Bench Sheko Zone Justice Department legal drafting

Bench Sheko Zone Justice Department legal drafting መብቱንና ግዴታውን ያወቁ ማህብረሰብ እንፈጥራለን!

05/11/2025
የወንጀል ምርመራ ውጤታማነትን ይበልጥ ለማጠናከር ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ተባለ ።ሚዛን አማን ጥቅምት 26/2018(ቤሸቴ) የቤንች ሸኮ ዞን ፍትህ መምሪያ እና የዞኑ...
05/11/2025

የወንጀል ምርመራ ውጤታማነትን ይበልጥ ለማጠናከር ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ተባለ ።

ሚዛን አማን ጥቅምት 26/2018(ቤሸቴ) የቤንች ሸኮ ዞን ፍትህ መምሪያ እና የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ከስር መዋቅሮቻቸው ጋር በጋራ በመሆን በወንጀል ምርመራ ውጤታማነትና ቅንጅታዊ አሰራሮች ዙሪያ የጋራ ምክክር መድረክ እያካሄደ ነው ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ተወካይ አቶ መስፍን ጉብላ የፍትህ አገልግሎት ስርዓትን ዘር፣ቀለም፣ብሔር ባለመለየት የህግ የበላይነትን በማስፈን የህግ አሰራሮችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

ወንጀል ቴክኖሎጂን መሠረት በማድረግ የሚፈጸምበት ወቅት ላይ ያለን በመሆኑ የምርመራ ስራዎችን የቴክኒክ ስልት ቀይሶ በመጠቀም ወንጀለኞችን ለህግ የማቅረብና የማስወሰን ስራ ባለድርሻ አካላት ከመቼውም ጊዜ በላቀ ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉም አቶ መስፍን ተናግርዋል ።

የዞኑ ፍትህ መምሪያ ኃላፊ አቶ መሠረት ወገስ የወንጀል ፍትህ አስተዳደር ስርዓት ውጤታማ እንዲሆን ፖሊስና ዐቃቤ ህግ ሚናቸው ከፍተኛ በመሆኑ ቅንጅታዊ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል።

ተቋማዊ ተግባራት በተናጠል ማከናወን እንደተጠበቀ ሆኖ የሁለትዮሽ ፣የሶስትዮሽ እና የአራትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ በማዘጋጀት እና በመፈራረም ሲሰራ መቆየቱንም አቶ መሠረት ተናግረዋል ።

ይህንን ስራ ይበልጥ ውጤታማ በማድረግ ከምርመራ እስከ ውሳኔ ያሉትን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመገምገምና በማስተካከል ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡም አቶ መሠረት ጠይቀዋል ።

ቅንጅታዊ ስራዎችን የተመለከተ ሰነድ በአቶ ኤፍሬም ደግቶ የቀረበ ሲሆን የቀረቡ አቤቱታዎች ምርመራ ተጠርቶባቸው ከማጠናቀቅ አኳያ በፖሊስ በኩል ውዝፍ መዝገቦች እየተጠራቀሙ መሆኑንና በዐቃቤ ህግ በኩልም ተጠናቅቀው የቀረቡ አቤቱታዎችን ውሳኔ ከማግኘት አንጻር የመወዘፍ ምጣኔው ከፍ እያለ በመሆኑ የመድረኩ ተሳታፊዎች ሊመክሩበት ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ ቅንጅታዊ አሰራርን የተመለከተ ሰነድ፣የስነምግባር ግንባታ የሙስና መከላከል ጥምረት እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ውጤታማነትና ቅንጅታዊ ስራዎች ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል።

መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የቤንች ሸኮ ዞን ፍትህ መምሪያ ከስር መዋቅሮቻቸው የሲዝ ከተማ አስተዳደርና የጊዲ ቤንች ወረዳ የ2018 በጀት ዓመት የአንደኛ ሩብ ዓመት ሪፖርትና ግብረመልስ ላይ በነገው ዕለት እንደሚመክሩበት ከወጣው የድርጊት መርሃግብር ማወቅ ተችሏል።

ታጠቅ አበበ

#መልካም እሴትን እንገነባለን #

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች መረጃዎችን ይከታተሉ
‎facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=61580291218857
‎Tiktok https://www.tiktok.com/?is_from_webapp=1...
‎Telegram https://t.me/benchshekotelevision

16/10/2025

አንዱ ፍትህ መስጫ መንገዱ ሕግ የበላይነት መርሆን መተግበር ነው።
ሕግ ከስልጣን ፣ከወገንተኝነት ፣ከገንዘብ በላይ ሲሆን ያኔ ፍትህ በየትኛውም መንግሥት ተቋማት ይሰፍናል ።ምክንያቱም ፍትህ ለሁሉም !!

አዲሱ የመንግሥት ሠራተኞች የቀንውሎ አበል መመሪያ
04/10/2025

አዲሱ የመንግሥት ሠራተኞች የቀንውሎ አበል መመሪያ

Yeri wobsmke!!!
17/09/2025

Yeri wobsmke!!!

17/07/2025
25/05/2025

"[ቼ]ክ ተላላፊ የገንዘብ ሠነድ እንደመሆኑ በዋስትና ሊሰጥ አይቻልም የሚል ድንጋጌም ስለሌለ በመርህ ደረጃ ቼክ ለዋስትና ሊሰጥ ይችላል:: ይሁንና አንድ ሰው ቼክ ጽፌ የሰጠሁት እንዲመነዘር ሳይሆን ካለን የንግድ ግንኙነት የተነሣ ለመተማመኛ/ለመያዣ/ለዋስትና ስለሆነ ቼኩን ስጽፍ ወይም ቼኩ ለክፍያ በቀረበበት ጊዜ በቼክ በማንቀሳቅሰው ሒሳብ ውስጥ በቂ ገንዘብ ባለመገኘቱ በወንጀል ልጠየቅ አይገባም ብሎ የሚከራከር ከሆነ ይህን ማስረዳት የሚችለው በንግድ ሕጉ [አንቀጽ 952] እና በፍትሐ ብሔር ሕጉ [አንቀጽ 2864-2866] መሠረት የተደረገ የመተማመኛ/የዋስትና/የመያዣ ውል በማቅረብ ነው እንጂ በሰው ምስክር ለማስረዳት አይቻልም:: ስለሆነም የመተማመኛ/የዋስትና/የመያዣ ውሉ በጽሑፍ መደረግ አለበት፣ የመያዣ ስምምነቱ ለምን ግዴታ እንደተደረገ፣ ለዋስትና የተሰጠው ቼክ ቁጥር፣ የግዴታው ከፍተኛ የገንዘብ መጠን፣ ስምምነቱ የተደረገበት ቀን፣ ቼኩ ለዋስትና ዓላማ እንደተሰጠ በውሉ ላይ በግልጽ ሊጠቀስ ይገባል:: ይህም ቢሆን ማለትም ቼኩ ሕጋዊ መሥፈርቱን ባሟላ መልኩ ለዋስትና የተሰጠ መሆኑ ቢረጋገጥም እንኳን ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ የሚያደርገው የዋስትና ግዴታውን ለመወጣት ግዴታ ከተገባበት ጊዜ በፊት ወይም በዋስትና ውሉ የተመለከተው ሁኔታ ከመፈጸሙ በፊት ቼኩ ለክፍያ ቀርቦ በቂ ገንዘብ በሒሳቡ የለም በሚል የእምቢታ ማስታወቂያ ቢሰጥና በዚህ ምክንያት የወንጀል ክስ ሲቀርብ ነው::
[ሰ/መ/ቁ.161448(ቅ.25)፣ 238847(ሰኔ 29/2015)—"መላከ ጥላሁን: የተጠቃለሉ የፌ/ጠ/ፍ/ቤ/ሰ/ሰ/ች/ውሳኔዎች ቁ.2፡ 2016 ዓ.ም" ላይ]በበሀይሉ ሀሰን👇👇

Address

Mizan Teferi

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bench Sheko Zone Justice Department legal drafting posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Bench Sheko Zone Justice Department legal drafting:

Share