Snnprs Yem Public Service and H R O

Snnprs Yem Public Service and H R O We aspire to see a public service which effectively and ethically achieves its mission by 2020

A growth mindset also helps when you are employed. Feel part of the company, share the same goals and always try to do y...
02/05/2023

A growth mindset also helps when you are employed. Feel part of the company, share the same goals and always try to do your best.

አምደ-ንባብ ምዕራፍ ሁለትየአገልጋይ መሪ ሚና እና የሠራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት
02/05/2023

አምደ-ንባብ
ምዕራፍ ሁለት
የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሠራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት

አምደ-ንባብ የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሠራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት
27/04/2023

አምደ-ንባብ
የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሠራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት

የየም ልዩ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ለጽህፈት ቤቱ አመራርና ባለሙያዎች በተቋማት አገልገሎት አሰጣጥ ሂደት የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሰራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት ላይ ስልጠና ሰጠ ። ሳጃ ...
12/04/2023

የየም ልዩ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ለጽህፈት ቤቱ አመራርና ባለሙያዎች በተቋማት አገልገሎት አሰጣጥ ሂደት የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሰራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት ላይ ስልጠና ሰጠ ።
ሳጃ :- ሚያዝያ 4/2015(የየም ልዩ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት)
የየም ልዩ ወረዳ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ለጽህፈት ቤቱ አመራርና ባለሙያዎች በተቋማት አገልገሎት አሰጣጥ ሂደት የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሰራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት ላይ ስልጠና ሰጥቷል ።
የስልጠናው ዋና አላማ የሥራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ስለ ስራ አመራርና መሪነት ጉዳዮች ግንዛቤ በመያዝ እውቀታቸውንና ክህሎታቸውን እንዲሁም በተግባር የሚገልጽ ቁርጠኝነታቸውን በስራ ቦታቸው በማዋል በተቋማቸው ላይ ከበፊቱ የበለጠ ስኬታማ ለውጥ ማምጣት እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑን የልዩ ወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አለማየሁ ገ/ሚካኤል ገልጸዋል ።
በስልጠና መድረኩ በልዩ ወረደው ፐብሊክ ሰርቪስ ና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት በኩል ለአመራርና ሠራተኞች የተዘጋጀ የአመራርና ባለሙያዎች በተቋማት አገልገሎት አሰጣጥ ሂደት የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሰራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት ላይ ና የመልካም አስተዳደር መርሆች ትግበራን ለማጠናከር የተዘጋጀ ዝርዝር የስልጠና ሰነድ ቀርቦ በቀረበው ሰነድ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱም ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት የስልጠና መድረኩ አስፈላጊና ተገቢነት ያለው መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ ለተግባር ስኬት ጥሩ መነሳሳትና ግንዛቤን ፈጥሮልናል ብለዋል።
ከሀሳብ አስተያየቱ መነሻ የውይይት መድረኩን በጋራ የመሩት አቶ ቸርነት ዘርፉና አቶ አለማየሁ ገ/ሚካኤል እንደገለጹት ሰልጣኞች ከስልጠናው ባገኙት እውቀት ልክ በተሰማሩበት የስራ መስክና ባሉበት ተቋም በተገቢው ማገልገል ይኖርባቸው ብለዋል።
ዘጋቢ :- ሀብታሟ ወ/ሃና

የየም ልዩ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓ/ም  3ኛ ሩብ  ዓመት የቀበሌ ሥራ አስኪያጆችን አፈጻጸም  ላይ እና በቀጣይ 3 ወራት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላ...
11/04/2023

የየም ልዩ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ጽ/ቤት የ2015 በጀት ዓ/ም 3ኛ ሩብ ዓመት የቀበሌ ሥራ አስኪያጆችን አፈጻጸም ላይ እና በቀጣይ 3 ወራት ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በፎፋ ከተማ የቀበሌ ሥራ አስኪያጆችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የጋራ የምክክር ዉይይት አደረገ ᎓᎓
ሚያዝያ 2/2015ዓ/ም

ክፍል ሶስት የቀጠለ……………….. የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሠራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት በሚል ከተዘጋጀ ሰነድ  ክፍል የቀጠለ በተቋም ውስጥ የሠራተኛ/የተከታይ ዓይነቶችአምስት ዓይነት ተከታዮች...
25/03/2023

ክፍል ሶስት የቀጠለ………………..
የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሠራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት በሚል ከተዘጋጀ ሰነድ ክፍል የቀጠለ
በተቋም ውስጥ የሠራተኛ/የተከታይ ዓይነቶች
አምስት ዓይነት ተከታዮች/ሠራተኞች ያሉ
ሲሆን በሚከተለው መልኩ ማሳየት ይቻላል፡፡
ሀ/ በበግ የሚመሰል ተከታይ (Sheep/Passive Follower)
ለ/ አዎ/እሺ እሺ ባይ ሰዎች (Yes People/Conformist)
ሐ/ የተገለሉ (Alienated)
መ/ ለመኖር ብቻ (Survivor)
ሠ/ ውጤታማ/ኮከብ ተከታይ (Effective/Star Follower)
ሀ/ በበግ የሚመሰል ተከታይ (Sheep/Passive Follower)
 እነዚህ ዓይነት ተከታዮች በአጠቃላይ ዳተኞች፣ ጥገኞች፣
ኃላፊነቶችና ተነሳሽነት የሌላቸው ናቸው።
 ብዙውን ጊዜ የመሪውን አስተሳሰብ የማይረዱ፣ ካልተነገራቸው
የማይፈጽሙና ሁሉን ነገር ለመሪው ብቻ የሚተው ናቸው፡፡
 ለእነዚህ ዓይነት ተከታዮች የማያቋርጥ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል።
 በዚህ ጊዜ መሪዎች በተቋም ውስጥ አወንታዊ የቲም እንቅስቃሴን
ለመፍጠርና ለማነሳሳት ለበግ ዓይነት ተከታዮች:-
o አንዳንድ የአፈጻጸም ግምገማና ግብረመልስ ወይም
o የማስተካከያ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል።
ለ/ አዎ/እሺ! እሺ! ባይ ሰዎች (Yes People/Conformist)
 የዚህ ዓይነት ተከታዮች ከመሪዎቹ የማያቋርጥ አቅጣጫ ያስፈልጋቸዋል፡፡
 ምንም እንኳን እነዚህ ዓይነት ተከታዮች ንቁ ቢመስሉም ሙሉ በሙሉ
በመሪያቸው ላይ ጥገኛ ስለሆኑ በጥሞና አያስቡም።
 መሪው የሚያቀርበው ሀሳብ ጠቃሚ ይሁን አይሁን እንደወረደ
የሚስማሙ ናቸው፡፡
 በመሆኑም ዋና ትኩረታቸው ተቀባይነት ያገኙ ስለሚመስላቸውና
ግጭትን ለማስወገድ ሲባል ብቻ ከመሪው ጋር ያለምንም ጥያቄ ይስማማሉ፡፡
 አንዳንድ ጊዜ የዚህ ዓይነት ተከታዮች ለጊዜው መሪውን የሚደግፉ ቢመስሉም ለመሪውም ሆነ ለራሳቸው አደጋ የሚፈጥሩ ፈታኝ የሆኑ አመለካከቶችን ማውጣት ስለማይፈልጉ ውጤት ሊኖረው ይችላል የሚል ዕይታ አለ፡፡
 በአመዛኙ ግን "አዎ፣ አለቃ እንዳለው!" የሚለው ሃሳብ የተሻለና የሚበረታታ ምላሽ አይደለም፡፡
ሐ/ የተገለሉ (Alienated)
 ኬሌይ የራቀውን ተከታይ ራሱን የቻለና በጥሞና የሚያስብ እንደሆነ ይገልፃል፣ ግን እነሱ ዳተኞች ወይም
ዘገምተኞች ወይም በጉዳዮች ላይ የነቃ ተሣትፎ የሌላቸው እንዲሁም የፈለገው ቢወሰን ደንታ ቢሶች ናቸው።
 ተግባቢ ቢሆኑም ጠንካራ ጎናቸውን ተጠቅመው ቲሙ ዒላመውን እንዲመታ አያግዙም።
 የሚያቀርቡት ዋጋ ያለው ነገር አላቸው ግን ላለመፈጸም የሚፈልጉ ናቸው።
 የእነርሱ ቅኝት ወይም እንግዳ ባህርይ ከመሪውና ከቲማቸው አባላት ያርቃቸዋል፡፡
 ራሳቸውን ያገለሉ ሠራተኞች ከአምስቱ ዓይነት ተከታዮች ሁሉ
በጣም የሚረብሹ ናቸው፡፡
 ለቲም ሥራ አይመቹም፣ አይሰሩም፣ አያሰሩም።
 በውሳኔ ወይም በአቅጣጫ አቀማመጥ ላይ ካልተስማሙ ብዙ ጊዜ ግብአታቸውን
አይሰጡም፣ በዝምታ ተቃውሞ ያቀርባሉ።
 ምክንያቱን ሳይናገሩ ለመተባበር ፈቃደኛ አለመሆን ደግሞ ግጭቱን ያጎላል።
 መሪዎች ከእንደዚህ ዓይነት ተከታይ ጋር ሲገናኙ አጋዥ መሆን ስላለባቸው ግጭትን ማርገብ የሚያስችል ዘይቤዎችን
በመጠቀምና በማሳመን ወደ መደበኛ ሥራ ማስገባት ይገባቸዋል፡፡

መ/ ለመኖር ብቻ (Survivor)
 ለመኖር ብቻ እሳቤ ያላቸው ሠራተኞች የእስስት ባህርይ ያላቸው ናቸው።
 እንደነዚህ ዓይነት ተከታዮች ለሆነው ሁሉ ተስማምተው የሚኖሩ ናቸው፡፡
ግን በአዎንታዊ መልኩ አይደለም፡፡
 ሁኔታው በሚፈጠርበት ጊዜ፡-
o አስተያየታቸውንና ባህርያቸውን መለዋወጥና ከአጋደለው ጋር አብረው የሚነፍሱ፣
o ለእነሱ መስሎ የመኖር ሁኔታ የሚመጣባቸውን ችግር በቀላሉ የመቋቋም መንገድ
መከተል በመሆኑ ከእሳት መስመር ያወጣናል የሚል ስሌት አላቸው፡፡
 በሌላ አገላለጽ ለመኖር ብቻ የሚያሰሉ ተከታዮች የአደጋን ኃላፊነት
ከመውሰድ ይልቅ የጥንቃቄ ካርድ መጫወት የሚፈልጉ ናቸው።
 ትልቁ ችግራቸው ደግሞ ስህተት የመሥራት ፍርሃት ነው፡፡
 ይህ ጤናማ ያልሆነ ፍርሃት ግን ሄዶ ሄዶ ጠላትነትን እንጂ ወዳጅነትን አያተርፍም።
ሠ/ ውጤታማ/ኮከብ ተከታይ (Effective/Star Follower)
 ይህ ዓይነት ተከታይ ንቁ፣ በራሱ የሚተማመን፣ ጥገኛ ያልሆነና በጥልቅ ማሰብ የሚችል
ሲሆን ውጤታማ ተከታይ በመሆኑ የመሪውን ኃላፊነትና ሥልጣን ያከብራል።
 ውጤታማ ተከታዮች የዕድሜ ልክ ተማሪዎች ናቸው።
 እራስን መምራትን ይለማመዳሉ፣ ኃላፊነት ይወስዳሉ፣ ቁርጠኞች ናቸው፡፡
 በመሆኑም አፈጻጸማቸውን ያለማቋረጥ ለማሻሻል አስተያየት ይፈልጋሉ።
 በተጨማሪም "ተለዋዋጭ ተከታዮች" በመባል ይታወቃሉ፡፡
 ለመሪዎችና ለቲሙ በጣም ጠቃሚ ናቸው፡፡
 በቋሚና ከፍተኛ ጥራት ባለው አስተዋጽኦ ምክንያት የዚህ ዓይነት ተከታዮች
በየደረጃው ለሚገኙት መሪዎች ብዙ ጊዜ ታማኝ አማካሪ ናቸው።

ክፍል ሁለት የቀጠለ……………….. የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሠራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት በሚል ከተዘጋጀ ሰነድ  ክፍል የቀጠለ ለ/ ሁኔታዊ የመሪነት ዘይቤ (Situational Leadership...
25/03/2023

ክፍል ሁለት የቀጠለ………………..
የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሠራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት በሚል ከተዘጋጀ ሰነድ ክፍል የቀጠለ
ለ/ ሁኔታዊ የመሪነት ዘይቤ (Situational Leadership style)
 በዚህ የመሪነት ዘይቤ ዕይታ አንደኛው የመሪነት ዘይቤ
ብቻ በሁሉም ጉዳዮች ውጤት አያመጣም የሚል ነው፡፡
 በመሆኑም ለእያንዳንዱ ጉዳይ የመሪነት ዘይቤው
ሊለዋወጥ ይገባል የሚል ሀሳብ አለ፡፡
 የአንድ መሪ ዘይቤን ጥሩነትና ጠቃሚነት የሚወስነው
የመሪነት ዘይቤው ለተጨባጭ ጉዳይ ተስማሚ ሊሆን
ይገባል የሚል እምነት ነው፡፡
 በመሪነት ዘይቤ ላይ ተጽዕኖ በሚያደርጉ ጉዳዮች (በሥራ መሪው፣ በሠራተኛውና በሁኔታው) ላይ በማተኮር እንደ ተጨባጩ ሁኔታ ተስማሚ የሆኑ የመሪነት ዘይቤዎችን እየመረጡ መጠቀም ያስፈልጋል የሚል ነው፡፡
 መሪው ይህን የመሪነት ሥልት መጠቀም የሚችል ቢሆንም በተገቢው ጊዜና ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ በቂ ዕውቀትና ክህሎት ከሌለው የሚሰጠው አመራር ሁኔታውን ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ በመውሰድ ለውድቀት ሊዳርግ ይችላል፡፡
ሐ/ ዘመናዊ የመሪነት ዘይቤዎች
1. የልውውጥ መሪነት ዘይቤ (Transactional Leadership Style)
 ይህ ዓይነት የመሪነት ዘይቤ መሠረት የሚያደርገው፡-
o ተግባራትን አከናውኖ ውጤታማ ከመሆን አንጻር
መሪው ተከታዮቹ ባበረከቱት አስተዋጽኦ ልክ
በሚያደርገው ቁሳዊ ልውውጥና ማበረታቻ ላይ ነው፡፡
o ለዚህም ነው የልውውጥ መሪነት ዘይቤ
(The concept of Give and Take) በሚል የሚገለጸው፡፡
 ይህ የመሪነት ዘይቤ ሥራ ላይ ባለው አሰራር፣ አደረጃጀት፣
የሰው ኃይልና ቢሮክራሲ መነሻነት የሚሰራ ነው፡፡
2. የሽግግር/የለውጥ አራማጅ መሪነት ዘይቤ (Transformational Leadership Style)
 ለውጥ አራማጅ መሪነት ዘይቤ ሌሎች የመሪነት ዘይቤዎች
ያሉባቸውን ውስንነቶች የሚሞላ ነው የሚል እሳቤ ነው፡፡
 ይህም መሪው፡-
o ተቋማዊ ራዕይ በመቅረጽና በማጋራትና በታሰበው ጊዜ
ለመድረስ የተከታዮቹን አስተሳሰብና አሰራር በመለወጥ፣
o ለተግባራዊነቱ ሁሉንም አሰልፎ በመስራትና በማሰራት፣
o ለተቋማዊ ባህል ማደግና መለወጥ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጥ አዲሱ የመሪነት ዕይታ ነው፡፡
 ለውጥ አራማጅ መሪ የተቋሙን ራዕይ የሚያስተካክልና ተገቢ የሆነ አቅጣጫ በማስያዝ ተቋማዊ ለውጥ ለማምጣት ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ብቃት ያለው ነው፡፡
 ይህ የመሪነት ዘይቤ ለውጥ ላይ ተመስርቶና ለለውጡ ምቹ የሆነ አዲስ አሰራር፣ አደረጃጀትና የተለወጠ የሰው ኃይል መነሻነት የሚሰራ ነው፡፡

የአገልጋይ መሪ ሚና ካለፈዉ የቀጠለሀ/ ቀደምት የመሪነት ዘይቤዎች 1. አንባገነናዊ የመሪነት ዘይቤ (Autocratic/Dictatorial Leadership Style) በዚህ የመሪነት ዘይቤ ...
22/03/2023

የአገልጋይ መሪ ሚና ካለፈዉ የቀጠለ
ሀ/ ቀደምት የመሪነት ዘይቤዎች
1. አንባገነናዊ የመሪነት ዘይቤ (Autocratic/Dictatorial Leadership Style)
 በዚህ የመሪነት ዘይቤ የሚንጸባረቁት፡-
o መሪው በውሳኔ አሰጣጥ ላይ ሙሉ ሥልጣን ያለውና
ሠራተኞችን የማያሳትፍ፣
o ሠራተኞችን ካለማመኑ የተነሣ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ፣
o ሥራዎች በአለቃና ትዕዛዝ ብቻ ይከናወናሉ ብሎ የሚያስብ፣
o እራሱን እንደ ሥልጣን ምንጭ የሚቆጥር፣
o ሠራተኛን ሳያማክር ደንብና መመሪያ የሚቀርጽ፣
o ከሠራተኛ ጋር ያለው ግንኙነት በጣም የላላ ነው፡፡
 በዚህ የመሪነት ዘይቤ ትኩረት የሚሰጠው ለሥራና ለምርት ብቻ
ሲሆን ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡
2. አሣታፊ የመሪነት ዘይቤ (Participatory Leadership Style)
 በዚህ ዘዴ መሪው፡-
o በቲም ስለሚያምን በጋራ አቅዶ እንዲተገበር ያደርጋል፣
o ምን ማድረግና እንዴት ማድረግ እንዳለበት ለመወሰን
በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ሰዎችን ያሣትፋል፣
o ሠራተኞች በብዙ የመሥሪያ ቤቱ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ
እንዲሰጡ ያደርጋል፣
o እራሱን ለይቶ ከፍ አድርጎ አያይም፣
o በሥራ ቦታም ሆነ ከሥራ ውጭ የቅርብ ግንኙነት አለው፣
 በዚህ የመሪነት ዘይቤ ለምርት ብቻ ሳይሆን ለሠራተኞች ደህንነትም
ትኩረት የሚሰጥበት በመሆኑ ከጉዳቱ ይልቅ ጥቅሙ ያመዝናል፡፡
3. ልጓም አልባ/ልቅ የመሪነት ዘይቤ (Laissez-faire/ Free Rein Leadership Style)
 በዚህ የመሪነት ዘይቤ መሪዎች ምንም ቁጥጥር የማያደርጉበት ወይም መጠነኛ የሥራ ቁጥጥር የሚያደርጉበት ነው፡፡
 እያንዳንዱ ሠራተኛ ኃላፊነቱን በራሱ ይወጣል የሚል እምነት አላቸው፣
 መሪው ሠራተኞችን አሰባስቦ ወደ አንድ አቅጣጫ የሚመራ አይደለም፣
 በሌላ አገላለጽ ሠራተኞች የራሳቸውን ውሳኔ እንዲወስኑ ያስችላቸዋል፣
 ይህም ሆኖ ለተደረጉት ውሳኔዎች ሁሉ መሪ አሁንም ተጠያቂ ነው፣
 ይህ ዘይቤ ለሰዎች የበለጠ ነፃነት እና ኃላፊነትን ይፈቅዳል፣
 የቲም አባላት የተቋሙን ፖሊሲ እስካልጣሉ ድረስ ያመኑበትን እንዲሰሩ ሙሉ ነፃነት ይሰጣል፣
 ይህን የመሪነት ዘይቤ ተግባራዊ ለማድረግ ግን በመሪው ዙሪያ ያሉት ሁሉ ብቁና ኃላፊነት የሚወስዱ መሆን አለባቸው። በአጠቃላይ ይህ የመሪነት ዘይቤ ጥቅምም፣ ጉዳትም አለው፡፡ ይቀጥላል በቀጣይ ክፍል………

.የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሠራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት ምንድነዉ  በሚል ተዘጋጀ የሥልጠና ሰነድ ላይ የተወሰደክፍል-1- የሥራ አመራር ሚናዎች በ3ት ዋና ዋና ሚናዎች ያላቸዉ ሲሆን እነሱም  ...
22/03/2023

.የአገልጋይ መሪ ሚና እና የሠራተኛው የሥራ ቁርጠኝነት ምንድነዉ በሚል ተዘጋጀ የሥልጠና ሰነድ ላይ የተወሰደ
ክፍል-1-
የሥራ አመራር ሚናዎች በ3ት ዋና ዋና ሚናዎች ያላቸዉ ሲሆን እነሱም
ሀ. የተግባቦት ሚና፡- የሥራ ኃላፊዎች ለማስተባበር፣ ከሠራተኞች ጋር ለመግባባት እና ለማቅረብ የሚያገለግል ተቋማዊ አቅጣጫ አመላካች ነው፡፡
ለ. መረጃ የመስጠትና የመቀበል ሚና፡- መረጃን በአግባቡ ተንትኖ በማደራጀት ሥራ ላይ የማዋልና ለሌለቹ ህጋዊ አካላት ከማስተላለፍ ጋር የተያያዘ ሲሆን ዝርዝር ሚናዎቹም የክትትል ሚና /monitoring role/፣ መረጃን የማሰራጨት ሚና /Disseminating role/ እና የቃል አቀባይነት ሚና /Spokesperson role/ ናቸው፡፡
ሐ. የውሳኔ ሰጭነት ሚና፡- የሥራ ኃላፊዎች ስትራቴጂያዊ ጉዳዮችን ለማቀድ፣
ሀብትን ለመጠቀምና ዓላማን ለማሳካት መረጃን ጥቅም ላይ የማዋል ሚና ነው፡፡ በዚህ ሥር አራት ዝርዝር ሚናዎች ማለትም የሥራ ፈጣሪነት ሚና /Entrepreneurship role/፣ የሁከት/የቀውስ አያያዝ ሚና /Disturbance handling role/፣ ሀብት የመመደብ ሚና /Resource allocating role/ እና የመደራደር ሚና /Negotiating role/ ናቸው፡፡
መሪ ማነው?
መሪዎች የሥራ አቅጣጫን የሚያሳዩና ቀድመው የሚገኙ፣ ያልተዳሰሰውን ድንበርና ያልተደረሰበትን ባህር ለመቃኘት የሚጥሩ፣ ችግሮችን የመፍታት ጥበብ ያላቸው፣ ያለውን አሰራር በየወቅቱ እየፈተሹ ጊዜውን በሚዋጅ አዳዲስ አደረጃጀትና አሰራር የመተካት ችሎታ ያላቸው፣ በተለይ ሠራተኞችን/ተከታዮችን በፈቃደኝነትና ከልብ ተነሳስተው ከፍተኛ የሥራ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚያደርጉ ቁርጠኛና ግንባር ቀደም የሆኑ ናቸው፡፡
የመሪነት አስፈላጊነት
በየትኛውም መስክ ከታለመለት ግብ ለመድረስ ብቁ የመሪነት ሥልት መከተል እንደሚገባ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም፡፡ በዚህ መሠረት አስፈላጊነቱ፡-
1. በምንሰራበት አካባቢ ወይም በማህበራዊ ሕይወታችን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ
የመሪነትን ሚና ለመጫዎት እራሳችንን ማዘጋጀት ስለሚገባ፣
2. የመሪነት ጉዳይ የሁሉንም ተቋም ሆነ አካባቢ የሚዳስስ ወሳኝ የኑሮና የሕይወት
ጉዳይ በመሆኑ፣
3. ትላልቅ ግኝቶች፣ የፈጠራ ሥራዎችና ሌሎች የዕለት ተዕለት ጉዳዮች በቲምና
በመልካም መሪነት አማካኝነት የሚገኙ ስለሚሆኑ፣
4. በተቀናጀ አሰራር ሰዎችን ወይም ቲሞችን ወደ አንድ አቅጣጫ በመምራት ውጤት
ማምጣት ስለሚያስችል፣
5. ጠንካራ መሪና ተከታይ ካለ በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚፈጠሩ ችግሮች
ተገቢ ምላሽ እንዲያገኙ ስለሚያስችል፣
6. በተቋማት የተመላከቱ የሥራ ዕቅዶችን ወደ ስኬት በማድረስ የዜጋውን የፍላጎት
ደረጃ ለማሟላት የሚያስችል ብቁ መሪ ስለሚያስፈልግ፣
7. መልካም መሪ በቤተሰብ የፍቅርና የስኬት ተምሳሌት እንዲሁም መበተን
የማያጋጥመው መሆኑንና በተቋማትም ኃላፊነት ሊሸከም የሚችል መሆኑን
ስለሚያስገነዝብ፣
 የመሪነትን ዘይቤዎችን ከጊዜ አንጻር በሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ማየት የሚቻል ሲሆን እነዚህም፡-
ሀ/ ቀደምት/የተለመዱ የመሪነት ዘይቤዎች
1. አንባገነናዊ የመሪነት ዘይቤ (Autocratic/Dictatorial Leadership Style)
2. አሣታፊ የመሪነት ዘይቤ (Participatory Leadership Style)
3. ልጓም አልባ/ልቅ የመሪነት ዘይቤ (Laissez-faire/ Free Rein Leadership Style)
ለ/ ሁኔታዊ የመሪነት ዘይቤ (Situational Leadership style)
ሐ/ ዘመናዊ የመሪነት ዘይቤዎች
1. የልውውጥ መሪነት ዘይቤ (Transactional Leadership Style)
2. የሽግግር/የለውጥ አራማጅ መሪነት ዘይቤ (Transformational Leadership Style)
ክፍል -2- ይቀጥላል

የዕለቱ መልዕክት====>
21/03/2023

የዕለቱ መልዕክት
====
>

ለቴ/ሙ/ት/ሥ/ ፈላጊዎች በሙሉ እንኳን ለ2015ዓም የመደበኛ ሰልጣኞች ቅበላ በሠላም አደረሳቹ እያልን፤የየም ልዩ ወረዳ ቴክንክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ጽ/ቤት የ2014ዓም የ12ኛ ክፍል መል...
20/03/2023

ለቴ/ሙ/ት/ሥ/ ፈላጊዎች በሙሉ እንኳን ለ2015ዓም የመደበኛ ሰልጣኞች ቅበላ በሠላም አደረሳቹ እያልን፤
የየም ልዩ ወረዳ ቴክንክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ጽ/ቤት የ2014ዓም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለወሰዳቹ እና በ2015ዓም በቴ/ሙ/ት/ሥ ለመማር ለምትፈልጉ በሙሉ ከዚህ በታች በተመላከተው መቁረጫ ነጥብ የምታሟሉ ተማሪዎች በየኮሌጆች በመቅረብ በአካል እንድትመዘገቡ እንገልፃለን፡፡
የቴክንክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ለሀገራዊ ሁለንተናዊ ብልፅግና ቁልፍ ነው✍️
የየም ልዩ ወረዳ ቴክንክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ጽ/ቤት፤

Address

Saja

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Snnprs Yem Public Service and H R O posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share