27/03/2023
የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገቢ ፅ/ቤት "ዘመቻ ገቢ"በሚል ስያሜ ከመጋቢት 1 እስከ15 ያደረገውን የተቀናጀ ገቢ የመሰብሰብ እንቅስቃሴ ያመጣውን ውጤት ገመገመ
የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገቢ ፅ/ቤት የገቢ አፈፃፀሙን ለማሳደግ ከተለመደው አሰራር በተለየ መንገድ አመራሩን ፣ባለሙያውን ፣አጋርና ባለድርሻ አካላትን ሊያሳትፍ የሚችል የንቅናቄ እቅድ በማቀድና ለአመራሩ አቅርቦ እውቅና በማሰጠት በእቅዱ መሰረት ለ15 ቀን የተቀናጀ ተግባራትን አከናውኗል፡፡ በ15 ቀኑ በተከናወነው የንቅናቄ ስራ የተፈፀሙ ተግባራትና የተገኘውን ውጤት በአመራሩ እንዲሁም በተቋሙ ማኔጅመንት ተገምግሟል፡፡በግምገማውም የተነሱ ሀሳቦች፡-
በቅድመ ስምሪት የተከናወኑ ተግባራት
የንቅናቄ እቅድ በማዘጋጀት አመራሩ የጋራ እንዲያድገው ተደርጓል፡፡
ማህበረሰቡ እውቅና እንዲኖረው ለግማሽ ቀን በሞንታርቦ ቅስቀሳ ተደርጓል እንዲሁም ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ዋናዋና ቦታዎች ማስታወቂያዎችንና ቀስቃሽ ሞቶዎችን በመለጠፍ መረጃው ለማህበረሰቡ ተደራሽ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
ከባለሙያዎች፤ከማኔጅመንት አባላት ከአጋር ሴክተሮች የተውጣጣ ቡድን በሁለት ቀጠና በመመደብ ስምሪት በመስጠት ወደስራ ተገብቷል፡፡
ገቢ ሊገኝባቸው የሚችሉ አርእስቶች ተለይተው ቼክሊስት በማዘጋጀት ወደ እንቅስቃሴ ተገብቷል፡፡
በስምሪት ወቅት የተከናወኑ ተግባራት
• ውዝፍ የፈጠረ አንድ ግብር ከፋይ ላይ ሀብት የማስከበር ስራ በመስራት ያልተከፈለው ግብር ውስጥ በውለታ ቅድሚያ ክፍያ 80,000 እንዲከፈል ማድረግ ተችሏል
• የልዩነት ውሳኔ ተወስኖ ካለከፈሉ 3 ግብር ከፋዮች 2 እንዲከፍሉ ማድረግ ተችሏል፡፡
• የሊዝ ውዝፍ ካልከፈሉ 184,656 ብር ገቢ ተደርጓል፡፡
• የአገልግሎት ክፍያ ያልከፈሉ 48 ግብር ከፋዮች ማስከፈል ተችሏል ፡፡
• ታክስ ካጭበረበረ አንድ ግብር ከፋይ ተከታትሎ 237,000 ብር ማስከፈል ተችሏል፡፡
• ዳግም ውሳኔ ከተወሰነባቸው 35 ግብር ከፋዮች 270,200.07ብር ማስከፈል ተችሏል፡፡
• የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮችን መረጃ በየቀበሌው የማጥራት፣አዳዲስ ግብር ከፋዮችን የመለየት ስራ ተከነውኗል፡፡
በተከናወኑ ተግባራት የተሰበሰበ አጠቃላይ ገቢ
መደበኛ ገቢ
• ከስምሪት በፊት የተሰበሰበ 19,360,348 በ15 ቀኑ የገባ 1,797,793.48 እስከ መጋቢት 15 የተደረሰበት 21,158,141.48
የአገልግሎት ገቢ
• ከስምሪት በፊት የተሰበሰበ 16,081,528.06 በ15 ቀኑ የገባ 345,439.9 እስከ መጋቢት 15 የተደረሰበት16,426,967.96
ጠቅላላ ገቢ
• ከስምሪት በፊት የተሰበሰበ 35,441,876.06 በ15 ቀኑ የገባ 2,143,233.38 መጋቢት 15 የተደረሰበት 37,585,109.44 በመሰብሰብ አፈፃፀሙን 98.3% ማድረስ ተችሏል፡፡
በአጠቃላይ የገቢ ተቋሙ ያደረገው የተቀናጀ እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን ተግባሩ እንዲሳካ ያስተባበሩ በእንቅስቃሴው ለተሳተፉ ሰራተኞች ምስጋና እያቀረበ በቀሪ ወራትም የታቀደውን እቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የተጀመረውን እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ፅ/ቤት ግ/ት/ኮ/ዋ/የስራ ሂደት
መጋቢት18/2015
መ/ሜዳ