Central Ethiopia Region Culture and tourism Bureau

Central Ethiopia Region Culture and tourism Bureau ይህ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ትክክለኛ የፌስቡክ ገፅ ነው !! ገፃችንን ይወዳጁ ያጋሩ !!

በትምህርት ዘርፉ ውጤት ለማስመዝገብ  የላቀ ድጋፍ እና ትብብር ይፈልጋል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)(ሳጃ፣ነሐሴ 29/2018)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 3ኛው የትምህርት ሴክ...
04/09/2026

በትምህርት ዘርፉ ውጤት ለማስመዝገብ የላቀ ድጋፍ እና ትብብር ይፈልጋል:- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)
(ሳጃ፣ነሐሴ 29/2018)

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል 3ኛው የትምህርት ሴክተር ጉባኤ በሆሳዕና ከተማ እየተካሄደ ነው

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በጉባኤው እንደገለጹት የትምህርት ስራ የላቀ ትብብር ይፈልጋል ብለዋል።

የትምህርት ስራ ተዋናዩ እና ባለድርሻ አካላት በርካታ ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በዘርፉ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ ልዩ ትኩረት ያሻል በማለት ገልጸዋል።

በማደግ ላይ ያሉ እና ያደጉ ሀገሮች ሀገራቸውን የለወጡት በትምህርት ነው ብለዋል።

በትምህርት ላይ ያላቸው አቋም ጠንካራ ስለነበረ ትምህርትን ተጠቅመው ሀገራቸውን ገንብተዋል ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል።

ፊላንድ፣ኖርዌይ፣ሲውዲን እና ሌሎች ሀገራት በትምህርት ላይ መስራት የጀመሩት ከዛሬ 50 ዓመታት ገደማ እንደነበር ርዕሰ መስተዳድሩ አስታውሰዋል።

እንደ ቻይና የመሳሰሉት ሀገሮች የትምህርት ስርዓታቸውን ገምግመው መስራት የጀመሩት የዛሬ 40 ዓመታት አካባቢ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

እነዚህ ሀገራት በትምህርት ላይ በሰሩት መጠን ሀገራቸውን መለወጥ መቻላቸውን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

ትምህርት የህዝብንም የመንግስትንም ትኩረት እንደሚያሻ ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አብራርተዋል።

የአንድን ሀገር ስርዓት ለማቃናትም ሆነ ለማፍረስ ትምህርት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።

ትምህርት ከተጠቀምንበት ሀገራትን ከአንድ ደረጃ ወደ ሌላ ደረጃ በቀላሉ እንዲሸጋገሩ ያስችላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ትምህርትታሪክ የ110 ዓመታት እድሜ እንዳለው ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ ለሚከሰቱ ችግሮች መንስኤ የትምህርት ውጤት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ አለመከባበር እና የግብረ ገብነት ችግር ከዚህ ይመነጫል ሲሉም ጠቅሰዋል።

በተስፋዬ መኮንን

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "በብዝሐነት የደመቀች፣ በምክክር የጸናች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሐሳብ ይከበራልሳጃ፤ ነሐሴ 26/2018  21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ...
01/09/2026

የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "በብዝሐነት የደመቀች፣ በምክክር የጸናች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሐሳብ ይከበራል

ሳጃ፤ ነሐሴ 26/2018

21ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን "በብዝሐነት የደመቀች፣ በምክክር የጸናች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሐሳብ በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር ተወሰነ።

ውሳኔው የተላለፈው የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር፣ የክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች አፈ-ጉባዔዎች፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የበዓሉን ረቂቅ ዕቅድ ለማጽደቅ በተካሄደ የምክክር መድረክ ላይ ነው።

በመድረኩ እንደተመላከተው፤ በዓሉ የተመረጠውን መሪ ሐሳብ መሠረት በማድረግ የሕዝቦችን አንድነት በሚያጠናክር፣ ብዝሐነትን በሚያጎላና የምክክር ባህልን በሚያዳብር መልኩ ይከበራል።

በዓሉን በታቀደው መሠረት በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የሚያስችሉ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ዝግጅቶች በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙም ተገልጿል።

ኢዜአ

ለክልሎችና ከተማ አስተዳደር  የቱሪዝም ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ቱሪዝም ፖሊሲ አተገባበር ላይ  የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም የኢትዮጵያን የቱሪዝም ፖሊ...
31/08/2026

ለክልሎችና ከተማ አስተዳደር የቱሪዝም ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ቱሪዝም ፖሊሲ አተገባበር ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ።

ነሃሴ 25/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያን የቱሪዝም ፖሊሲ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማጠናከር፣ በፌዴራልና በክልል ተቋማት መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ለማጎልበት እና በፖሊሲው ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ የንቅናቄና የአቅም ግንባታ ስልጠና ለክልልና ከተማ አስተዳደር የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሰጥቷል።

የቱሪዝም ሚኒስቴር ባዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ስልጠናውን የሰጡት የስትራቴጂክ ዩኒቲ ክፍል አስተባባሪ አቶ ቴዎድሮስ ደርበው እንደገለጹት፣ የቱሪዝም ፖሊሲው የቱሪዝም ተወዳዳሪ እና ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን ለማረጋገጥ ፓሊሲው ዋና መሰረት መሆኑን ጠቅሰዋል።

አክለውም በፖሊሲው ሰነድ ላይ በዝርዝር የተቀመጡትን የነባርና አዳዲስ የቱሪዝም መስህቦች ልማት፣ የመሠረተ ልማት መስፋፋት፣ የገበያና ማስተዋወቅ ስራዎችን ማጠናከር፣ የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻል እና የዘርፉን ተቋማዊ አቅም ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች በፖሊሲው በተቀመጡት አዳዲስ ስልቶች ላይ ሰፊ ገለጻና ውይይት ተካሂዷል።

በስልጠናው ወቅት የቱሪዝም ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የፖሊሲው ዋነኛ የትኩረት መስክ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ዘርፉን ከጥንታዊ አሰራር ለማላቀቅ የሚያስችል የዲጂታል ቱሪዝም ሮድማፕና ስትራቴጂ በተግባር እንደሚውል ተብራርቷል።

ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችን (Smart Tourism Destinations) በማልማት የጎብኚዎችን ተመክሮ ለማሻሻልና የመዳረሻዎችን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራም ተጠቁሟል።

በመጨረሻም፣ ፖሊሲው በመንግሥት፣ በግሉ ዘርፍ፣ በማህበረሰብ እና በልማት አጋሮች መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና ሀገሪቱን በአፍሪካና በዓለም አቀፍ የቱሪዝም ገበያ ተመራጭ መዳረሻ ለማድረግ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው በስልጠናው ተገልጿል።

ቱሪዝም ሚኒስተር

በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከክልል ቱሪዝም ቢሮዎች እና  ከከተማ አስተዳደሮች  ጋር የዕቅድ ትስስርና የተመክሮ ልውውጥ ወይይት ተደረገ።ነሀሴ 24/22018 ዓ.ም ዉይይቱ የክልሎችና የከ...
30/08/2026

በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከክልል ቱሪዝም ቢሮዎች እና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር የዕቅድ ትስስርና የተመክሮ ልውውጥ ወይይት ተደረገ።

ነሀሴ 24/22018 ዓ.ም

ዉይይቱ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ዕቅዶች ከቱሪዝም ሚኒስቴር እና ከዘርፉ ስትራቴጂያዊ ግቦች ጋር ተናብበው እንዲፈጸሙ እንዲሁም የተሻለ ቅንጅትና ትብብር እንዲኖር ያስችላል ተብሏል።

የክልልና የከተማ አስተዳደሮች የቱሪዝም ቢሮ የ2019 የቱሪዝም ዘርፍ እቅዳቸውን አቅርበው ሀሳብና አስተያየት ተሰጥቶባቸዋል።

በውይይቱ የ2019 የሪፖርት አቀራረብ ፎርማት፣ የዕቅድ አፈጻጸምን ለመለካት የሚያስችሉ የክትትልና ድጋፍ ሥርዓቶች፣ የመለኪያ መስፈርቶች እና የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ደረጃዎች ላይ ሰፊ ምክክር ተካሂዷል።

በተለይም በአገልግሎት ጥራት ማሻሻያ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የቱሪስት አገልግሎቶች ቁጥጥር፣ የእውቅናና የደረጃ ማረጋገጫ ሥርዓት፣ የአጠቃላይ የጥራት አስተዳደር ፣ የሆስፒታሊቲ ባለሙያዎች ምዘና እንዲሁም የመዳረሻዎች መረጃ ሥርዓት ድጋፍ ጉዳዮች በውይይቱ ተዳሷል።

እንዲሁም በሚኒስቴሩ እና በክልሎች ደረጃ የፖሊሲ ትግበራ፣ የስትራቴጂያዊ ግቦች አፈጻጸም፣ የትልልቅ ፕሮጀክቶች ክትትል እና የፋይናንስ አጠቃቀም ቁጥጥር ሂደቶች ቀርበው ልምድ ልውውጥ ተደርጓል።

በመጨረሻም በቱሪዝም ሚኒስቴር የእቅድና በጀት ክትትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብስራት ታደሰና በሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ እና ማብራሪያ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተዋሳኝ አካባቢዎች የጋራ ጥምረት የፀጥታ ኮማንድ ፖስት  የኮማንድ ፖስቱን የእሰከ አሁን አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል...
30/08/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተዋሳኝ አካባቢዎች የጋራ ጥምረት የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የኮማንድ ፖስቱን የእሰከ አሁን አፈፃፀም ሪፖርት ገምግሟል ፤በቀጣይ ጊዜ ጠቋሚ ዕቅድ ላይም ተወያይቷል

ነሐሴ 24 2018 ፦ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ ( ዶ/ር) በተገኙበት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ተዋሳኝ አካባቢዎች የጋራ ጥምረት የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የተዋሳኝ አካባቢዎች ጥመረት ኮማንድ ፖስትን የእሰከ አሁን አፈፃፀም ሪፖርት ዛሬ በሆሳዕና ከተማ ገምግሟል ፤በቀጣይ ጊዜያት ጠቋሚ ዕቅድ ላይም ተወያይቷል።

በመድረኩ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ሀላፊ አቶ ተመስገን ካሳ፣ የጥመረት ኮማንድ ፖስቱን የእሰከ አሁን አፈፃፀም ሪፖርት እና የቀጣይ ጊዜ ጠቋሚ ዕቅድ አቅርበዋል፤ ዝርዝር ውይይትም ተደርጎበታል።

ዘላቂ ሠላምን ማስፈን ፣ የህዝቦችን አንድነት እና ትስስር ማጎልበት በሚቻልባቸዉ ሁኔታዎች ላይ የተጀመረዉን የቅንጅት ሥራ አጠናከሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸዉ አግባቦች ላይ ዉይይት ከመካሔዱም በላይ በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችም ተለይተዉ መቀመጣቸው ተገልጿል ።

በዉይይት መድረኩ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሰት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሰት ፖሊስ ኮሚሽን፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና በሁለቱ ክልሎች ተዋሳኝ ዞኖች እና ወረዳዎች አመራሮች ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ  ወደ ላቀ ደረጃ ለማሽጋገር በተቀናጀ አሰራር፣ በጋራ እቅድ እና በተናበበ ሪፖርተር  መተግበር እንደሚገባ ተገለፀ።ቱሪዝም ሚኒስቴርነሐሴ 2018 ዓ.ም.በቱሪዝም ዘ...
29/08/2026

የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሽጋገር በተቀናጀ አሰራር፣ በጋራ እቅድ እና በተናበበ ሪፖርተር መተግበር እንደሚገባ ተገለፀ።

ቱሪዝም ሚኒስቴር
ነሐሴ 2018 ዓ.ም.

በቱሪዝም ዘርፍ የመካከለኛ ዘመን የልማት ኢንቨስትመንት ዕቅድና 2019-2021 በተዋረድ ዕቅድ ትስስር ላይ የፌደራል፣ የክልልና የቱሪዝም ተቋማት ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ያሳተፈ ወይይት በአዳማ እየተካሄደ ነው።

የቱሪዝም ዘርፉ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት ያለውን ጉልህ ድረሻ አስተዋጽኦ ብሎም ለሥራ እድል ፈጠራና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ያለውን ሚና ለማጠናከር የተቀናጀ አሰራር ተግባራዊ ማድግር አስፈላጊነትን ተገልጿል።

በተለይም በፌደራል፣ በክልልና በከተሞች የሚከናወኑ የቱሪዝም ሥራዎች የጋራ እቅድ፣ የጋራ ትግበራና የጋራ ክትትል ስርዓት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ በአንክሮ አመላክተዋል ።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ላይ የተገኙት የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ.ር ) እንደገለጹት ከ2019 እስከ 2021 ዓ.ም. በሚተገበረው የመካከለኛ ዘመን የልማት እቅድ መነሻነት የቱሪዝም ዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የፖሊሲ፣ የስትራቴጂ፣ የሀብት ልየታ እና የተቋማዊ አቅም ግንባታ ሥራዎች በቅንጅት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው ፣ የእቅዱ ስኬት በሁሉም አስተዳደራዊ እርከኖች ባለው የትብብር ደረጃ እንደሚወሰንም ገልጸዋል።

አክለውም የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች በተቀናጀ ሁኔታ ለዓለም አቀፍ ገበያ ማስተዋወቅ፣ አዳዲስ የቱሪስት ምንጭ ገበያዎችን መለየት፣ የጋራ የማስተዋወቂያ መድረኮችን ማዘጋጀትና የዲጂታል ማስተዋወቂያ አሰራሮችን ማጠናከር በቀጣይ ጊዜ ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተገልጿል።

በተጨማሪም የቱሪዝም አገልግሎት ጥራትን ማሻሻል፣ የዘርፉን ኢንቨስትመንት ማበረታታት፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እና የጎብኚዎችን እርካታ ማሳደግ የቅድሚያ ትኩረት የሚያገኙ ጉዳዮች መሆናቸው ተጠቅሷል።

መድረኩ በየክልሉ ያሉ ልዩ የቱሪዝም አቅሞችን በመጠቀም የባህል፣ የኮንፈረንስና የንግድ ጉባኤ (MICE)፣ የጤና፣ የምግብና የስፖርት ቱሪዝም ምርቶችን በጥራት ለማበልጸግ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን መለየትና እነዚህ የቱሪዝም ምርቶች የሀገሪቱን የቱሪዝም ገቢ ከማሳደግ ባሻገር የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ለኢኮኖሚው ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቶት እንዲኖራቸው ታሳቢ አድረጎ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዋል።

የመካከለኛ ዘመን የልማት ኢንቨስትመንት ዕቅድና በ2019-2021 ዕቅድ ትስስር የተመለከተው ሰነድ በአቶ ብስራት ታደስ የእቅድና በጀት ክትትል ስራ አስፈጻሚ በኩል ቀርቦ ውይይት ተደረጎበታል።

በመጨረሻም በተነሱ ጥያቄዎች ላይ በአቶ ግርማ መላኩ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ እና በሚመለከታቸው የሥራ ክፍል ኃላፊዎች በኩል ምላሽና ማብራሪያ የተሰጡ ሱሆን የመድረኩ ተሳታፊዎች የቱሪዝም ዘርፉን ውጤታማነት ለማሳደግ በጋራ እቅድ ዝግጅት፣ በተቀናጀ ትግበራ፣ በመደበኛ ክትትልና ግምገማ እንዲሁም በተቋማት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለኪነጥበብ ባለሙያዎች የስራ ዲሲፕሊንና የመብት-ግዴታ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ።​ነሐሴ 23/2018 ዓ/ም ወልቂጤማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ...
29/08/2026

በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለኪነጥበብ ባለሙያዎች የስራ ዲሲፕሊንና የመብት-ግዴታ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ።

​ነሐሴ 23/2018 ዓ/ም ወልቂጤ

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለክልሉ የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተዘጋጀው ሦስተኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና በመዉሰድ ላይ ለምገኙ ሰልጣኞች ሰራተኞች መብትና ግዴታ እንዲሁም በስራ ዲሲፕሊን ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እየተሰጠ ይገኛል።

​ስልጠናው በዋናነት በመንግስት ሰራተኞች መብትና ግዴታ እንዲሁም በስራ ዲሲፕሊን ዙሪያ የላቀ ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ሰነዱን በቢሮው የሰው ሀብት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ሀምዛ አቅራቢነት እየቀረበ ይገኛል።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የተዘጋጀው 3ኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ተጀመረ።ነሐሴ 23/2018 ዓ/ም /ወልቂጤማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከ...
29/08/2026

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች የተዘጋጀው 3ኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና መድረክ ተጀመረ።

ነሐሴ 23/2018 ዓ/ም /ወልቂጤ
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለክልሉ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ያዘጋጀውን ሦስተኛ ዙር የአቅም ግንባታ ስልጠና በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተጀምሯል።

በስልጠናው መክፈቻ መድረክ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ፤ ስልጠናው በክልሉ ሦስት አበይት ዓላማዎችን ለማሳካት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

ይኸውም የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎችን የንድፈ-ሀሳብ እውቀት ከተግባር ጋር በማጣመር የሙያ ብቃታቸውን ማሳደግ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ ማድረግ እንዲሁም ሰልጣኞች ያገኙትን እውቀት ወደየመጡበት ዞንና ወረዳ በመውሰድ ሌሎች አዳጊ ባለሙያዎችን እንዲያሰለጥኑ ማስቻል መሆኑን አብራርተዋል።

አክለውም ባለሙያዎቹ በቀጣይ በሚከበሩ ህዝባዊና መንግስታዊ በዓላት ላይ የክልሉን ባህል፣ ታሪክና እሴት በጥበብ ስራዎቻቸው ጎልቶ እንዲወጣ በማድረግ በኩል የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አሳስበዋል።

ኪነ-ጥበብ የህዝቦችን ባህል፣ ታሪክና ማንነት ከማስተላለፍ ባሻገር ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ ለቱሪዝም ልማትና ለኢኮኖሚ እድገት የሚያበረክት ዘርፍ መሆኑ በስልጠናው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ተጠቁሟል።

በመሆኑም የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ሙያዊ አቅማቸውን በማሳደግ የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ወደ ገበያ ማቅረብ እንዲችሉ የሚያስችል አቅጣጫም ተሰጥቷል።

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ እና የቋንቋ ፣ባህልና ሀገር በቀል ዕውቀት ማዕከል ዳይሬክተር ዶክተር ፀጋማርያም ዱላ በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው ከተሰጠው የማህበረሰብ አገልግሎት እና የምርምር ተልዕኮ ጎን ለጎን የክልሉን የኪነ-ጥበብ፣ የባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ለማሳደግ ለሚደረጉ ጥረቶች ተገቢውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረው መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ባለሙያው በሳይንሳዊ እውቀት ታንጾ የተሻለ የጥበብ ስራ እንዲያበረክት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸውም ጠቁመዋል።

የጉራጌ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋ በሰጡት አስተያየት፤ በዞኑና በክልሉ የሚገኙ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በህዝባዊ መድረኮች ላይ የሚያቀርቧቸውን ስራዎች በጥራትና በብቃት እንዲያቀርቡ ይህ ስልጠና ወሳኝ መሆኑን ገልጸው። ሰልጣኞች የገበዩትን እውቀት ወደ ተግባር በመለወጥ የህዝብን ባህልና ታሪክ በጥበብ የማስተዋወቅ ድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በመክፈቻ መርሀግብሩ ላይ የቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊና ባህል ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደግነህ ቦጋለ እና የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ዶክተር ፀጋማርያም ዱላ ጋር በመሆን ስለስልጠናዉ ዉይይት አድርገዋል።

በመቀጠልም ለስልጠናው መጀመር አስተዋጽኦ ላደረጉት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች እንዲሁም ለአሰልጣኞች ምስጋና የቀረበ ሲሆን፤ ሰልጣኞችም የስልጠናውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም የክልሉን የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ወደ ተሻለ ደረጃ እንደሚያሸጋግሩት ተገልጾ ስልጠናው በይፋ ተከፍቷል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ ዛሬ በካሄደዉ  ስብሰባ በተለያዩ አጃንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፣ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ በካሄደዉ መደበኛ ስብሰባ...
28/08/2026

መስተዳድር ምክር ቤቱ ዛሬ በካሄደዉ ስብሰባ በተለያዩ አጃንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፣

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት፣ መስተዳድር ምክር ቤት ዛሬ በካሄደዉ መደበኛ ስብሰባ፦ በቀረቡለት የኢንቨስትመንት ልማት ፕሮጀክቶች ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፤ በገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም ደንብ ላይም ተወያይቶ ደንቡን አፅድቋል።

መስተዳድሩ ምክር ቤቱ በቀረቡለት አስራ ሦስት የኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጀክቶች ጥያቄዎች ላይ በዝርዝር በመወያየት እና በፕሮጀክቶቹ አስፈላጊነት ላይ መግባባት በመፍጠር ፕሮጀክቶቹ ወደ ልማት እንቅስቃሴ እንዲሸጋገሩ ወስኗል።

ከቀረቡት አስራ ሶስት የኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጀክቶች ጥያቄዎች መካከል ዘጠኙ በኢንዱስትሪ ፣ ሁለቱ በግብርና የተቀሩት ሁለቱ ደግሞ በአገልግሎት ዘርፎች ለመሠማራት የተዘጋጁ መሆናቸዉ ተጠቁሟል።

ከኢንቬስትመንት ልማት ፕሮጀክቶቹ መካከል ሶስቱ የዉጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንቶች መሆናቸዉም ተጠቅሷል ።

መስተዳድር ምክር ቤቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 32/2016 ማስፈፀሚያ ደንብ ላይም ተወያይቷል፤ ደንቡ ቀደም ሲል የወጣዉን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 32/2016 ለማስፈጸም አስፈላጊ መሆኑ ተብራርቷል።

መስተዳድር ምክር ቤቱ በደንቡ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ አፅድቋል።

27/08/2026

Address

Saja

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Central Ethiopia Region Culture and tourism Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Central Ethiopia Region Culture and tourism Bureau:

Shortcuts

Share