Menz Gera werda Comunication office

Menz Gera werda Comunication  office Ensure smooth flow of information between the Menz Gera Government and the public and facilitate the

ለመላው የመንዝ ጌራ ወረዳና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ መጪውን የጳጉሜ 3 በዓል ለማክበር  ከመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ  ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ጥሪ ቀርቧል።የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሪት ማህሌ...
06/09/2026

ለመላው የመንዝ ጌራ ወረዳና አካባቢው ነዋሪዎች በሙሉ መጪውን የጳጉሜ 3 በዓል ለማክበር ከመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ጥሪ ቀርቧል።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሪት ማህሌት የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመጀመሪያ እንኳን ለ2018 ዓ.ም ጳጉሜ 3 ለሚከበረው ምስአለ ማርያም ደብረ-ሀይል ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ

ምስሓለ ማርያም ቅዱስ ሩፋኤል ከመሐል ሜዳ በቅርብ ርቀት በተሽከርካሪ በስተምዕራብ በኩል ፀሐይ ሲና ድረስ 13 ኪ.ሜ ተጉዘው ከዋናው መስመር በስተ ደቡብ የ6 ኪ ሜ ርቀት በመኪና ከተጓዙ በኃላ የሚገኝ ቅዱስ ስፍራ ነው ::

ምስሓለ ማርያም ላይ በኢትየጵያ ታሪክ የመካከለኛው ክፍለ ዘመን ነገስታት አሻራቸውን እንዳሳረፉበት ታሪክ ይናገራል ፡፡

የመጀመሪያው አፄ አምደ ፅዮን (1297-1327) ሲሆን በዚህ ቦታ ላይ ቤተ መቅደስ አሰርቶ ቦታውን ምስአለ ማርያም ብሎ መሰየሙ ይነገራል፡፡

ትርጉሙም ማርያምን የምለምንበት ማለት ነው፡፡ በአፄ ይስሀቅ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግስት (1414-1429) አባ ጊዮርጊስ የጋስጫው በምስሓለ ማርያም ተቀምጠው ታቦተ ማርያምን እያለገሉ መፅሐፈ ምስጢር የተባለውን መፅሀፍ እንደፃፉም ይነገራል፡፡ መፅሐፉም ጋሞ ጎፉ በርበር ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

አፄ ዘርአ ያእቆብ በ1434-1468 ዘመን ወደ አዳል ሀገር ሲዘምት እድል ከእርሱ ጋር እንዲሆን ምስአለ ማርያምን ተማፅኖ እና ድል አድርጎ ከተመለሰ ቤተ- ክርስቲያን በቦታው ላይ ለማሰራት ስለት ተሳለ፣በዘመቻውም ድል አድርጎ ከተመለሰ በኋላ በቦታው ላይ ቤተ ክርስትያን የማሰራት ውጥኑን ሳያሳካ እንደሞተ ይነገራል፡፡

ነገር ግን በዱካው የተተካው የአፄ ዘርዓያእቆብ ልጅ አፄ በእደ ማርያም (1468-1478) ለዘመቻ በዚህ ቦታ ሲያልፍ ምስአለ ማርያምን አይቶ በቦታው ውበት ተደንቆ በጊዜው የነበሩ አባቶችን የዚህችን ቦታ ታሪክ እንዲያጫውቱት አጥብቆ ይጠይቃቸዋል፡፡

ታሪክ አዋቂ አባቶችም ታቦተ ማርያም በቦታው ላይ እንዳለች ነግረውት አባቱም አፄ ዘርአያዕቆብ ቤተ-ክርስቲያን ለማሰራት የተሳለውን ስለት ሳያሳካ እንደሞተ ያስረዱታል፡፡

በእደ ማሪያም በዚህ ታሪክ እጅግ ይደነቃል፡፡ በኋላም አባቱ የተሳለውን ስለት ብቻም ሳይሆን እርሱም አሁን በሚሄድበት ዘመቻ ላይ ድል ከቀናው ቤተክርስትያኗን እንደሚያሰራ ምስአለ ማርያምን ተማፅኖ ዘምቶ ድል አድርጎ ተመለሰ፡፡

እንዳለውም ቤተክርስቲያኗን አንፆ ሰርቶ ታቦቷን በማስገባት ያባቱንም ቁጭት ተወጣ፣ ለራሱም ለምሰጋና የሚሆን የስለት ስጦታውን ምስአለ ማሪያም አበረከተ፡፡አፄ በእደ ማርያም በዚህ ብቻ አላበቃም በዚያው ባሰራው ቤተክርስትያን አቅራቢያ የራሱን ቤተ- መንግስት አሰርቶ ምስአለ ማሪያምን መናገሻ ከተማው አድርጎ ኖረ፡፡

በዚህም ምክንያት፡- ታቦቱ ልደታ ማርያም ገዢው በእደ ማርያም አቃቢቷ ወ/ማርያም ሀገሩ ምስአለ ማርያም ይባል ነበር፡በተጨማሪም በዩዲት ጉዲት የተሰደዱትን በዋሻ ውስጥ ተቀብረው የቆዩ ክርስትያኖችን ከመርሀ ቤቴ ነጭ ገደል ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ አስመጥቶ በዚህ ቦታ ላይ አብረው ተዳብለው እንዲኖሩ አድርጎ ለመተዳደሪያ የሚሆን ሀብት፣ ንብረት እና አልባሳት እንደሰጠ ይነገራል፡፡

በ1988 ከፈረንሳይ የመጡ አርኪዮሎጂስቶች በፊት አውራሪ ገብረ ህይወት (የʻʻአራዳʼʼ መፅሃፍ ደራሲ) አስተባባሪነት በዚህ አካባቢ ላይ በተደረገው 1 አመት የፈጀ ቁፋሮ እና ምርምር የአፄ በእደ ማርያም ቤተ -መንግስት ግምጃ ቤት እና ሌሎች ክፍሎች ፍርስራሾችን ጨምሮ ከሸክላ እና ከተለያዩ ቁሳቁሶች የተሰሩ የመመገቢያና የመገልገያ እቃዎች ተገኝተዋል፡፡

እነዚህም የተገኙት የመገልገያና መመገቢያ መሳሪያዎች አሁን አዲስ አበባ በአራት ኪሎ ብሄራዊ ሙዚየም በቅርስነት ተቀምጠው ይገኛሉ፡፡ ምስአለ ማሪያም በየአመቱ ጳጉሜ 3 ታቦቱ የሚነግስ ሲሆን ይህ በዓል ከድግምሻ ሃምሳ ማረሻ፣ ከገደምቦ ሃምሳ ገንቦ፣ ከአፍተነት ሃምሳ ነት፣ ከቄውላ ሃምሳ ዱላ እየተባለ ሲከበር የኖረ ታሪካዊ በዓል ነው፡፡

በየአመቱ በዚሁ እለትም የሚውል ታሪካዊ የገበያ ስረዓት አለ፡፡ በአፈ ታሪክ እንደሚነገረው በዕለቱ ለገበያ የቀረበ ማንኛውም የገበያ ሸቀጥ እና የቁም እንስሳት ግብይት ላይ ከተወደደ በቀጣዩ አመትም ተወዶ ይቆያል፤ ከረከሰም አመቱን ሙሉ ረክሶ ይውላል እየተባለ የቀጣዩ አመት የገበያና የኑሮ ሁኔታ የሚተነበይበት ነው፡፡

ሌላው በዚህ ዕለት ዝናብ ቢዘንብ ዣን ጥላን ዘርግቶ የሚከለል የለም እንደውም የሚዘንበው ዘናብ በደንብ እንዲመታው ተሰተካክሎ ይቆማል እንጅ ምክንያቱ ደግሞ ይህ ዝናብ በአመት አንድ ጊዜ የሚገኝ ድንቅ ፀበል ሰልሆነ ነው፡፡ በከተማና እራቅ ባለ አካባቢ በሚኖረው ማህበረሰብ ዘንድ ደገሞ ከወዲሁ በዋዜማው ጳጉሜ 2 ለሊት ከዘነበ ፀበል ለማግኘት ሰፋ ያለ እቃ ተደቅኖ ያድራል በተገኘው ፀበልም ቤትና ገቢ ይረጫል ለበረከት ዱቄት በማዘጋጀትም ይቦካል ወዘተ፡፡

ምስአለ ማርያም ላይ ሌላው ለየት ያለው ታቦቱን ለማንገስና አካባቢውን ለመጎብኘት የሄደ ሰው የአካባቢው ተፈጥሯዊ አቀማመጥ እድሜ ጠገብ የጽድ ዛፎች ፣ወይራ ዝግባ እና ሌሎችም ሀገር በቀል ዛፎች ያሉበት በመሆኑ ወደ ውስጥ ሲገቡበት መንፈስን የሚያድስ ጸጥታ ካካባቢው ውጡ ውጡ የማይል ስሜትን ይፈጥራል መንፈስንም ያድሳል፡፡ ከዚህ ባሻገር ቦታው ከ713 አመታትን በላይ ወደ ኋላ የሚመልስ የታሪክ አሻራዎች ያረፉበት ቦታ ነው፡፡ይህ ቦታ ከሀይማኖታዊ ቦታነቱም ባሻገር የቱሪስት መስህብ እንዲሁም የጥናትና የምርምር ቦታ የሆነናበቀጣይ ሰፊ በዘርፉ ሰፊ ስራ ሊሰራበት የሚችል ነው፡፡

ይህ ውብና ማራኪ የሆነ ታሪካዊ፣ባህላዊና ሀይማኖታዊቱውፊቶች የሚከናወኑበት ስፋራ ለወረዳችን ትልቅ የመስህብ ሀብትናመዳረሻ አድርጎ ከመጠቀምና የወረዳችንና የአካባቢው ማህበረሰብ ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ሁለንተናዊ ጥቅም እንዲያገኝ አልሞ መስራት ይጠይቃል የወረዳው ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ፅ/ቤትም በያዝነው ዓመት ይህንን ቅዱስ የሆነ ጥናታዊና ታሪካዊ ስፍራ በቱሪስት መዳረሻነት በመያዝ በዘርፉ የሚታዩትን የመሰረተ ልማት አውታሮች ችግር ከወረዳው መንግስት፣ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር ለማሟላት ዕቅድ በመያዝ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡ ከዚህ አኳያ የመስህብ ስፍራው የተለያዩ የመሰረተ ልማቶችን አልተሟሉለትም በህዝቡና በመንግስት ትብብር የ24 ሰዓት መብራት ተጠቃሚ ሆኗል ይሁን እንጂ ክረምት ከበጋ የሚያስገባ መንገድ፣ የእንግዶች /የእምነት ቱሪስት ማረፊያ፣መጸዳጃ ቤት፣ንፅህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት አልተሟላለትም፡፡ በመሆኑም ይንን ቅዱስ፣ጥንታዊና ታሪካዊ የሆነውን ስፍራ እንደወረዳ በማልማት ወረዳችንና ህዘቡ ከቱሪዝም ዘርፉ ማግኘት የሚገባውን ዘርፈ ብዙጥቅም ማግኘት እንዲችሉ ሁላችንም የሚጠበቅብንን ድርሻ ልንወጣ ይገባናል በማለት መልዕክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

የመንዝጌራ ምድር ወረዳ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ጽ/ቤት ስ.ቁ0116850600

06/09/2026

በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ተቋማት ሃላፊዎች፣የመንግስት ሰራተኞች፣አርሶ አደሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት #ጳጉሜን 1_"የዕመርታ_ቀን' በሚል የፓናል ውይይትና የመስክ ጉብኝት በማድረግ ተከብሯል።

 #ጳጉሜን 1_"የዕመርታ_ቀንን አስመልክቶ የፓናል ውይይትና የመስክ ጉብኝት በማድረግ ተከበረ፤መ/ሜዳ፤ጳጉሜ 1/2018(መጌወመኮ)በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ተቋማት ሃላፊዎች፣የመንግስት ሰራተኞች...
06/09/2026

#ጳጉሜን 1_"የዕመርታ_ቀንን አስመልክቶ የፓናል ውይይትና የመስክ ጉብኝት በማድረግ ተከበረ፤

መ/ሜዳ፤ጳጉሜ 1/2018(መጌወመኮ)

በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ተቋማት ሃላፊዎች፣የመንግስት ሰራተኞች፣አርሶ አደሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት "የዕመርታ_ቀን' በሚል የፓናል ውይይትና የመስክ ጉብኝት በማድረግ ተከብሯል።

የእለቱን ፕሮግራም አስመልክቶ መልዕክት ያስተላለፉት የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ም/አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡስማን ኢብራሂም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ የኢትዮጵያን እምርታን እናረጋግጣለን ብለዋል።

በወረዳው ዱዋትና ቄውላ በክላስተር የለማ የስንዴ ሰብል የመስክ ጉብኝት በማድረግ የልምድ ልውውጥ ተደርጓል።

በመስክ ምልከታው የተሳተፉ አካላትም ተረጅነትን ለመቀነስ እንደ ወረዳ የተሰሩ የግብርና ስራዎችና የተለያዩ ልማቶች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን አድናቆትና አስተያየት ሰጥተዋል።

‎የዘንድሮው የጳጉሜ ቀናት “የኢትዮጵያ
‎መንሰራራት!” በሚል አብይ መሪ ሐሳብ የሚከበሩ ሲሆን ዋና ዓላማውም ሀገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች ወደ ላቀ ከፍታ መገስገስ መጀመሯን በማብሰር፣ ለበለጠ ሀገራዊ ስኬት መነሳሳትንና የተስፋ መንፈስን መፍጠር ነው።

በቀጣዮቹ ቀናትም‎ አምስቱ የጳጉሜን ቀናት የተለያዩ ስያሜዎች ይዘው በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራሉ፦

‎ ጳጉሜን 1 ፦ "የዕመርታ ቀን"
‎ ጳጉሜን 2 ፦ "የመንሰራራት ቀን"
‎ ጳጉሜን 3 ፦ "የጽናት ቀን"
‎ ጳጉሜን 4 ፦ "የኅብር ቀን"
‎ ጳጉሜን 5 ፦ "የነገ ቀን" ናቸው።

ባለ ልዩ ጣዕሙ የመንዝ በግ መጪውን አዲስ ዓመት አስመልክቶ በተመጣጣኝ ዋጋ በሁሉም የመንዝ አካባቢዎችና የሀገሪቱ መዲና በስፋት ቀርቧል።ከመንዝ በግ በተጨማሪም የመንዝ ቅቤና እንቁላል በተመሳ...
05/09/2026

ባለ ልዩ ጣዕሙ የመንዝ በግ መጪውን አዲስ ዓመት አስመልክቶ በተመጣጣኝ ዋጋ በሁሉም የመንዝ አካባቢዎችና የሀገሪቱ መዲና በስፋት ቀርቧል።

ከመንዝ በግ በተጨማሪም የመንዝ ቅቤና እንቁላል በተመሳሳይ መልኩ ቀርቧል።

በክረምት ሲሰጥ የነበረው የኮምፒዩተር ስልጠና ተጠናቀቀ፤ መ/ሜዳ፤ነሐሴ 29/2018(መጌወመኮ)በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ የስራ ቡድን ተዘጋጅቶ ለተከታታይ ...
04/09/2026

በክረምት ሲሰጥ የነበረው የኮምፒዩተር ስልጠና ተጠናቀቀ፤

መ/ሜዳ፤ነሐሴ 29/2018(መጌወመኮ)

በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ የስራ ቡድን ተዘጋጅቶ ለተከታታይ 45 ቀናት በክረምት ሲሲሰጥ የቆየው የኮምፒዩተር ስልጠና ተጠናቆ ለሰልጣኞች የእውቅናና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ መልዕክት ያስተላለፉት የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ጌትዬ እንደገለፁት በስልጠናው መሠረታዊ ኮምፒዩተርና ኢትዮ ኮደርስ ተካተው የተሰጡ ሲሆን በቀጣይ ሁሉንም የወረዳውን መንግስት ሰራተኛ የስልጠናው አካል ለማድረግ አቅደን እንሰራለን ብለዋል።

በሌላ መልኩ የወረዳው ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ አቢዮት ተራመደው በስልጠናው የተሳተፉ መንግስት ሰራተኞችና በበጎ ፈቃደኝነት ስልጠናውን ለሰጡ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበው ከወረቀት ነፃ የሆነ በቴክኖሎጂ የታገዘ አገልግሎትና አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ስልጠናውን በኃላፊነት ሲያስተባብሩ የነበሩት የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ ወ/ሮ አፀደ ወ/አረጋይ በስልጠና ወቅት የነበሩ ችግሮችን ለማለፍ የተባበሩ አካላትን በማመስገን በቀጣይ ከስልጠና መስጠት ባሻገር በቢሯቸው ለማማከር ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በመጨረሻም ለሰልጣኞች እውቅናና ሰርተፍኬት ተሰጥቶ መርሃ ግብሩ ተጠናቋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UC2sGeulo1xi7MFoOM1X3-rg
በዌብሳይት http://www.menzgera.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/menzegeracom
ትዊተር https://twitter.com/MenzgeraCom
https://www.youtube.com/watch?v=DskFVQ6Av0M
ቲክ ቶክ www.tiktok.com/

በአዲሱ የግዢ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ባለማወቅ ወደ ስህተት እንዳንገባና ጥራት ያው እቃ ለማቅረብ ያስችለናል  ሲሉ ሰልጣኞች ተናገሩ፤መ/ሜዳ፤ነሐሴ  29/2...
04/09/2026

በአዲሱ የግዢ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ባለማወቅ ወደ ስህተት እንዳንገባና ጥራት ያው እቃ ለማቅረብ ያስችለናል ሲሉ ሰልጣኞች ተናገሩ፤

መ/ሜዳ፤ነሐሴ 29/2018(መጌወመኮ)

በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እና የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤቶች በአዲሱ የግዢ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 144/2018 ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለተቋሙ የግዥ ባለሙያዎች፣ቡድን መሪዎች፣የክልል ተጠሪ ተቋማት፣ጤና ተቋማት፣2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ሰጥተዋል።

በአዲሱ የግዢ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የተሰጠው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ባለማወቅ ወደ ስህተት እንዳንገባና ጥራት ያው እቃ ለማቅረብ ያስችለናል ሲሉ ሰልጣኞች ተናግረዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UC2sGeulo1xi7MFoOM1X3-rg
በዌብሳይት http://www.menzgera.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/menzegeracom
ትዊተር https://twitter.com/MenzgeraCom
https://www.youtube.com/watch?v=DskFVQ6Av0M
ቲክ ቶክ www.tiktok.com/

አዲስ ለተመደቡ 30ኛ ሻለቃ የአድማ መከላከል አባላት የምግብ እህልና ዘይት ድጋፍ ተደረገላቸው፤መ/ሜዳ፤ነሐሴ 29/2018(መጌወመኮ)ድጋፉን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ አስተዳደር እና መ/ሜዳ ከ...
04/09/2026

አዲስ ለተመደቡ 30ኛ ሻለቃ የአድማ መከላከል አባላት የምግብ እህልና ዘይት ድጋፍ ተደረገላቸው፤

መ/ሜዳ፤ነሐሴ 29/2018(መጌወመኮ)

ድጋፉን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ አስተዳደር እና መ/ሜዳ ከተማ በጋራ ያደረጉ ሲሆን የወረዳው ም/አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡስማን ኢብራሂም፣የሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ኃላፊ ፶ አለቃ ነጋሽ አሰፋ፣የመ/ሜዳ ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ወንዳፈር ዘይቱ እና ሌሎች የሁለቱም ወረዳዎች የስራ ኃላፊዎች አስረክበዋል።

ድጋፉ የተደረገላቸው የአድማ መከላከል አመራሮችና አባላትም በተደረገላቸው ድጋፍ መደሰታቸውን ገልፀው የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከወረዳው የፀጥታ መዋቅር ጋር ተባብረው እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UC2sGeulo1xi7MFoOM1X3-rg
በዌብሳይት http://www.menzgera.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/menzegeracom
ትዊተር https://twitter.com/MenzgeraCom
https://www.youtube.com/watch?v=DskFVQ6Av0M
ቲክ ቶክ www.tiktok.com/

በአዲሱ የግዢ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው፤መ/ሜዳ፤ነሐሴ  29/2018(መጌወመኮ)በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እና የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገን...
04/09/2026

በአዲሱ የግዢ አፈፃፀም መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ነው፤

መ/ሜዳ፤ነሐሴ 29/2018(መጌወመኮ)

በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ እና የመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤቶች በአዲሱ የግዢ አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 144/2018 ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለተቋሙ የግዥ ባለሙያዎች፣ቡድን መሪዎች፣የክልል ተጠሪ ተቋማት፣ጤና ተቋማት፣2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት እየተሰጠ ነው።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የወረዳው ም/አስተዳዳሪና የግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡስማን ኢብራሂም የግዢ ስርዓቱን በማዘመን የመንግስትን ወጪ በመቀነስ የተፋጠነ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ገልፀዋል።

የግዢ አፈፃፀም መመሪያው 144/2018 በሚል በአዲስ የተሻሻለ በመሆኑ የተቋሙ ባለሙያዎችና ባለ ድርሻ አካላት ወቅቱን የሚመጥን እውቀትና ብቃት ጨብጠው አገልግሎት መስጠት የሚያስችላቸውን አቅም ለመፍጠር የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን የወረዳው ገንዘብ ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ይልማ ከበደ ገልፀዋል።

አቶ ይልማ አክለውም የቀደሙት አሰራሮች የነበሩባቸውን ክፍተቶች ለመድፈን፣ ግዥን የተቀላጠፈና ጥራት ያለው ለማድረግ፣ እንዲሁም ከወቅታዊው የኢኮኖሚ እና ቴክኖሎጂ እድገት ጋር ለማጣጣም ይህ መመሪያ ተዘጋጅቶ ስራ ላይ ውሏል ብለዋል።

የስልጠና ሰነዱን የግዥና ፋይናንስ ቡድን መሪ አቶ አበበ ጌታቸው እያቀረቡ ሲሆን የሁለቱም ወረዳ የገንዘብ ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና ሰልጣኞች እየተሳተፉ ነው።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UC2sGeulo1xi7MFoOM1X3-rg
በዌብሳይት http://www.menzgera.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/menzegeracom
ትዊተር https://twitter.com/MenzgeraCom
https://www.youtube.com/watch?v=DskFVQ6Av0M
ቲክ ቶክ www.tiktok.com/

የእናቴ ሜዳ ቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ምልከታ ተደረገመ/ሜዳ፦ ነሐሴ 28/2018 (መጌወመኮ)በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገይ ቀበሌ እናቴ ሜዳ ትምህርት ቤት በወረዳው ምክትል አስተዳዳ...
03/09/2026

የእናቴ ሜዳ ቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ምልከታ ተደረገ

መ/ሜዳ፦ ነሐሴ 28/2018 (መጌወመኮ)

በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ገይ ቀበሌ እናቴ ሜዳ ትምህርት ቤት በወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዑስማን ኢብራሂም የተመራ ልዑክ የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ምልከታ ተደረገ።

የቅድመ-መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታው በወረዳው መደበኛ በጀት 12 ሚሊዮን 919 ሺህ 378 ብር ከ88 ሳንቲም በጀት ተይዞለት ወደ ሥራ ተገብቷል።

በምልከታው ወቅትም ግንባታው በ2018 በጀት ዓመት መጨረሻ ወራት ላይ የተጀመረ ሲሆን ከ60 ፐርሰንት በላይ መድረሱ ተጠቁሟል።

በዚህም ምልከታ ፕሮጀክቱ በቅርብ ቀናት ተጠናቆ በ2019 የትምህርት ዘመን ወደ ሥራ እንዲገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

ግንባታው ሲጠናቀቅ የመማሪያ ክፍል፣ የሕፃናት ማረፊያና መመገቢያ፣ የመምህራን ማረፊያ፣ የመምህራን ቢሮ እና ሌሎች ተያያዥ ክፍሎችን ጨምሮ ሰባት ክፍል እና ሶስት የመፀዳጃ ቤት የሚኖረው ይሆናል።

በእናቴ ሜዳ ትምህርት ቤት በወረዳው መደበኛ በጀት ከሚገነባው በተጨማሪ በማህበረሰብ ተሳትፎ እና በመንግስት በጀት አንድ ብሎክ ግንባታ የተጀመረ ስለመሆኑ መዘገባችን ይታወሳል።

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ ስራዎችን ገመገመ፤መ/ሜዳ፤ነሐሴ 28/2018(መጌወመኮ)በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ለማስተባበር የተቋቋመው ቴክኒክ...
03/09/2026

የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቴክኒክ ኮሚቴ ስራዎችን ገመገመ፤

መ/ሜዳ፤ነሐሴ 28/2018(መጌወመኮ)

በመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን ለማስተባበር የተቋቋመው ቴክኒክ ኮሚቴ አጠቃላይ ስራዎችን ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።

የግምገማ መነሻ እና ሪፖርተ የወረዳው ሴቶች ህፃናት፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ስንታየሁ አበበ አቅርበው በተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቶበታል።

በውይይቱም ቃል የገቡ በጎ ፈቃደኞች ነሚሰጡት የትምህርት ቁሳቁስና የገንዘብ ድጋፍ እየተሰበሰበ ሲሆን ትምህርት ከመጀመሩ ቀድመን ጳጉሜ 3 /2018 የተማሪዎች ደብተር ስርጭት ስለሚደረግ ተጠናቆ እንድሰበሰብ አቅጣጫ ተቀምጧል።

እስከ አሁን በነበረው የሀብት ማሰባሰብ ስራ 703 ደርዘን ደብተር ፣32 ፓኮ እስኪብርቶ፣400000/አራት መቶ ሺ ብር ፣አልባሳት እና ለአረጋዊያን ቤት ግንባታ የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁሶች ገቢ መሆኑን ወ/ሮ ስንታየሁ በሪፖርታቸው ገልፀዋል።

Address

Mehal Meda
251

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Menz Gera werda Comunication office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Menz Gera werda Comunication office:

Shortcuts

Share