Mizan Aman city Admin Prosperity Party /የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ

  • Home
  • Ethiopia
  • Mizan Teferi
  • Mizan Aman city Admin Prosperity Party /የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ

Mizan Aman city Admin Prosperity Party /የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ Media

“ሃሳብ አልቦነት የመደመር መንግሥት እንቅፋት ነው”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
30/08/2026

“ሃሳብ አልቦነት የመደመር መንግሥት እንቅፋት ነው”
- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

አመራሩ የአፈጻጸም ደረጃውን ወደ ተቀራራቢ ደረጃ በማድረስ ውጤታማ ተግባራትን እንዲያከናውን ግምገማና ምዘና ወሳኝ ነው። አቶ ተመስገን ከበደየቤንች ሸኮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት  "ከድ...
29/08/2026

አመራሩ የአፈጻጸም ደረጃውን ወደ ተቀራራቢ ደረጃ በማድረስ ውጤታማ ተግባራትን እንዲያከናውን ግምገማና ምዘና ወሳኝ ነው። አቶ ተመስገን ከበደ

የቤንች ሸኮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት "ከድል ማግስት ጠንካራ መንግስት" በሚል መሪ ቃል የአመራር ግምገመና ምዘና መድረክ እየተካሄደ ነው።

በቤንች ሸኮ ዞን የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ ግምገማና የአመራር ምዘና መድረክ በሚዛን አማን ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

ምዘናው በ2018 በጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን አጠቃላይ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የመንግሥትና የፓርቲ የልማት ሥራዎች በሕዝብ ውግንና የተመሩበትን አግባብ ለመፈተሽ ያለመ መሆኑን የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ ተናግረዋል።

በተለይም የተገኙ ስኬቶችንና ያጋጠሙ ክፍተቶችን በመለየት ለቀጣይ ሥራዎች አመራሩ ራሱን እንዲፈትሽና እንዲያዘጋጅ የሚያስችል መድረክ መሆኑም ጠቁመዋል።

የአመራር ምዘናው አመራሩ እርስ በርሱ የሚገነባበትና የታዩ ክፍተቶችን የሚያርምበት እንደሚሆን ተናግረዋል።

አመራሩ ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታዎችን በትክክል ገምግሞና ተረድቶ ከመምራት አንጻር የሚታዩ ውስንነቶችን በማረም፣ የአስተሳሰብ አንድነት ፈጥሮ ውጤታማ ሥራ ለማስመዝገብ ምዘናው አጋዥ ሊሆን እንደሚገባም አቶ ተመስገን አስረድተዋል።

በቀጣይም አመራሩ የአፈጻጸም ደረጃውን ወደ ተቀራራቢ ደረጃ በማድረስ ውጤታማ ተግባራትን ለመፈጸም በትኩረት መስራት ላይም ያተኮረ መሆኑን ተናግረዋል።

የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ምዘና የአመራሩን የተግባር ውጤታማነት፣ ኃላፊነትን በብቃት የመወጣት አቅም፣ የአመራር ስብዕናን ከመላበስ እና ሌሎች የፓርቲ ግዴታዎችን ከመወጣት አንጻር የአመራሩ ቁመና የሚታይበት መሆኑን ገልጸዋል።

የመንግሥትና የፓርቲ ተግባራትን መሠረት ያደረገ የአመራር ምዘና ማካሄድ ሁለንተናዊ ልማትን ማረጋገጥ የሚችል ብቁ አመራር ለመፍጠር አቅም እንደሚሆንም አቶ ተመስገን ተናግረዋል።

ለሦስት ተከታታይ ቀናት በሚቆየው የምዘና መድረክ፣ ለውይይት መነሻ የሚሆን አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ የዳሰሰ ሰነድ በዞኑ ረዳት የመንግሥት ተጠሪና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፍርድአወቅ አለሙ አማካኝነት እየቀረበ ይገኛል።

የአመራር ምዘናው አመራሩ በነበረው የሥራ አፈጻጸም የታዩ ጥንካሬዎችንና ድክመቶችን በግልጽ የሚያይበት፣ እንዲሁም የተቋማት ኃላፊዎች አመታዊ የሥራ አፈጻጸማቸው ወደ ምዘና ውጤት ተቀይሮ የሚገመገምበት ተግባር መሆኑም ተገልጿል።

መድረኩን የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ ወንድሙ ኩርታ ፣ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተመስገን ከበደ እና የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትልና የቤቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸብር ኢካሎ በጋራ እየመሩ የሚገኙ ሲሆን በመድረኩ የዞን አጠቃላይ አመራር እንዲሁም የሁሉም ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተሳትፈዋል።
Mizan Aman city Admin prosperity party

"ህዝብን እየዘረፉና እያሰቃዩ በጎን ደግሞ በሕዝብ ስም የሚምሉ ልሂቃን ተወግደው፣ ታታሪና ብቁ ሰዎች ወደ አመራርነት እንዲመጡ ከተፈለገ አመራርን ከብሔር ውክልና ጋር ብቻ አጣብቀን የምናይበት...
28/08/2026

"ህዝብን እየዘረፉና እያሰቃዩ በጎን ደግሞ በሕዝብ ስም የሚምሉ ልሂቃን ተወግደው፣ ታታሪና ብቁ ሰዎች ወደ አመራርነት እንዲመጡ ከተፈለገ አመራርን ከብሔር ውክልና ጋር ብቻ አጣብቀን የምናይበት መነጽር ሊስተካከል ይገባዋል"

#መደመር

የአመራር ቁመና ከብልፅግና ፓርቲ መርሆችና ዕሴቶች ጋር የተጣጣመ ሊሆን ይገባል፦ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት ማ...
25/08/2026

የአመራር ቁመና ከብልፅግና ፓርቲ መርሆችና ዕሴቶች ጋር የተጣጣመ ሊሆን ይገባል፦ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የአመራር ግምገማና ምዘና መድረክ በቦንጋ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ ተልዕኮዎችን በተሻለ መልኩ በመፈጸም የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ መጠነ ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን እና ከአፈጻጸም አኳያም ከጊዜ ወደ ጊዜ አዎንታዊ መሻሻሎች መታየታቸውን ገልጸዋል።

ይሁን እንጅ በአስፈፃሚ ተቋማት መካከል የሚታየውን የተግባር አፈጻጸም ልዩነት ማጠበብ እንደሚያስፈልግ የገለፁት ርዕሰ መስተዳድሩ በሂደቱ የአመራር ቁመና በብልፅግና ፓርቲ መሠረታዊ መርሆችና ዕሴቶች ላይ የተመሠረተ መሆን እንዳለበትም አሳስበዋል።

መድረኩ በየደረጃው የሚገኘውን አመራር የአመለካከትና የተግባር አንድነት ለመመዘን፣ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም እንዲሁም አመራሩ በቀጣይ የሕዝብ ተጠቃሚነትን በተሟላ ሁኔታ እንዲያረጋግጥ ለተልዕኮ የሚያዘጋጅ መሆኑንም ርዕሰ መስተዳድሩ የጠቆሙት።

የመድረኩ ዋና ዓላማ አስፈጻሚዎች የፓርቲና የመንግሥት ተግባራትን በጥራትና በውጤታማነት እንዲያከናውኑ ማብቃት መሆኑን የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን የገለጹት።

መድረኩ ድክመቶችን በማረም ለቀጣይ ተልዕኮ ከማዘጋጀት ባሻገር፣ የውስጠ ፓርቲ ጤንነትና የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት መርህን በማረጋገጥ የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳካት የሚያዘጋጅ መሆኑንም አቶ ፍቅሬ አክለው ገልጸዋል ሲል የክልሉ መንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።

በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የ2019 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ እየተካሄደ ነው።በከተማ አስተዳደሩ በአጠቃላይ ...
24/08/2026

በቤንች ሸኮ ዞን በሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የ2019 የትምህርት ዘመን በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ እየተካሄደ ነው።

በከተማ አስተዳደሩ በአጠቃላይ በ53 የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑም ተገልጿል።

በ2019 የትምህርት ዘመን ከቅድመ አንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል ባሉ የክፍል ደረጃዎች 42 ሺህ 673 ነባርና አዲስ ተማሪዎችን በመመዝገብ ወደ ትምህርት ገበታ ለማስገባት ታቅዶ ወደ ተግባር መገባቱን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ኩይክ ገልጸዋል።

ትምህርት የዝግጅት፣ የተግባርና የማጠቃለያ ምዕራፎች ያሉት መሆኑን የገለፁት ኃላፊው በዝግጅት ምዕራፉ ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤቶች ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የንቅናቄ መድረክ መካሄዱን ኃላፊው አክለው ገልጸዋል።

የተማሪዎችን ምዝገባ በቀናት ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ ወደ ተግባር መገባቱን የገለፁት ኃላፊው የተማሪ ወላጆችና ቤተሰቦች ቀድመው ተማሪዎችን በማስመዝገብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የ2019 ዓ/ም ትምህርት መስከረም 5/2019 ዓ/ም በይፋ የሚጀመር መሆኑም ተገልጿል።

በአዲስ ከተማ ቀበሌ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥሏልበሚዛን አማን ከተማ በአዲስ ከተማ ቀበሌ የ2018/19 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉ ተገለ...
22/08/2026

በአዲስ ከተማ ቀበሌ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥሏል

በሚዛን አማን ከተማ በአዲስ ከተማ ቀበሌ የ2018/19 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት በተጠናከረ መልኩ መቀጠሉ ተገለጸ።

የሚዛን አማን ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የክረምት በጎ ፈቃድ የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ኬዚ እንደገለጹት፤ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት በከተማው በተለያዩ አካባቢዎች በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል ብለዋል።

አቶ ብርሃኑ ኬዚ አክለው፤ በዛሬው ዕለት በአቅመ ደካማ ወገኖች የቤት ግንባታ መርሃ ግብር ሁለት ቤቶች እየተገነቡ ሲሆን ከእነዚህም በአዲስ ከተማ ቀበሌ ቀጠና 01 አንድነት መንደር ለአቶ አሸናፊ አለማየሁ እንዲሁም በቀጠና 02 ለንደን መንደር ለወ/ሮ አድሴ አባሪ እያንዳንዳቸው 52 ቆርቆሮ የመኖሪያ ቤቶች እየተሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

“በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በሚካሄደው የዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በሚዛን አማን ከተማ ለአቅመ ደካማ ወገኖች 21 የመኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ እስካሁን 19 ቤቶች መገንባታቸውን አቶ ብርሃኑ ገልጸዋል።

የአዲስ ከተማ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አማኑኤል ዘለቀ በበኩላቸው፤ የ2018/19 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ በቀበሌው እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አቶ አማኑኤል አክለውም፤ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር የብልጽግና ፓርቲ ሰው ተኮር ሥራዎች አካል መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ፓርቲ ሰባዊ ልዕልና ለማረጋገጥ ከሚሰራቸው ስራዎች የሚመደብ እንደሆነ አንስተዋል።

በቀበሌው ለተግባሩ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በጎ ፍቃደኛ የሕብረተሰብ እና በተለያዩ አካላት ተሳትፎ እየተሰራ መሆኑን አቶ አመኑኤል ዘለቀ አስረድተው በ16 ዘርፎች በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆኑ ገልፀዋል።

አቶ አማኑኤል ዘለቀ እንደገለፁት፤ የአቅመ ደካማ ወገኖች የቤት ግንባታ በዚህ የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባር ከሚከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎች አንዱ መሆኑንም ጠቁመው በዛሬው ዕለት እየተገነቡ ያሉት ሁለት ቤቶች ብቻ ግምታዊ ወጪያቸው ከ800 ሺህ ብር በላይ መሆኑን ገልጸው፣ እስካሁንም በቀበሌው አምስት ለአቅመ ደካማ ወገኖች የተሰሩ የመኖሪያ ቤቶች መገንባታቸውን አንስተዋል።

በቀበሌው የሚካሄዱት የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት አቅመ ደካማ ወገኖችን በመደገፍ፣ የመኖሪያ ችግሮቻቸውን በማቃለል እና በማህበረሰቡ ውስጥ የመተባበርና የመረዳዳት እሴቶችን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆናቸው አቶ አማኑኤል ዘለቀ ገልጸል።

የአማን ቀበሌ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ተካሄደበሚዛን አማን ከተማ የአማን ቀበሌ 4ኛ ዙር የ14ኛ ዓመት 2ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤ ተካሂዷል።ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የቀበሌው...
22/08/2026

የአማን ቀበሌ ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ ተካሄደ

በሚዛን አማን ከተማ የአማን ቀበሌ 4ኛ ዙር የ14ኛ ዓመት 2ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤ ተካሂዷል።

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የቀበሌውንና የቀጠናዎችን አመራሮች ሹመት በመወያየት አጽድቋል።

የቀበሌውን እጩ አመራሮች ሹመት ያቀረቡት የሚዛን አማን ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እና ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ አቢዮት ጫራይት ናቸው።

በጉባኤው ላይ የምክር ቤቱ አባላት በተሰናባች አመራሮችና በቀረቡት እጩዎች ዙሪያ የተለያዩ አስተያየቶች፣ ሐሳቦችና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ሲሆን፣ ለቀረቡት ጉዳዮችም በአቶ አቢዬት ጫራይት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በዚሁ መሠረት ምክር ቤቱ የአቶ ፈለቀ ሙሴን የአማን ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪነት ሹመት አጽድቋል።

በተመሳሳይም የቀጠና አመራሮች ሹመት ለምክር ቤቱ የቀረበ ሲሆን፣ በአማን ቀበሌ የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሪት ገነት ናካ የቀረቡት የእጩ አመራሮች ሹመትም በምክር ቤቱ ጸድቋል።

በምክር ቤቱ የጸደቁት አመራሮች በሚዛን አማን ከተማ ፍርድ ቤት ዳኛና በቀበሌው ማህበራዊ ፍርድ ቤት ዳኛ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።

በመጨረሻም ተሰናባቹ የአማን ቀበሌ የቀድሞ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ፎታ፣ ከሹመት ቀናቸው ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከጎናቸው በመቆም ለደገፏቸው የምክር ቤት አባላትና ለሌሎች አካላት ምስጋና አቅርበው አዲሱ የአማን ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ፈለቀ ሙሴም በአዲሱ ኃላፊነታቸው መልካም ስኬት እንዲያዲገጥማቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ከመንግስት ካዝና ሊወጣ የሚገባውን 25,361, 824 ብር በላይ ማትረፍ መቻሉን ተገለጸ በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ስር በወጣቶች እና ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት የተከናወ...
21/08/2026

ከመንግስት ካዝና ሊወጣ የሚገባውን 25,361, 824 ብር በላይ ማትረፍ መቻሉን ተገለጸ

በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ስር በወጣቶች እና ሴቶች ክንፍ አስተባባሪነት የተከናወኑ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ

በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ስር የሰላም ሚኒስቴር ከቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ ወጣቶች እና ሴቶች ክንፍ ጋር በመቀናጀት ያከናወናቸው የ2018/19 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ግምገማ ተካሄዷል።

በግምገማ መድረኩ ላይ የተገኙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወጣት ሰይድ ኢብራሂም የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ዶሻ በጋራ በመሆን መድረኩን መርተውታል::

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በመገንባት፣ ደም በመለገስ፣ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ፣ የአካባቢ ፅዳት በማከናወንና የወጣቶችን ትስስር በማጠናከር ረገድ በቀጣይነት በትኩረት መሥራት እንደሚገባ ተገልጿል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወጣት ሰይድ ኢብራሂም በበኩላቸው በዚህ ክረምት በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር የተሰሩት ስራዎች የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ ወጣቱን በማሳተፍ ተግባራቱን በማስቀጠል ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል

በቤንች ሸኮ ዞን ሚዛን አማን ከተማ በ14 የሥራ መስኮች ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ ተጠቁሟል በተለይም የደም ልገሳ፣ የአካባቢ ፅዳት፣ የችግኝ ተከላ፣ የትራፊክ ደህንነት አገልግሎት ድጋፍ፣ የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብና ለተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠት ዋነኞቹ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

በሪፖርቱም በጠቅላላ በዚህ ክረምት ወንድ 10,955ወጣቶችን ለማሳተፍ ብሎም ሴት 10,954 ድ 21,909 ታቅዶ ክንውን 11,785 ሴ 10,269 ድ 22,054 አፈጻጸም 100% በማሳካት ከመንግስት ካዝና ሊወጣ የሚገባውን 25,361, 824 ብር በላይ ማትረፍ መቻሉን እና አፈጻጸሙ ከ 96% በላይ መሳካቱን በሪፖርቱ ላይ ተመላክቷል

በቀረበው ሪፖርት ላይ ጠለቅ ያለ ውይይት ከተደረገበት በኃላ ደካማ እና ጠንካራ ጎኖች ተነስተውበታል በተነሱ ጠንካራ ጎኖች ላይ በጥንካሬ ማስቀጠል እንደሚገባ ተነስቶ በደካማ የተነሱ ነጥቦችን በቀጣይ በጥንካሬ በመቀየር ሊሰራበት እንደሚገባ ተነስቷል

በመድረኩም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የወጣቶች ክንፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወጣት ሰይድ ኢብራሂም
የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ሚዲያ እና ኮሚዩኒኬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ዶሻ ጨምሮ ሌሎች የሰላም ሚኒስተር ተወካይ የዞን እና የከተማ ወጣት ኃላፊ ተገኝተውበታል

Mizan Aman city Admin prosperity party

በሚዛን አማን ከተማ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የተከናወኑ ተግባራት ተገመገሙበደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ክትትልና ሱፐርቪዥን ቡድን በሚዛን አማን ከተማ...
21/08/2026

በሚዛን አማን ከተማ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የተከናወኑ ተግባራት ተገመገሙ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ ክትትልና ሱፐርቪዥን ቡድን በሚዛን አማን ከተማ ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ከከተማው ስትሪንግ ኮሚቴ ጋር በመወያየት ገመገመ።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ በከተማው ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎችን በመገምገም፣ የተገኙ ውጤቶችን፣ ያሉ ተግዳሮቶችንና ቀጣይ ሊከናወኑ የሚገቡ ተግባራትን በመለየት የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።

በውይይቱ የሰብዓዊ ድጋፍ ተረጂነትን በራስ አቅም ለመቀነስና በዘላቂነት ለመፍታት የተዘጋጁ ዕቅዶች፣ ተጋላጭ የሕብረተሰብ ክፍሎችን የመለየት ሥራ፣ ሀብት የማሰባሰብ እንቅስቃሴዎች፣ የምግብ ክምችት ማዘጋጀትና ከምግብ ውጭ ያሉ አስፈላጊ የሰብዓዊ ድጋፍ ቁሳቁሶችን የማዘጋጀት ሥራዎች ላይ ገለጻ ተደርጓል።

በተጨማሪም፣ የከተማ አስተዳደሩ ተረጂነትንና ልመናን በማስቀረት ሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።

ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ አደጋዎች በሚከሰቱበት ወቅት በራስ አቅም ለመቋቋምና ተጋላጭ ለሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ወቅታዊና ተገቢ ድጋፍ ለማድረግ የተያዙ አቅጣጫዎች በተግባር እየተተገበሩ መሆኑ ተመልክቷል።

ከውይይቱ ጎን ለጎን በከተማው የተከናወኑ የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራዎችም ተጎብኝተው ተገምግመዋል። በዚህም የክምችት መጋዘኖችን ማዘጋጀት፣ ለሰብዓዊ ድጋፍ የተሰበሰበ እህልን በአግባቡ ማከማቸት፣ በጥሪ የተሰበሰበ ገንዘብ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀ የባንክ ሂሳብ እንዲገባ ማድረግ እንዲሁም በቀበሌ ደረጃ ኮሚቴዎችን በማደራጀት ወደ ተግባር መግባት የተከናወኑ ተግባራት መሆናቸው ተገልጿል።

በመጨረሻም፣ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም የመሸፈን አቅምን ለማጠናከር የሀብት ማሰባሰብ፣ የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ የድጋፍ ቁሳቁሶችን ማሰባሰብና ማከማቸት፣ ተጋላጭ የሕብረተሰብ ክፍሎችን በትክክል መለየትና በተቀናጀ መልኩ ድጋፍ ማድረስ እንዲሁም የተደራጀ የአመራርና የክትትል ሥርዓትን ማጠናከር የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸው ተጠቁሟል።

በዚህ አመት የምንሰራው ሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ሽግግርም የምናደርግበት እያንዳንዱ መዋቅር እራሱን የሚችልበት ሁኔታን ማዘጋጀት ነው ፍርዳወቅ አለሙ።በ2019 ዓ,ም በፓርቲ የሚመሩ ወቅታዊ ...
21/08/2026

በዚህ አመት የምንሰራው ሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ሽግግርም የምናደርግበት እያንዳንዱ መዋቅር እራሱን የሚችልበት ሁኔታን ማዘጋጀት ነው ፍርዳወቅ አለሙ።

በ2019 ዓ,ም በፓርቲ የሚመሩ ወቅታዊ ተግባራት እና ኢኒሼቲቭ አጀንዳዎች የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው
በቤንች ሸኮ ዞን አጠቃላይ በፓርቲ የሚመሩ ወቅታዊና መደበኛ የንቅናቄ ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው ።

በመድረኩ የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ እና የፖለቲካ እና ዲሞክራሲ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ፍርዳወቅ አለሙ እንደገለፁት በንቅናቄ የሚመሩ ተግባራትን ለመፈጸምና ለማስፈጸም የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ቀይሶ ህዝቡን በማሳተፍ ለውጤታማነቱ መረባረብ እንደሚገባም አሳስበዋል።

አመራሩ እያንዳንዱን ተግባር ቆጥረዉ ወስደዉ እታች ሠራዊት በመፍጠር በዉሎ ግምገማ አቅጣጫ እያስቀመጠ ሊመራ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

ወጣቶች የነገ ተስፋ ብቻ አይደሉም፤ የዛሬ አቅምና የልማት ሞተር ናቸው። ስለሆነም የወጣቶችን ሥራ ዕድል መፍጠር ለወጣቱ ብቻ የሚሰጥ ድጋፍ ሳይሆን፣ ለሀገር ኢኮኖሚ፣ ለቤተሰብ ደህንነትና ለዘላቂ ልማት የምንሰጠው ወሳኝ አስተዋፅኦ ነው።

ዛሬ ከፊታችን ያሉት ወጣቶች ችግር ብቻ ሳይሆን መፍትሔም እንዳላቸው በግልጽ ማየት ይገባናል። በግብርና፣ በቴክኖሎጂ፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በአገልግሎት፣ በንግድ፣ በፈጠራና በዲጂታል ሥራዎች የሚያሳዩት ተሰጥኦ በትክክል ከተደገፈ ብዙ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር ይችላል። ስለዚህ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራችን ከሥራ ፈላጊ ወጣት ብቻ ወደ ሥራ ፈጣሪ ወጣት ማሸጋገርን ማስቀደም ይኖርበታል ስሉም ተናግረዋል።

በዚህ አመት የምንሰራው ሰብአዊ ድጋፍ በራስ አቅም ሽግግርም የምናደርግበት እያንዳንዱ መዋቅር እራሱን የሚችልበት ሁኔታን ማዘጋጀት ነው።

አመራሩ ሁሉንም ተጎባራት በፓርቲ እሳቤ ቅኝት በመምራት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ከየትኛዉም ጊዜ በላይ በትኩረት ሊሠሩ እንደሚገባ ተናግሯል።

የዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ከሚሰሩት ሥራዎች አኳያ የፋይዳ መታውቂያ እና ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ሚናው ከፍተኛ ስለሆነ በትኩረት መመራት እንዳለበት ተናግሯል ።

በመድረኩም ሪፖርቶች እየቀረቡ ሲሆን በመድረኩ የቤንች ሸኮ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ እና የፖለቲካ እና ዲሞክራሲ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ፍርዳወቅ አለሙ የዞን አጠቃላይ አመራር የወረዳ አስተዳደሮች እና የከተማ ከንቲባዎች የወረዳ እና የከተማ ፓርቲ ኃላፊዎች ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተውበታል፣

Mizan Aman city Admin Prosperity party

Address

Mizan Aman
Mizan Teferi

Telephone

+251995000968

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mizan Aman city Admin Prosperity Party /የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Mizan Aman city Admin Prosperity Party /የሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ:

Shortcuts

Share