Menz Gera Council Office

Menz Gera Council Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Menz Gera Council Office, Government Organization, Mehalmeda Showa, Mehal Meda.

03/08/2023
03/08/2023

ሁሉም በየአካባቢው ያለውን ትንኮሳ በአስቸኳይ በማስቆም ወደ ሰላማዊ ውይይትና ምክክር እንዲመለስ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ጥሪ አቀረቡ።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) በመግለጫቸው ስለሰላም አማራጭ ያነሷቸው ነጥቦች፦

የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ ያለውን ችግር በሰላምና በውይይት ለመፍታት አሁን መረባረብ ይገባል፡፡

የክልሉ የፀጥታ ችግር መንስኤ የኾኑትን በውይይት መፍታት አለብን ብለን በተደጋጋሚ ተናግረናል ብለዋል።

የሰላም ጉዳይ በክልሉ ምክር ቤትም አቋም ተወስዶ ተመራጮች i በመሄድ ውይይት እያደረጉ መኾናቸውንም ገልጸዋል፡፡

ማንኛውም ችግር በውይይት እና በሰላማዊ መንገድ ቢፈታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ሰብዓዊ ኪሳራን ማስቀረት ይቻላል ነው ያሉት፡፡

የሰላም ዋጋው ከፍተኛ ስለኾነ ሁሉም ጥያቄ አለኝ የሚል ወገን ሁሉ ያለምንም ገደብ በየደረጃው እየተወያየ ችግሩን ለመፍታት መረባረብ ይገባል ፡፡

ከውይይት ውጭ ያለው ሂደት ክልላዊ ኪሳራ ከማምጣት ውጭ መፍትሔ እንደማያመጣም ተናግረዋል፡፡

ሁሉም ልዩነት ያለው አካል ነፍጡን አስቀምጦ ወደ ሰላማዊ ውይይት በመመለስ፣ በየደረጃው ወደ ተቋቋመው፣ የሀገር ሽማግሌ፣ የሃይማኖት አባት፣ የሕዝብ ተወካዮች፣ ወጣቶችና ሌሎች አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ችግሩ የሚፈታበትን አቅጣጫ ነድፎ መረባረብ ይገባዋልም፡፡

ለሰላም ዘብ በመቆም ልዩነታችንን አቻችለን፣ የሕግ የበላይነትን አስከብረን ችግሮቻችንን መፍታት ይገባናል፡፡

ሊመጣ የሚችለውን ክልላዊ ጉዳት አስቀድሞ በማሰብ አሁኑኑ ለሰላም መረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

አሁን ላይ በአንዳንድ አካባቢ ያለው ትንኮሳ እያደረ ሲሄድ ክልላዊ አለመረጋጋትና ሥርዐት አልበኝነት እንደሚፈጥርም ገልጸዋል፡፡

ክልሉን ለበለጠ አደጋ የሚጥል በመኾኑ ችግሩን የክልሉ ሕዝብ እንዲገነዘበውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከችግር መውጣት አዳጋችና ከባድ መኾኑን ከሌሎች መማር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

እርስ በእርስ መገዳደል ለውጥ አላመጣልንም ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ሰላማዊ አማራጭን በመከተል ችግሩ እንዲፈታም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለሰላም ሁሉም እንደሚያገባው የተናገሩት ርእሰ መሥተዳድሩ በየአካባቢው ያለውን ትንኮሳ በአስቸኳይ በማቆም ወደ ሰላማዊ ውይይት፣ ምክክር እንዲመለስ እና ክልሉ የተረጋጋ ኾኖ እንዲቀጥል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ ብለዋል፡፡

አሚኮ
•~•~•

"የጎሃ ቃልኪዳናችን የከፍታችን ልክ - ቃላችንን ፈፅመን ከፍታው ላይ እንገናኝ"
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- https://twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- https://youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቲክቶክ፡- https://www.tiktok.com/

31/07/2023
25/07/2023

Address

Mehalmeda Showa
Mehal Meda

Opening Hours

Monday 02:30 - 11:30
Friday 02:30 - 11:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Menz Gera Council Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Menz Gera Council Office:

Share