Bench Sheko Zone Prosperity Party Branch Office

Bench Sheko Zone Prosperity Party Branch Office Prosperity party

ፍትኃዊነት ላይ የተመሠረተ ግብር እና ታክስ ለመሰብሰብ የግብር አሰባሰብ ሥርዓቱን ማዘመን   ይገባል ሲሉ የቤንች ሸኮ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ትዕዛዙ ተናገሩ ።የገቢ ግብር አ...
05/11/2025

ፍትኃዊነት ላይ የተመሠረተ ግብር እና ታክስ ለመሰብሰብ የግብር አሰባሰብ ሥርዓቱን ማዘመን ይገባል ሲሉ የቤንች ሸኮ ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ትዕዛዙ ተናገሩ ።

የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 መሠረት በማድረግ ለደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዮች የሂሳብ መዝገብ አቀራረብ ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት በሚዛን- አማን ከተማ ተካሂዷል ።

የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 መሠረት በማድረግ ለደረጃ “ሀ” ግብር ከፋዬች የሂሳብ መዝገብ አቀራረብ ላይ የተደረገ ውይይት በሚዛን- አማን ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ መስፍን ጉብላ መንግሥት በውስጥ ገቢ ሙሉ በሙሉ ወጪን ለመሸፈን እየሠራ እንዳለ ጠቁመው ቴክኖሎጂን በመጠቀም የግብር ሥርዓቱን ለማዘመን በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የዞኑ ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙሉቀን ትዕዛዙ ህጋዊነትን ጠብቀው የሚሠሩ ለህዝብ እና ለመንግሥት እንዲሁም ለራሳቸው ታማኝ የሆኑ ሕጋዊ ግብር ከፋዮች እንዲበረታቱ የገቢ ግብር አዋጁ ይረዳል ሲሉ ገልፀዋል።

ከግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ጋር የተለያዩ የውይይትና የምክክር፤ እንዲሁም የእውቅና መድረኮችን በመፍጠር ዘመናዊ የግብር ሥርዓቶችን በመተግበር በሁሉም የገቢ አማራጮች የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ እየተሠራ እንደ ሚገኝ ተገልጿል።

የወጡ የታክስ ህጎችን በማሥከበር እና የደረሰኝ ቁጥጥሩን ማጠናከር የህግ ተጠያቂነት ባለው መልኩ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርን ለመቀነስ የራሱ የሆነ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው የሚዛን- አማን ከተማ ምክትል ከንቲባና የገቢዎች ጽ/ቤት ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ታገል ወንድሙ ጠቁመዋል።

ግብር ከፋዩ የገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 በተለይም ደግሞ የአዋጁን አንቀፅ 87 በጥልቀት እንዲረዱት በማስቻል የሚጠበቅባቸውን የመንግሥት የግብር ግዴታን በወቅቱ እንዲፈፅሙ በማስቻል አቅማቸውን ሊፈትኑ ከሚችሉ ከፍተኛ የግብር ወለድ እና ቅጣት እንዲተርፉ ያግዛቸዋል ሲሉም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡ ነጋዴዎች መካከል አቶ አበባው ተክሉ ፣ አቶ ኡመር ሙስጠፋ እና አቶ ግርማ ወንድሙ በበኩላቸው መንግሥት ሕጋዊ ያልሆኑ ነጋዴዎችን በአሥራ ሥርዓት ሕጋዊ መስመር እንዲያስገባ አጭበርባሪዎችን ተከታትሎ ለሕግ እንዲያቀርብ ጠይቀዋል።

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2018 ሀገር አቀፍና ክልላዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማትና ተማሪዎች የእውቅና መርሐግብርና የ2018 ዓ/ም የአንደኛ ሩብ ዓ...
05/11/2025

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2018 ሀገር አቀፍና ክልላዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማትና ተማሪዎች የእውቅና መርሐግብርና የ2018 ዓ/ም የአንደኛ ሩብ ዓመት የተግባር አፈፃጸም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀመረ።

በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት የ2018 ሀገር አቀፍና ክልላዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማትና ተማሪዎች የእውቅና መርሐግብርና የ2018 ዓ/ም የአንደኛ ሩብ ዓመት የተግባር አፈፃጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።

መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ተስፋዬ ጊስካር እንዳሉት እንደ ሀገር የገጠመንን የትምህርት ስብራት ለመጠገን በየደረጃው በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል።

ሃላፊው አክለውም በርካታ ፈተናዎችን አልፈው ውጤት ማስመዝገብ የቻሉ ተማሪዎችና ውጤት እንዲመዘገብ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የትምህርት ተቋማት፣ መምህራንና የተማሪ ወላጆች ሊመሰገኑና እውቅና ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል።

የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ደረጀ ኩይክ በበኩላቸው በ2017 ዓ/ም ከተቀበልናቸው ተማሪዎች መካከል 6ኛ ክፍል 65 በመቶ፣ 8ኛ ክፍል 67 በመቶ እና ሀገር አቀፍ 12ኛ ክፍል 18.3 በመቶ ተማሪዎች ውጤት በማምጣት ወደ ቀጣዩ ክፍል ማለፍ ችለዋል ብለዋል።

በትምህርት ዘመኑ ሀገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 137 ተማራዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ ማስገባት መቻሉን ሃላፊው አክለው ገልጸዋል።

በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት አፈፃጸም በጽህፈት ቤቱ የትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪ አቶ አዲሱ አዳል እየቀረበ ይገኛል።

የፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ  ከዚህ በፊት በመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ ቦታው ድረስ በመሄድ ምልከታ  አደረጉ።የፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክ...
04/11/2025

የፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ከዚህ በፊት በመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ ቦታው ድረስ በመሄድ ምልከታ አደረጉ።

የፌደራል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በቤንች ሸኮ ዞን ከዚህ በፊት በመሬት መንሸራተት አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ ቦታው ድረስ በመሄድ ምልከታ አድረገዋል።

የቋሚ ኮሚቴ ምልከታው በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት በተለይም በሰሜን ቤንች እና ሼይ ቤንች ወረዳዎች ላይ የተፈናቀሉትን ሰዎች ቦታው ድረስ በመሄድ በመመልከት ለዜጎች ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት የተሰሩ ስራዎችን በማየት ግብረ መልስ በመስጠት በፌደራል በክልል፣በዞን ፣ እና በወረዳው መሰራት የነበረበት ቀሪ ስራዎች የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ በፍጥነት ምላሽ ለመስጠት ያለመ እንደሆነ የቤንች ሸኮ ዞን ልዩ አማካሪ አቶ አሰፋ ፋይኒኮምስ ገልጸዋል።

በዞናችን በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎች እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ የተፈናቀሉ 826 አባዎራ 809 ቤቶች የፈረሱበት እንዲሁም 221.4 ሄ/ር መሬት በአደጋው የወደመ መሆኑ ይታወቃል።

በዞኑም ሰፋፊ ስራዎች እየተሰራ ሲሆን ለተፈናቀሉ ዜጎች ጊዜያዊና ሰብዓዊ ድጋፎች በፌደራል ፣በክልሉ ፣በዞን እስከ ቀበሌ ያለዉ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ማድረጋቸዉም አንስተው ለተፈናቀሉት ዜጎች ዘላቂ መፍተሔ ማምጣት ስለሚያስፈልግ በነዚህ ዙርያ ከቋሚ ኮሚቴ ጋር በመግባባ ውይይቱ ተጠናቋል።

የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ለወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ለኢንስፔክሽን እና ኮሚሽን ፅህፈት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋ...
04/11/2025

የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ለወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ለኢንስፔክሽን እና ኮሚሽን ፅህፈት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል ።

በስልጠና መድረኩ ንግግር ያደረጉት የዞኑ ኢንስፔክሽን ስነ ምግባር ኮሚሽን ፅህፈት ኃላፊ አቶ ካጁ አቤል እንደገለፁት የኢንስፔክሽን መዋቅር በፓርቲ ውስጥ የሚታዩ የአሰራር ሥርዓት ጉድለትን በማረም ጠንከራ የፓርቲ መዋቅር እንዲፈጠር በዋናነት ይሰራል ብለዋል።

የስልጠና ሰነድ ያቀረቡት አቶ ሽፈራው ኮምት የዞኑ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ፅህፈት ምክትል ኃላፊ ስልጠናው በዋናነት የብልፅግና ፓርቲ የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን የተሻሸለ አደረጃጀትና የአሰራር መመሪያ እና በአቤቱታ አቀራረብ ላይ ግልጸኝነትን መፍጠር ላይ ያተኮረ ሰነድ አቅርበዋል።

የኮሚሽን መዋቅሩ በፓርቲ የፖለቲካ ጤንነት ፣የአበላት መብት ማስከበር እና በፓርቲ ሀብትና ንብረት ላይ ትኩረት አድርጎ በሪፎርሙ በኮሚሽን መዋቅረ ተቋም ለተቀላቀሉት አመራሮች ወሳኝ ስልጠና መሆኑን አስረድተዋል ።

በመድረኩ የ6 ወረዳ እና 4ቱ ከተማ አስተዳደር
የኢንስፔክሽንና ስነ ምግባር ኮሚሽን ፅህፈት አመራሮች ስልጠናው ወሳኝ እና ወቅታዊ ለቀጣይ ተግባር የሚያነሳሳ መሆኑን ጠቁመዋል ።

የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በላቀ ሁኔታ በማሳደግ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ከምን ጊዜውም በላይ የበረታን ሁነን መገኘት አለብን፦ ወ/ሮ ውባለም በዛብህ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝ...
04/11/2025

የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በላቀ ሁኔታ በማሳደግ ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ከምን ጊዜውም በላይ የበረታን ሁነን መገኘት አለብን፦ ወ/ሮ ውባለም በዛብህ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት የቦንጋ ማዕከል ክልል ተቋማት የሴቶች ክንፍ ህብረት የ 2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ሴቶች ክንፍ ቅ/ጽ/ቤት ም/ኃላፊ ወ/ሮ ውባለም በዛብህ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት የሴቶችን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በተደረገው ዘርፈ ብዙ ስራዎች ስኬታማ አፈጻጸሞች ተመዝግበዋል።

የሴቶች ክንፍ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚሰራ አደረጃጀት መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ውባለም ሴቶች ስለ መብቶቻቸዉ የሚሞግቱበ፣ የስራ ባህላቸዉ የሚቃናበትና የዉሳኔ ሰጭነት ተሳትፎቸአዉ የሚረጋገጥበት አደረጃጀት እንደሆነም አመላክተዋል።

በዚህም የሴቶች አደረጃጀት የፓርቲውን ተልዕኮ በብቃት እየተወጡ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል።

ባለፉት ዓመታት ሁለንተናዊ ለውጥ በተመዘገቡ ስኬቶች ውስጥ የሴቶች ሚና አይተኬ መሆኑን የገለጹት ኃላፊዋ
ሴቶች ከተናጥል ይልቅ በህብረት በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል ።

የ2018 በጀት ዓመት የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ይበልጥ ለማረጋገጥና ለላቀ ውጤት የምንተጋበት ዓመት መሆኑን በውል በመገንዘብ የፓርቲያችን ድርብ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ከምንጊዜውም በላይ የበረታን ሁነን መገኘት መቻል አለብን ብለዋል።

አብሮነትን ፣ መተሳሰብን ፣ እርስ በርስ መረዳዳትን ማዕከል በማድረግ ሰው ተኮር ተግባራትን በማስቀደም በርካታ ተገባራትን የክንፉ ጽ/ቤት ማከናወኑን ገልጸው በዛሬው መርሃ ግብርም ይህንኑ የበጎነት ተግባር የሚያጠናክር ማከናወን መቻሉን ጠቁመዋል።

አስካሁን በተግባር አፈጻጸም የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል የታዩ ክፍተቶችን ፈጥኖ በማረም ለቀጣይ ርብርብ በማድረግ የሚጠበቅብን ኃላፊነት ከወዲሁ ዝግጁነት መፍጠር እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

የቦንጋ ማዕከል የሴቶች ክንፍ ህብረት ሰብሳቢ ወ/ሮ ገነት አቲሞ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በርካታ ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል።

ሴቶችን ጠንካራና ተልዕኮን በቁርጠኝነት የሚወጡ አደረጃጀቶችን በማጠናከር ለሁለንተናዊ ብልጽግና መትጋት ይጠበቃል ብለዋል።

በአጋርነት የዳበረ ኮሚኒኬሽን ለህዝብ  ዕምነት ና ለሀገር ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የቤንች ሸኮ ዞን ኮሚኒኬሽን የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው። የምክክር መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቤን...
04/11/2025

በአጋርነት የዳበረ ኮሚኒኬሽን ለህዝብ ዕምነት ና ለሀገር ብልጽግና በሚል መሪ ቃል የቤንች ሸኮ ዞን ኮሚኒኬሽን የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

የምክክር መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እሸቱ ሻንበል እንደተናገሩት ኮሚኒኬሽን ወቅታዊና ተዓማኒ መረደጃዎችን ለህብረተሰቡ በማድረስ በመንግስት ፖሊሲ ናዕቅዶች ላይ ዕምነት እንዲያሳድር ልዩ ሚና አለው ብለዋል።

በኤሌክትሮኒክስ ማህበራዊ ሚዲያ የሚሠራጬ መረጃዎች ትክክለኛ ና ተዓማኒ መሆን እንዳለባቸውሞ ነው የተናገሩት።

ኮሚኒኬሽን በመንግስትና በህዝብ መካከል ተዓማኒነት ያለው መረጃ በማሰራጨት ለዞኑ ህዝብ የኮሚኒኬሽን አገልግሎት መስጠት አለበት ብለዋል።

የቤንች ሸኮ ዞን የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በላቸው ጎንደር እንዳሉት የመንግስት ኮሚኒኬሽን በህዝብና በመንግስት መካከል ቀልጣፋ የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

የዞኑን ህዝብ ወቅታዊና ተዓማኒነት ያለው መረጃ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከሚዲያ ተቋማት ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር እየተሰራ ይገኛል ብለዋል አቶ በላቸው ጎንደር።

ለሁለት ተከታታይ ቀናት በሚዛን አማን ከተማ በሚካሄደው ስልጠናና የምክክር መድረክ የዞን፣ የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ናባለሙያዎች እንዲሁም በዞኑ የሚገኙ የሚዲያ ተቋማት ኋላፊዎችና ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛል።

በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች የወባ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛል።‎‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የወባ በሽታ መከላከያና መቆጣጠ...
04/11/2025

በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች የወባ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛል።

‎በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በተለያዩ አከባቢዎች የወባ በሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛል።

‎የክልሉ ጤና ቢሮ እስከታችኛው መዋቅር የሚገኙ የዘርፉ አመራሮችንና ባለሙያዎችን በማስተባበር የመከላከልንና አክሞ የማዳን ስራዎችን በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የቢሮው ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም ይገልፃሉ።

‎በዚህም የወባ በሽታ ስርጭት አምና በተመሳሳይ ወቅት ከነበረው ተመላላሽ ታካሚ በ34%፣ተኝቶ ታካሚ በ30% እና የሞት ምጣኔ በ18% መቀነሱን አቶ ኢብራሂም ገልጸዋል።

‎በተለይ ማህበረሰቡ የወባ መከላከያ መንገዶችን ዘውትር ተግባራዊ ሊያደርግ እንደሚገባም አቶ ኢብራሂም አሳስበዋል።

‎ቢሮው የወባ መከላከያ የአልጋ አጎበር፣ የፀረ ወባ ኬሚካልን ጨምሮ መድኃኒቶችንና ሌሎች የህክምና መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኝም አስረድተዋል።

‎በየደረጃው የሚገኙ የጤና ዘርፍ ተዋናዮች በተለይ ማህበረሰቡን ግንዛቤ የማስጨበጥና የማነቃነቅ ስራዎችን በተገቢው በመስራት ላይ እንደሚገኘም ተጠቅሷል።

‎አልጋ አጎበርን በአግባቡ መጠቀም፣ ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን ማዳፈን፣ የመኖሪያ ቤቶችን በፀረ ወባ ኬሚካል ማስረጨት እንዲሁም የህመም ስሜት ስሰማ በፍጥነት ወደ ጤና ተቋም መሄድና የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መውሰድ እንደሚገባም አስረድተዋል።
‎SMN

የፓርቲና የመንግስት ተግባራቶች ላይ ለወረዳ አጠቃላይ አመራሮች የስምሪት ኦረንቴሽን ተሰጠ።በሰሜን ቤንች ወረዳ ለጠቅላላ አመራር  ከመስክ መልስ መደበኛ  የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ግምገማና...
03/11/2025

የፓርቲና የመንግስት ተግባራቶች ላይ ለወረዳ አጠቃላይ አመራሮች የስምሪት ኦረንቴሽን ተሰጠ።

በሰሜን ቤንች ወረዳ ለጠቅላላ አመራር ከመስክ መልስ መደበኛ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎች ግምገማና የስምሪት ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።

የስምሪት አረንቴሽኑን መድረክ የሰሜን ቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘማች አዳ እና የሰሜን ቤንች ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታደለ ጁለት በጋራ ኦረንቴሽኑን ሰጥተዋል።

የሰሜን ቤንች ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘማች አዳ አመራሩ መደበኛ የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎችን አጣጥሞ በመስራት የተሻለ ውጤት እንዲመጣ አቀናጅቶ መሰራት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።

የሰሜን ቤንች ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፋ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ታደለ ጁለት ተቆጥረው የተሰጡትን የፓርቲ ተልዕኮዎች በሚፈለገው መልኩ ለማሳካት ሁሉም አመራር ህዝቡን በንቃት አሳትፎ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

አመራሩ በየቀበሊያቱ የተሰጠውን የፓርቲ ስምሪት በልዩ ትኩረት ስራዎችን መምራት እንዳለባቸው ተገልጿል።

ከፓርቲ ተግባራት አንፃር፣ የቀበሌ አደረጃጀቶችን ማጠናከር፣ የፓርቲው ሀብት አሰባሰብ ፣የፓርቲ ህንፃ ግንባታ ሀብት አሰባሰብ በአግባቡ መምራት እንደሚያስፈልግ በኦረንቴሽኑ ላይ በዋናነት ተነስቷል።

ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከሚሰሩ ተግባራት መካከል የፓርቲው መዋጮ ሀብት አሰባሰብ ፣ የፓርቲ ህንፃ ግንባታ ገቢ አሰባሰብ እንዲሁም ታች ቀበሌ የህዝብ ንቅናቄ መድረክ መካሄድ ጨምሮ ትኩረት ተሰጥቶት እንድሰራ ሰፊ ወይይት ተድርጓል።

ባለፉት ሶስት ወራት በገጠር እና ከተማ  ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ብድር ማሰራጨቱን የቤንች ሸኮ ዞን ስራ እና ክህሎት መምሪያ ገለፀ ።መምሪያው ባለድርሻ አካላትን በ...
03/11/2025

ባለፉት ሶስት ወራት በገጠር እና ከተማ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ከ21 ሚሊየን ብር በላይ ብድር ማሰራጨቱን የቤንች ሸኮ ዞን ስራ እና ክህሎት መምሪያ ገለፀ ።

መምሪያው ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ ባለፉት 3 ወራት በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ እየመከረ ነው።

የቤንች ሸኮ ዞን ስራ እና ክህሎት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛው ሩብ ዓመት አፈጻጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር እየገመገመ ነው ።
የመምሪያው ም/ሃላፊ የሆኑት አቶ ታምራት ከተማ ባለፉት ሶስት ወራት በገጠር እና ከተማ ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች 21 ሚሊዮን 873 ሺህ 629 ብር መሰራጨቱን አስረድተዋል ።
በገጠር ለተደራጁ ኢንተርፕራይዞች በመንግስት በፕሮጀክት ድጋፍ 266 ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ 16.2 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በከተማ 53 ዜጎችን ተጠቀሚ የሚያደርግ 5.6 ሚሊዮን ብር ተሰራጭቷል ።

በከተማ በ2018 በጀት ዓመት ከግል ባንኮች ጋር በመተባበር ከዚህ በፊት ወደ ስራ ገብተው የገንዘብ ችግር ላለባቸው ወጣቶች ስልጠና በመስጠት ለነባር እና አዲስ ኢንተርፕራይዞች እና በሴቶች የሚመሩ 302 ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል ።

በተያያዘም በአንደኛው ሩብ ዓመት በገጠር እና ከተማ 3 ሚሊዮን 503 ሺህ 738 ብር ዕዳ ለማስመለስ ታቅዶ 4 ሚሊዮን 928 ሺህ 269 ብር ማስመለስ የተቻለ ሲሆን ከተዘዋዋሪ ብድር አመላለስ ዙሪያ እየተሰራ ያለው ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉም አቶ ታምራት ተናግረዋል ።
የቤንች ሸኮ ቴሌቭዥን ዘግቧል።

በጥራትም በብዛት ቡናን ለገበያ በማቅረብ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን በአዲስ መልክ ይሰራል -አቶ ጌታሁን ተክሌየቤንች-ማጂ የጫካ ቡና አምራቾች ህብረት ስራ ዩንየን በ1997 ዓ.ም የተመሰረ...
03/11/2025

በጥራትም በብዛት ቡናን ለገበያ በማቅረብ አርሶ አደሩ ተጠቃሚ እንዲሆን በአዲስ መልክ ይሰራል -አቶ ጌታሁን ተክሌ

የቤንች-ማጂ የጫካ ቡና አምራቾች ህብረት ስራ ዩንየን በ1997 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን 14 መሠረታዊ የህብረት ስራ ማህበራትና 209 አባላትን ይዞ በ201 ሺ ብር ካፒታል ነው ወደ ስራ የገባው።

ዩንየኑ በሂደት እያደገ በመምጣት 85 መሠረታዊ ማህበራትና 21ሺ 350 አባላት የደረሰበት ሁኔታም እንደነበር ይታወሳል ።

በተለያዩ ምክንያቶች አሁን ላይ ዩኒየኑ 63 መሠረታዊ ማህበራትና 14ሺ 300 አባላትን ይዞ እየሰራ ይገኛል።

ዩንየኑ አርሶአደሩ ከቡና ምርቱ በቀጥታ ተጠቃሚ እንዲሆን በአውሮፓ ከሚገኙ ቡና ተረካቢ ካንፓኒዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የቤንች ሸኮ ዞን ግብርና የአካባቢ ጥበቃና ህብረት ስራ መምሪያ ምክትል ሀላፊና የቡናና ሻይ ቅመማ ቅመም ዘርፍ ሀላፊ ወ/ሪት ወርቅነሽ ባድንስ ዞኑ ለቡናና ቅመማ ቅመም ምርት ምቹ ስነ-ምህዳር ያለው በመሆኑ በአካባቢው በብዛት እንደሚመረት ገልፀዋል።

የቡናን ምርታማነትና ጥራትን በማሣደግም አርሶአደሩን ተጠቃሚ ለማድረግ በሰፊው እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል።

በዞኑ በየአመቱ ከ25ሺ እስከ 30ሺ ቶን ቡና ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረበ ይገኛል ያሉት ሀላፊዋ አርሶአደሩን በመሠረታዊ የህብርት ስራ ማህበራት በማደራጀት የገበያ ትስስር እንዲፈጠር እየተደረገ መሆኑን ገልፀዋል ።

የቤንች-ማጂ ጫካ ቡና አምራች ዩኒየን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ጌታሁን ተክሌ ዩኒየኑ ቀድሞ ከነበረበት 85 መሠረታዊ ህብረት ስራ ማህበርና ከ21ሺ አባላት ውስጥ የራሣሳቸውን ዩኒየን እንመሠርታለን ያሉ እና የምዕራብ ኦሞ ዞን ራሱን ችሎ ሲወጣ አሁን ላይ 63 መሠረታዊ ማህበራትና 14ሺ 300 አባላት መኖራቸውን አውስተዋል።

በአንድ ድርጅት ውስጥ ከፍታም ዝቅታው ይኖራል ያሉት ስራ አስኪያጁ በዚህ ሂደት የሚገጥሙትን ተግዳሮቶች በመቋቋም የተሻለ ስራ ለመስራት መነሳሳት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመሆኑም ዩኒየኑ እንደ አውሮፓውያን የጊዜ ቀመር ከ2026 አስከ 2030 ድረስ የሚፈፀም የአምስት አመት እቅድ በመንደፍ በጉባኤው መፅደቁን አመልክተዋል።

በተፈጠረው ችግር ምክንያት የአባለት እምነት ወደ ኋላ መመለሱንና ያንን እምነት ከመመለስ ባለፈ መንግስት ያወጣቸውን አዲሱን ፖሊሲና ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ እና ከቀድሞ ቡና ገዥዎቻችን ጋር ለመስራት በአዲስ መልክ ትኩረት መደረጉን ገልፀዋል።

ከአውሮፓ ህብረት ቡና ከሚገዛው ካንፓኒ ድጋፍ ተደርጎ ወደ አዲሱ የቴክኖሎጂ አሰራር የተገባ መሆኑንም ተናግረዋል።

በዚህ አሰራር መሠረት በሰሜን ቤንች ወረዳ በአንድ በደቡብ ቤንች ወረዳ በሁለት ማህበራት አዲስ የቴክኖሎጂ አሰራር ተግባራዊ መደረጉን አመልከተው በቀጣይ ቡና ባሉባቸው ቦታዎች ሁሉ በማህበራቱ ላይ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

የዩኒየኑ ምክትል ስራ አስኪያጅና የምርት ክፍል ሀላፊው አቶ ወልዱ ባጪ የውይይቱ ዋና አለማ ከአውሮፓ የሚመጡ የቡና ገዥዎች አሉ ከእነሱ ጋር ያለው የግብይት ስርአትና ወደፊት በሚኖረው የምርት ዝግጅት ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል።

"ሶሊዳር ሞንድ " የተባለው የፈረንሳይ ቡና ገዥ ካንፓኒ ከዩኒየኑ ጋር ከዚህ ቀደምም ቡናን በብዛት ሲገዛ የቆየ ካንፓኒ መሆኑን አመልክተዋል ።

ካንፓኒው ዩንየኑና መሠረታዊ ማህበራቱ ያጋጠማቸው ችግሮች ምንድናቸው እንዴትስ መፈታት አለባቸው በሚሉት ዙሪያም ውይይት በማድረግ በፕሮጀክት መልክ እገዛ እንዲኖር ለማድርግም ጭምር

በገጠር እና በከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚደረገው ርብርብ የወጣቶች እና የሴቶችን  ተጠቃሚነት ለማሳደግ ፋይዳው የጎላ ነው ተባለ።የቤንች ሸኮ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያየ2018 ዓ.ም የ...
03/11/2025

በገጠር እና በከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ የሚደረገው ርብርብ የወጣቶች እና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ፋይዳው የጎላ ነው ተባለ።

የቤንች ሸኮ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ
የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተግባር አፈጻጸም ግምገማ እና የቀሪ ወራቶች ዕቅድ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየመከረ ነው።

ባለድርሻ አካላት በሥራ ዕድል ፈጠራ ፣ብድር ስርጭት እና አመላለስ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉም ተጠይቋል።

የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደሪ ተወካይ እና የንግድ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሃላፊ አቶ መስፍን ጉብላ በምክክር መድረኩ እንደተናገሩት ተቋሙ በገጠርና በከተማ ስራ አጥን ለይቶ በዕውቀት እና በክህሎት በማሰልጠን ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።

በዞኑ ብዙ ስራ አጦችን ለይቶ ተገቢውን የክህሎት ስልጠና በመስጠት ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል ።
አሁን ባለው ሁኔታ ወጣቶች በግብርና ዘርፍ በእንስሳት፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን፣ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኮሌጅ እና በግብርና ቴክኒክ ና ሙያ ኮሌጅ ገብተው ዕውቀትን ወደ ተግባር መለወጥ አለባቸው ብለዋል ።

የቤንች ሸኮ ዞን ስራና ክህሎት መምሪያ ም/ሃላፊ አቶ ታምራት ከተማ በበኩላቸው በሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት በክህሎትና ቴክኖሎጂ በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠኑ ብቁ የሰው ሃይል የማፍራት ይገባል ብለዋል።

በገጠር እና በከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ላይ የሚደረገው ርብርብ የወጣቶች እና የሴቶችን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ ፍይዳው እጅግ የጎላ መሆኑን በመግለጽ ባለፈው ዓመት በርካታ ውጤቶች ተመዝግቧል ብለዋል ።

በሩብ ዓመቱ በየዘርፉ የተግባር አፈጻጸም ወጣ ገባነት ያለው በመሆኑ የታዩ ጉድለቶች እንዳይደገሙ የተገኙ ውጤቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው የተጠናከረ ክትትልና ድጋፍ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል ብለዋል። (ቤሸቴ)

የቤንች ማጂ አንድነት የገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒየን አባላቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ። አቶ ፈተና ሽፋ ዩኒየኑ 13ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን...
03/11/2025

የቤንች ማጂ አንድነት የገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒየን አባላቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራትን አከናውኗል ። አቶ ፈተና ሽፋ

ዩኒየኑ 13ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በሚዛን አማን ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

በጉባኤው ላይ የተገኙት የዩኒየኑ ሥራ አስኪያጅ አቶ ፈተና ሽፋ ዩኒየኑ በ2017 ዓ/ም አባላቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል።

በሂደቱም በጥንካሬ የተመዘገቡ ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እና በድክመት ከተመዘገቡት አፈፃፀሞች ትምህርት በመውሰድ የተሻለ ስራ እንደሚሰራም ገልጸዋል ።

በ13ኛ ዓመት 11መደበኛ ጉባኤ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የኦዲት ሪፖርት፣ የቁጥጥር ኮሚቴና አጠቃላይ የዩኒየኑ አመታዊ የስራ እንቅስቃሴዎች ለጉባኤ አባላት ቀርቦ በመገምገም እንደሚጸድቅም ተናግርዋል ።

በጉባኤው የዩኒየኑ አባል ማህበራት ተወካዮች፣ ባንኮችና አጋር ድርጅቶች እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን ለጉባኤው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ቀርቦ እንደሚፀድቅም ተጠቁሟል።

በጉባኤው በክብር እንግድነት የተገኙት የዞኑ አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ መስፍን ጉብላ በዩኒየኑ ከ2011 ዓ/ም ወዲህ ሰፊ ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይም ዩኒየኑ እና አባል ማህበራት ተቀናጅተው በመስራት ለቡና ጥራት መጠበቅ ብሎም ለአርሶ አደሩ ሕይወት መለወጥ ሊሰሩ ይገባል ብለው ዞኑም ለስኬታቸው ከጎናቸው እንደሚሆን ገልፀዋል።

Address

Mizan Teferi

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bench Sheko Zone Prosperity Party Branch Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share