Habru Woreda Road And Transport Office

Habru Woreda Road And Transport Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Habru Woreda Road And Transport Office, Government Organization, Mersa.

አድስ ታሪፍ
28/02/2021

አድስ ታሪፍ

12/01/2021
26/12/2020

የተሽከርካሪ ቀረጥና ታክስ አወሳሰን

ተሽከርካሪ ወደ ሀገር ሲገባ ቀረጥና ታክስ የሚታሰበው ተሽከርካሪው ዓይነት (የቤት አውቶሞቢል፣ የህዝብ ማመላለሻ ወይም የዕቃ ማመላለሻ፣ ልዩ ልዩ) የተሸከርካሪዉን የመጫን አቅም(የሰው ብዛት፣ የጭነት ኪሎ መጠን)፣ ጉልበት (ለቤት አውቶሞቢሎች) መሰረት በማድረግ እንዲሁም CIF (የተገዛበት ዋጋ + የትራንስፖርት ወጪ + የኢንሹራንስ ወጪ እና ሌሎች ወጪዎችን ጨምሮ) በሚገኘዉ ጠቅላላ ወጪ ነው፡፡

ተገጣጥመው ወደ ሀገር የሚገቡ አዲስ የቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪዎች ጉልበታቸው እስከ 1300 ከሆነ 75.67%ሲሆን ጉልበታቸው ከ1301 እስከ 1800 ደግሞ 116.79% እንዲሁም ከ1800 በላይ ጉልበት ያላቸው ከሆኑ ደግሞ 231.9% አጠቃላይ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡ ሹፌሩን ጨምሮ እስከ 16 የመቀመጫ አቅም ያላቸው የሰው ማጓጓዣዎች እና እስከ 1.5 ቶን እቃ የመጫን አቅም ያላቸው የእቃ ማጓጓዣዎች አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ 52.5% ሲሆን ከ16 ሰው በላይ የሚጭኑ የህዝብ ማመላለሻዎች እና ከ1.5 ቶን በላይ እቃ የሚጭኑ ተሸከራካሪዎች ደግሞ 29.5% አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ ተጥሎባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል ሀገር ውስጥ ለመገጣጠም በአምራች ድርጅቶች ወደ ሀገር የሚገቡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የተበተኑ (CKD/SKD) የሆኑ ተሽከራካሪዎች በተመለከተ በአዲስ ይዞታ ተገጣጥመው ወደ ሀገር ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በተለየ በዝቅተኛ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ የሚስተናገዱ ሲሆን በተቃራኒው ያገለገሉ(USED) ተሽከራካሪዎች ደግሞ ከፍተኛ የኤክሳይዝ ታክስ ስለተጣለባቸው በአዲስ ይዞታ ከሚገቡ ተሸከራካሪዎች በአንፃራዊነት በጣም ከፍተኛ አጠቃላይ የቀረጥና ታክስ ምጣኔ አላቸው፡፡

የተሽከርካሪው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ (duty paying value) በተሽከርካሪው ጠቅላላ ቀረጥና ታክስ ማስከፈያ ምጣኔ ተባዝቶ የብዜቱ ውጤት ተከፋዩ ቀረጥና ታክስ ይሆናል፡፡ እንደ ተሽከርካሪው አይነት ወደ ሀገር የሚገቡ የተሸከርካሪዎች ላይ እስከ አራት ዓይነት የቀረጥና ታክስ ዓይነት የሚጣልባቸው ሲሆን ከአምራች ድርጅቶች ውጪ የሚገቡ ተሽከርካሪዎች ከሆኑ ደግሞ በተጨማሪነት የዊዝሆልዲንግ ታክስ ይሰበሰባል፡፡ የቀረጥና ታክስ ማስከፈያ መሠረት(Tax base) የሚሆነው የእቃው ዋጋ(CIF) እና በቅድም ተከተል የሚሰላው የቀረጥ ወይም ታክስ መጠን (የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ፣ ሱር ታክስ) ድምር ይሆናል፡፡

የቀረጥና ታክስ መጠኑን እንዴት እንደሚታሰብ ለምሳሌ ሁሉም ዓይነት ታክስ በሚመለከተው በቤት አውቶሞቢል ተሽከርካሪ በምሳሌነት እንመልከት፡፡

የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋው ብር 400,000፣ የሲሊንደር አቅሙ 1300 የሆነ አዲስ አውቶሞቢል ወደ ሀገር ሲገባ:-

በቅድሚያ የጉምሩክ ቀረጥ የሚሰላ ሲሆን ማስከፈያ ዋጋው በጉምሩክ ቀረጥ ምጣኔ በማባዛት የሚሰላ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ 400,000 X 30%(ከፍተኛው መጣኔ) = 120,000 ይሆናል፡፡

ቀጥሎ ኤክሳይዝ ታክስ የሚሰላ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉ የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ እና ተከፋዩ የጉምሩክ ቀረጥ በመደመር በኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ ማባዛት ነው፡፡ በዚህ ስሌት መሰረት ተከፋዩ ኤክሳይስ ታክስ መጠን (400,000 + 120,000) 5%= 26,000 ብር ይሆናል፡፡

በሶስተኛ ደረጃ የሚሰላው ተከፋይ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ሲሆን በዚህ ስሌት የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ እና ኤክሳይዝ ታክስን በመደመር በተጨማሪ ዕሴት ታክስ መጣኔ ይባዛል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (400,000 + 120,000 + 26,000) 15% = 81,900 ብር ይሆናል፡፡

በአራተኛ ደረጃ የሚሰላው ሱር ታክስ ሲሆን ስሌቱ የአውቶሞቢሉን የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋ፣ ተከፋይ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ኤክሳይዝ ታክስ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ በመደመር በሱር ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የሚከፈለው ሱር ታክስ (400,000 + 120,000 + 26,000 +81,900)10%= 86,190 ብር ይሆናል፡፡

ተሽከራካሪው በመደበኛ አስመጪ(ከአምራች ድርጅት ውጪ…) የሚመጣ ከሆነ በአምስተኛ ደረጃ ተከፋዩን ዊዝሆልዲንግ ታክስ ነው፡፡ ይህ ታክስ የሚሰላው የቀረጥ ማስከፈያ ዋጋን በዊዝሆልዲንግ ታክስ መጣኔ በማባዛት ነው፡፡ በዚህ መሰረት ተከፋዩ የዊዝሆልዲንግ ታክስ 400,000 X 3%= 12,000 ብር ይሆናል፡፡

በመጨረሻም የስሌት ደረጃ ሁሉም ተከፋይ ቀረጥና ታክስ የሚደመሩ ሲሆን በዚህ መሰረት መንግስት ከዚህ አውቶሞቢል የሚሰበስበው ቀረጥና ታክስ ስሌት

120,000 + 26,000 + 81,900 + 86,190 + 12,000= 326,090 ብር ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡- ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች የአገልግሎት ጊዜያቸው መሠረት በማድረግ የተለያየ ኤክሳይዝ

25/11/2020
የትራንስፖርት ታሪፍ በኪ.ሜ
25/11/2020

የትራንስፖርት ታሪፍ በኪ.ሜ

23/10/2020
19/10/2020

በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመክፈት የተዘጋጀ የአደረጃጀት መመሪያ
~~~~~~~~~~~~~
1. መግቢያ
በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያ የተዘጉ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመክፈት የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ሲሰራ ቆይቷል። የክልላችን ትምህርት ቢሮ የወረርሽኙን ስርጭት በመከላከል ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የነፃ የክፍል ክፍል ሽግግር ማስፈፀሚያ አቅጣጫ፤ የተማሪ ምዝገባ ማስፈፀሚያ እቅድ እና በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠውን ትምህርት አንደገና ለማስጀመር የሚያስችል ጋይድላይን ተዘጋጅቶና የተቋረጠውን ትም/ ለማካካስ በየክፍል ደረጃው የትም/ይዘቶች ተለይተው ት/ቤት እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የሚያስችል ምቹ መደላድል መኖሩን ለማረጋገጥ በአንድ ሽፍት፤በሁለት ሽፍት፤ በሶስት ሽፍትና ከዚያ በላይ የተማሪ ማስተናገድ አቅም የሌላቸው ት/ቤቶች መረጃ የማደረጀትና ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር ያለባቸውን ሁለት የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የዳሰሳ ጥናት በማካሄድ በሶስት ሽፍትና ከዚያ በላይ የሆነ የተማሪ ቁጥር ያለባቸው ዞኖችና ት/ቤቶች መረጃ የመተንተን ስራ ተሰርቷል፡፡
ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመክፈት ምን ቅድመ ዝግጅቶች መከናወን እንደሚገባቸው፣ ትምህርት ቤቶቹ ማሟላት ስለሚገባቸው ስታንዳርድ፣ የትምህርት ቤቶችን አከፋፈት የሚከታተል፣የሚደግፍና የሚያረጋግጥ አካል አደረጃጀት መፍጠር፣ ስታንዳርዱን ለማሟላት አደረጃጀቶቹ ስለሚከተሏቸው የማስፈጸሚያ ስትራቴጂና የባለድርሻ አካላትን ሚናና ሃላፊነት በግልጽ ሊያሳይ የሚችል መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ ይህ መመሪያ ተዘጋጅቷል።
በመሆኑም ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የተለየ ግብረ ሃይል ከፌደራል እስከ ትምህርት ቤት የሚዋቀር ሲሆን ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት በቅድሚያ የተቀመጡ ስታንዳርዶች መሟላት ይኖርባቸዋል።የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ለማሟላት በየደረጃው የተዋቀረው ግብረ ሃይል ወሳኝ የሆኑ ግብአቶችንና መሰረተ ልማት በማሟላት ዝግጁ መሆናቸውን የትምህርት አመራርና የፖለቲካ አመራሩ ከወላጆች፣መምህራን፣ ተማሪዎች ጋር እየተወያዩ በጥብቅ ዲሲፒሊን የሚተገብሩት ፕሮቶኮል ተዘጋጅቶ ይፈራረማሉ።
ከላይ የተቀመጠው ሀገራዊና ክልላዊ የትምህርት ቤት አከፋፈት የጊዜ ሰሌዳ እንደተጠበቀ ሆኖ የቫይረሱ ስርጭት ጋር ተያይዞ በልዩ ሁኔታ መታየት የሚገባቸው ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በየደረጃው ያሉ የትምህርትና ጤና ዘርፎች እንደተጨባጭ ሁኔታ እያዩ ውሳኔ የሚሰጡ ይሆናል።
2. የመመሪያው አስፈላጊነት
የክልላችን ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት ሁለት የጊዜ ሰሌዳ የተቀመጠ ቢሆንም ተቋማቱ የተቀመጠውን አጥጋቢ መስፈርት ማሟላታቸው ካልተረጋገጠ መከፈት የለባቸውም። ሆኖም ግን የተቀመጠውን የጊዜ ሰሌዳ ብቻ በመመልከት ትምህርት ቤቶች የመክፈት አዝማሚያ የሚኖር በመሆኑና ይህም የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ጫና የሚያሳድር በመሆኑ፡-
• ከፌደራል እስከ ቀበሌ ያለው መዋቅር ኮቪድን ለመከላከል በትምህርት ቤቶች አከፋፈት ላይ የበኩሉን ሚና እንዲጫወት መዋቅርበመዘርጋት ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ፤
• የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶችን ለትምህርት ማህበረሰቡ በማስተማርና እንዲተገብር በማድረግ የቫይረሱን ስርጭት እንዳይባባስ ለማድረግ ፤
• ሁሉም ትምህርት ቤቶችበተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት በፍጥነት ዝግጁ እንዲሆኑ ህብረተሰቡ፣ የግሉ ዘርፍ ባለሃብቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ አጋር ድርጅቶች በግብአት አቅርቦት ላይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ይህ መመሪያ አስፈላጊ ሆኗል።

3. ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት የሚከናወኑ ቅድመ ዝግጅቶች
• ትምህርት ቤቶች ከመከፈታቸው በፊት ተቋማቱ በሚገኙባቸው አካባቢዎች የቫይረሱ ስርጭት ያለበት ሁኔታ ተጠንቶና በማህበረሰብ ጤና ላይ የጎላ ጉዳት አለማድረሱ በጋራ ግብረ ሃይል ይረጋገጣል።
• ትምህርት ቤቶች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አካባቢያዊ መፍትሄዎችን ጨምሮ በቂ የመማርያ ክፍሎች፣ የተማሪ ዴስክ፣ የውሃ መሰረተ ልማት ፤አካላዊ ርቀትና ንፅህና ለማስጠበቅ የተሟሉ መሆናቸው በዝርዝር ይረጋገጣል።
• ት/ቤቶች ካላቸው የተማሪና የክፍል ጥምርታ አኳያ በአንድ፤በሁለት፤በሶስት እና በላይ ሽፍት የሚሰሩ መሆናቸውና ለዚህም በቂ መማሪያ ክፍል ፤መምህርና መቀመጫ ዴስክ ማሟላታቸው ይረጋገጣል፤
• የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል (Barrier Mask) አቅርቦት በተማሪዎች ልክ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት መደረሱ ይረጋገጣል፤
• ትምህርት ቤቶች የተዘጋጀውን ስታንዳርድ መሰረት በማድረግ ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር ተወያይተው ወላጆች፣መምህራን፣ተማሪዎች በጥብቅ ዲሲፒሊን የሚተገብሩት ፕሮቶኮል ተዘጋጅቶ መፈራማቸው ይረጋገጣል።
• በትምህርት ቤት ደረጃ የትምህርት አከፋፈትን የሚከታተልና የሚያረጋግጥ አደረጃጀት ይኖራል፤

4. ትምህርት ቤቶች ማሟላት የሚገባቸው አነስተኛ ስታንዳርድ
• ሁሉም ተማሪ፣ መምህር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግ አለበት፤
• በልዩ ሁኔታ በክል ግብረ ሀይል ካልተወሰነ በቀር በአንድ ትምህርት ቤት በፈረቃ ከአንድ ሺ ተማሪ መብለጥ የለበትም፣
• በአንድ መማርያ ክፍል30 ተማሪዎች ብቻ እንዲስተናገዱ ይደረጋል፣
• አንድ መምህር በሳምንት እስከ 45 ክፍለ ጊዜ እንዲያስተምር በማድረግ የመምህር እጥረትን መፍታት፣
• በአንድ የተማሪ መቀመጫ (Combined Desk) አንድ ተማሪ ብቻ መቀመጥ አለበት፣
• በትምህርት ቤት ውስጥ በ2 ሜትር አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ግዴታ መሆኑ መረጋገጥ አለበት፤
• ትምህርት ቤቶች በኬሚካል ለማጽዳት፤ ለሳኒታይዘር/ለእጅ ንጽህና መጠበቂያ ውሃና ሳሙና በተማሪ ልክ መቅረብ አለበት
• በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ለብቻ እንዲገለሉ የተደረጉ ተማሪዎች ካሉ ትምህርት ቤት ሳይመጡ ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት ስርዓት ይዘረጋል።
የክልላችን ትምህርት ቤቶች ከላይ በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን አሟልተው ከተገኙ በሁለት ዙር እንዲከፈቱ ይደረጋል፡፡
በመጀመሪያ ዙር ጥቅምት 9/2013 ዓም የሚከፈቱ፡-በገጠር የወረዳ ከተማዎች እና ከዚያ በታች ባሉ ሁሉም ትምህርት ቤቶች እና በሁሉም የክልሉ ትምህርት ቤቶች ያሉ 8ኛ እና 12ኛ ተፈታኝ ተማሪዎች ሲሆን
በሁሉተኛ ዙር ጥቅምት 16/2013 የሚከፈቱ፡- በሁሉም የዞን እና የክልል ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ት/ቤቶች ተማሪዎች ትምህርት ይጀመራሉ።

5. አደረጃጀት
ትምህርት ቤቶችን ዳግም ለመክፈት የተቀናጀና የተደራጀ አመራር የሚያስፈልግ በመሆኑ ከፌደራል እስከ ቀበሌ ድረስ ያለው አመራር ሂደቱን ፖለቲካዊ ትርጉም ሰጥቶት መምራት የሚያስፈልገው በመሆኑ በየደረጃው ባሉ ከፍተኛ አመራሮች ሰብሳቢነት ይመራል።

5.1. በፌደራል ደረጃ
❖ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትሩ የሚመራ ግብረ ሀይልኮሚቴ እና በትምህርት ሚንስትሩ የሚመራ የቴክኒክ ኮሚቴ ይዋቀራል።
በግብረ ሀይል ኮሚቴ ውስጥ
• የትምህርት ሚኒስትር፣
• የጤና ሚንስትር፣
• የሰላም ሚንስትር፣
• የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣
• የትራንስፖርት ሚንስትር፣
• የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር፣
• የሀገር አቀፍ የተማሪ ወላጆች ማህበር የሚካተቱ ሲሆን ስትሪንግ ኮሚቴው በመጀመሪያ ሶስት ሳምንታት በሳምንት አንድ ቀን ይሰበሰባል፤ግብረ መልስ ይሰጣል።
 የቴክኒክ ኮሚቴው በትምህርት ሚንስትሩ ሰብሳቢነት የየመስሪያ ቤቱ ሚኒስትር ዴኤታዎች/ከፍተኛ ባለሙያዎች አባላት ይሆናሉ። ቴክኒክ ኮሚቴው በመጀመሪያ ሶስት ሳምንታት በሳምንት ሁለት ቀን ይሰበሰባል።

5.2. በክልል ደረጃ
5.3. ❖ በርዕሰ መስተዳድሩ/ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩየሚመራ ግብረ ሀይል ኮሚቴ እና በትምህርት ቢሮ የሚመራ የቴክኒክ ኮሚቴ ይዋቀራል።በየደረጃው በቴክኒክ ኮሚቴው ውስጥ የመምህራን ማህበር ሊቀመንበር/ተወካይ አባል ይሆናል፡፡
በግብረ ሀይል ኮሚቴ ውስጥ
• የትምህርት ቢሮ፣
• የጤና ቢሮ፣
• የሴቶች፤ወጣቶችና ህፃናት ቢሮ
• የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
• የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ
• የውሃ ቢሮ
• የሰላምና ደህንነት ቢሮ
• ኮሙኒክሽን
• ቴክኒክና ሙያ ቢሮ
• ብልፅግና ፖርቲ
• ክልል መምህራን ማህበር
• የክልል ፖሊስ ኮሚሽን፣
• የትራንስፖርት ቢሮ ሲሆኑ ግብረ ሀይል ኮሚቴው በመጀመሪያ ሶስት ሳምንት በሳምንት ሁለት ቀን ይሰበሰባል፤ ግብረ መልስ ይሰጣል።
 የቴክኒክ ኮሚቴው በትምህርት ቢሮ ሃላፊ ሰብሳቢነት ሆኖ የየቢሮምክትል ቢሮ ሃላፊዎች/ከፍተኛ ባለሙያዎች አባላት ይሆናሉ።
ቴክኒክ ኮሚቴው በመጀመሪያ ሶስት ሳምንት በሳምንት ሶስት ቀን ይሰበሰባል።

5.4. በዞንአስተዳዳሪ/ምክትል አስተዳዳሪ/ከተማ አስተዳደር ከንቲባ/ ወይም ም/ከንቲባ የሚመራ ግብረ ሀይል ኮሚቴ እና በትምህርት መምሪያ/ሃላፊ የሚመራ የቴክኒክ ኮሚቴ ይዋቀራል።
 በግብረ ሀይል ኮሚቴ ውስጥ
• የትምህርት መምሪያ፣
• የጤና መምሪያ፣
• የሴቶች፤ወጣቶችና ህፃናት መምሪያ፣
• የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ፣
• የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር መምሪያ፣
• የውሃና ኢነርጅ መምሪያ፣
• የሰላምና ደህንነት መምሪያ፣
• ኮሙኒክሽን
• ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች መምሪያ
• ብልፅግና ፖርቲ
• መምህራን ማህበር
• የፖሊስ መምሪያ፣
• የመንገድና ትራንስፖርት መምሪያ
• የተማሪ ወላጆች ማህበር የሚካተቱ ሲሆን ግብረ ሀይልኮሚቴው በመጀመሪያ ሶስት ሳምንት በሳምንት ሶስት ቀን ይሰበሰባል። ግብረ መልስ ይሰጣል።
 የቴክኒክ ኮሚቴው በትምህርት መምሪያሃላፊ ሰብሳቢነት ከላይ የተዘረዘሩት የመምሪያምክትል ሃላፊዎች/ከፍተኛ ባለሙያዎች አባላት ይሆናሉ። ቴክኒክ ኮሚቴው በመጀመሪያ ሶስት ሳምንት በየቀኑ ይሰበሰባል።
 በወረዳ አስተዳዳሪ/ምክትል አስተዳዳሪ/ከተማ አስተዳደር ከንቲባ/ ወይም ም/ከንቲባ የሚመራ ግብረ ሀይል ኮሚቴ እና በትም/ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የሚመራ የቴክኒክ ኮሚቴ ይዋቀራል። በግብረ ሀይል ኮሚቴ ውስጥ
• ትምህርት ፣
• ጤና ፣
• የሴቶች፤ወጣቶችና ህፃናት ፣
• የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፣
• የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ፣
• የውሃና ኢነርጅ ፣
• የሰላምና ደህንነት ፣
• ኮሙኒክሽን
• ቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች
• ብልፅግና ፖርቲ
• መምህራን ማህበር
• ፖሊስ ፣
• የመንገድና ትራንስፖርት
• በጎፈቃድ ወጣቶች
• የተማሪ ወላጆች ማህበር የሚካተቱ ሲሆን ግብረ ሀይልኮሚቴው በመጀመሪያ ሶስት ሳምንት በሳምንት ሶስት ቀን ይሰበሰባል። ግብረ መልስ ይሰጣል።
 የቴክኒክ ኮሚቴው በትም/ጽ/ቤት ሃላፊ ሰብሳቢነት ከላይ የተዘረዘሩት የየጽህፈት ቤት ምክትል ሃላፊዎች አባላት ይሆናሉ።ቴክኒክ ኮሚቴው በመጀመሪያ ሶስት ሳምንት በየቀኑ ይሰበሰባል።

5.5. በቀበሌ ደረጃ
❖ በቀበሌ አስተዳዳሪ የሚመራ ኮሚቴ የሚቋቋም ሲሆን
• የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራን፣
• የጤና ኢክስቴንሽን/የጤና ጣቢያ ባለሙያዎች፣
• በጎፈቃድ ወጣቶች
• የጉድኝት ሱፐርቫይዘር
• የወላጅ መምህራን ህብረት ተወካይ አባል ይሆናሉ።ኮሚቴው በመጀመሪያ ሶስት ሳምንት በየቀኑ ይሰበሰባል፤ ግብረ መልስ ይሰጣል።

5.6. በትምህርት ቤት ደረጃ
❖ በትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር የሚመራ ሲሆን
• በቀበሌ አመራር የሚወከል
• የትምህርት ቤት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ አስተባባሪ፣
• የወላጅ መምህራን ህብረት ሰብሳቢ
• ተማሪ ህብረት ተወካይ፣
• የት/ቤት መምህራን ማህበር ተወካይ
• የአካባቢ ሚሊሻ ተወካይ የሚሳተፉ ይሆናሉ።ኮሚቴው ት/ቤቱ እስከሚከፈትና ከተከፈተ በኋላ እስከ ሶስት ስምንት ድረስ በየቀኑ ፤ከዚያ በኋላ በሳምንት ሀለት ጊዜ እስከ መጀመሪያው ወሰነ ትምህር ድረስ ይሰበሰባል፤ ግብረ መልስ ይሰጣል

6. የማስፈጸሚያ ስልት
• ት/ቤቶች ከኮቪድ ወረርሽኝ ስጋት ነፃ እንዲሆኑ የሚመለከታቸውን አካላት እንዲሳተፉ ማድረግ፤
• የትምህርት ቤቶችን አከፋፈት የሚከታተልና ዝቅተኛውን ደረጃ አሟልተው እንዲከፈቱ ማረጋገጫ የሚሰጥ አደረጃጀት ማቋቋም፤
• አስፈላጊ በሚሆኑባቸው ት/ቤቴች ተጨማሪ የመማርያ ጣቢያዎችን ማመቻቸት፣ ተጨማሪ የመማርያ ክፍሎችን መገንባት፣ጊዚያዊ የመማርያ ጣቢያዎችን ማቋቋም፣
• ተጨማሪ መምህራን ከማሟላት አኳያ ቀድሞ መምህር የነበሩና በሌላ ሙያ የተሰማሩ በጎ ፍቃደኞችን ማስተባበርና እጥረት በሚታይባቸው የትምህርት ዓይነቶች ተጨማሪ መምህራን መቅጠር፣
• ለትምህርት ቤቶች የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የንጽህና መጠበቂያ ለማሟላት ህብረተሰብን ማስተባበር፣ በቦቲ ውሃ ማቅረብ እና በትምህርት ቤቶች አካባቢ ከሚገኙ የውሃ ጣቢያዎች መስመር በመዘርጋት ለትምህርት ቤቶች የውሃ አገልግሎት ማድረስ፤
• ወላጆች ለልጆቻቸው የንፅህና መጠበቂያ ውሃ ይዘው እንዲመጡ ማደረግ ፤
• ኮቪድ 19ኝን ለመከላከልና መስፈርቱን ለማሟላት በአካባቢው የሚገኙ አማራጮችን መጠቀም፤

7. የኮሚቴ የተግባርና ሃላፊነት
7.1. የክልል ግብረ ሀይል ኮሚቴ
• የትምህርት ቤት አከፋፈት ንቅናቄን በበላይነት ይመራል፣ ያደራጃል፣ የፖለቲካ አቅጣጫ ይሰጣል፤
• ለትምህርት ቤት አከፋፈት የሚያስፈልገውን የፋይናንስና የማቴሪያል አቅርቦት በጀት ይመድባል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል
• በቴክኒክ ኮሚቴ የዳሰሳ ጥናት ላይ ተመስርቶ ትምህርት ቤቶች እንዴትና መቼ እንደሚከፈቱ ፖለቲካዊ አቅጣጫ ይሰጣል፤ወቅታዊ ግምገማ እንዲካሄድ ያደርጋል፤
• በየደረጃው የተቋቋመው ግብረ ሀይል ኮሚቴና ቴክኒክ ኮሚቴ ሀላፊነቱን መወጣቱን ይከታተላል፤ይቆጣጠራል፤

7.2. የክልል ቴክኒክ ኮሚቴ
• የትምህርት ቤት አከፋፈት ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና አለም አቀፍ የጤና ድርጅት ባስቀመጡት መመሪያና ፕሮቶኮል ላይ በመንተራስ ክልላዊ የአከፋፈት መመሪያ፣ ስልቶችንና ቼክሊስት ያዘጋጃል፣
• ለመመሪያው ተፈጻሚነት ዞኖችንና ወረዳዎችን በመመሪያው ላይ ስልጠና ይሰጣል፡፡ ውይይት ያዘጋጃል፡፡
• ለክልሉ ግብረ ሀይል ኮሚቴ ለትምህርት ቤት አከፋፈት የሚያስፈልገውን የበጀት ፍላጎት በዝርዝር ያቀርባል፡፡
• በተጨማሪም ከሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት የሀብት ማፈላለግ ሥራ ያካሄዳል
• የትምህርት ቤት አከፋፈት ፍኖተ ካርታን ያዘጋጃል ለክልሉ ግብረ ሀይል ኮሚቴ ያቀርባል ያጸድቃል፡፡
• የእያንዳንዱን ዞን የኮቪድ ስርጭትን ባገናዘበ ሁኔታ እያንዳንዱ የዞን ግብረ ሀይል ኮሚቴ ትምህርት ቤት የሚከፍትበት ሁኔታ እና ጊዜን ተለይቶ እንዲቀርብለት ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
• የጸደቀው በጀት ላይ በመንተራስ ክልላዊ ግዢዎችን ያካሄዳል በሌላ አካል ተገዝቶ ሲቀርቡም ክልላዊ ድልድል በማደረግ ለእያንዳንዱ ወረዳ እንዲደርስ ያደርጋል
• መምህራንና የትምህርት አመራሮችን በኮቪድ ወቅት ሊኖራቸው ስለሚገባ ተጨማሪ ሃላፊነት የግንዛቤ ማሳደጊያ መድረኮችን ያመቻቻል፡ ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ስራ ያሰማራል።
• ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራር የረጅም ጊዜ የትምህርት ቤት መዘጋትንና ኮቪድ ከሚያመጣው ተጽዕኖ ባገናዘበ ሁኔታ ለመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር የሥልጠና ማኑዋሎችን ያዘጋጃል፤
• የተዘጋጁትን የሥልጠና ማኑዋሎች የአሰልጣኞች ስልጠና በማካሄድ ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አስተዳደር እንዲደርሱ ያመቻቻል
• ትምህርት ቤት ከተከፈተ በኋላ የትምህርት አካሄዱን በተመለከተ የየዕለት ግብዓት የሚያገኝበትን መንገድ ያዘጋጃል፡፡ አስቸኳይ የመፍትሄ ግብረ ምልስ ይሰጣል፡፡

7.3. የዞን/ ከተማ መስተዳድር ግብረ ሀይል ኮሚቴ
• የዞኑን አጠቃላይ የትምህርት ቤት አከፋፈት ንቅናቄን በበላይነት ይመራል፣ ያደራጃል፣ የፖለቲካ አቅጣጫ ይሰጣል
• የዞኑንለትምህርት ቤት አከፋፈት የሚያስፈልገውን የፋይናንስና የማቴሪያል አቅርቦት በተመለከተ ለሚሰጠው የበጀት ማጽደቅ ሥራ ካቢኔውን በመሰብሰብ ውሳኔ ይሰጣል
• ከወረዳ ግብረ ሀይልኮሚቴ በሚደርስለት የዳሰሳ ጥናት ላይ ተመስርቶ ትምህርት ቤቶች እንዴትና መቼ እንደሚከፈቱፖለቲካዊ አቅጣጫ ይሰጣል፤ይከታተላል፤ይደግፋል፤
• በወረዳና በት/ቤት ደረጃ መማር ማስተማሩ ሰላማዊ ሁኖ መካሄዱን ወቅታዊ ግምገማ እንዲካሄድ ይመራል፤
• የወረዳ ቴክኒክ ኮሚቴና ባለሙያዎችን በማቀናጀት ለትምህርት አከፋፈት ንቅናቄ ወደ እያንዳንዱ ቀበሌ ስምሪት ያደርጋል ፣ ያቀናጃል፣ በየዕለቱ ግብረ መልስ በመውሰድ ፖለቲካዊ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡

7.4. የዞን ቴክኒክ ኮሚቴ
• በመመሪያው ላይ ለወረዳዎችና ለት/ቤቶች አመራሮች ስልጠና ይሰጣል፡፡ ውይይት ያዘጋጃል፡፡
• ለዞኑ ግብረ ሀይል ኮሚቴ ለትምህርት ቤት አከፋፈት የሚያስፈልገውን የበጀት ፍላጎት በዝርዝር ያቀርባል፡፡
• ከሌሎች ባለድርሻ አካላትን በማቀናጀት የሀብት ማፈላለግ ሥራ ያካሄዳል
• የዞኑን የትምህርት ቤት አከፋፈት ፍኖተ ካርታን (በአንድ/ በሁለት/ በሶስት ሽፍት የሚሰሩትን ) ያዘጋጃል ለዞን ግብረ ሀይል ኮሚቴ ያቀርባል ያጸድቃል፡፡
• የእያንዳንዱን ወረዳ የኮቪድ ስርጭትን ባገናዘበ ሁኔታ እያንዳንዱ የወረዳ ግብረ ሀይል ኮሚቴ ትምህርት ቤት የሚከፍትበት ሁኔታ እና ጊዜ ተለይቶ እንዲቀርብለት ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤
• የጸደቀው በጀት ላይ በመንተራስ ዞናዊ ግዢዎችን ያካሄዳል በሌላ አካል ተገዝቶ ሲቀርቡም ድልድል በማደረግ ለእያንዳንዱ ወረዳ እንዲደርስ ያደርጋል
• በዞኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮችን በኮቪድ ወቅት ሊኖራቸው ስለሚገባ ተጨማሪ ሃላፊነት የግንዛቤ ማሳደጊያ መድረኮችን ያመቻቻል፡ ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ስራ ያሰማራል።
• የተዘጋጁትን የሥልጠና ማኑዋሎች የአሰልጣኞች ስልጠና በማካሄድ ለመምህራንና ለትምህርት ቤት አመራር እንዲደርሱ ያመቻቻል
• ትምህርት ቤት ከተከፈተ በኋላ የትምህርት አካሄዱን በተመለከተ የየዕለት ግብዓት የሚያገኝበትን መንገድ ያዘጋጃል፡፡ አስቸኳይ የመፍትሄ ግብረ ምልስም ለወረዳ ይሰጣል፡፡

7.5. የወረዳ ግብረ ሀይል ኮሚቴ
• የወረዳውን አጠቃላይ የትምህርት ቤት አከፋፈት ንቅናቄን በበላይነት ይመራል፣ ያደራጃል፣ የፖለቲካ አቅጣጫ ይሰጣል
• ከወረዳ ቴክኒክ ኮሚቴ የቀረበውን ለትምህርት ቤት አከፋፈት የሚያስፈልገውን የፋይናንስና የማቴሪያል አቅርቦት ውሳኔ ይሰጣል፤
• ከቀበሌና ከት/ቤት ግብረ ሀይልኮሚቴ በሚደርስለት የዳሰሳ ጥናት ላይ ተመስርቶ ትምህርት ቤቶች እንዴትና መቼ እንደሚከፈቱፖለቲካዊ አቅጣጫ ይሰጣል፤ይከታተላል፤ይደግፋል፤
• በቀበሌና በት/ቤት ደረጃ መማር ማስተማሩ ሰላማዊ ሁኖ መካሄዱን ወቅታዊ ግምገማ እንዲካሄድ ይመራል፤
• የወረዳ ቴክኒክ ኮሚቴና ባለሙያዎችን በማቀናጀት ለትምህርት አከፋፈት ንቅናቄ ወደ ት/ቤት ስምሪት ያደርጋል ፣ ያቀናጃል፣ በየዕለቱ ግብረ መልስ በመውሰድ ፖለቲካዊ አቅጣጫ ይሰጣል፡፡
• የት/ቤት ግብረ ሃይል መረጃ/ሪፖርት መሰረት የቀረበውን የትምህርት ቤት አከፋፈት ፍኖተ ካርታ ያጸድቃል፡፡
• የት/ቤት መክፈት ጥያቄ ሲቀርብለት በሁለት ቀናት ውስጥ ምላሽ ይሰጣል፤አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በአካል ተገኝቶ ያረጋግጣል፤

7.6. የወረዳ ቴክኒክ ኮሚቴ
• ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመክፈት የተዘጋጀውን መመሪያና የትምህርት ቤት ስታንዳርድ ለትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንና የኮቪድ 19 ግብረ ሃይል ተወካይ ስልጠና እንዲሰጥ ያደርጋል፤
• የወረዳ የህዝብ ንቅናቄ መፍጠርያ መድረክ ያዘጋጃል። በየትምህርት ቤቱ የንቅናቄ ስራን የሚመሩ አመራሮችና ባለሙያዎችን ይመድባል፡አፈጻጸሙን ይከታተላል።
• በወረዳው ውስጥ ያሉ የእንዳንዱን ት/ቤት ፍኖተ ካርታ (የተቀመጡ አነስተኛ ስታንደርድን እና ሌሎች ግብዓቶችን ማሟላታቸው እንዲሁም በአንድ ሽፍት፤በሁለት ሽፍት፤በሶስት ሽፍትና ከዚያ በላይ የሆኑትን) በመለየትና በመተንተን ለወረዳ ግብረ ሀይል ያቀርባል፤ችግር ያላባቸው ት/ቤቶችን በፍጥነት እዲያስካክሉ ይደግፋል፤ይቆጣጠራል፤
• የመምህር እጥረትን ለመቅረፍ (በመጀመሪያና በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች)
o በየት/ቤቱ ያሉ መምህራን በሳምንት ውስጥ በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት መያዝ ያለባቸውን ሳምታዊ ክፍለ ጊዜ እንዲይዙ ማድረግ፤
o እያንዳንዱ ት/ቤት በትርፍነት የሚገኙ መምህራንን (በሜጀርና በማይነር) በመለየት መረጃውን ለወረዳ ቴክኒክ ኮሚቴ እነዲያሳወውቅ ማድረግ፤
o በትርፍነት የሚገኙ መምህራንን ከት/ቤት ት/ቤትና ከጉድኝት ጉድኝት በጊዚያዊነት በማዛወር መማር ማስተማሩ በአግባቡ እንዲካሄድ ያደርጋል፤
• የግብዓትና የመሰረተ ልማት ክፍተት ያለባቸውን ት/ቡቶች ይለያል፡ የምላሽ እቅድ ያዘጋጃል፡ የማስፈጸሚያ በጀት ፍላጎት በዝርዝር ለወረዳው ግብረ ሀይል ኮሚቴ ያቀርባል፡፡
• በስታንዳርዱ መሰረት ዝግጁ የሆኑ ትምህርት ቤቶችን መረጃ ከት/ቤት ግብረ ሀይል ይረከባል ዝግጁነታቸውን ያረጋግጣል፤እንዲፈቀድ ለወረዳ ግብረ ሀይል በአንድ ቀን ውስጥ እንዲደርስ ያደርጋል፤ሲፈቀድ እነዲከፈት ያደርጋል፤
• ወቅታዊ የት/ቤቶች አከፋፈት መረጃ ይሰበስባል፡ ይገመግማል፡ በወረዳ ግብረ ሀይል በኩል ለዞን ግብረ ሀይል ይልካል፡ግብረ መልስ ለትምህርት ቤቶች ይሰጣል።
• ለኮቪድ መከላከያ የሚያገለግሉ ቁሳቁስ ተገዝተው በሚቀርቡበት ጊዜ ድልድል በማደረግ ለእያንዳንዱ ትምህርት ቤት እንዲደርስ ያደርጋል፤
• መምህራንና የትምህርት አመራሮችበኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝ ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ ሃላፊነት የግንዛቤ ማሳደጊያ መድረኮችን ያመቻቻል፡ ግንዛቤ በመፍጠር ወደ ስራ ያሰማራል።
• ለትምህርት ቤት አመራር፡መምህራንና ባለድርሻ አካላት በኮቩድ 19 ወረርሽኝ ወቅት በመማር ማስተማርና የክፍል ውስጥ የተማሪ አያያዝ በተመለከተ ስልጠና ይሰጣል።
• ከእያንዳንዱ ት/ቤት ግብረ ሀይል አጠቃላይ መረጃ ለማግኘት የመከታተያ ቸክሊስተ አዘጋጅቶ ይልካል፤ የየዕለት የትምህርት ሂደት ሁኔታን መረጃ ያሰባስባል፣ ያጠናቅራል በወረዳ ግብረ ሀይል በኩል ለዞን ግብረ ሀይል ሪፖርት ያደርጋል፡፡ ለት/ቤቶችም ግብረ መልስ ይሰጣል፤
• እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የጤና ኮሚቴ እንዲኖረው ይሰራል፤አፈፃፀሙን ይከታላል፤
• በወረዳ ጽ/ቤት ያሉትን ባለሙያዎች በማቀናጀት ጉድኝቶችን በመከፋፈል ሙያዊ ድጋፍና ክትትል እንዲያደርጉ ያሰማራል፡፡
• ወቅታዊ የግንዛቤ ማስጨበጥ፡ ተግባቦትና የህብረተሰብ ንቅናቄ መድረክ ያዘጋጃል፡ ትምህርት ይሰጣል፡
• እያንዳንዱ ትምህርት ቤት በበሽታው የተጠረጠረ ተማሪን/ሰውን በጊዜያዊነት ለማቆያነት የሚያገለግል የማቆያ ቦታ እንዲያዘጋጁ ድጋፍ፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
• እያንዳንዱ ት/ቤት ኮቪድ ወረርሽኝን የሚከታተል ቋሚ ተወካይ እንዲኖረውና ስልጠና በጠየና ባለሙያዎ እንዲሰጥው ያደርጋል፤አፈፃፀሙን ይከታላ፤

7.7. የቀበሌ ግብረ ሀይል
• የትምህርት ቤት አከፋፈት የህዝብ ንቅናቄ ስራን በበላይነት ያስተባብራል፡
• በትምህርት ቤት አከፋፈት የተዘጋጀውን መመሪያ ያሟሉ ትምህርት ቤቶችን ከት/ቤት ግብረ ሀይል ጋር በመሆን ማረጋገጫ ይሰጣል፡ በወረዳ ግብረ ሀይል ሲፈቀድለት እንዲከፈቱ ያደርጋል።
• የትምህርት ቤት አከፋፈት ግብረ ሀይል ኮሚቴን ያስተባብራል፤ ይመራል፡፡
• የትምህርት ቤቶች ግብዓቶች እንዲሟሉ አማራጮችን ያዘጋጃል፡ ህብረተሰቡንና ወላጆችን በማስተባበር በወቅቱ እንዲሟ ያደርጋል፤አፈጻጸሙን ይከታተላል።
• በቀበሌው ውስጥ እድሚያው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ትምህርት ቤት እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

7.8. የትምህርት ቤት ግብረ ሀይል
• ት/ቤቱን ለመክፈት የሚያስችል ዝርዝር የድርጊት መርሀ ግብር በማውጣት ያፀድቃል፤የተጓደሉ ግብዓቶች የሚሟሉበትን መንገድ ያስቀምጣል፤
• በድርጊት መርሀ ግብር መሰረት ት/ቤቱን መክፈት የሚችል መሆኑን ያረጋግጣል፤ሲፈቀድለት ይከፍታል፤
• በትምህርት ቤት ደረጃ ኮቪድ 19 በመከላከል መማር ማስተማሩ በአግባቡ ማከናውን እንዲቻል የት/ቤቱን ማህበረሰብና ወላጆችን ያወያያል፤ የጋራ መግባባት ይፈጥራል፤
• ትምህርት ሲጀመር በመጀመሪያው ቀን ከተማሪዎች ጋር ስለኮቪድ ወረርሽኝና ስለመማር ማስተማሩ ውይይት በማድረግ መግባባት ላይ ይደርሳል፤ በመጨረሻ የፕሮቶኮል ፊርማ ይፈራረማል፤
• የቀበሌውን ማህበረሰብ በማቀናጀት የሀብት ማፈላለግ (የማቴሪያል፣ የጉልበት፣ የንብረት፣ የገንዘብ፣ የዕውቀት ዕገዛ) እንዲያደርጉ ንቅናቄ ያደርጋል፡፡
• የትምህርት ቤት አከፋፈት ፍኖተ ካርታ (በአንድ /በሁለት / በሶስት ሽፍት እና ከዚያ በላይ) እንደት/ቤቱ ተጨባጭ ሁኔታ ለይ ያዘጋጃል ለወረዳ ግብረ ሀይል በማቅረብ ያጸድቃል፡፡
• በመንግስት ለኮቪድ መከላከያ የሚያገለግሉ ቁሳቁስ ሲመደቡ በፍጥነት ወደ ትምህርት ቤት መደረሳቸውን ያረጋግጣል፤
• በት/ቤቱ አከፋፈት ላይ ወላጆችን ያወያያል፤በመጨረሻም የፕሮቶኮል ፊርማ ይፈራረማል፤
• የትምህርት ቤቱን እለታዊ መረጃ ይሰበሰብባል፣ ለሚፈጠሩ ሁነቶች መረጃ ለወረዳ ግብረ ሀይል ይሰጣል፤ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን አስፈላጊውን ምላሽ ይሰጣል።
• በትምህርት ቤት አከፋፈት ሂደት ኮቪድን ከመከላከል አኳያ የተቀመጡት አስገዳጅ መስፈርቶች ሥራ ላይ ስለመዋላቸው ኃላፊነት በመውሰድ ያረጋግጣል፡፡
• በትምህርት ቤት ተከታታይ የኮሚኒኬሽን ሥልት በማዘጋጀት የመከላከያ መንገዶችን ያስተምራል፣ የባህሪ ለውጥ እንዲመጣና ቀጣይነት ያለው የአህዝቦት ስራ ይሰራል።
• ትምህርት ቤቱ የጤና ኮሚቴ እንዲኖረውደርጋል፤ከኮቪድ ጋር የተያያዙ ስራዎችን ያስተባብራል፤ መፍትሄ የሚሹ ጉዳዮችን ወደቀጣይ አካል ያቀርባል፤
• በት/ቤቱ ውስጥ አጠቃላይ የኮቪድ ወረርሽኝን የሚከታተል ተወካይ ይመድባል፤ከወረዳ ቴክኒክ ኮሚቴ ጋር በመመካከር ስልጠና እንዲያገኝ ያደረጋል፤
• በበሽታው የተጠረጠረ ተማሪን/ሰውን በጊዜያዊነት ለማቆያነት የሚያገለግል የማቆያ ቦታ ያዘጋጃል፤

8. ሌሎች የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች የስራ ድርሻና ሃላፊነት
8.1. የክልል ጤና ቢሮ
• ክልላዊ የኮቪድ መረጃ በተመለከተ አጠቃላይ እና የየዕለት ሁኔታን ለትምህርት ቢሮ ይሰጣል፡፡ በጋራ ጥምር ኮሚቴ አማካይነት በትምህርት ቤት አከፋፈትና አዘጋግ ላይ ምክረ ሃሳብ ያቀርባል፡ ያረጋግጣል።
• በትምህርት ቤት አከፋፈት ዙርያ ጤና ተኮር የሆኑ ፕሮቶኮሎች ላይ ለትምህርት አመራሮች ስልጠና ይሰጣል፡
• ወቅታዊ የበሽታ ስርጭት ቅኝት በትምህርት ቤቶችና በዙርያቸው ያደርጋል፡ መረጃውን ለሚለከታቸው አካላት በፍጥነት ያቀርባል፡
• በትምህርት ቤቶች የወረርሽኝ ክስተት ለማረጋገጥ የላብራቶሪ ምርመራ ያካሂዳል።
• የጤና ነክ ግብዓቶች ለትምህርት ቤት ግዢ ከመፈጸማቸው በፊትና በኋላ ስለጥራታቸውን አግባብነታቸው ሙያዊ ምክር ይሰጣል፡፡
• ለኮቪድ 19 ቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት ልዩ ድጋፍ (የመተንፈሻ ችግርና ሌሎች ተዘማጅ ችግር ላሉባቸው) ያደርጋል፡
• በትምህርት ቤቶች የኮቪድ 19 ተጠቂ/ ተጠርጣሪ ሲገኝ የአደጋ ምላሽና አመራር ስርዓት ይዘረጋል።
• ወቅታዊ የግንዛቤ ማስጨበጥ፡ ተግባቦትና የህብረተሰብ ንቅናቄ መድረክ ያዘጋጃል፡ ትምህርት ይሰጣል፡

8.2. የክልል ውሃ ቢሮ
• በትምህርት ቤቶች የውሃ መሰረተ ልማት ለማስፋፋት በስራ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን በመፈተሽና ለተፈላጊ ዓላማ ዳግም በማቀድ (Re-programming WaSH Projects) ፈጣን እርምጃዎች እንዲወሰዱ ያደርጋል።
• በክልሉ ትምህርት ቤቶች አጠቃላይ የውሃ አቅርቦት ዳሰሳ ላይ በመንተራስ የትምህርት ቤቶች ውሃ አቅርቦት ስትራቴጂ በማዘጋጀት እገዛ ያደርጋል፡፡
• በትምህርት ቤቶች የእጅ መታጠቢያ መሰረተ ልማቶችን በተለያየ አማራጭ (ከከተማው ውሃ ተስቦ የሚመጣበትን፣ በተንቀሳቃሽ ተሽኸርካሪ ውሃ በቦቲ የሚዳረስበትንና በሌሎች የውሃ አቅርቦት ዘዴዎች ውሃ እንዲደርስ ያደርጋል) እንዲቀርቡ ድጋፍ ያደርጋል።
• የንጽህና መጠበቂያና የቆሻሻ ማስወገጃ ስልቶችን በመቀየስ ሙያዊ እገዛ ያደርጋል።

8.3. የክልል የሴቶች ወጣቶችና ህፃናት ቢሮ
• ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጋላጭ የሆኑ ህፃናትና ሴቶችን በመለየት ሀብት ያሰባስባል፣ ድጋፍ እንዲደርሳቸው ያደርጋል
• ሴቶችና ተጋላጭ ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ ስልት በመቀየስ ንቅናቄ ከመፍጠር አኳያ ከትምህርት ቢሮ ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡
• በኮቪድ ምክንያት ለጾታዊ ጥቃትና ለሥነ ልቦና ቀውስ ተጋላጭ ለሆኑ ተማሪዎች የሥነ ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ የሚያደርጉ የማህበረሰብ (Social Workers) ሰራተኞችን ይመድባል፡ ያስተባብራል፡
• በማህበረሰብ ሰራተኞች አማካይነት ለመምህራንና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያና መቆጣጠርያ ግብረ ሃይል ስልጠና ይሰጣል።

8.4. የክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ
• ከትምህርት ቤት አከፋፈት ጋር በተያያዘ በጀት ይመድባል። የበጀት እጥረት ባለበት ጊዜ የቅድሚያ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን በመለየት በጀት ይመድባል።
• ከማእከል የሚላከውን የትምህርት ቤት ድጎማ በጀት በፍጥነት ስራ ላይ እንዲውል ድጋፍ ያደርጋል፡ አፈጻጸሙን ይከታተላል።
• የክልሉን የትምህርት ቤት አከፋፈት የሚያግዝ ሃብት ያሰባስባል፡ ስራ ላይ እንዲውል ድጋፍ ያደርጋል።
• የተሳለጠ የግዢና የፋይናንስ አካሄድ ስልት ይቀይሳል፤ ሥራ ላይ ያውላል፡፡
• የጸደቀው በጀት ላይ በመንተራስ የወረዳ ግዢዎችን ያካሄዳል

8.5. የከተማ መስተዳድር/ወረዳ ጤና ጽ/ቤት
• የከተማ መስተዳድር/የወረዳውን የኮቪድ መረጃ በተመለከተ አጠቃላይ እና የየዕለት ሁኔታን ለትምህርት ጽ/ቤት ይሰጣል፡፡ በጋራ ጥምር ኮሚቴ አማካይነት በትምህርት ቤት አከፋፈት ላይ ምክረ ሃሳብ ያቀርባል፡ ያረጋግጣል።
• በትምህርት ቤት አከፋፈት ዙርያ ለትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንና ፎካል ፐርሰን ስልጠና ይሰጣል፡
• ወቅታዊ የበሽታ ስርጭት ቅኝት በትምህርት ቤቶችና በዙርያቸው ያደርጋል፡ መረጃውን ለሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት ያቀርባል፡
• በትምህርት ቤቶች የወረርሽኝ ክስተት ለማረጋገጥ የላብራቶሪ ምርመራ ያካሂዳል።
• የጤና ነክ ግብዓቶች ለትምህርት ቤት ግዢ ከመፈጸማቸው በፊትና በኋላ ስለጥራታቸውና አግባብነታቸው ሙያዊ ምክር ይሰጣል፡፡
• ለኮቪድ 19 ቫይረስ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት ልዩ ድጋፍ (የመተንፈሻ ችግርና ሌሎች ተዘማጅ ችግር ያሉባቸው) ያደርጋል፡
• በትምህርት ቤቶች የኮቪድ 19 ተጠቂ/ ተጠርጣሪ ሲገኝ የአደጋ ምላሽና አመራር ስርዓት ይዘረጋል።
• ወቅታዊ የግንዛቤ ማስጨበጥ፡ ተግባቦትና የህብረተሰብ ንቅናቄ መድረክ ያዘጋጃል፡ ትምህርት ይሰጣል፡

8.6. የከተማ አስተዳድር/ወረዳ ውሃ ጽ/ቤት
• በከተማ አስተዳድር/በወረዳ ያሉትን ትምህርት ቤቶች አጠቃላይ የውሃ አቅርቦት ዳሰሳ ላይ በመንተራስ የትምህርት ቤቶች ውሃ አቅርቦት ስትራቴጂ በማዘጋጀት እገዛ ያደርጋል፡፡
• በትምህርት ቤቶች የእጅ መታጠቢያ መሰረተ ልማቶችን በተለያየ አማራጭ እንዲቀርቡ ድጋፍ ያደርጋል።
• የንጽህና መጠበቂያና የቆሻሻ ማስወገጃ ስልቶችን በመቀየስ ለወረዳ ትምህርት ትምህርት /ጽ/ቤት ሙያዊ ዕገዛ ያደርጋል፡፡
• ውሃ የሌላቸው ትምህርት ቤቶችን በመለየት ከከተማው ውሃ ተስቦ የሚመጣበትን፣ በተንቀሳቃሽ ተሽከርካሪ ውሃ በቦቲ የሚዳረስበትንና በሌሎች የውሃ አቅርቦት ዘዴዎች ውሃ እንዲደርስ ያደርጋል፡

8.7. የከተማ አስተዳድር/ወረዳ የሴቶች ወጣቶችና ህፃናት ጽ/ቤት
• ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጋላጭ የሆኑ ህፃናትና ሴቶችን በመለየት ሀብት ያሰባስባል፣ ድጋፍ እንዲደርሳቸው ያደርጋል
• ሴቶችና ተጋላጭ ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ ስልት በመቀየስ ንቅናቄ ከመፍጠር አኳያ ከትምህርት ጽ/ቤት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡
• በኮቪድ ምክንያት ለጾታዊ ጥቃትና ለሥነ ልቦና ቀውስ ተጋላጭ ለሆኑ ተማሪዎች የሥነ ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ የሚያደርጉ የማህበረሰብ ሰራተኞችን ይመድባል፡ ያስተባብራል፡
• በማህበረሰብ ሰራተኞች አማካይነት ለመምህራንና የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያና መቆጣጠርያ ግብረ ሃይል ስልጠና ይሰጣል።

8.8. የከተማ አስተዳድር/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
• የከተማ መስተዳድርየወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ከትምህርት አከፋፈት ጋር በተያያዘ በጀት ይመድባል፡ የበጀት እጥረት ባለበት ጊዜ የቅድሚያ ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን በመለየት በጀት ይመድባል።
• ከክልል የተላከውን በጀት በፍጥነት ስራ ላይ እንዲውል ድጋፍ ያደርጋል፡ አፈጻጸሙን ይከታተላል።
• የተሳለጠ የግዢና የፋይናንስ አካሄድ ስልት ይቀይሳል ሥራ ላይ ያውላል፡፡
• የጸደቀው በጀት ላይ በመንተራስ የወረዳ ግዢዎችን ያካሄዳል

8.9. የቀበሌ ጤና ጣቢያ ወይም ጤና ኬላ
• የቀበሌው የኮቪድ መረጃ በተለይም ተማሪዎች ላይ ትኩረት በማድረግ አጠቃላይ እና የየዕለት ሁኔታን/መረጃ ለትምህርት ቤት ይሰጣል፡፡
• የተዘጋጁ ማኑዋሎችን በመጠቀም ጤና ነክ ስልጠናዎችን ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ ይሰጣል
• ከኮቪድ አኳያ ሙያዊ ድጋፍና ክትትል የሚያደርጉ ባለሙያዎችን የጤና ጣቢያው ወይም የጤና ኬላ ባለሙያዎችን ያሰማራል፡፡
• በትምህርት ቤት ከተመደበው የኮቪድ ተወካይ ጋር በቅርብ ቁርኝት ይሰራል፡፡ ኮቪድን ከመከላከል አኳያ የተቀመጡት አስገዳጅ መስፈርቶች ሥራ ላይ ስለመዋላቸው ኃላፊነት በመውሰድ ያረጋግጣል፡፡

8.10. የቀበሌ የሴቶችና ወጣቶች አደረጃጀት
• ተጋላጭ ለሆኑ ህፃናትና ሴቶች የትምህርት ቤት ቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ ሀብት ማሰባሰብና ከትም/ት ቤቱ ጋር በጋራ በመሆን መደገፍ
• ሴቶችና ተጋላጭ ህፃናት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ ስልት በመቀየስ ንቅናቄ መፍጠር
• በኮቪድ ምክንያት ለጾታዊ ጥቃትና ለሥነ ልቦና ቀውስ ተጋላጭ ለሆኑ ተማሪዎች የሥነ ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ ማድረግ

የጊዜ ሰሌዳ
ተ.ቁ የሚከናወነው ተግባር የሚከናወንበት ጊዜ ምርመራ
1 የወረዳና የት/ቤት አመራር በመመሪያው ላይ ተወያይተው እቅድ ያቅዳሉ እስከ መስከረም 30/2013
2 ት/ቤቶች በዝርዝር የመክፈት አቅማቸውን ለይተው ዝግጁ መሆናቸውን ለወረዳ ግብረ ሀይል ማሳወቅ እስከ ጥቅምት 4/2013 ድረስ
3 የወረዳው ግብረ ሀይል የሚከፈቱ ት/ቤቶችን አረጋግጦ ምላሽ መስጠት ጥቅምት 6/2013
4 በሂደቱ የማይከፈቱ ት/ቤቶች ካሉ በአጭር ጊዜ መስፈርቱን አሟልተው እንዲከፈቱ የወረዳ ግብረ ሀይል እቅጣጫ ያስቀምጣል፤በትኩረት ማነስ የማይከፈቱ ካሉ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤ሀላፊነቱን የማይወጣውን ተጠያቂ ያደርጋል፤ ከጥቅምት 6-9/2013

በመጀመሪያው ዙር ለሚከፈቱ
ከጥቅምት 9-15/2013 በሁለተኛ ዙር ለሚከፈቱ
5 ሁሉም ት/ቤቶች እንዲከፈቱ ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ማድረግ ከጥቅምት1-15/2013
አባሪ-1
የትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም መረጃ ( በአንድ መማሪያ ክፍል 30 ተማሪዎች)
ተ.ቁ ዞን / ከተማ አስተዳደር በአንድ ፈረቃ/በሙሉቀን ማስተማር የሚችሉ በሁለት ፈረቃ ማስተማር የሚችሉ በሶስት ፈረቃ ማስተማር የሚችሉ መረጃቸው ያልተጣራ ት/ቤቶች ጠቅላላድምር
የመጀ/ ደረጃ 2ኛ ደረጃ የመጀ/ ደረጃ 2ኛ ደረጃ የመጀ/ ደረጃ 2ኛ ደረጃ የመጀ/ ደረጃ 2ኛ ደረጃ የመጀ/ ደረጃ 2ኛ ደረጃ
1 ባህርዳር 0 0 48 9 16 6 16 6 80 21
2 ምዕ/ጎጃም 131 0 373 10 356 29 86 24 946 63
3 አዊ 22 0 282 6 199 18 37 18 540 42
4 ምስ/ ጎጃም 0 0 543 17 315 20 82 33 940 70
5 ጎንደር 0 0 16 3 18 2 10 7 44 12
6 ማዕ/ ጎንደር 182 3 509 8 221 8 105 29 1017 48
7 ምዕ/ ጎንደር 103 0 124 8 0 2 0 0 227 10
8 ሰ/ ጎንደር 1 0 42 1 155 6 257 12 455 19
9 ደ/ጎንደር 110 3 534 13 242 20 213 32 1099 68
10 ሰሜን ወሎ 173 4 368 10 227 37 3 4 771 55
11 ዋግኸምራ 48 11 128 6 77 6 20 1 273 24
12 ደሴ 0 0 48 13 0 0 0 0 48 13
13 ደቡብ ወሎ 89 1 730 21 40 20 375 25 1234 67
14 ኦሮሞ 2 3 104 13 139 5 17 0 262 21
15 ሰሜን ሸዋ 60 3 758 17 245 26 12 18 1075 64
ድምር 921 28 4607 155 2250 205 1233 209 9011 597
10.22% 4.69% 51.12% 25.96% 24.96% 34.33% 13.68% 35.00%

አባሪ-2
የትምህርት አሰጣጥ አማራጮች
አማራጭ አንድ
ዝቅተኛ የተማሪ ቁጥር ባለባቸው ት/ቤቶች በአንድ ዴስክ የተማሪዎች ቁጥር ካንድ በላይ ካልሆነና በክፍል ውስጥ 30 የሚሆኑ ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ት/ቤት በነበረው አሰራር በሙሉ ቀን ወይም በሁለት ፈረቃ ትምህርቱን ማካሄድ ይችላሉ፡፡ እነዚህ ት/ቤቶች መጠነኛ የሆነ የክፍል ጥበት የሚገጥማቸው ከሆነም ጊዚያዊ መማሪያ ክፍሎችን ከአካባቢው ማህረሰብ ጋር በመነጋር መፍትሄ በመስጠት መማር ማስተማሩን ማካሄድ ይችላሉ፡፡

አማራጭ ሁለት
ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር ባለባቸው ት/ቤቶች የአንድ ክፍለ ጊዜ መጠንን ከ40 ደቂቃ ወደ 30 ደቂቃ በመቀነስ በ 2 ፈረቃ ይሰጥ የነበረውን ትምህርት በ3 ፈረቃ እንዲሰጥ ማድረግ
በዚህ መሰረት የአንድ ቀን ትምህርት ጧት በ1፡30 ተጀምሮ በ11፡40 የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
የፈረቃ አደረጃጀቱም በሚከተለው መልኩ ይሆናል፡፡
ክፍለ ጊዜ የመጀመሪያ ፈረቃ ሁለተኛ ፈረቃ ሶስተኛ ፈረቃ
1ኛ 1፡30- 2፡00 5፡00- 5፡30 8፡30- 9፡00
2ኛ 2፡00- 2፡30 5፡30- 6፡00 9፡00- 9፡30
3ኛ 2፡30-3፡00 6፡00-6፡30 9፡30-10፡00
ረፍት 3፡00፡3፡10 6፡30፡6፡40 10፡00-10፡10
4ኛ 3፡10-3፡40 6፡40-7፡10 10፡10-10፡40
5ኛ 3፡40-4፡10 7፡10-7፡40 10፡40-11፡10
6ኛ 4፡10- 4፡40 7፡40- 8፡10 11፡10-11፡40
ከአንድ ፈረቃ ወደ ሌላ ፈረቃ ሲሸጋገር የ20 ደቂቃ የመለዋወጫ ጊዜ ይኖራል፡

አማራጭ ሶስት
በዚህ አማራጭ ውስጥ ሚገቡ ት/ቤቶች ከፍተኛ የሆነ የተማሪ ቁጥርና ዝቅተኛ የመማሪያ ክፍል ያላቸው ሲሆኑ ትምህርቱ በሳምንት ለ5 ቀናት (ከሰኞች እስከ አርብ) መሰጠቱ ቀርቶ ቅዳሜ ጨምሮ በ3 እና 4 ቀናት ሆኖ በፈረቃ እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ይህ አማራጭ ከሰኞ እስከ ረቡዕ አንድ ፈረቃ፤ ከሀሙስ እስከ ቅዳሜ ሁለተኛ ፈረቃ አድርጎ መጠቀም ነው፡፡ በየሳምንቱ የፈረቃ መቀያየር የሚኖር ሲሆን ከሰኞ እስከ እሮብ የነበረው ፈረቃ በሚቀጥለው ሳምንት ከሀሙስ እስከ ቅዳሜ እንዲማር ይደረጋል፡፡ በዚህ አማራጭ ትምህርቱ በ40 ደቂቃ ይሰጣል ነገርግን የሁለት የትምህርት ቀን የሚቀንስ ሲሆን ት/ቤቶች በራሳቸው ተጫባጭ ሁኔታና ከመምህራን ጋር በመመካከር ተማሪዎችን የመደገፍ ሥራ መስራት ያስፈልጋል፡፡

(ቅፅ አንድ፡ የተማሪ)
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
በ---------------------ዞን/ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ
በ-----------------------ወረዳ ትም/ጽ/ቤት
በ-------------------------ት/ቤት
ኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል መማር ማስተማሩ በውጤታማነት እንዲፈፀም ለማድረግ የተዘጋጀ የስምምነት ሰነድ
እኔ ተማሪ----------------------------በ-----------------------ት/ቤት የ-----------ክፍል ተማሪ ስሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የኮቪድ-19ኝ ወረርሽኝ መከላካያ መስፈርቶችን በመፈፀም ሀላፊነቴን እወጣለሁ፡፡
መስፈርቶች
1. የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) በማድረግ ትምህርቴን እከታተላለሁ፤፤
2. በአንድ መቀመጫ (Combined Desk) ብቻየን እቀመጣለሁ፣
3. በትምህርት ቤት ውስጥ በ2 ሜትር ርቀት ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ንክኪን እከላከላለሁ ፤
4. ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ማንኛውንም ነገር (እስክርቢቶ፤መፃህፍት፤ደብተር ወዘተ) አልዋስም/በጋራ አልጠቀምም፤
5. በት/ቤቱ ውሃ ከሌለ ለንፅህና መጠበቂያ የሚሆን ውሃ ከቤቴ በማምጣት ንፅህናየን እጠብቃለሁ፤
6. በመምህራን የሚሰጡ የክፍልና የቤት ስራዎችን በግሌ ብቻ እሰራለሁ፤

የተማሪ ስም--------------------------------ፊርማ -------------ቀን-----------------
የሥም ጠሪው መምህር ስም----------------------------ፊርማ ------------ቀን----------
የት/ቤቱ ማህተም
(ቅፅ ሁለት፡ የወላጅ/ያሳዳጊ)
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
በ---------------------ዞን/ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ
በ-----------------------ወረዳ ትም/ጽ/ቤት
በ-------------------------ት/ቤት
ኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል መማር ማስተማሩ በውጤታማነት እንዲፈፀም ለማድረግ የተዘጋጀ የስምምነት ሰነድ
እኔ ወላጅ/አሳዳጊ----------------------------በ-----------------------ት/ቤት የ-----------ክፍል ተማሪ----------------------ወላጅ/አሳዳጊ ስሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የኮቪድ-19ኝ ወረርሽኝ መከላካያ መስፈርቶችን በመፈፀም ሀላፊነቴን እወጣለሁ፡፡
መስፈርቶች
1. ልጄ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) በማድረግ ትምህርቱን እንዲማር እከታተላለሁ፤፤
2. ልጄ በትምህርት ቤትም ሆነ ከት/ቤት ውጭርቀቱን/ቷንእንዲጠብቅ/ እንድትጠብቅእከታተላለሁ
3. ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ማንኛውንም ነገር (እስክርቢቶ፤መፃህፍት፤ደብተር ወዘተ) በጋራ አንዳይጠቀም/እንዳትጠቀም በማሟላት እከታተላለሁ፤
4. በት/ቤቱ ውሃ ከሌለ ለንፅህና መጠበቂያ የሚሆን ውሃ ከቤት በመውሰድ ንፅህናውን/ዋን እንዲጠብቅ/እንድትጠብቅ አደርጋለሁ፤
5. በመምህራን የሚሰጡ የክፍልና የቤት ስራዎችን በግሉ/ሏ ብቻ እንዲሰራ/እንድትሰራ አደርጋለሁ፤
6. ት/ቤቱ ኮቪድ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚያደረገው ድጋፍ አቅሜ በፈቀደ በጉልበት፤በምክር፤በገንዘብና በማቴሪያል እደግፋለሁ፤
የወላ/አሳዳጊ ስም--------------------------------ፊርማ -------------ቀን-----------------
የስም ጠረ መምህር ስም----------------------------ፊርማ ------------ቀን----------
የት/ቤቱ ማህተም
(ቅፅ ሶስት፡ የመምህራን)
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
በ---------------------ዞን/ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ
በ-----------------------ወረዳ ትም/ጽ/ቤት
በ-------------------------ት/ቤት
ኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል መማር ማስተማሩ በውጤታማነት እንዲፈፀም ለማድረግ የተዘጋጀ የስምምነት ሰነድ
እኔ መምህር----------------------------በ-----------------------ት/ቤት የ-------------ትምህርት ስሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ የኮቪድ-19ኝ ወረርሽኝ መከላካያ መስፈርቶችን በመፈፀም ሀላፊነቴን እወጣለሁ፡፡
መስፈርቶች
1. የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) በማድረግ አስተምራለሁ፤፤
2. አንድ ተማሪ በአንድ መቀመጫ (Combined Desk) ተቀምጦ/ጣ እንድትማር እከታተላለሁ፣
3. በትምህርት ቤት ውስጥ በ2 ሜትር ርቀት በመሆን ከሌሎች ተማሪዎችና ጋር ንክኪን እከላከላለሁ ፤
4. ተማሪዎች እስክርቢቶ፤መፃህፍት፤ደብተር ወዘተ በጋራ እንዳይጠቀሙ እቆጣጠራለሁ፤
5. ተማሪዎች የግል ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ እደግፋለሁ፤እቆጣጠራለሁ፤
6. በመምህራን የሚሰጡ የክፍልና የቤት ስራዎችን በግላቸው እንዲሰሩ ክትትል አደርጋለሁ፤
7. ኮቪድ ወረርሽኝን ለመከላከል ሲባል ት/ቤቱ በሚዘረጋው የጊዜ ሰሌዳ እስከ ሁለት ፈረቃ በማስተማር ተማሪዎችን አግዛለሁ፤
8. ት/ቤቱ ኮቪድ ወረርሽኝን ለመከላከል በሚፈጥረው አደረጃጀት በፈቃደኝነት/ስመደብ እሰራለሁ፤

የመምህሩ ስም--------------------------------ፊርማ -------------ቀን-----------------
የር/መምህር ስም----------------------------ፊርማ ------------ቀን----------
የት/ቤቱ ማህተም
(ቅፅ አራት፡ የት/ቤት)
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
በ---------------------ዞን/ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ
በ-----------------------ወረዳ ትም/ጽ/ቤት
ኮቪድ 19 ወረርሽኝን በመከላከል መማር ማስተማሩ በውጤታማነት እንዲፈፀም ለማድረግ የተዘጋጀ የስምምነት ሰነድ
የ--------------------------------የመጀመሪያ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት በኮቪድ19 ምክንያት የተዘጉ ት/ቤቶችን መልሶ ለመከፈት የተቀመጡ መስፈርቶችን ት/ቤቱ ያሟላ መሆኑን ያረጋገጥን ስለሆነ እንዲከፈት እንጠይቃለን፡፡
መስፈርቶች
1. ት/ቤቱ ለሁሉም ተማሪየአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) አዘጋጅቷል፤
2. ት/ቤቱ በአንድ በፈረቃ ከአንድ ሺ ተማሪ በላይ አለማስተናገዱን አረጋግጧል፤
3. በአንድ መማርያ ክፍል 30 ተማሪዎች ብቻ እንዲስተናገዱ ተደርጎ የክፍል ድልድል ተደርጓል፣
4. አንድ መምህር በሳምንት እስከ 45 ክፍለ ጊዜ እንዲያስተምር በማድረግ የመምህር እጥረትን ለመፍታት ከመምህራን ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል፣
5. በአንድ የተማሪ መቀመጫ (Combined Desk) አንድ ተማሪ ብቻ ለማስቀመጥ ዝግጅት ተጠናቋል፣
6. በትምህርት ቤት ውስጥ በ2 ሜትር አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ግዴታ መሆኑ መረጋገጥ የጋራ መግባባት ተደርሷል፤
7. ትምህርት ቤቱን በኬሚካል ለማጽዳት፤ ለሳኒታይዘር/ለእጅ ንጽህና መጠበቂያ ውሃና ሳሙና ተዘጋጀቷል
8. ት/ቤቱ ካለው የተማሪና የክፍል ጥምርታ አኳያ ሊያስምር የሚችልበት አቅም በአንድ/ በሁለት/በሶስት/ እና በላይ ሽፍት የሚሰራ መሆኑ ተለይቷል፤
9. ት/ቤቱ በመስፈርቱ መሰረት መሟላት የሚገባውን ግብዓቶች (የውሃ አቅርቦት፤ የዴስክ፤ በቂ መምህር፤የመፀዳጃ ቤት) አሟልቷል፤
10. በትምህርት ቤቱ አስፈላጊ የሆኑት አደረጃጀቶች (ግብረ ሀይል፤የጤና ኮሚቴ፤ኮቪድ ወረርሽኝን የሚከታተል ፎካል ፐርሰን ወዘተ) ተደራጅተው ወደሥራ ገብተዋል፤
11. መማር ማስተማሩን ለማስጀመር የተማሪ ድልድል፤የክ/ጊዜ ድልድል፤የሽፍት ድልድል ወዘተ ተጠናቋል፤
የት/ቤት ግብረ ሀይል አባላት
1. ስም--------------------------------ፊርማ -------------ቀን-----------------
2. ስም--------------------------------ፊርማ ------------ቀን------------------
3. ስም---------------------------------ፊርማ-----------ቀን-------------------
4. ስም---------------------------------ፊርማ-----------ቀን------------------
5. ስም----------------------------------ፊርማ-----------ቀን-------------------
የት/ቤቱ ማህተም

አማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
መስከረም 2013
ባህር ዳር

Address

Mersa

Opening Hours

Monday 08:30 - 05:30
Tuesday 04:00 - 04:00
Wednesday 08:30 - 05:30
Thursday 20:30 - 05:30
Friday 08:30 - 05:30

Telephone

+251333330549

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habru Woreda Road And Transport Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share