31/08/2026
ዜና እረፍት
ነሀሴ 25/2018 /ሀብሩ ኮሙዩኒኬሽን
የሀብሩ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ ወርቅዋ ጌታቸው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትላንት ነሀሴ 24/12/2018 ዓ,ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል ።
ወ/ሮ ወርቅዋ ጌታቸው በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ አስተዳደር 01 መርጦ ቀበሌ ከአባታቸው አቶ ጌታቸው ካሳዬ ዘገዬና ከእናታቸው ወ/ሮ እማዋይ ተበጄ ይማም መስከረም 14 ,1969ዓ,ም ነበር የተወለዱት።
ወ/ሮ ወርቅዋ የ1ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በመርጦ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፣የ2ኛ ደረጃቸውን በወልደያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትለዋል ። በመቀጠልም በ1999ዓ,ም በአልፋ ዩኒቨርስቲ ኮሎጅ በማኔጅመንት የትምህርት ዘርፍ ድፕሎማቸውን እንዲሁም በ2010ዓ,ም ደግሞ በህዝብ አስተዳደር የመጀመሪያ ድግሪዋን አግኝታለች ።
ወ/ሮ ወርቅዋ ከ1999-2001 ዓ,ም በመርሳ ግብርና ኮሌጅ ፣ከ2002-2007ዓ,ም በሀብሩ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት፣ከ2008 ጀምሮ ትላንት ህይወቷ እስካለፈበት ጊዜ በሀብሩ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ባለሙያ በመሆን ለ 22 አመታት የወረዳችንን ህዝብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ አገልግለዋል ።
ወ/ሮ ወርቅዋ የአንድ ወንድ ልጅ እናት ነበሩ።
ወ/ሮ ወርቅዋ ለነበራቸው መልካም አገልግሎት በሀብሩ ወረዳ አስተዳደር ስም ታላቅ ምስጋና እያቀረብን የቀብር ስነስራታቸው በመርሳ ፈለገ አክሊል ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን በዛሬው እለት ከቀኑ 6:00 ጀምሮ የሚፈፀም ይሆናል። ለመላው ወዳጅ ቤተሰቧና ለስራ ባልደረባቸው መፅናናትን እንዲሰጥልን እንመኛለን ።
•~•~•
•~•~•
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የተቋማችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ዩቲዩብ:https://www.youtube.com/
ፌስቡክ:https://www.facebook.com/share/19dpbXvN69/
ቲክቶክ:http://tiktok.com/.communcatio
ቴሌግራም:https://t.me/+J-1GwMayZ2Y4YzVk
ትዊተር:https://x.com/Habrucomncation