን በመከተል ለውጤት መትጋት እንደሚገባውም አፅኖት ሰጥተዋል።

ጥናቱ በአፋጣኝ ተጠናቆ በ2019 የትምህርት ዘመን ለመፍትሄው ወደ ተግባራዊ ስራ መግባት እንዲቻል የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን እገዛ እና ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑንም ገልፀዋል።

የአቅም ግንባታና ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይረክተር ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ትምህርት የአንድ ሀገር አጠቃላይ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገት መሰረት እንዲሁም የሰው ሀይል ልማት ዋና መሳርያ በመሆኑ ለውጤታማነቱ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ትብብር የሚሻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የችግሩን መንስኤዎች በሳይንሳዊ ጥናት እና ምርምር በመለየት የመፍትሔ እርምጃዎችን መውሰድ ቁልፍ መሆኑንም ጠቅሰው፤ ለዚህ የክልሉ መንግስት ያሳየውን ቁርጠኝነት አድንቀዋል፡፡

የታቀደውን ጥናት ሳይንሳዊ የጥናት ስልቶችን በመጠቀም ከፍ ባለ አግባብ መስራት እንደሚያስፈልግም አክለዋል፡፡

የክልሉ መንግስት ለማህበራዊ ብልጽግና ትልም ስኬት መሠረት ለሆነው የትምህርት ዘርፍ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለዘርፉ ውጤታማነት የህብረተሰብን ተሳትፎ እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ትብብርና ቅንጅትን ባረጋገጠ መልኩ በትኩረት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

"በጎነት በተግባር ስገለጥ የተቸገሩ ወገኖችን ቶሎ ከችግር ለማላቀቅ ያግዛል" ዶ/ር ቦጋለ ቦሼ         ካራት:ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢ...
03/09/2026

"በጎነት በተግባር ስገለጥ የተቸገሩ ወገኖችን ቶሎ ከችግር ለማላቀቅ ያግዛል" ዶ/ር ቦጋለ ቦሼ

ካራት:ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቦጋለ ቦሼ የተመራ ልዑክ፣ በኮንሶ ዞን ኮልሜ ወረዳ በመገኘት ለአንድ አቅመ ደካማ ወገን የሚገነባ ቤት ግንባታን አስጀመሩ።

የክልሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቦጋለ ቦሼን ጨምሮ የቢሮው የማኔጅመንት አባላት እና በየደረጃ ያሉ የዞንና የኮልሜ ወረዳ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን፣ በወረዳው ማዕከል በደልቤና ለሚገነባው ቤት የሚያስፈልጉ የፋብሪካ ውጤቶችንና ሌሎች የግንባታ ግብዓቶችን በማቅረብ ግንባታውን በይፋ አስጀምረዋል።

“በጎ ተግባር በተግባር መገለጥ አለበት ያሉት ዶ/ር ቦጋለ ቦሼ በግንባታ ሥፍራው ሆኖ እንደገለጹት፣ "የተጀመረው ሥራ ከማህበራዊ ኃላፊነት አንፃር ከፍተኛ ትርጉም ያለው በጎ ተግባር በመሆኑ ለሥራው በተለየ ትኩረትና በተቀናጀ መልኩ መሥራት ይገባል።

“እየሠራን ያለነው ተግባር በጎ ተግባር መሆኑን ከግንዛቤ ወስደን ለሥራው ከፍተኛ ትኩረት መስጠት አለብን ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው ግንባታ ያለውን ግለት በመጠበቅ በአፋጣኝ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ ያቀረቡት ዶ/ር ቦጋለ፣ ቤቱ በ15 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቆ ለተጠቃሚው እንዲደርስ አስፈላጊው ርብርብ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

ቤቱ በብሎኬት የሚገነባ ሲሆን፣ ለግንባታው የሚያስፈልጉ የፋብሪካ ውጤቶችና ሌሎች ግብዓቶች ተጓጉዘው ወደ ሥፍራው እንዲደርሱ ተደርጓል።

ይህም ግንባታው በተቀመጠለት አጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ያመላክታል።

ዶ/ር ቦጋለ እንዳስገነዘቡት፣ የቤቱ ግንባታ ፍጥነት ብቻ ሳይሆን ጥራትን ጠብቆ መገንባት እኩል ትኩረት የሚሻ ጉዳይ ነው። ቤቱ አራት ክፍሎች የሚኖሩት ሲሆን፣ በኮንክሪትና በጥራት እንዲገነባ ተገቢው ትኩረት እንዲሰጠውም አሳስበዋል።

በጎነት በበጀት ብቻ አይለካም ያሉት ዶ/ር ቦጋለ "ለዚህ የበጎ ተግባር ሥራ በተለይ የተመደበ በጀት ባይኖርም፣ በተቀናጀ የሰው ኃይል፣ የቁሳቁስና የሎጂስቲክ አቅም በመጠቀም ሥራውን ማሳካት ይቻላል።

በክልሉ ደረጃ በርካታ የበጎ ተግባር ቤት ግንባታዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ከተያዙት 70 ቤቶች ውስጥ ሁለቱ በኮልሜ ወረዳ እንደሚገነቡ ገልጸው “ይህ በጎ ሥራ ነው፤ የአቅማችንን ሁሉ አዋጥተን መሥራት ይጠበቅብናል።”

በመሆኑም በኮልሜ ወረዳ የተጀመረው ይህ የቤት ግንባታ ከአንድ ቤት ግንባታ በላይ፣ በጎነትን በተግባር የሚያሳይ፣ ማህበራዊ ኃላፊነትን የሚያጎለብትና ተባብሮ መሥራት የሚችልበትን አቅም የሚያሳይ ተግባራዊ ምሳሌ ሆኖ ተጀምሯል።

በ15 ቀናት ውስጥ በጥራት ተጠናቆ የአንድ ወገንን ኑሮ የሚያሻሽል ቤት ለተጠቃሚው ማስረከብ ፤ የዛሬው ግንባታ ዋና ግብ ነው" ሲሉ ሐሳባቸውን አቅርበዋል ።

በአጠቃላይ በማስጀመሪያው የተገኙት የወረዳው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች የክልሉ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ያደረጉትን በጎ ሥራና ድጋፍ አመስግነዋል ስል ኮልሜ ወረዳ መንግሥት ኮሙኑኬሽን አገልግሎት ዘግቧል።

‎የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካራት ቅርንጫፍ ከኮንሶ ዞን ግብርና መምሪያ ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ፣ ‎ካራት:ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)‎‎የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካራት...
03/09/2026

‎የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካራት ቅርንጫፍ ከኮንሶ ዞን ግብርና መምሪያ ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ፣

‎ካራት:ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

‎የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካራት ቅርንጫፍ ከዞኑ ግብርና መምሪያ ጋር የዲጂታል ቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ለማቅረብ የውል ስምምነት ተፈራርመዋል።

‎ይህ የዲጂታል ቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ውል ስምምነት የመፈራረሙ ዓላማዎች ድርጅቱ የሰራተኞቹን የፋይናንስ ፍላጎት ለሟሟላት በባንኩ የሚስጠውን ዲጂታል ቁጠባና ብድር አገልግሎት ለሰራተኞቹ ለማመቻቸት ፍላጎት ያለው መሆኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካራት ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ አቶ ኦርካይዶ ኩሴ ገልጸዋል።

‎ስራ አስኪያጁ አቶ ኦርካይዶ አክለውም ባንኩ እንዲህ ያሉትን የዲጂታል ቁጠባና ብድር አገልግሎቶች ለማቅረብ የሚያስችል እውቀትና የፋይናንስ አቅም ያለው በመሆኑ በዚህ ውስጥ ባሉት ውሎች እና ሁኔታዎች ላይ በጋራ በመስማማት፣ተዋዋይ ወገኖች በስምምነት እንደሚሰሩም ጠቅሰዋል።

‎የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ጉራሾ ጎስኬ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካራት ቅርንጫፍ ያመቻቸው የዲጂታል ቁጠባ እና ብድር አገልግሎት ለሠራተኞች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው የገለጹ ሲሆን በብድር አቅርቦት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራልም ብለዋል።

የኮንሶ ዞን አስተዳደር በጋሞ ዞን በሚከበረው “ዮ ማስቃላ” በዓል ላይ ለመታደም የቀረበለትን ጥሪ ተቀበለካራት፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)የኮንሶ ዞን አስተዳደር በጋሞ...
03/09/2026

የኮንሶ ዞን አስተዳደር በጋሞ ዞን በሚከበረው “ዮ ማስቃላ” በዓል ላይ ለመታደም የቀረበለትን ጥሪ ተቀበለ

ካራት፦ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

የኮንሶ ዞን አስተዳደር በጋሞ ዞን በሚከበረው “ዮ ማስቃላ” የጋሞ ዘመን መለወጫ በዓል ላይ እንዲታደም ከጋሞ ዞን አስተዳደር የቀረበለትን ጥሪ ተቀበለ።

ጥሪውን የተቀበሉት የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ገለቦ ጎልቶሞ እና የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ግርማ በሌ ሲሆኑ፣ ለመላው የጋሞ ዞን ሕዝብ እንኳን ለ“ዮ ማስቃላ” በዓል በሰላም አደረሳችሁ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

“ዮ ማስቃላ” የጋሞ ሕዝብ የዘመን መለወጫ ባህላዊ በዓል ሲሆን፣ በዓሉ መስከረም 12/2019 ዓ.ም እንደሚከበር ተገልጿል።

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ አያያዝ ላይ የተፈጠረው ግንዛቤ የግብር አሰባሰብን ከማሳለጥ ባለፈ ግብር ከፋዮችን ከአላስፈላጊ ቅጣትና ወንጀል ይታደጋል – አቶ ካቱሳ ካቢሌካራት፣ ነሐሴ 28/201...
03/09/2026

የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ አያያዝ ላይ የተፈጠረው ግንዛቤ የግብር አሰባሰብን ከማሳለጥ ባለፈ ግብር ከፋዮችን ከአላስፈላጊ ቅጣትና ወንጀል ይታደጋል – አቶ ካቱሳ ካቢሌ

ካራት፣ ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

የኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ ለደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ አያያዝና አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና መስጠቱን የዞኑ ገቢዎች መምሪያ የታክስ ሥርዓት አስተባባሪ አቶ ካቱሳ ካቢሌ ገለጹ።

የኮንሶ ዞን ገቢዎች መምሪያ የታክስ ሥርዓት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቶ ካቱሳ ካቢሌ በሥልጠናው ወቅት እንደገለጹት፣ ግብር ከፋዮች የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያውን በሚመችና በግልጽ በሚታይ ቦታ በማስቀመጥ በሚያከናውኑት የሽያጭ ሂደት በአግባቡ መጠቀም ይገባቸዋል።

ይህም የገቢና ወጪ መዝገብ አያያዝን በማሳለጥ የንግድ ሥራን በተሻለ ሁኔታ ለማከናወን እንደሚያግዝ አቶ ካቱሳ አስገንዝበዋል።

መምሪያው የQR ደረሰኝ አሰጣጥ ሥርዓትን በመጠቀም ዘመናዊ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የሽያጭ ሂደትን ለማስፋፋት አዲስ የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ለገዙ የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች ሥልጠናውን ማዘጋጀቱንም ገልጸዋል።

ሥልጠናው ከአርባ ምንጭ ንግድና ኢንቨስትመንት ኃ.የተ.የግል ማኅበር የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ግብረ ኃይል ጋር በመተባበር መዘጋጀቱን አቶ ካቱሳ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ለነባር ግብር ከፋዮች የመሣሪያ እድሳትና ጥገና ሥራዎችን ከማከናወን ባለፈ በመሣሪያው አጠቃቀምና በግብር ሥርዓት ዙሪያ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሠራቱ ተገልጿል።

በሥልጠናው ከከተማ አስተዳደርና ከወረዳ መዋቅሮች የተውጣጡ የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች የተሳተፉ ስሆን ፣ሥልጠናውም የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያን በአግባቡ ስለመያዝና ስለመጠቀም ሰፊ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ሰልጣኞች ገልጸዋል።

ግብር መክፈል የዜግነት ግዴታ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ካቱሳ፣ ግብርን በወቅቱና በታማኝነት መክፈል የሥልጡን ማኅበረሰብ መገለጫ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በመሆኑም በሒሳብና በመዝገብ አያያዝ ላይ በሥልጠናው የተፈጠረው ግንዛቤ ለመንግሥት የሚከፈለው ግብርና ታክስ ሳይስተጓጎል እንዲሰበሰብ ከማገዝ ባለፈ፣ ግብር ከፋዮች በአላስፈላጊ ቅጣትና የሕግ ተጠያቂነት እንዳይጋለጡ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል።

ሥልጠናውን የንግድና ኢንቨስትመንት ኩባንያ ኃ.የተ.የግል ማህበር አርባምንጭ ማዕከል የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ቴክኒሻን አቶ አማኑኤል አላያ በመሣሪያው አያያዝ እና አጠቃቀም አሰጣጥ ላይ ሰፊ ማብራሪያ እና ግንዛቤ ሰጥተዋል።

አቶ ካቱሳ በመጨረሻም፣ ግብር ከፋዮች በሥልጠናው የተሰጣቸውን ግንዛቤ በተግባር በመተርጎም የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያዎቻቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ አሳስበዋል።

‎የስራ ዕድል መፍጠር የዳቦ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገር ግንባታ ህልውና ጉዳይም ነው -አቶ ስምኦን ገልገሎ‎‎ካራት:ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)‎‎የኮንሶ ዞን ስራና ክህሎ...
03/09/2026

‎የስራ ዕድል መፍጠር የዳቦ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገር ግንባታ ህልውና ጉዳይም ነው -አቶ ስምኦን ገልገሎ

‎ካራት:ነሐሴ 28/2018 ዓ.ም (ኮንሶ ዞን ኮሙኒኬሽን)

‎የኮንሶ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ለወረዳዎችና ለከተማ አስተዳደር ባለሙያዎች የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ የክህሎት ስልጠና መስጠት ጀመረ፣

‎መምሪያው ለወረዳዎችና ለከተማ አስተዳደር ባለሙያዎች የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ የክህሎት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

‎በስልጠና መድረኩ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ የዞኑ ስራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ስምኦን ገልገሎ እንደገለጹት የስራ ዕድል መፍጠር የዳቦ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገር ግንባታ ህልውና ጉዳይም ነው ሲሉ አሳስበዋል።

‎ክህሎት የሁሉም ስኬት መሠረት ሲሆን የሚፈጠሩ የስራ ዕድሎች ክህሎትን መሠረት ሊያደርጉ ይገባል ያሉት አቶ ስምኦን፤ያለ በቂ ክህሎት በዘርፉ ውጤት ሊመጣ ስለማይችል የስልጠና መድረኩ በክህሎት የዳበረ ስራ ፈጣሪ ባለሙያን ለመፍጠርና የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ የታለመ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‎የሚደራጁ ኢንተርፕራይዞች ከፋይዳ እና ከELMIS ምዝገባ ጋር በማስተሳሰር ከስልጠናው የሚናገኘው የክህሎት እውቀትን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማቀናጀት የዕሴት ሰንሰለታቸው የተጠበቁ ኢንተርፕራይዞችን ለመፍጠር መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል።

‎በስራ ዕድል ፈጠራ አዲሱ ዕሳቤ ዙሪያ የተዘጋጀ የክህሎት ስልጠና ሰነድ እየቀረበ የሚገኝ ሲሆን መምሪያ በሚኖረው የስልጠና ጊዜ በተለያዩ የስልጠና ርዕሶች ሰነዶች የሚቀርቡ ሲሆን በነገው ዕለት ደግሞ የ2019 በጀት ዓመት የ2 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ይገመግማል ተብሎም ይጠበቃል።

Address

Main Road
Konso
P.BOX33

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Konso Zone Government Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Konso Zone Government Communication:

Shortcuts

Share