Bench Sheko Zone Revenue Authority

Bench Sheko Zone Revenue Authority Pay tax today for better tomorrow!

የደረጃ ለ ግብር ከፋዮች ጊዜው እየሄደ ስለሆነ ሳትዘናጉ ሂሳብ መዝገባችሁን እንድታስገቡ እናሳስባለን።
11/08/2021

የደረጃ ለ ግብር ከፋዮች ጊዜው እየሄደ ስለሆነ ሳትዘናጉ ሂሳብ መዝገባችሁን እንድታስገቡ እናሳስባለን።

04/08/2021

ሂሳብ መዝገብ የመያዝ ጠቀሜታ
 ግብር ከፋዮች የድርጅታቸውን ገቢ እና ወጪ በትክክል እንዲይዙና በሂሳብ ዘመኑ ማብቂያ ላይ ድርጅታቸው አትራፊ ወይም አክሳሪ መሆኑን በቀላሉ ለማወቅ ያስችላቸዋል፣
 የግብር እና የታክስ ግዴታቸውን በተመለከተ ተዓማኒነትና ተቀባይነት ያለው መረጃ ለማቅረብ የሚያስችል የመረጃ አደረጃጀትና አያያዝ ስለሚኖራቸው ከግብር አስገቢው መስሪያ ቤት ጋር መልካም የስራ ግንኙነት ለመፍጠር ይረዳቸዋል፣
 የግምት አሠራርን በማስቀረት በድርጅቱ ላይ የሚሰጡ የግብር እና ታክስ ውሳኔዎች ፍትሃዊና ትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ያግዛል፣
 ከግብር አወሳሰን ጋር ተያይዞ በግብር ከፋዩ በኩል ሊቀርቡ የሚችሉ ቅሬታዎችን ይቀንሳል፣
 ግብር ከፋዮች በገቢ ግብር ህጉ የተፈቀዱ የተለያዩ መብቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፣
 በህግ የተፈቀዱ ወጪዎችን የማቀናነስ (ለምሳሌ ለስራ ማስኬጃ; ለመድህን ዋስትና: ለባንክ ወለድ: ለእርጅና ቅናሽ: ለጥገና: ለጥሬ ዕቃ: ለተጨማሪ እንቨስትመንት ወዘተ) መብት ለመጠቀም የሂሳብ መዝገብ ዋነኛ ቅድመ ሁኔታ ነው
 ለንግድ ስራው የሚጠቀማቸውን ሀብቶች (ገንዘብ: ንብረት ወዘተ) እንዲሁም ወጪዎች: ገቢዎችና ሌሎች ሂሳቦችን የተሟላ መረጃ እንዲያገኝ ስለሚያስችለው በንግድ ስራ ላይ ያዋለውን ሀብት በአግባቡ ለመቆጣጠርና ወቅታዊ የድርጅቱን የጥሬ እቃ አቅርቦትና ክምችት መጠን በዓይነት የሚገኝበትን ሁኔታ ለማወቅ ያስችለዋል፣
 ኪሳራን የማሸጋገር መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችላቸዋል፣
 መዝገብ ባለመያዝ ከሚጣል መቀጫ መከላከል ይችላል፣
 የእርጅና ቅናሽ የማካካስና ሌሎች በህግ የተፈቀዱ መብቶች ተጠቃሚ እንዲሆን ያስችለዋል፡፡
 ግብር ከፋዩ ከገንዘብ አበዳሪና መሰል ተቋማት ጋር ለሚኖረው የሥራ ግንኙነት የንግድ ድርጀርቱን የተሟላ መረጃ መስጠት ስለሚያስችለው ከነዚህ ተቋማት ሊያገኝ የሚፈልገውን አገልግሎት በቀላሉ ለማግኘት ያስችለዋል፡፡

02/08/2021

በዚህ ገጽ ስለ ዞናችን የገቢ አሰባሰብና ተቋማችን ስለሚሰጠው አገልግሎት ያለዎትን ሀሳብ እና አስተያየት ይጻፉ ያጋሩን፡ለአገልግሎታችን መሻሻል የእርስዎ ሚና ከፍተኛ ነው።፡የቤንች ሽኮ ዞን ገቢዎች ፔጅን ላይክ ያድርጉ ለጓደኛዎትም ያጋሩ።

የደረጃ "ሐ" ግብር መክፈያ ጊዜ ሊጠናቀቅ ነው፡፡
02/08/2021

የደረጃ "ሐ" ግብር መክፈያ ጊዜ ሊጠናቀቅ ነው፡፡

22/07/2021

የኢፌዴሪ ገቢዎች ሚኒስቴር አምስት ተቋማዊ ዕሴቶች፤
1. ታማኝነት፣
2. አገልጋይነት፣
3. መሰጠት፣
4. ሙያዊ ብቃትና
5. ቡድን ሥራ ስሆኑ
አምሰቱ ስተራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች
1. ተቋማዊ አቅም
2. የአሠራር ልህቀት
3. ስትራቴጂያዊ አጋርነት
4. የህግ ተገዢነት አመራር
5. ዘላቂ የገቢ ዕድገት
አምስቱ የአፈጻጸም አቅጣጫም
1. ታክስን በፍቃደኝነት የመክፈል ባህልን ማሳደግ
2. ዲጂታል ታክስ አስተዳደር ሥርዓት መገንባት
3. የታክስ ፍትሐዊነትን ማረጋገጥ
4. የዉስጥና የዉጪ ስትራቴጂያዊ አጋሪነትን ማጠናከር
5. የዳበረ የሥራ ባህልን ማምጣት

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!
20/07/2021

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!

20/07/2021

ገቢ ለልማት!
የሚጠበቅብንን ግብር በመክፈል የሀገራችን ብልጽግና እናፋጥን፡ወቅቱ የደረጃ ሐ ግብር የሚሰበሰብበት በመሆኑ ተጨማሪ ቅስቀሳ ሳያስፈልግ አቅራቢያችን በሚገኙ የአንድ ማዕከል በመቅረብ ግብራችን በመክፈል ንግድ ፍቃዳችን በማሳደስ በመጨረሻ ቀናት ሊከሰት ከሚችል መጨናነቅ ራሳንን እንከላከል።

15/07/2021
የደቡብ ቤንች ወረዳ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ግብር ከፋይ ደንበኞችን በመጠባበቅ ላይ
15/07/2021

የደቡብ ቤንች ወረዳ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ግብር ከፋይ ደንበኞችን በመጠባበቅ ላይ

Address

SNNPR
Mizan Teferi

Telephone

+251473351458

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bench Sheko Zone Revenue Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Bench Sheko Zone Revenue Authority:

Share