24/08/2026
የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ የወቅታዊ ክስተት አስተዳደር ሥርዓት /IMS/ ተግባራት ግምገማ አካሄደ፤
በመድረኩ የIMS ተግባራት ሪፖርት ያቀረቡት የእናቶችና ሕፃናት ጤናና ሥርዓተ ምግብ ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ በርሻ ጎሣያ የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ በመዋቅሮች በመለየት አቅርበዋል፡፡
አቶ በርሻ ባቀረቡት ሪፖርት የታዩ ጠንካራ ጎኖች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለባቸው እና የተለዩ ዋና ዋና ማነቆዎች ላይ በየደረጃው ትኩረት ተሰጥቶ መመራት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡ የሪፖርት ሙሉዕነት እና ወቅታዊነት ላይ ክፍተቶች እንዳሉና ሊታረም እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የተለያዩ የክትትልና ግምገማ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ አሠራሮችን በታችኛው መዋቅር መስመር ማስያዝ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል፡፡ ችግር ያለባቸውን አከባቢዎች በዝርዝር በመለየት ምላሽ የሚሹ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባትን በመፍጠር የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባልም ተብሏል፡፡
የጤና መምሪያው ምክትል መምሪያ ኃላፊ አቶ አራርሶ ጋሮ በማጠቃለያው የወባ መከላከል ተግባራትን ጨምሮ የሥርዓተ ምግብ ሊየታውን በሚገባ የተለትርጉም ሰጥቶ መምራት ይፈልጋል ብለዋል፡፡
የጤናው ሴክተር ከሚከውናቸው የመከላከል ተግባራት በተጨማሪ የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሥራት የሕብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ላይ የምክክርና የውይይት መድረኮችን በሕብረተሰቡ ውስጥ በመፍጠር ሊሠራ እንደሚገባ አቶ አራርሶ አስገንዝበዋል፡፡
የኮንሶ ዞን ጤና መምሪያ
Telegram; https://t.me/konsohealth
Facebook; https://www.facebook.com/profile.php?id=61550645678671
WhatsApp; https://whatsapp.com/channe/0029VbBfsnD2phHOw0LeHd1m
E-mail; [email protected]