መቅደላ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Masha
  • መቅደላ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

መቅደላ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ሰለመቅደላ ወረዳ ስላሉ ከተሞች ያለወትን አስተያየት በውስጥ መስመር ያጋሩን አጋዥ ይሁኑ..

‎"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"‎‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ግንባታው በቅርቡ ተጠናቆ ለአ...
07/09/2026

‎"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"

‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ግንባታው በቅርቡ ተጠናቆ ለአቅመደካሞች ቤት ለማስተላለፍ ሌት ተቀን እየሰራን እንገኛለን።
‎ጳጉሜን 2 "የማንሰራራት ቀን

‎"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"‎‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።‎‎ነሀሴ 27/2018ዓ.ም
02/09/2026

‎"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"

‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

‎ነሀሴ 27/2018ዓ.ም

በመቅደላ ወረዳ የክረምት የዜጎች በጎ ፍቃድ አብይ ኮሚቴ አባላት በክረምት በጎ ፍቃድ እየተሰራ የሚገኘዉን አድስ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ስራ ጎበኙ።በማሻ ከተማ በክረምት የዜጎች በጎ ፍቃ...
12/08/2026

በመቅደላ ወረዳ የክረምት የዜጎች በጎ ፍቃድ አብይ ኮሚቴ አባላት በክረምት በጎ ፍቃድ እየተሰራ የሚገኘዉን አድስ የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ስራ ጎበኙ።

በማሻ ከተማ በክረምት የዜጎች በጎ ፍቃድ ተሳታፊወች እና በማሻ መሪ ማዘጋጃ ቤት እየተገነባ ያለዉ የአቅመ ደካሞች ቤት ያለበት ደረጃ ተጎብኝቷል።

በጉብኝቱ የዜጎች በጎ ፍቃድ አብይ ኮሚቴ አባላት ተገኝተዋል።

‎"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"‎‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።‎‎
05/08/2026

‎"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"

‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የክረምት የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

 #በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ🇪🇹የመቅደላ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ጽ/ቤት ለአቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ የሚዉል የ67 ሽህ ብር ድጋፍ አደረገ።የወረዳዉ መንገድ ትራንስፖርትና ሎ...
30/07/2026

#በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ🇪🇹
የመቅደላ ወረዳ መንገድ ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክ ጽ/ቤት ለአቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ የሚዉል የ67 ሽህ ብር ድጋፍ አደረገ።

የወረዳዉ መንገድ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክ ጽ/ቤት የትራ/አገ/አቅ/ስምሪት ቡድን መሪ አቶ ሙሀመድ አህመድ እና የስምሪት ባለሙያዉ አቶ ጀማል አያሌዉ እንደገለጹት የመለስተኛ የህዝብ ማመላለሻ ባለንብረቶች ማህበርን በማስተባበር ለክረምት የዜጎች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ ስራ የሚዉል 67 ሽህ ብር በማሰባሰብ የግንባታ ሂደቱን ለሚያስተባብሩ የወረዳ አመራሮች ለወ/ሮ መኪያ መሀመድ እና አቶ አህመድ መሀመድ አስረክበዋል።

የወረዳዉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሉልሰገድ አድማሱ፣ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ይመር አመደና የመቅደላ ወረዳ ምክርቤት አፈ ጉባኤ አቶ ቁምላቸዉ ይማም ቦታዉ በመገኘት የግንባታ ሂደቱን ጎብኝተዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ "በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል የክረምት ወራት የዜጎች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ከተሞች ውብ፣ ፅዱ ለኖሪዎች ምቹ የመኖርያ አካባቢ የማጽ...
26/07/2026

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ "በጎነትና አብሮነት ለኢትዮጵያ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል የክረምት ወራት የዜጎች በጎ ፍቃድ አገልግሎት ከተሞች ውብ፣ ፅዱ ለኖሪዎች ምቹ የመኖርያ አካባቢ የማጽዳት ዘመቻ በየኮሶ ታዳጊ ከተማ እና አደጉያ ታዳጊ ከተማበተለያዬ ከተሞች የቦይ ጠረጋ፣ የከተማ የወበት ዛፍ ተከላ ተካሂዷል።

‎"ከህልም ወደ እውን" - በመቅደላ ወረዳ የ"ጽዱ ተቋም" እና የጤና አገልግሎት ስኬት በደማቅ ሁኔታ ተመረቀ! ‎‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ስር በሚገኙ 5 ጤና ጣቢያዎች በ...
19/07/2026

‎"ከህልም ወደ እውን" - በመቅደላ ወረዳ የ"ጽዱ ተቋም" እና የጤና አገልግሎት ስኬት በደማቅ ሁኔታ ተመረቀ!

‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ስር በሚገኙ 5 ጤና ጣቢያዎች በዋሽፊት (WASH FIT) ቴክኖሎጂ እና መለኪያ የተሰሩ የ"ጽዱ ተቋም" ግንባታዎች እና ማሻሻያዎች ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተመርቀዋል። የጤና ተቋማት ማህበረሰቡን ለማከም የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ፈጥረው ታይተዋል።

‎የመርሀ ግብሩ ዋና ዋና ትኩረቶች ይህንን ይመስሉ ነበር፦

‎ "ጽዱ ተቋም ለእኛ ህንፃ ቀለም መቀባት ብቻ አይደለም" - አቶ እንዳልካቸው አረጋ (የመቅደላ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ) አስተዳዳሪው በንግግራቸው፤ ሀገራዊውን የ"ጽዱ ኢትዮጵያ" ንቅናቄ መሰረት በማድረግ የተሰራው ይህ ፕሮጀክት፡
‎👉 ለታካሚው ምቾት፡ ከመድሃኒት ባልተናነሰ ስነ-ልቦናዊ እፎይታን የሚሰጥ አካባቢ መፍጠሩን፣
‎ 👉 ከበሽታ ነጻ መሆን፡ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን በማዘመን ተላላፊ በሽታዎችን መከላከል መቻሉን፣ እና
👉 "በራስ አቅም መስራት ይቻላል" የሚለውን መርህ
‎በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን አብራርተዋል።

‎የማህበረሰብ ተሳትፎ እና የፋይናንስ አፈጻጸም - አቶ እብራሂም አባቡ (የመቅደላ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ) ለዚህ ግዙፍ የጤና ተቋማት ማሻሻያ ፕሮጀክት በአጠቃላይ 18.5 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 1.5 ሚሊዮን ብሩ በማህበረሰቡ በማህበረሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ የተሸፈነ ነው። በአገልግሎት ጥራት በኩልም አስደሳች ስኬቶች ተመዝግበዋል፡
‎ በ2 ሚሊዮን ብር ካፒታል የተጀመረው የማህበረሰብ አቀፍ መድሃኒት ቤት ካፒታሉን ከ 3.6 ሚሊዮን ብር በላይ አድርሷል።
‎ ከሰኔ 2017 እስከ ሰኔ 2018 ብቻ ከ21,000 በላይ ተገልጋዮች የህክምና አገልግሎት ያገኙ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ 90% የሚሆኑት የጤና መድህን ተጠቃሚዎች ናቸው።

‎ ዲጂታላይዜሽን - አቶ ጌታቸው (የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ) የመምሪያ ኃላፊው የመቅደላ ወረዳ ስራ ለሌሎች ወረዳዎች ምርጥ ተሞክሮ (Model) የሚሆን መሆኑን አድንቀው፤ በቀጣይ የጤና አገልግሎቱን ወደ ዲጂታል አሰራር በማሳደግ (Digitalization) ላይ ትኩረት ተደርጎ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

‎ በዚህ የለውጥ ስራ ምረቃ ላይ፤ የደቡብ ወሎ ዞን ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ም/ኃላፊ አቶ ይበልጣል፣የአገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢሳያስ፣ የሴቶች ክንፍ ኃላፊ ወ/ሮ የሻረግ ሰይድ፣ የወጣት ክንፍ ኃላፊ አቶ ታምራትን ጨምሮ የወረዳው አስተባባሪዎች፣ የሌሎች ወረዳ አስተባባሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።


‎ #ጽዱተቋም #ጤናችንለሀገራችን
Ethiopia

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"‎🙏🙏🙏🙏‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ   የማሻ ከተማ ነጋዴ ዎች በበጎ ፍቃድ  ማሻ ከተማ  እየተገነባ  ለሚገኘው    የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ጎብኝት  በማድ...
18/07/2026

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"

🙏🙏🙏🙏‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የማሻ ከተማ ነጋዴ ዎች በበጎ ፍቃድ ማሻ ከተማ እየተገነባ ለሚገኘው የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ ጎብኝት በማድረግ 60,000(ስልሳ ሽህ)ብር ድጋፍ አደርገዋል።

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"‎‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ 02 ቀበሌ በበጎ ፍቃድ  ማሻ ከተማ  እየተገነባ  ለሚገኘው    የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ  700 ፍልጥ  ድጋፍ  አደረገ።
17/07/2026

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"

‎በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ 02 ቀበሌ በበጎ ፍቃድ ማሻ ከተማ እየተገነባ ለሚገኘው የአቅመ ደካሞች ቤት ግንባታ 700 ፍልጥ ድጋፍ አደረገ።

በጎነት በክረምት የመቅደላ ወረዳ ከተማና መሠረተ ልማት የሚያስገነባውን የክረምት ስራ ተገኝተን በጎነት ቀጥሎ 15 ደካሞች ሠርቶ ቤት ለማስገባት በወረዳ ና በህዝብ ደረጃ እየተደረገ ያለው በጣ...
16/07/2026

በጎነት በክረምት
የመቅደላ ወረዳ ከተማና መሠረተ ልማት የሚያስገነባውን የክረምት ስራ ተገኝተን በጎነት ቀጥሎ 15 ደካሞች ሠርቶ ቤት ለማስገባት በወረዳ ና በህዝብ ደረጃ እየተደረገ ያለው በጣም ደስ የሚል ሆኖ በዕለቱም #አቶ ደባልቄ ሙሀመድ ለደካሞቹ መስሪያ #10000 ብር ለመስጠት ቃል ገብቷል ሁሉንም ሰው ርብርብ ይጠይቃል።
በተጨማሪ የወረዳው ፖርቲ ፅ/ቤት አቶ ተስፋየ ወዶኝ የበጎ ተግባሩ አስተባባሪ ና አመራሮቻቸውን ይዘው ህዝብም ተቀናጅቶ በጋራ ደግነት ነገ ለወገን የሚሆን ተግባር ስናከናውን አርፍደናል።
በጎነቱ ይቀጥላል __________
አካባቢያችን በተባበረ ክንድ ደግነትን እናብዛ

Address

Wollo Mekdela
Masha

Telephone

+251914357346

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when መቅደላ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share