Southwest Revenue Bureau

Southwest Revenue Bureau የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የገቢዎች ቢሮ ይፋዊ የፌስ ቡክ ገፅ ነዉ፡፡

በሼይ ቤንች ወረዳ የታቀደውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በተቀናጀና በባለቤትነት የገቢ ስራን መሥራት እንደሚገባ ተጠየቀነሀሴ 09/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)በቤንች ሸኮ ዞን በሼይ ቤንች ...
15/08/2026

በሼይ ቤንች ወረዳ የታቀደውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በተቀናጀና በባለቤትነት የገቢ ስራን መሥራት እንደሚገባ ተጠየቀ

ነሀሴ 09/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

በቤንች ሸኮ ዞን በሼይ ቤንች ወረዳ በበጀት ዓመቱ የታቀደውን የገቢ ዕቅድ በማሳካት የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎችን ለመፍታት ሁሉንም የገቢ አማራጮችን ለይቶ እና አሟጦ መሰብሰብ ያስፈልጋል ተብሏል።

ይህ የተገለጸው በሼይ ቤንች ወረዳ ከዘርፉ ባለ ድርሻ አካላት ጋር እየተደረገ ባለው የገቢ ስራዎች ውይይት መድረክ ነው።

በውይይቱ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ክፍሌ ጎበዜ እንደገለጹት በበጀት ዓመቱ የታቀደውን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት በተቀናጀና በባለቤትነት የገቢ ስራን መሥራት ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።

ዕቅዱን ለማሳካት ሁሉንም የገቢ አማራጮችን ለይቶ እና አሟጦ መሰብሰብ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።

ፈጣን የልማት ዕድገት ቀጣይነት እንዲኖረው የህብረተሰቡን አዳጊ የልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት ገቢን በሚጠበቀው ፍጥነትና ቅልጥፍና መሰብሰብ ይገባል ብለዋል።

የወረዳው ም/ል አስተዳዳሪና ትራንስፖርት ጽህፈትቤት ኃላፊ አቶ ጎበዜ ተሰማ በበኩላቸዉ ኢኮኖሚ የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ ለመሰበሰብ እና መልሶ ለልማት ለማዋል ተግቶ መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የመደበኛ የገቢ ስራዎችንና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች የገቢ አሰባሰብ ሂደትን ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ ማስኬድና ማቀላጠፍ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።

በወረዳው በ2019 በጀት ዓመት ከሁሉም ገቢ አማራጮች ከ418 ሚልዬን በላይ ገቢ ለመሰበሰብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገልጸዋል።

ዘገባው የወረዳው የመንግስት ኮምንኬሽን ነው

የህዝቡን የመልማት ፍላጎት በተገቢው እየመለሱ ለመሄድ የገቢ አሰባሰብን አጠናክሮ መምራት እንደሚገባ ተመላከተ።ነሀሴ 09/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)የኮንታ ዞን የ2019 በጀት ዓመት ...
15/08/2026

የህዝቡን የመልማት ፍላጎት በተገቢው እየመለሱ ለመሄድ የገቢ አሰባሰብን አጠናክሮ መምራት እንደሚገባ ተመላከተ።

ነሀሴ 09/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

የኮንታ ዞን የ2019 በጀት ዓመት የበጀት ሰሚ መድረክ ተካሂዷል።

በበጀት ዓመቱ ከ1.9 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ እየተሰራ እንደሚገኝ ታውቋል።

በተያያዘም በመድረኩ የዞኑ የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት በፋይናንስ መምሪያ በኩል ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

ውስን የህዝብ ሀብትን ለታለመለት ዓላማ ብቻ በማዋል የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በበለጠ መትጋት እንደሚገባ ተነግሯል።

መድረኩን የመሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ በዞኑ የሚሰበሰበው ገቢና የሚበጀተው በጀት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለስ በሚያስችል መልኩ እየተመራ መቆየቱን በማንሳት ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

ዞኑ ከሚያመነጨው ኢኮኖሚና ከሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ አንፃር በየዓመቱ የገቢ አቅማችን እየጨመረ መጥቷል ያሉት አቶ ታከለ ይህንንም ወደ ተግባር በመቀየር የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች እየተሰሩበት ይገኛሉ ብለዋል።

የሚስተዋሉ ጥንካሬዎችን በማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም የአሰራር ስርዓትን ተከትሎ ተግባራትን መፈፀም እንደሚገባ በመግለፅ ለዚህም በየደረጃው የሚገኘው አመራር መላውን ህብረተሰብ በማስተባበርና በማስገንዘብ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል።

ውስን የህዝብ ሀብትን ለታለመለት ዓላማ ብቻ ማዋል ያሻል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በተለይም የህዝብ መሠረታዊ ፍላጎቶችና ዘላቂ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮሩ ስራዎችን መስራት ብሎም ለቀጣይ ጊዜያት አደዲስ የገቢ ምንጭ መፍጠርና የገቢ አማራጮችን ማስፋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድማገኝ ወጁ የህዝብን የመልማት ፍላጎት ለማርካት የገቢ አሰባሰብ ስራ በትኩረት እየተከናወነ እንደሚገኝ በማንሳት በ2018 በጀት ዓመት የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማጠናከር በ2019 በጀት ዓመት ኢኮኖሚ ከሚያመነጨው የሚጠበቀውን ገቢ ለመሰብሰብ በበለጠ ትኩረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።

በ2019 በጀት ዓመት 1.95 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ግብ መጣሉን በማመላከት ይህም የበጀቱን 74.9% በውስጥ ገቢ ለመሸፈን የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል።

ለገቢ መጨመር ዘርፈ ብዙ አስቻይ ሁኔታዎች መኖራቸውን ያብራሩት አቶ ወንድማገኝ በዞኑ በጉድለት በሚስተዋሉ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ለተሻለ ገቢ አፈፃፀም ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል።

በመድረኩ የዞኑን የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት የፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አግደው አሰፋ ያቀረቡ ሲሆን በ2014 በጀት ዓመት 407.6 ሚሊዮን ብር የነበረው የዞኑ አጠቃላይ በጀት እያደገ መጥቶ በ2018 በጀት ወደ 1.26 ቢሊዮን ብር ላይ መድረሱን አንስተዋል።

የ2019 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት 2.6 ቢሊዮን ብር እንዲሆን መቅረቡን የገለፁት ኃላፊው የሚበጀተው በጀት በተሰበሰበው ልክ ተገቢውን የአሰራር ስርዓት ተከትሎ የህብረተሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መመለስ በሚችል መልኩ ሊመራ እንደሚገባ አመላክተዋል።

ከበጀቱ 653 ሚሊዮን ብር ብቻ ከመንግስት ግምጃ ቤት የሚሸፈን ሲሆን ቀሪው ከ74% በላይ ብር በውስጥ ገቢ የሚሸፈን ስለመሆኑ ያመላከቱት አቶ አግደው በጀቱም ለሰብዓዊ ወጪዎችና ለካፒታል ፕሮጀክት ግንባታዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ መደልደሉን ገልፀዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በዞኑ ህዝቡ የሚያነሳቸውን የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን በማንሳት የሚሰበሰበው ገቢ በየደረጃው ለልማት እየዋለ በመሆኑ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።

በገቢ አሰባሰብ ላይ የባለሙያዎችን አቅም እየገነቡና ለህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ እየፈጠሩ መሄድና ቅንጅታዊነትን ማጠናከር እንደሚያሻ አንስተዋል።

በማዘጋጃ ቤት፣ በገጠር መሬት መጠቀሚያና መሠል ዘርፎች ላይ ያለውን የገቢ አቅም ማሻሻል ይገባልም ተብሏል።

በመድረኩ በ2019 በጀት ዓመት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚረዱ 16 ነባር እና 18 አዳዲስ ካፒታል ፕሮጀክቶች ግንባታ ለማከናወን ዞናዊ ግብ መጣሉ ተጠቁሟል።

በመድረኩ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ፣ የዞኑ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ብርሃኑ አቱሞን ጨምሮ ሌሎች የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር አመራር አካላት፣ የገቢና የፋይናንስ ሴክተር አመራሮችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

ዘገባው የኮ/ዞ/መ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር ክፍያ በተዘጋጁ አራት የክፍያ መስኮቶች መክፈል ተጀመረ።ነሀሴ 08/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)በወረዳው የግብር ክፍያ በአራት የክፍያ ...
14/08/2026

በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ የንግድ ትርፍ ገቢ ግብር ክፍያ በተዘጋጁ አራት የክፍያ መስኮቶች መክፈል ተጀመረ።

ነሀሴ 08/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

በወረዳው የግብር ክፍያ በአራት የክፍያ መስኮቶች እንዲከፈል መደረጉ ግብር ከፋዮች በሥርዓት እንዲገለገሉ፣ የክፍያ ሂደቱን በቀላሉ እንዲያጠናቅቁ እና የግብር ግዴታቸውን በወቅቱ እንዲወጡ የሚያግዝ እንደሆነም ተገልጿል።

በክፍያ ሂደቱ የተሳተፉ ግብር ከፋዮች እንደገለጹት፣ ግብር መክፈል የዜግነት ግዴታ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢውና ለሀገር ልማት የራስን ድርሻ የሚወጡበት ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

ግብር በመክፈል የልማት ሥራዎችን፣ የማኅበራዊ አገልግሎቶችንና ሌሎች የሕዝብ ጥቅም ሥራዎችን ለማስፈጸም ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ፣ ሌሎችም ግብር ከፋዮች የግብር ግዴታቸውን በወቅቱ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ግብራቸውን በወቅቱ ለከፈሉ ግብር ከፋዮች የማበረታቻ የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

ምንጭ :- የካፋ ዞን ገቢዎች መምሪያ ነው

ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎች እና ኪሳራዎች ነሀሴ 08/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)▫️  የካፒታልነት ባህርይ ያላቸው ወጪዎች፤▫️  የኩባንያ አክሲዮን ወይም የሽርክና ማህበር መሠረት የሆ...
14/08/2026

ተቀናሽ የማይደረጉ ወጪዎች እና ኪሳራዎች

ነሀሴ 08/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

▫️ የካፒታልነት ባህርይ ያላቸው ወጪዎች፤
▫️ የኩባንያ አክሲዮን ወይም የሽርክና ማህበር መሠረት የሆነውን ካፒታል ለማሳደግ የሚወጣ ወጪ፤
▫️ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15% (አሥራ አምስት መቶኛ) በላይ በፈቃደኝነት የሚደረግ የጡረታ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ መዋጮ፤
▫️ የአክሲዮን ድርሻ እና የትርፍ ድርሻ ክፍፍል፤
▫️ በመድን፣ በካሳ ወይም በዋስትና ውል መሠረት የተመለሰ ወይም ሊመለስ የሚችል ወጪ ወይም ኪሳራ፤
▫️ ማንኛውንም ሕግ ወይም ውል በመጣስ የሚጣል የገንዘብ ቅጣት ወይም የሚከፈል ካሳ፤
▫️ ግብር ከፋዩ በሂሳብ መዝገቡ የሚይዘው በወቅቱ ወጪ ያልተደረገ ነገር ግን ለወደፊት በግብር ዓመቱ ለሚከሰቱ ወጪዎች ወይም ኪሳራዎች መጠባበቂያ ይሆን ዘንድ የሚያዝ ገንዘብ ወይም የመጠባበቂያ ሂሣብ፤
▫️ ግብር ከፋዩ ለራሱ የሚያወጣው የግል ውጪ፤
▫️ በገቢ ግብር አዋጅ ወይም በውጭ ሀገር የታክስ ሕግ መሠረት የተከፈለ የገቢ ግብር ወይም ተመላሽ የሚደረግ የተጨማሪ እሴት ታክስ፤
▫️ መሥሪያ ቤቱን ወክሎ በተለያዩ ቦታዎች ለሚገኝ ተቀጣሪ ከተቀጣሪው ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ 10% (አሥር በመቶ) በላይ የሚከፈል የኃላፊነት አበል፤
▫️ ከሚከተሉት በስተቀር ለመዝናኛ የሚወጣ ወጪ፤
ሀ. የግብር ከፋዩ የንግድ ሥራ የመዝናኛ አገልግሎት መስጠት ሲሆን፤ወይም
ለ. ተቀናሽ እንዲደረግ በሚፈቅደው ልክ በማዕድን ማውጣት፣ በማኑፋክቸሪንግ ወይም በግብርና ሥራ የተሠማራ ቀጣሪ ሠራተኞቹን ለማዝናናት የሚያወጣው ወጪ፤
▫️ ለበጎ አድራጎት ከሚሰጥ ስጦታ ውጭ የሚደረግ ስጦታ ወይም እርዳታ፤
▫️ ግብር ከፋዩ አንድን የንግድ ሥራ ሀብት ግንኙነት ላለው ሰው ሲያስተላልፍ የሚደርስ ኪሳራ፤
▫️ ማናቸውም ግብር ከፋይ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ ከሚደረግ ቼክ፤ ወደ ባንክ ሂሳብ ገቢ ከሚደረግ የባንክ ድራፍት፤ ከአንድ የባንክ ሂሳብ ወደሌላ የባንክ ሂሳብ እና ወይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ በተሰጣቸው የክፍያ መፈፀሚያ መንገዶች ገንዘብ ከማስተላለፍ ውጪ በአንድ ቀን ውስጥ ለአንድ ሰው ከብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በላይ በሆነ ጥሬ ገንዘብ የፈጸመው ወይም የፈጸማቸው ክፍያዎች፤
(በአዋጅ ቁጥር 49/2018 እና በመመሪያ ቁጥር 40/2012 መሠረት/

በታክስ ሕግ ተገዢነት ማሻሻያ ረቂቅ እቅድ (Draft Compliance Improvement Plan) ሰነድ ላይ ሲያካሄድ የነበረው ወርክሾፕ ውጤታማ እንደነበር ተገለጸ ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም...
13/08/2026

በታክስ ሕግ ተገዢነት ማሻሻያ ረቂቅ እቅድ (Draft Compliance Improvement Plan) ሰነድ ላይ ሲያካሄድ የነበረው ወርክሾፕ ውጤታማ እንደነበር ተገለጸ

ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ሕግ ተገዢነት ማሻሻያ ዕቅድ ረቂቅ ሰነድ ላይ ለሲኒየር ማናጅመንት ሲያካሂደው የነበረው ወርክሾፕ የማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የስራ አቅጣጫ የሰጡት በሚኒስቴሩ የታክስ ስርአት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ መስከረም ደበበ ወርክሾፑ ጠቃሚ ግብዓት የተገኘበትና ውጤታማ እንደነበር ገልጸዋል።

‎‎የወርክሾፑ ዓላማ ረቂቅ ሕጉን ይበልጥ ለማዳበር፤ ግብረ መልስ ለመሰብሰብ፤ እቅዱን ከተቋማችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር ለማጣጣም እና በትግበራ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን አስቀድሞ ለመለየት፤ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች ላይ አስቀድሞ ዝግጁነትን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እንዲሁም የውሳኔ አሰጣጥ በመረጃ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን የሚያስችሉ ግብዓቶችን ለማግኘት ያለሙ መሆናቸውን ወ/ሮ መስከረም አስታውሰዋል፡፡

የታክስ አስተዳደር የመጨረሻው ግብ በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የታክስ ሕግ ተገዢነትን ማስፈን መሆኑን በመግለጽ በዚህ ወርክ ሾፕ የተገኘው ግብዓት በረቂቅ እቅድ ትግበራ ወቅት ሊገጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን አስቀድመን እንድንረዳና መፍትሄ እንድናዘጋጅ ትልቅ እገዛ እንደሚያደረግም ሚ/ር ዴኤታዋ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የእቅድ ረቂቅ ሰነድ ላይ የተሰጡ ግብዓቶችን በመተንተን ጥቅም ላይ ማዋል፤ የተሻሻለውን ሰነድ ለትግበራ ይሁንታ እንዲያገኝ ማድረግ፤ ያልተሟሉ መረጃዎች በተፋጠነ ሁኔታ እንዲሟላ በማስቻል ሰነዱን ማጠናቀቅ፤ እቅዱ የሁሉንም ስራ ክፍሎች ያማካለ ለማድረግ ሰነዱ ላይ ሊጨመሩ የሚገቡ ነጥቦች ተካትተውበት ለተግባራዊነቱ በጋራ መስራት እንደሚገባም ሚ/ር ዴታዋ አስገንዝበዋል፡፡


‎በሚኒስትሩ የታክስ ትራንስፎርሜሽን ጽ/ቤት ያዘጋጀው ይህ ታክስ ሕግ ተገዢነት ማሻሻያ እቅድ ረቂቅ ሰነድ ከተቋም ነባራዊ ሁኔታ ጋር የተናበበና በቀጣይነትም ዳብሮ የትግበራ እቅድ እንደሚዘጋጅለትም ይጠበቃል፡፡

ተቀናሽ የሚደረግ ወጪ (Deductible Expenses) ነሀሴ 06/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)ማንኛውም ወጪ በግብር ከፋዩ ገቢ ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማስገኘት፣ ለስራው ዋስትና...
12/08/2026

ተቀናሽ የሚደረግ ወጪ (Deductible Expenses)

ነሀሴ 06/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

ማንኛውም ወጪ በግብር ከፋዩ ገቢ ውስጥ የተካተቱትን ገቢዎች ለማስገኘት፣ ለስራው ዋስትና ለመስጠት እና ስራውን ለማስቀጠል በግብር ዓመቱ ውስጥ የተደረገ አስፈላጊ የሆነ ወጪ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ እንደ ወጪ እንደሚያዝ ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ከላይ የተገለፀው አጠቃላይ አገላለፅ እንደተጠበቀ ሆኖ አስፈላጊ ወጪዎች የሚከተሉትን እንደሚጨምር ስለተቀናሽ ወጪዎች የወጣው መመሪያ ቁጥር 40/2012 ይደነግጋል፡፡

አስፈላጊ ወጪዎች
 በነፃ በሚጠቀምበት ወይም በተከራየው ህንፃ ስራውን ሲያከናውን ቤቱን በሰጠው ወይም በአከራዩ ስም በሚታወቀው የመብራት፣የውሀ ወይም የስልክ ቆጣሪ የተጠቀመ እንደሆነ እነዚህ ክፍያዎች በግብር ከፋዩ እንደሚከፈሉ በግልፅ በውል ውስጥ የተካተተ ስለመሆኑ ከተረጋገጠ እና ወጪው የተከፈለበትን ደረሰኝ ኦሪጅናል ካቀረበ
 ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የተከፈለ ክፍያ
 የተመዘገበ የኤክሳይስ ታክስ እንዲሁም ተመላሽ ያልተደረገ ወይም በጊዜው ባለመቅረቡ ተመላሽ የማይደረግ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣
 የተበላሸ እቃ ዋጋ፣የአገልግሎት ጊዜ ያለፈባቸው እና የተወገዱ ዕቃዎች ዋጋ እና ለማስወገድ የወጣ ወጪ፣
 ግብር ከፋዩ ለንግድ ድርጅቱ እና መኖሪያ ቤት በአንድ የመብራት የስልክ ወይም የውሃ ቆጣሪ የሚጠቀም በሚሆንበት ጊዜ የመብራት፣ ስልክ እና የውሃ ወጪ በወጪ ተቀናሽ የሚያዘው ከወጪው 75 በመቶ ብቻ ይሆናል፡፡
 አንድ ግብር ከፋይ የንግድ ስራ እንቅስቃሴው በተቋረጠበት በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ወይም ስራ ባላገኘበት ጊዜ ያወጣው ወጪ ለምሳሌ (የቤት ኪራይ ፣የሰራተኛ ደመወዝ፣ መብራት፣ውሃ፣ስልክ፣የመሳሰሉት ወጪዎች ሊሆኑ ይችላሉ)
 የኃላፊነት አበል ወይም የውክልና አበል 10 በመቶ
 በኢትዮጵያ ነዋሪ ያልሆነ ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ ላለው በቋሚነት ለሚሰራ ድርጅቱ ጥቅም ያደረገውን ትክክለኛ ወጪ ለመተካት በኢትዮጵያ ውስጥ በቋሚነት የሚሰራው ድርጅት የሚፈፅመው ክፍያ (ወጪው የንግድ ስራ ገቢ ለማስገኘት፣ ለስራው ዋስትና ለመስጠት ወይም የንግድ ስራውን ለማስቀጠል የተደረገ እና በቋሚነት በሚሰራው ድርጅት ሊሰራ የማይችል ከሆነ ብቻ)፡፡
 በዲዛይን ለውጥ ምክንያት ህንፃ ፈርሶ ሲገነባ የፈረሰው ህንፃ የመዝገብ ዋጋ
 የተሽከርካሪ ጎማ የሚሰጠው ከአንድ አመት ያነሰ ከሆነ እንደ አላቂ ዕቃ ተቆጥሮ በተቀነሽ ወጪነት ይያዛል

የወለድ ወጪ
 በብድር የተገኘው ገንዘብ ለንግድ ስራ እንቅስቃሴ መዋሉ ሲረጋገጥ የወለድ ወጪ
 ግብር ከፋዩ በዱቤ ለሚገዛው ዕቃ ወይም አገልግሎት ዋጋውን እስኪከፍል ድረስ ወለድ እንደሚከፍል ውል የገባ እንደሆነ የከፈለው የወለድ መጠን
 ግብር ከፋዩ ህንፃ ለመገንባት ብድር የወሰደ እንደሆነ ህንፃው እስኪጠናቀቅ ድረስ የተከፈለው ወለድ በእርጅና ተቀናሽ የሚካተት ሆኖ ተገንብቶ ከተጠናቀቀ በኋላ የተከፈለው ወለድ በወጪ ተቀናሽ ይፈቀዳል

የምርት ብክነት
 በሚመለከተው የመንግስት አካል በቀረበ ጥናት መሰረት የሚወሰን በምርት ዝግጅትና አቅርቦት ሂደት የሚያጋጥም ብክነት

የመዝናኛ ወጪ
 የማዕድን ማውጣት እና ፍለጋ፤ የማኑፋክቸሪንግና የግብርናና ሆርቲ ካልቸር ስራ ላይ የተሰማራ
ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብ እና መጠጥ ዋጋ በወጪ የሚያዘው በአንድ ወር የሚያወጣው ወጪ በወሩ ለተቀጣሪዎቹ ካወጣው አጠቃላይ የደሞዝ ወጪ ከ 30% ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡
 ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች ወይም ሌሎች የምግብ አገልግሎት የሚያቀርቡ ተቋማት ውስጥ ለተሰማሩ ሰራተኞች ለተቀጣሪዎች የሚያቀርቡት የምግብ እና መጠጥ ወጪ ተቀናሽ የሚያደርገው በአንድ ወር የወጣው ወጪ በወሩ ለተቀጣሪዎቹ ከወጣው አጠቃላይ የደሞዝ ወጪ 20% ያልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡

 ከላይ የተገለፁት ተቋማት የምግብ አገልግሎት የሚያቀርቡት በራሳቸው አዘጋጅተው ከሆነ ከምግብ ዝግጅት ጋር በተያያዘ የተደረጉት የግብዓት ወጪዎች ህጋዊ ደረሰኝ/ የግዢ ማስረጃ
 ከላይ የተገለፁት ተቋማት የምግብ አገልግሎት የሚያቀርቡት በ3ኛ ወገን አማካይነት ከሆነ ወጪው ተቀባይነት የሚኖረው ከአቅራቢው ጋር የተደረገ ውል፣ አገልግሎቱ ስለመገኘቱ ከድርጅቱ በሚቀርብ ማረጋገጫ እና ለአቅራቢው ገንዘቡ ስለመከፈሉ በሚቀርብ ህጋዊ ደረሰኝ መሠረት

የማስታወቂያ ወጪ

 ግብር ከፋይ ምርቱን ወይም አገልግሎቱን ለማስተዋወቅ በተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የሚያደርገው የማስተዋወቅ ስራ በገንዘብ ወይም በምርት ወይም በአገልግሎት የሚፈጽመው ክፍያ በወጪ ተቀናሽ የሚያዘው ከጠቅላላ ገቢው (3% በመቶ) ባልበለጠ መጠን ብቻ ነው፡፡
 ለመገናኛ ብዙሀን ወይም ለማስታወቂያ ድርጅት የሚከፍለው ክፍያ ሙሉ በሙሉ በወጪ ተቀናሽነት ይያዛል፡፡

የእርጅና ተቀናሽ
 ግብር ከፋዩ ገቢውን ለማስገኘት በግብር ዓመቱ ጥቅም ላይ ላዋላቸው ዋጋቸው ለሚቀንስ ሀብቶች እና ግዙፋዊ ሀልዎት ለሌላቸው የንግድ ሥራ ሀብቶች ዋጋቸው በቀነሰው የገንዘብ መጠን ልክ የእርጅና ቅናሽ ለማድረግ ይፈቀድለታል

ለበጎ አድራጎት የሚደረጉ ስጦታዎች
 ግብር ከሚከፈልበት ገቢው ላይ ከ10 በመቶ ባልበለጠ
(ይህ የሚፈቀደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም የክልል መንግስት ካቢኔ ባደረገው ጥሪ መሰረት የአገሪቱን አንድነት እና ሉዓላዊነትን ለማስከበር ወይም ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ አደጋ ወይም ወረርሽኝ ለመከላከል ለተመሳሳይ ጥሪዎች ምላሽ ለመስጠት የሚውል ከሆነ ነው)

11/08/2026



ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ የህግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የላቀ አበርክቶ አለው - ወ/ሮ ህይወት አሰግድነሀሴ 05/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)የደምኢህክመ ...
11/08/2026

የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ የህግ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ የላቀ አበርክቶ አለው - ወ/ሮ ህይወት አሰግድ

ነሀሴ 05/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ በክልሉ ገቢ አሰባሰቡ ፍትሃዊና ዘመናዊ እንዲሆን በሚወጡ የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ ቢሮው በክልሉ ከሚመነጨው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ልክ ግብርና ታክስን ለህዝቦች ሁለንተናዊ ልማት ይውል ዘንድ አሟጦ የመሰብሰብ ስልጣን የተሰጠው ተቋም ነው ብለዋል።

ይህንኑ ስልጣኑን መሰረት በማድረግ የተለያዩ የህግ ማዕቀፎችን አውጥቶ ተግባራዊ በማድረግ ለክልሉ ህዝቦች ሁለንተናዊ ልማት የሚውል ገቢ በመሰብሰብ ባለፋት አምስት ዓመታት የክልሉን መንግስት ወጪ ትርጉም ባለው መልኩ ሲሸፍን መቆየቱን አውስተዋል።

በቀጣይ የሚወጡ የህግ ማዕቀፎችም ከአጠቃላይ የክልሉ የልማት እንቅስቃሴ ጋር የተጣጣመ ይሆን ዘንድ ከባለድርሻ አካላት ጋር መመካከር ወሳኝ እንደሆነ ያብራሩት ኃላፊዋ

ይህም የሚወጡ የህግ ማዕቀፎች ዘመኑን የዋጁና የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቁልፍ አበርክቶም ይኖረዋል ብለዋል።

በውይይቱ የተቋሙ ባለድርሻ አካል የሆኑት የፍትህ ቢሮ፣ የፋይናንስ ቢሮ እና የከተማ ልማት ቢሮ ከፍተኛ አመራሮች እና ዳይሬክተሮች ተሳትፈዋል።

የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ ሒሳብ ሲቀርብ መሟላት ያለባቸዉ ሰነዶችነሀሴ 04/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)1.   ዓመታዊ ሽያጭ ማጠቃለያ (summery report)2.   ከሽያጭ መመ...
10/08/2026

የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ ሒሳብ ሲቀርብ መሟላት ያለባቸዉ ሰነዶች

ነሀሴ 04/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

1. ዓመታዊ ሽያጭ ማጠቃለያ (summery report)
2. ከሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ ዉጪ የእጅ በእጅ ደረሰኝ የተደረገ ሽያጭ ካለ ማጠቃለያ ሪፖርት
3. ድርጅቱ ከሚጠቀምበት ባንክ የባንክ ስቴትሜንት
4. የሂሳብ መግለጫዎች ማለትም የትርፍና ኪሣራ መግለጫ (Profit and loss statement) ፣የሀብት እና የዕዳ መግለጫ (balance sheet) ፣ የጥሬ ገንዘብ ገቢ እና ወጪ መግለጫ (Cash flow statement)፣የባለቤቶቹ ሁኔታ (owners’ equity position) እንዲሁም የመረጃ ቋት(Ledger)
5. ተከፋይ ሂሳብ(withholding tax) ካለ ማጠቃለያ ሪፖርት እና ዋናዉን ደረሰኝ
6. ለጥገናና ማሻሻያ የወጡ ወጪዎች ለየትኛዉ ቋሚ ዕቃ መጠገኛ ስለመዋሉ የሚያስረዳ ማስረጃና ማጠቃለያ ሪፖርት
7. የቋሚ ንብረት ደረሰኝ ወይም ማስረጃ
8. የእርጅና ቅናሽ የተያዘለት የንግድ ሥራ ሀብት በሠንጠረዥ የተሰላ ቅጽ
9. የተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች ዝርዝር መግለጫ
10. በግብር እፎይታ ላይ ያለ ግብር ከፋይ ይሄንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ
11. ለበጎ አድራጎት ዓላማ የሚደረጉ ስጦታዎች ካሉ ለበጎ አድራጎት የተቋቋመ ድርጅት መሆኑን የሚያሳይ መረጃ እንዲሁም የጥሪ ደብዳቤና ገቢ የተደረገበት የባንክ ስሊፒ
12. የየወሩን VAT ሪፖርት ዝርዝር መረጃ የሚያሳይ ኤክሴል
13. ኦንላይን ያሳወቁበት ዓመታዊ ሪፖርት ሀርድ ኮፒ
14. በኦዲት ቦርድ የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ቅጂ
15. ሒሳቡ በተፈቀደላቸዉ የሒሳብ አዋቂዎች የተሠራ ከሆነ የሒሳብ ሠራተኛዉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቅጂ
16. ሂሳቡ በድርጅቱ የሒሳብ ሠራተኛ የተሠራ ከሆነ የሂሳብ ሠራተኛዉ የትምህርት ማስረጃ እና ተቀጣሪ መሆኑን የሚያመላክት መረጃ ተያይዞ መቅረብ አለበት
17. ዓመታዊ ሂሳብ ማሳወቂያ ቅጽ ከደንበኞች አገልግሎት ወስዶ መሙላት ያስፈልጋል፡፡
▫️ በሠንጠረዥ ‘ሐ’ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታ ያለበት እና ከአንድ በላይ የንግድ ሥራ መስክ ገቢ የሚያገኝ የደረጃ “ሀ” ግብር ከፋይ፣ በዚህ አዋጅ እና በሌሎች ተፈጻሚነት ባላቸው ሕጎች መሠረት ለእያንዳንዱ የተለየ የሥራ መስክ የሂሳብ መዝገቦችን እና ደጋፊ መረጃዎችን በተናጠል መያዝ አለበት።(በተሻሻለው የክልሉ ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 49/2018መሠረት)

የሰሜን ቤንች ወረዳ ከ456 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቀደነሀሴ 02/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት በ2019 በጀት ዓ...
08/08/2026

የሰሜን ቤንች ወረዳ ከ456 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ አቀደ

ነሀሴ 02/2018 (የደምኢህክመ ገቢዎች ቢሮ)

በቤንች ሸኮ ዞን የሰሜን ቤንች ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት በ2019 በጀት ዓመት 456 ሚሊዮን 826 ሺህ 508 ብር ገቢ ለመሰብሰብ ዕቅድ መያዙን ገለጸ።

ይህ የተገለጸው የሰሜን ቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘማች አዳ በተገኙበት የ2019 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድና የሐምሌ ወር የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም በተገመገመበት መድረክ ነው።

ዋና አስተዳዳሪው አቶ ዘማች አዳ በመድረኩ እንደገለጹት፣ የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን በማዘመን፣ ያሉ የገቢ ምንጮችን በአግባቡ በመለየትና ገቢን በሙሉ አቅም በመሰብሰብ የሕብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ በ2019 በጀት ዓመት ትኩረት ይሰጣል።

የገቢ ዕቅዱን ለማሳካትም በአመራር፣ በተቋማትና በባለሙያዎች መካከል የሃሳብና የተግባር አንድነት በመፍጠር የጋራ አቅምን በማስተባበር መሥራት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተቋሙ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት የደረጃ "ለ" ግብር ከፋዮችን የዕለት ገቢ ግመታ በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ የሲስተም ችግሮች ቢኖሩም፣ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ችግሮቹን በመፍታት በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለመፈጸም እንደሚሠራ ተገልጿል።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ጤና ዘለቀ በበኩላቸው፣ በ2018 በጀት ዓመት የታዩ ድክመቶችን በማረምና ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የተያዘውን የ2019 በጀት ዓመት የገቢ ዕቅድ ለማሳካት ወደ ሥራ መገባቱን ገልጸዋል።

በተጨማሪም በግብር ከፋዮች በኩል የሚፈጸሙ የሕግ ጥሰቶችንና በውስጥ አሠራር የሚስተዋሉ የዲሲፕሊን ክፍተቶችን በማረም፣ ያለውን የሰው ኃይል በብቃት በመጠቀም የተሻለ የገቢ አፈጻጸም ለማስመዝገብ እንደሚሠራ አስገንዝበዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ፣ በዘርፉ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች በፈጠሩት ጠንካራ ቅንጅት የወረዳው የገቢ አፈጻጸም ከዓመት ወደ ዓመት መሻሻል ማሳየቱ የሚበረታታ ውጤት ነው።

በመድረኩ የተሳተፉ አስተያየት ሰጪዎችም በ2018 በጀት ዓመት የተገኘው ውጤት የቅንጅት ሥራ ውጤት መሆኑን ጠቁመው፣ በ2019 በጀት ዓመት የታቀደውን ከፍተኛ የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የአመራር ድጋፍን፣ የተቋማትን ቅንጅት፣ የግብር ከፋዮችን ግንዛቤና የሰው ኃይል አቅም ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በቀጣይም የታቀደውን ገቢ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የገቢ ተቋማትን አቅም በማጎልበት፣ የገቢ ምንጮችን በማስፋትና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረትና በቅንጅት በመሥራት የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸሙን ለማሻሻል እንደሚሠራ ተገልጿል።

የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማገዝ፣ በሀብት አጠቃቀም ላይ ግልጽነትን ማስፈንና የግብር ከፋዮችን እንግልት መቀነስ በቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች መካከል እንደሚገኙም ተጠቁሟል።

ዘገባው የወረዳው የመንግስት ኮምንኬሽን ነው

Address

Mizan Teferi

Telephone

+251900452940

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Southwest Revenue Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Southwest Revenue Bureau:

Shortcuts

Share