West Omo Zone Plan and Development Department

West Omo Zone Plan and Development Department plan department Governmental sectors

25/03/2026

የምዕራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ የ2017 የሶሽዮ-ኢኮኖሚ መረጃ ማጥራት፣ በአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት እና የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ከክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ለዞን...
23/03/2026

የምዕራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ የ2017 የሶሽዮ-ኢኮኖሚ መረጃ ማጥራት፣ በአንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት እና የስነ-ህዝብ ጉዳዮች ከክልል ፕላንና ልማት ቢሮ ባለሙያዎችን በመጋበዝ ለዞን መምሪያ ኃላፊዎች፣ለልማት ዕቅድ ባለሙያዎች፣ለወረዳ ፕላን ጽ/ቤት ማኔጅመንት አካላት እና የወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

13/03/2026

ምዕራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ
የምህራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ በዞኑ ከሚገኙ መምሪዎች አንዱ ሲሆን በሰባት(7) የወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የተዋቀረና በሶስት(3) የከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች የተዋቀረ ሲሆን በዞኑ በድምሩ አስር(10) መዋቅሮች ሲኖሩት የፕላን ልማት ጽ/ቤት የተዋቀረባቸው በሰባቱ(7) ወረዳዎች ሲሆን የከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት ጽ/ቤቶች መዋቅር ሲስተካከል እንደሚዋቀሩ ያለዉ መረጃ ያመላክታል፡፡

በዞኑ ያሉ የወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

በዞኑ ያሉ የከተማ አስተዳደሮች የፕላን ልማት ፅ/ቤት

1. መኤኒት ጎልዲያ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

2. ጋችት ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

3. መኤኒት ሻሻ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

4. ጎሪ ጌሻ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

5. ማጂ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

6. ሡሪ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

7. ቤሮ ወረዳ ፕላንና ልማት ጽ/ቤት

1. ባቹማ ከተማ አስተዳደር

2. ጀሙ ከተማ አስተዳደር

3. ማጂ ቱም ከተማ አስተዳደር ናቸው፡፡



አቶ ዘሪሁን ወርቁ

የምህራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ

Background Of West Omo Zone

Location and Area

ምዕራብ ኦሞ ዞን በደ/ምዕራብ ኢትዮጲያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ከሚገኙ ዞኖች በሚያዝያ 23/2011 ዓ.ም በአድስ መልክ መመስረቱ ይታወቃል፡፡ ዞኑ በሀገሪቱ በደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ከአዲስ አበባ 671 ኪ/ሜትርና ከክልሉ ርዕሰ ከተማ ቦንጋ 200 ኪ/ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ዞኑ በሰሜንና በሰሜን ምስራቅ ከከፋ ዞን፣ በሰሜን ምዕራብ ከቤንች ሸኮ ዞን፣ በደቡብ ምሥራቅ ከደቡብ ኦሞ ዞን፣ በደቡብ ምዕራብ ከጋምቤላ ክልልና በደቡብ ከደቡብ ሱዳን ሪፖብሊክ ጋር ይዋሰናል።

ዞኑ 3 ክፍለ ከተማዎችና በ7 ወረዳዎች በ114 ቀበሌ አስተዳደር የተከፋፈለ ሲሆን የቆዳ ስፋቱ 1,458,400 ሄ/ር እንደሚሆንና በ1ስኩዌር ኪሎ ሜትር በአማካይ 20.6 ህዝብ እንደሚኖር ይገመታል።

ዞኑ የሚገኝበት በስተምስራቅ /Latitude/ 6.6384755 እና በስተ ምዕራብ /Longitude/ 35.7817109 ይገኛል፡፡

Population size and distribution

የ1999 ዓ.ም የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤትን መሰረት በማድረግና በዞኑ ካሉ ወረዳዎች የህዝብ ቁጥር መረጃ በመሰብሰብ በተገኘው መረጃ በ2017 ዓ.ም የዞኑ ህዝብ ብዛት ወ 163,542 ሴ 174,236 ድ 337,778 በዞን ማዕከል ፣ በከተማ አስተዳደርና በ7ቱ ወረዳዎች የሚገኙ አራቱ /4/ ነባር ብሄረሰቦች ማለትም የመኤኒት፣የዲዚ፣የሱርማና ዚልማሞ ብሔረሰቦችንና በሰፈራ ጣቢያዎች ተካቶ ያሉ የአማራ፤ የከምባታና የሲዳማ ብሔረሰቦችን ያካተተና በተጨማሪም በዞኑ ዉስጥ ባሉ ወረዳ ከተማዎች በንግድና በመንግስታዊ ስራ የተሰማሩ ሌሎች ኢትዮጵያዊ ብሔረሰቦች ይገኛሉ፡፡

በዞኑ ዉስጥ በዋናነት የመኤኒት፣ የዲዚ፣የሱርማና የዚልማሞ ብሔረሰቦች የሚኖሩ ሲሆን ከነባሩ ህዝብ ጋር በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚገኙ ሌሎች ብሄር ብሔረሰቦች በአንድነት ተሳስበዉና ተፈቃቅደዉ ተከባብረዉ የሚኖሩበት ዞን ነዉ ፡፡ አብዛኛዉ ህዝብ የሚተዳደረዉ በከፊል አርብቶ አደርነት፤ በግብርና እና በማዕድን ምርት የሚተዳደር ህዝብን ጨምሮ የያዘ ነዉ፡፡

የህዝብ አሰፋፈሩ በመኖሪያ አካባቢ በገጠር 294,179 (87.09%) እና በከተማ 43,599 (12.9

በምዕራብ ኦሞ ዞን የሥነ ህዝብ ምክር ቤት በማቋቋም በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ዉይይት ተደርጓል።ጀሙ:-መስከረም 21 ቀን 2018ዓምበምዕራብ ኦሞ ዞን የሥነ ህዝብ ምክር ቤት በማቋቋም በቀጣይ ...
05/10/2025

በምዕራብ ኦሞ ዞን የሥነ ህዝብ ምክር ቤት በማቋቋም በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ዉይይት ተደርጓል።

ጀሙ:-መስከረም 21 ቀን 2018ዓም
በምዕራብ ኦሞ ዞን የሥነ ህዝብ ምክር ቤት በማቋቋም በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ላይ ባለድርሻ አካላት ዉይይት አድርጓል።

በመድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ቦኒ እንደተናገሩት የሥነ ህዝብ ዓላማ የህዝብ ቁጥር ዕድገት በኢኮኖሚ በማህበራዊ ዕድገት ጋር እንዲሁም ከተፈጥሮ ሃብት ሚዛን ጋር እንዲያጠናክር ለማድረግ የማህበረሰቡ ኑሮ ለማሻሻል የታሰበው መሆኑ ተናግሯል።

በዞናችን በፍጥነት እያደገ የመጣው የህዝብ ቁጥር በዞኑ በሚካሄደው ሁሉም የልማት እንቅስቃሴ ላይ የረሱ ጫና እያሳደረ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ ጫና ለመቅረፍ ሚና ከፍተኛ መሆኑ አስገንዝበዋል።

የዞኑ የፕላን ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ዘርይሁን ወርቁ በበኩላቸው የህዝብ ቁጥር ማህበረሰቡ በማህበራዊ በኢኮኖሚ እና በአስተዳደራዊ ጉዳይ ላይ የሚያሳድረው አውንታዊ ሆነ አሉታዊ ተጽዕኖ ለይቶ መፍትሔ ለመስጠት የታሰበው መሆኑ ገልጸዋል።

የሴቶች የኢኮኖሚ እና ሁለተናዊ ተጠቃሚነት ችግሮች ለመቅረፍ እና የሴቶች የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ሚና ከፍተኛ ነው ብልዋል።

የማህበረሰቡ የአመጋገብ የክትባት አሰጣጥ የቤተሰብ ምጣኔ የጤና ንፅህና አጠባበቅ ሥራዓት ለማሻሻል እንደሚረዳ ተናግሯል።

ምክር ቤቱ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ እድገት እያሳየ ያለው የህዝብ ቁጥር መጨመር በትምህርት በጤና በሴቶች በግብርና በገቢ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ያለው ችግር ለመቅረፍ በቀጣይ እንደሚረዳ ገልጸዋል።

24/09/2025

የማይሳኩ ዕቅዶችና የማይጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ሁለንተናዊ ብልፅግና እንቅፋት ናቸው።
የምዕራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ

24/09/2025

ዛሬ ላይ የሚተጠየቁት የሶሽዮ-ኢኮኖሚ መረጃ ነገ ላይ በጀት ሆኖ ስለሚመጣ በኃላፊነትና በተጠያቂነት እንዲትሞሉ እናሳስባለን።
ምዕራብ ኦሞ ዞን ፕላንና ልማት መምሪያ

ምዕራብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ቢሮ ግንባታ
20/09/2021

ምዕራብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ቢሮ ግንባታ

14/09/2021

Address

Jemu
Mizan Teferi
NONE

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when West Omo Zone Plan and Development Department posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share