የጐፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ Gofa Zone Police Dep't

የጐፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ Gofa Zone Police Dep't Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የጐፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ Gofa Zone Police Dep't, Government Organization, Sawla Felege Neway.
(1)

👉"ነሀሴ 17/2013ዓ.ም "  #በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ከ7ቱ ወረዳና ከ2ቱ ከተማ አስ/ር ፖሊስ አመራርና አባላት እንድሁም ከሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት "ለአገረ እዘምታለሁ!የት...
23/08/2021

👉"ነሀሴ 17/2013ዓ.ም "


#በጎፋ ዞን ሣውላ ከተማ ከ7ቱ ወረዳና ከ2ቱ ከተማ አስ/ር ፖሊስ አመራርና አባላት እንድሁም ከሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት "ለአገረ እዘምታለሁ!የትም፣መቼም፣በምንም"በሚል መሪ ቃል ጠንካራ ሠላማዊ ሠልፍ መካሄዱ ተገለፀ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

=የጎፋ ዞን ፖሊስ መዋቅር አመራሮችና አባላት ፣የማረሚያ ፖሊስ አመራርና አባላት፣ የቀበሌ ሚሊሻዎችና እንድሁም ተቀናሽ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በጋራ በመሆን "አገሬን ለማዳን እዘምታለሁ! የትም፣መቼም፣በምንም"በምል መሪ ቃል በዞኑ ርዕሰ ከተማ ሣውላ ጠንከር ያለ ሠለማዊ ሠልፍ መካሄዱን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮ/ር ዘላለም ደምሴ ገለፁ።

=አክለውም አዛዡ "የእናት ጡት ነካሽ" የሆነው ጁንታው ለ27ዓመታት በሙሉ በአገርቱ ላይ በፖለቲካው፣በኢኮኖሚውና በማህበራዊ ዘርፎች የመዘበረውና ያቃወሰው እንድሁም በተለይም በሰብዓዊ መብቶች ረገድ የፈፀማቸው ምህረት የለሽ በደሎች ከቁጥር በላይ መሆኑ በታርክ የማይረሳ ጠባሳ እንደሆነም አንስቷል።

=አያይዘውም አዛዡ ጁንታው በዚህ ሁሉ ጥፋቱ ሳይፀፀትና ሳይማር የአገር አለንታና ደጀን በሆኑ ጀግና ሠራዊቶችና በንፁሃን ዜጎች ላይ እንድሁም በንብረታቸው ላይ ጭምር በተደጋጋሚ ጊዜ የክህደት ወንጀል እየፈፀመ ወራትን እያስቆጠረ ያለ ባንዳ ቡድን መሆኑንም አንስተዋል።

=አክለውም አዛዡ በጁንታው የአገር ክህደት ተግባር መላው የፀጥታ መዋቅሮች በመማረራቸው ምክንያት ለአገር መከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ ከወር ደመወዛቸው በ12ወር ተቆርጦ የምያልቅ የገንዘብ ድጋፍ በሞራል እያደረጉ መቀጠላቸውን ጠቅሰዋል።

=ይህ በእንዲህ እንዳለ አገራችንን ከጁንታውና ከኦነግ ሺኔ እንድሁም ከምዕራባዊያን ጣልቃ ገብነት ለማዳን ከጀግናው የአገር መከላከያ ሠራዊት ጎን እንቆማለን፣ከመንግሥት ጥሪ ስቀርብም እንዘምታለን! በሚል ወኔ መላው የዞናችን የፀጥታ ሃይል በአደባባይ ላይ በነቅስ በመውጣት ሠላማዊ ሠልፍ እንደተካሄደም በሰጡት መግለጫ አሳስበዋል።

=በዚህም የጀግንነት ሠለማዊ ሠልፍ ላይ መፈክራቸውን በመያዝ የተገኙ ሠራዊቶች "አገር ስትኖር መኖራችን ይረጋገጣል!ስለሆነም ለአገራችን በጀግንነት እንሰዋለ"አንላቀቅም በማለት ቁጭት በተሞላበት መንገድ ድምፃቸውን በአንድነት አሰምተዋል።

=ስለዚህም አሉ አዛዡ መላው የአካባቢያችን ህዝቦች እስከአሁን ላደረጋችሁት የፀጥታ ትብብር አመስግነው" በመቀጠልም ወጣቶች፣አዛውንቶች፣የአገርና የኃይማኖት ሽማግሌዎች እንድሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት መሪዎች በያላችሁበት ቦታ ከሚገኙ የፀጥታ መዋቅሮች ጋር በመቀናጀት ለአካባቢያችሁ የሠላም ዘብ በመቆም የዜግነት ግዴታቸውን እንድወጡ ሲሉም ጥር አስተላልፈዋል።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🇪🇹ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ!የትም፣መቼም፣በምንም🇪🇹

👉ም/ኢ/ር ደሳለኝ ጩቱሎ/ዘጋቢ/

"ነሀሴ /2013ዓ.ም"  #የጎፋ ዞን ፖሊስ አመራርና አባላት ለአገር መከላከያ ሠራዊት የገንዘብና የደም ልገሳ ድጋፍ ለማድረግ መስማማታቸው ተገለፀ።🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪...
20/08/2021

"ነሀሴ /2013ዓ.ም"

#የጎፋ ዞን ፖሊስ አመራርና አባላት ለአገር መከላከያ ሠራዊት የገንዘብና የደም ልገሳ ድጋፍ ለማድረግ መስማማታቸው ተገለፀ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

=የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አመራርና አባላት ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ከወር ደመወዛቸው የገንዘብ ድጋፍ እና ከአካላቸው የደም ልገሳ ለማድረግ እንድሁም ከጀግናው አገር መከላከያ ሠራዊት ጎን ለመሰለፍ መስማማታቸውን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮ/ር ዘላለም ደምሴ ገለፁ።

=አዛዡ እንዳሉት የመምሪያችን ፖሊስ አመራርና አባላት ከአከባቢው ሚልሻና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀትና በመናበብ በአከባቢው ሠላምና መረጋጋት እያበረከቱ የሚገኙት መልካም አስትዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ከልባቸው አድንቀዋል።

=አክለውም አዛዡ ለአገራችን ሉዓላዊነት በሰሜናዊ የአገራችን ክፍል ግምባራቸውን ለጥይት፣አከላቸውን ለአሞራ በመስጠት በጀግንነት እየተዋደቁ ለሚገኙት እንኳን የገንዘብና የደም ሊገሳ ከማድረግ ያለፈ ወደ ጦር ግምባር ጭምር ለመዝመት የፖሊስ አመራሩና አባሉ ዝግጁ መሆናቸውን በቆራጥነት ተናግረዋል።

=የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑ የፖሊስ አመራሩና አባላትም እጅግ በጣም ከፍ ባለ ወኔ በመሞላት ምትክ ካለው ድጋፍ በተጨማሪ መንግስት ለጀግናው መከላከያ ሠራዊት ጎን የመቆም ጥር ካስተላለፈ "ምትክ የለለውን ሕይወታቸውን ለመስጠት" በወረቀት ላይ በመፈራረም ቃል ስለመግባታቸው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

=አያይዘውም አዛዡ በየአካባቢው ሠርጎ ገቢ የሆኑ የባንዳ/ጁንታ/ ተላላኪዎች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ የአካባቢያቸውን ሠላም በማደፍረስ እኩይ ተግባራቸውን በማሳካት ድካማችንን የከንቱ ከንቱ እንዳያደርጉ አበክረው አሳስበዋል።

=ስለዚህም አሉ አዛዡ ፦ሆቴሎች ፣አልጋ ቤቶች ፣መሸታ ቤቶች ፣የኪራይ ቤቶች እና የህዝብ መሰብሰቢያ ሥፍራዎች ፣መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን እንድሁም የመሠረተ ልማት አውታሮችንና ወዘተ… የመሳሰሉ ነገሮችን ከወትሮው በተሻለ መልኩ ክትትል ቁጥጥርና ፍተሻ እንድሁም ጥበቃ ማጠናከር ይኖርብናል ሲሉ በጥብቅ አሳስበዋል።

# በመጨረሻም"
==========
=ሠላም ወዳዱ የአከባቢያችን ማህበረሰብ ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ ሠላምን ለማረጋገጥ መሞከር በአንድ እጅ እንደ ማጨብጨብ መሆኑ ታውቆ በያላችሁበት ቦታ ለግዜው ልዩነትን ወደ ጎን በመጣል ከፀጥታው ክፍል ጋር እጅ ለእጅ በመያያዝ የዘወትር ትብብራችሁን እንድትቀጥሉበት በማክበር እንጠይቃለን።

👉ለበለጠ መረጃ፦0467771367
-0467770487

#ፖሊስ ያለ ህብረተሰብ ዓሣ ያለ ውሃ መኖር አይችልም❗

👉 ሪፖርቴር፦ም/ኢ/ር ደሳለኝ ጩቱሎ

19/06/2021
ግንቦት 13/2013ዓ.ም                  #ወቅታዊ መግለጫ                  🔊🔊🔊🔊🔊🔊🔊ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ ዓለም እንደ አንድ መንደር መተሳሰር ችሏል፡፡ በዚህም የህ...
22/05/2021

ግንቦት 13/2013ዓ.ም

#ወቅታዊ መግለጫ
🔊🔊🔊🔊🔊🔊

🔊ዘመኑ የቴክኖሎጂ በመሆኑ ዓለም እንደ አንድ መንደር መተሳሰር ችሏል፡፡ በዚህም የህዝቦች ትስስርና መረጃ ልውውጥ ፍጥነት መጨመር፣ ቤተሰባዊና ማህበራዊ ግንኙነት መጠናከር፣ ዓለምዐቀፋዊና አገራዊ ሁኔታ መረጃ በቀላሉ ማግኘት እና መሠል ጥቅሞች በግልፅ የሚታዩ ናቸው፡፡

🔊ይሁን እንጂ ቴክኖሎጂው ይዞ የመጣውን መልካም እድል ለአሉታዊ ተግባር መፈጸምም የወቅቱ ፈታኝ ችግር ሆኖ ቀይቷል፡፡ እንደአከባቢያችንም የፌስቡክ “ድብቅ” አካውንቶች /fake accounts/ በአሉታዊ መልኩ ማህበረሰቡን በስፋት እየረበሸ ይገኛል፡፡

🔊ከዚህ ጋር ተያይዞ በዞናችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፀጥታ ኃይሉ (መደበኛና ልዩ ኃይላችን) ላይ ያነጣጠሩ አሉታዊ መልዕክቶች እየተነዙ መሆናቸው ሊወገዝ የሚገባ ነው፡፡ ሠራዊቱ በስራ ባህሪው ችግር በሚፈጠርበት ቦታ የሚሰማራ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

🔉 በዚህ ተልዕኮው ቀንና ሌሊት ሳይል፣ ዝናብና ፀሐይ ሳይል፣ ብርድና ሙቀት ሳይል፣ ማህበረሰቡን ለማገልገል ደፋ ቀና በሚልበት ወቅት ሚዛናዊነትን ያልጠበቀና የሰራዊቱን ክብር በማይጠብቅ መልኩ ህዝብንም በሚያሳዝን መልኩ የሚገለፁ ቃላቶች ሊወገዙ ይገባሉ፡፡

🔊ሠራዊቱ የ“ሰዎች” ስብስብ በመሆኑ በተግባር አፈፃፀም ወቅት ጉድለት ሊያጋጥም እንደሚችል ምንም ጥያቄ የለም፡፡ ነገር ግን የህዝብ አገልግሎት እያገለገለ በሚደርስበት ድንገተኛ አደጋና የአካል መጓደል ጭምር ኢ-ሰብዓዊና ኢ-ሞራላዊ በሆነ መልኩ መዝለፍ፣ እንቅስቃሴዎችን ሁሉ እየተከታተሉ በአሉታ መልኩ መተርጎም የሚኮነን ተግባር ነው፡፡

🔉እንደዚህ ዓይነት መልዕክቶችን በማሰራጨት ለህዝብ ጥቅም የሚሰራ በማስመሰል ችግር የመፍጠርና የአከባቢው ሰላምና መረጋጋት ስጋት ውስጥ እንዲገባ የማድረግ ተልዕኮ ያነገበ በመሆኑ ህዝባችን ጥንቃቄ በመውሰድ ተግባራትንም ማውገዝ አለበት፡፡

🔊አከባቢያዊ ድብቅ አካወንቶች በሠራዊቱ ላይ ብቻ ሳይሆን ለማህበረሰቡ በሚሰጡ ሌሎች መንግስታዊ አገልግሎቶችን መነሻ በማድረግ የሚደረጉ ትችቶች በህዝብ መሃል ጥላቻን የሚፈጥሩ፣ ስድብና ስብዕናን የሚነኩ ቃላትን በመጠቀም ግጭት ቀስቃሽ ስሜት መፍጠር ሚዛናዊነትን ያልጠበቀ ትችት ተገቢነት የለለው መሆኑንም እየገለፅን ህዝቡ እንዲያወግዘው እናሳውቃለን፡፡

🔊እነዚህ በሠራዊቱ ላይ ያለበቂ ምክንያትና ባልተገኘበት የሚሰጡ ጥላቻና ኢ-ሞራላዊ አገላለጾች በድምሩ አከባቢያዊ መረጋጋትን የማሳጣት፣ የሚፈጠር ችግር ደግሞ ለአድራጊዎች ጥቅም አምጪነት ያለመ በመሆኑ አድራጊዎች ከተግባራቸው እንዲታቀቡ አጥብቀን እያሳወቅን ህዝባችን እነዚህን ተግባራትን በማውገዝም ሆነ የህግ ተጠያቂነትን ለማስፈን በምናደርገው ተግባር ላይ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

➤መግለጫው ፦ከዞኑ ህዝብ ግኑኝነት ድቭዥን/ሣውላ/

ግንቦት 03/2013ዓ.ም                                                     #ለመላው ጎፋ ዞን ነዋሪዎች በሙሉ========================የጎፋ ዞን ...
11/05/2021

ግንቦት 03/2013ዓ.ም


#ለመላው ጎፋ ዞን ነዋሪዎች በሙሉ
=======================
=የጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ም/ኮማንደር ዘላለም ደምሴና የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ድቪዥን ሃላፊ ኮማንደር ታርኩ አክልሉ ጋር በጋራ በመሆን በወቅታዊ የዝናብ ሁኔታ አደገኛነት ተከትሎ ለመላው የአከባቢው ህዝብ በተለይም ለአረጋውያን፣ለሴቶችና ህፃናት ይበልጥ ጥንቃቄ እንድደረግ የጥንቃቄ መልዕክት አስተላልፈዋል።

#የጥንቃቄ መልዕክታቸውም እነሆ.........

=ከሁሉ በማስቀደም የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለሁሉም የዞኑ ማህበረሰብ ሠላምንና ጤናን እንደምመኝ በመግቢያ ንግግራቸው ገልፀውታል።

=ዞኑ አሁን ለደረሰበት ሠላምና መረጋጋት የህዝባችን ተሳትፎና ድጋፍ ትልቁን ድርሻ የሚይዝ ስለሆነ ለቀጣይም ይህ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በሠላም ፈላጊው ህብረተሰብ ሙሉ እምነት አለን ሲሉም አሳስበዋል።

=በመቀጠልም የወቅቱ ከፍተኛ ዝናብ በተለያዩ የአገራችን ክፍል በተለያዬ መልኩ ሊገለጽ የሚችል ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝም ጠቅሰው፤ በዞናችንም በአንዳንድ ቦታዎች በሰው ሕይወትና ንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳትና ኪሳራ እያደረሰ ያለ ሲሆን ዝናቡም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በሚድያ ዘወትር እየተገለፀ እንዳለም ገልፀዋል።

=በተለይም ህዝባችን ወንዝ ሲያቋርጡ /ሲሻገሩ /፣የመሬት ናዳ ሊገጥም በሚችል አከባቢ መኖሪያ ቤትና የእርሻ ማሳ ያላችሁ፣አሽከርካሪዎች ጎርፍ በሚመጣበት አከባቢ ሲያቋርጡ ፣በመኖሪያ ቤት ግቢና አከባቢ የፈሳሽ መንገድ ማሳለጫ ከወድሁ ባልተዘጋጀበት ፤

=እንድሁም በከተሞችና መንገድ ዳር ያሉ የፈሳሽ ማስወገጃ ዲቾች/ቱቦዎች/በቆሻሻ መደፈናቸው ለከፍተኛ ጉዳት ሊዳርጉ ስለሚችሉ ህዝባችንም ሆነ የሚመለከታቸው አካላት ከወድሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉና በመቀናጀት የማስተካከያ እርምጃዎችን እንድወስዱበትም በአንክሮ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

=አክለውም የተቋማችን ከፍተኛ አመራሮች እንደገለፁት ከሆነ ለአረጋውያን ፣ለሴቶችና ህፃናት ሁሉም ዜጋ ልዩ ትኩረት እንድሰጥ እና ሃላፊነት እንድወስዱም ጥቆማ ሰጥተዋል።

@በመጨረሻም➤
==========
➤ የዞናችንን ፖሊስ አመራርና አባላትም ከሠላም ወዳዱ የአከባቢያችን ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀትና በመናበብ ከላይ የተጠቀሱ የተፈጥሮ አደጋዎች በየአካባቢያችው ሲከሰቱ ፈጥኖ በመድረስ ከህዝብ አብራክ የወጣን የህዝብ ልጅ መሆናችንን ህይወትን በመታደግ እንድትገልጹ እናሳስባችኋለን።

➤እግዚአብሔር አከባቢያችንን ብሎም አገራችንን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን የመጨረሻ መልዕክታችን ነው!! ዘጋቢ የዞኑ ህ/ግ/ገ/ግ/ድቭዥን

 #የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ም/ኮ/ር ዘላለም ደምሴ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን  አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹     @ሚያዝያ 21/20...
29/04/2021

#የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ም/ኮ/ር ዘላለም ደምሴ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹

@ሚያዝያ 21/2013ዓ.ም ሳውላ!

የጎፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ም/ኮማንደር ዘላለሞ ደምሴ ለመላው የአካባቢያችን ብሎም የአገራችን የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለፋስካ በዓል በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰን በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል።

ስቀጥሉም አዛዡ በባዓሉ ወቅት አብሮ መብላትና መጠጣት፣ከሩቅና ከቅርብ ከምገኙ ወዳጅ ዘመዶቻችን ጋር ያለንን ህብረት ማጠናከር ወዘተ...የሆኑ ብዙ መልካም እሴቶችን በተግባር የምናሳይበት ወቅት መሆኑን በአጭሩ አንስተው ሲያበቁ

በዝያም ልክ እራሳችንን ላይ፣ ቤታችንን ላይና ባለን ሃብት እንድሁም አከባቢያችንን ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ጥቃት ለማድረስ ሆን ብለው አቅደው የሚንቀሳቀሱ የፀረ ሠላም ሃይሎች እንዳሉ ከግንዛቤ በማስገባት ሁሉም ማህበረሰብ በየቀጣናው ተመድበው ከሚገኙ የፖሊስና ሚልሻ ሃይሎች እንድሁም ከሠላም ወዳዱ ህ/ሰብ ጎን በመቆም እንድተባበሩ ጥሪም ጭምር አስተላልፈዋል።

አክለውም ያልተጠበቀ ድንገተኛ የሆኑ የእሳት አደጋ፣የህፃናት መጥፋትና መሰል ድንገተኛ አደጋዎች እንዳይከሰቱ በዝህ ወቅት የበለጠ መጠንቀቅ ይኖርብናል ሲሉም አሳስቧል።

በባዓሉ ወቅት ለሚያጋጥማችሁ የወንጀል ክስተቶችና መረጃዎች፣ ሥጋቶችና ድንገተኛ ለሆኑ አደጋዎች እንድሁም የተለያዩ የወንጀል ጥቆማዎች ሲኖር ከታች ባለው የመረጃ ስልክ በመደወል የዜግነት ግዴታችንን እንወጣ ስሉም ጠቁመዋል!!
➤0467770487/0467771367/

#በመጨረሻም አዛዡ
==============

💙ለመላው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለፋሲካ በዓል በሠላም በጤና አደረሳችሁ /አደረሰን ብለው
በዓሉ የሠላም፣የፍቅር ፣የአንድነትና በያለንበት ለአገራችን ሠላምና ፀጥታ ንስሓ በመግባት ወደ እግዝአብሔር ፀሎት የምናደርስበት መልካም የፋስካ በዓል እንድሆን በድጋሚ አሳስቧል።

 # ወላጅ አፋልጉኝ  ማስታወቂያ !    👊👊👊👊👊👊👊👊👊=ህፃን ኦዝል ርስቱ ይባላል የመጣበትን አድራሻና የወላጆቹን ሙሉ ስም በውል አያውቀውም ነገር ግን በቀን 19/08/2013ዓ.ም በጎፋ ዞ...
28/04/2021

# ወላጅ አፋልጉኝ ማስታወቂያ !
👊👊👊👊👊👊👊👊👊

=ህፃን ኦዝል ርስቱ ይባላል የመጣበትን አድራሻና የወላጆቹን ሙሉ ስም በውል አያውቀውም ነገር ግን በቀን 19/08/2013ዓ.ም በጎፋ ዞን ሳውላ ከተማ ውስጥ ለውስጥ እያለቀሰ ስመላለስ በማህበረሰቡ ጥቆማ ህፃኑ ተይዞ ወላጅ ቤተሰብ እስክገኝ ድረስ በሳውላ ከተማ አስ/ር ፖሊስ ጽ/ቤት በኩል እየተረዳ ይገኛል።
=ሰለዚህ የህፃኑ ወላጅና ቤተሰብ የሆናችሁ በሙሉ በሳውላ ከተማ አስ/ር ፖሊስ የመረጃ ስልክ ቁጥር 0467770487/0949659200/በሆነው ላይ በመደወል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

=ህፃን ወዳድ የአካባቢያችን ቢሎም የአገራችን የfbook ተጠቃሚዎች ይህንኑ ጉዳይ ሼር በማድረግ ሃላፊነታችሁን እንድትወጡ በማክበር እናሳስባችኋለን።

👊ህፃናትን መወደድ ሀገርን መወደድ ነው!!

ሚያዝያ 10/2013ዓ.ም  #የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ በመንደር ሦስት አከባቢ ነዋሪዎችና በደቡብ ኦሞ ዞን ድሜ ጋሮ አከባቢ ሰፍረው ከሚኖሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ አባላት ጋር የፀጥታ ም...
17/04/2021

ሚያዝያ 10/2013ዓ.ም

#የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ በመንደር ሦስት አከባቢ ነዋሪዎችና በደቡብ ኦሞ ዞን ድሜ ጋሮ አከባቢ ሰፍረው ከሚኖሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ አባላት ጋር የፀጥታ ምክክር መደረጉ ተገለፀ።
👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊

👊የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ በመንደር ሦስት አከባቢ ነዋሪዎችና በደቡብ ኦሞ ዞን ድሜ ጋሮ አከባቢ ሰፍረው ከሚኖሩ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ አባላት ጋር የፀጥታ ምክክር መደረጉን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ሉዑክ የመሩ የክፍላችን ፖሊስ አዛዥ ም/ኮ/ር ዘላለም ደምሴ አሳስበዋል።

👊አክለውም አዛዡ በመሎ ኮዛ መንደር 3 አከባቢ ነዋሪችና ደቡብ ኦሞ ዞን ድሜ ጶድዎች መካከል ከቅርብ ግዜያት ጀምሮ "ከድንበር ይገባኛል ጥያቄና አለመግባባት" የተነሳ ጶዲዎች በጦር መሣሪያ በመታገዝ በከብቶችና ሰዎች ላይ በአሳቻ ሰዓት ዘረፋና ግድያ አካል ጉዳት ወንጀሎችንና የተለያዩ መሰል ጥቃቶችን በተደጋጋሚ ጊዜ እየፈፀሙ መቆየታቸውንም አንስተዋል።

👊ይህ ድግግሞሽ የፀብ አጫሪነት ክስተቶች እያደሩ እየዋሉ አደብ ካለመግዛታቸው የተነሳ ለዞኑ ብሎም ለክልሉ ፀጥታ እራስ ሚታት እየሆነ መቀጠሉንም አዛዡ ለክፊሉ ህዝብ ግንኙነት ድቭዥን በስልክ በሰጡበት መረጃ አንስተዋል።

👊እንድህ ዓይነት ግጭቶችና አለመግባባቶች እንዳይቀጥሉ ከጎረቤት ደቡብ ኦሞ ዞን ጋር መረጃ በመለዋወጥ እርምጃ እየተወሰደበት እንድሁም የአከባቢውንና ክልላዊ ፀጥታ ሃይሎችን ጭምር በማሰማራት የማረጋጋት ሥራ እየተሰራ የቆየ ቢሆንም ተደጋጋሚ ወንጀለኞች በተለይም በከብት ዝርፍያና በተለያዩ ወንጀሎች ላይ የተሰማሩ ጥቅት ባንዳዎች አለመያዛቸውም ሠላሙ ወደ አስተማማኝ ደረጃ አለመድረሱን የምያመላክት ነው ሲሉም ከአንደበታቸው አክለዋል።

👊ስለሆነም የድሜ አርብቶ አደሮች ሁኔታ ውሎ ሲያድር በሁለቱ ዞን ህዝቦች መካከል ለረጅም ዘመናት የተገመደውን መልካም እሴት በማጨለም ወደ ከፋ አለመግባባትና ግጭት እንዳያመራ ከደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን በተላኩ የፖሊስና የልዩ ሃይል አመራሮች ጋር በመናበብ ግጭቱ በሚከሰትበት የሁለቱ ድንበር መካከል በመገኘት ከ2ቱ ማህበረሰብና ከዞንና ከወረዳ ከተወጣጡ አመራሮችና አገር ሽማግሌዎች ባሉበት የጋር ምክክር በማድረግ ችግሩ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንድፈታ ተደርጓል።

👊በመጨረሻም አዛዡ ሁለቱም የማህበረሰብ ክፍል በሥራቸው ሰግስገው የገቡ የሰላምና የፍቅር ጠላቶች ወይም ፀብና ግጭት ቀስቃሽ ሱስ ያለባቸውን ሰዎችን በመለየት ለህግ አሳልፎ በመስጠት ለአካባቢው ሰላም ዘብ እንድቆሙም አስምረውበታል።

👊ሠላም ከየትኛውም ዓለም ገበያ አይገኝም ስለዚህ ሁላችንም ለሠላም ዘብ እንቁም መልዕክታችን ነው!!!

➤ዘገባው=የጎፋ ዞን ህዝብ ግንኙነት ክፈል #ሣውላ

መጋቢት 13/2013ዓ.ም በጎፋ ዞን ውስጥ ለሚገኙ የወንጀል መርማሪዎች የዞኑ ሙስና ወንጀል ምርመራ ዲቭዥን ሃላፊ ም/ኢ/ር ታረቀኝ አጥናፉ በኩል ስልጠና መስጠቱ ተገለፀ።👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊...
23/03/2021

መጋቢት 13/2013ዓ.ም

በጎፋ ዞን ውስጥ ለሚገኙ የወንጀል መርማሪዎች የዞኑ ሙስና ወንጀል ምርመራ ዲቭዥን ሃላፊ ም/ኢ/ር ታረቀኝ አጥናፉ በኩል ስልጠና መስጠቱ ተገለፀ።
👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊👊

=በጎፋ ዞን ሥር ለሚገኙ ለ7ቱ ወረዳና ከ2ቱ ከተማ አስተዳደር በአጠቃላይ ከዘጠኙ የፖሊስ መዋቅሮች ተወጣጥተው ለመጡ እንድሁም የዞኑን ፖሊስ ጨምሮ በድምሩ 40 መርማሪዎች ስለ ሙስና ወንጀል ምርመራ ላይ የሚስተዋሉ ብልሹ አሰራሮችን ለመቅረፍ ታስቦ በተዘጋጀው ሠነድ ዙሪያ ለሠልጣኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መሰጠቱን የዞኑ ፖሊሲ ሙስና ምርመራ ድቭዥን ሃላፊ ም/ኢ/ር ታረቀኝ አጥናፉ ገለፁ።

=ሃላፊው በመግቢያው ንግግራቸው እንደገለፁት የሙስናና ብልሹ አሰራር በአንድ አገር ውስጥ ሁለንተናዊ እድገትና ለወጥ በማምጣት የህዝቦችን እኩል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንድቻል የልማት ሩጫዎችን በማዳከም ህዝቦች ከድህነት ጋር የምቆዩበትን ዕድሜ የሚያራዝም አደገኛ ወንጀል መሆኑን አስምረውበታል።

=አክለውም ሥልጠናውን የሰጡ ሃላፊው ስለሙስና ወንጀል ባህሪይውና አፈፃፀም ስያብራሩት ሙስና ወንጀል በባህርይው ከመደበኛ ወንጀል የሚለይና ፈፃሚዎቹም የተማሩ እና ሥልጣን ላይ ያሉ አካላት በመሆናቸው እንድሁም በወንጀሉ ላይ የግል ተበዳይ የሌለና ሰጭም ተቀባይም ሁለቱም ተጠቃሚ በመሆናቸው ምርመራውን ውስብስብ ያደርገዋል ሲሉ አስገንዝበዋል።

=ስለዚህም አሉ የሙስና ሃላፊው መርማሪዎች ከሙስና ወንጀል ባህርይና አፈፃፀም ተግዳሮቶችን በደንብ ለይተው በማወቅና በመገንዘብ ልዩ ትኩረት በመስጠት ምርመራውን ማጣራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

#የዕለቱ ሥልጠና ትኩረት ያደረገባቸው ርዕሶች ዋና ዋናዎቹ ፦
(ሀ)የሙስና ወንጀል እና ሥ/ሥራዓት ህጎች
(ለ)የሙስና ወንጀል የምገልፀው የህግ ድንጋጌ
(ሐ)የሙስና ወንጀል ጥቆማ አቀባበል ፣አመዘጋገብ፣ጥቆማ የሚቀበል አካል
(መ)የሙስና ወንጀል ምርመራ ዕቅድ፣ ማስረጃ አሰባሰብና ተጠርጣሪ ስለመያዝ
(ሠ)ስለ ንብረት ዕግድ
(ረ)የሙስና ወንጀል እና ሥነ ሥራዓታዊ ጉዳዮችን የማየት ሥልጣን ያለው ፍ/ቤት
(ሰ)ስለ ዋስትና
(ሸ)የቂም በቀል እርምጃዎች በተመለከተ በመርማሪዎቹ በበቂ ሁኔታ ሲመጣና የሰጠ ሲሆን ወዘተ… በመሳሰሉት አብይ ጉዳዮችን አንድባንድ በመተንተን ሥልጠናው እንደተሰጣቸው ሃላፊው ለዞኑ ህዝብ ግኑኝነትና ገፅታ ግንባታ በሰጠው መግለጫ አስታውቀዋል።

#በመጨረሻም፣
==========

= በዕለቱ በተሰጠው የሙስና ወንጀል ሠነድ አዘገጃጀትና አሰጣጥ እንድሁም የቀጣዩ የሥራ አቋም ጭምር በተመለከተ አስተያየትና ሀሳብ ከመድረክ በተጠየቁበት፤

=መርማሪዎች ከሥልጠና ሠነድ አዘገጃጀት እስከ ሥልጠና አሰጣጥ ድረስ ያለው ሁኔታ እጅግ አስደማሚና ለወደፊቱ ሥራ ላይ ውጤት ማስመዝገብ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ሥልጠና መሆኑን ገልፀዋል።

=የተነሱ ጥያቄና አስተያየቶችን አስመልክቶ ምላሽ የሰጡ የሙስና ወንጀል ምርመራ ድቭዥን ሃላፊው ሁሉም መርማሪ ከሥልጠናው ያገኘውን ዕውቀትና የሥራ ልምድ በመጠቀም በያለበት አከባቢ የተሻለ ወጤት በማስመዝገብ ህዝባዊና መንግስታዊ ግዴታችንን ብሎም ሃላፊነታችንን መውጣት ይኖርብናል ሲሉ አጠቃለዋል ።

👊ሙስናና ብልሹ አሰራር ለአገር ዕድገትና ለወጥ ፀር ስለሆነ ሁላችንም ተባብረን እንታገል!!!!!!!

👊አዘጋጅ የዞኑ ፖሊስ ህዝብ ግኑኝነት ድቭዥን
@ ሳውላ2013ዓ.ም

15/03/2021
 #6ኛውን አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በተዘጋጀው ሁለቱ ሠነዶች ዙርያ ለጎፋ ዞን ፖሊስ አመራሮች ሥልጠና መሰጠቱ ተገለፀ።================================-6ኛውን አገራዊ ምር...
12/03/2021

#6ኛውን አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በተዘጋጀው ሁለቱ ሠነዶች ዙርያ ለጎፋ ዞን ፖሊስ አመራሮች ሥልጠና መሰጠቱ ተገለፀ።
================================
-6ኛውን አገራዊ ምርጫ አስመልክቶ በተዘጋጀው 2ቱ ሠነዶች(1ኛ) የፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዕቅድ ሠነድና(2ኛ )በደቡብ ክልል ደረጃ የተዘጋጀና ዞናዊ ነባራዊ ሁኔታን የቃኘ የፖሊስ የፀጥታ መሪ ዕቅድ ዙርያ ከ7ቱ ወረዳና ከ2ቱ ከተማ አስተ/ር ከመጡ የፖሊስ አመራሮች እንድሁም ከዞኑ የድቭዥን ሃላፊዎችና የቡድን መሪዎች በተገኙበት በዞኑ ድርጅት አደራሽ ውስጥ በጎፋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ም/ኮ/ር ዘላሌም ደምሴ በኩል ሥልጠና መሰጠቱ ተገለፀ።

-ሠነዱን በማንበብ አዛዡ ሥልጠና ከመስጠቱ በፊት የዕለቱ ክብር እንግዳና የዞኑ ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ብራኑ ጅፋሬ ለሥልጠና በቀረቡት 2ቱ ሠነዶች አዘገጃጀትና አፈፃፀም አስመልክቶ አጠር ያለ ንግግር በማድረግ ሥልጠናው በይፋ መጀመሩን አብስረዋል።

-ከዚህ በመቀጠልም የዞኑ ፖሊስ አዛዥ የሥልጠና ሠነዶችን ጥልቅ ሚስጥር፣ይዘትና ዓላማ እንድሁም አገራዊ ምርጫውን አስመልክቶ ሠነዱ ላይ የተቀመጡ ውጫዊና ውስጣዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን ካለንበት ነባራዊ ሁኔታዎች አንፃር በማነፃፀር አመራሩ በደንብ እንድገነዘቡ አስችሏል።

-አክለውም አዛዡ በአገራችን ብሎም በአካባቢያችን እየተስተዋለ ያሉ የፀጥታ ችግሮች በርካታና ውስብስብ መሆናቸውን ከግምት ውስጥ በማስገባት የምርጫ ሂደቱና ውጤቱ ነፃ፣ፍታዊና ታዓማኒነት ያለው ሆኖ ከሁከትና ብጥብጥ የፀዳ እንድሆን የፀጥታው መዋቅሮች የበኩላቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት በድስፕሊን መውጣት የግዴታ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

-ለዚህም በፀጥታ መዋቅር በኩል የተቀናጀ የምርጫ ደህንነት ዕቅድ በማውጣት በጥብቅ ድስፕሊን እየተመራ መፈፀም አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የፀጥታ መዋቅሩን ሰፊ ዝግጅት ፣ቅንጅትና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ወሳኝነት እንዳለውም በአንክሮ አሳስቧል።

-ቅንጅት ስባልም በአካባቢያችን ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት ለማስፈንና የሰው ሃይል ችግሮችን ለማጥበብ በእጃችን የሚገኙ የገለልተኛ አ/ም/ቤት ኮሚቴዎችን ፣ሚልሻዎችንና ተቀናሽ የሠራዊት ሃይሎችን እንድሁም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የባለድርሻ አካላትን በማደራጀትና ከእነሱም ጋር የምክክር መድረኮችን በመፍጠር በአግባቡ በመያዝ መምራት እንዳለባቸውም በጥብቅ አንስተዋል።

-በተለይም በአገራችን ኢትዮጵያ ከ1987ዓ.ም ወዲህ ለ5ኛ ዙር የተካሄደው የምርጫ ሂደት ሥራዓት አልበኝነት የነገሰበት ፣ህገመንግስት የተጣሰበት፣ዜጎች በነፃነትና በሠላም የመኖርና የመንቀሳቀስ መብታቸውን የተነፈጉበት እንድሁም የህይወት ና የአካል ደህንነት መብታቸውን ያጡበት ግዜ መሆኑን አንስተው ሲያበቁ፤

# አሁናዊ አገራዊ የፀጥታ ሁኔታም ስገመገም በቅድመ ምርጫ ፣በዕለተ ምርጫና ድህረ ምርጫ ወቅት ይህንኑ ዓላማ ለማሳካት ከሩቅ ና ከቅርብ የፀረ ሠላም ሃይሎች የራሳቸውን Network በመዘርጋት በህዝቡ ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖሌትካዊ ቅኝቱ እንድዛባ አጋንታዊ ተልዕኳቸውን በማንገብ ቅንጅት ፈጥረው እየተንቀሳቀሱ ያሉ ሃይሎች በርካታ መሆናቸውን መዘንጋት የለበትም ሲሉም አንስተዋል።

#አክለውም አዛዡ በምርጫ አፈፃፀም መመሪያው መሠረት ከቅድመ ምርጫ፣በዕለተ ምርጫና ድህረ ምርጫ ወቅት አንድም ዓይነት የፀጥታ ችግር ሳይፈጠር እንድጠናቀቅ እና ምናልባት የፀጥታ ችግር ብከሰት በገለልተኝነት የሚያጣራ የወንጀል ምርመራ ቡድን አወቃቀርና አፈፃፀም ላይ ከፍ ያለ ትኩረት መሰጠት እንዳለባቸው ካሰመሩ ቡኋላ በምርጫ ቀጠና የተመደቡ የፖሊስ አባላት በራሀብና ጥማት እንዳይጎዱ ከምመለከታቸው ጋር በመነጋገር አስፈላጊው ቅድመ ሁኔታ ከወድሁ መሟላት እንዳለባቸውም አስገንዝቧል።

#ስቀጥል በምርጫ ቀጠና የተመደቡት የፖሊስ አባላት ዓላማ የምርጫ ኮሮጆ እንዳይጭበረበርና አደጋ እንዳያጋጥመው በቅርብ ርቀት በመሆን መከታተል መቆጣጠርና መከላከል ሆኖ ግን በም/ቦርድ ሰብሳቢ ጥር ስደርስ ብቻ ጣልቃ መግባት

-በመሆኑም 6ኛውን አገራዊ ምርጫ በመልካም መንፈስ ፣በገለልተኝነት፣በቁርጠኝነትና በከፍተኛ ሀገራዊ ስሜት መፈጸም እንደምገባ ለሁሉም ፖሊስ አመራሮች ካስገነዘቡ ቡኋላ ከቤቱ ለተነሱ ጥያቄና አስተያዬት መልስ ሰጥተው ሲያበቁ አመራሩ በሚሄዱበት አከባቢም ለሚገኙ የፀጥታ ሃይል ሥልጠና በመስጠትና ሠነዱን በውይይት በማዳበር እንድሁም የምርጫ አፈፃፀም አጭር ዕቅድ ጭምር በማዘጋጀት ግብረ መልሱን በሪፖርት እንድያሳውቁ በማለት የዕለቱን መድረክ አጠቃሏል።

Address

Sawla Felege Neway

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጐፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ Gofa Zone Police Dep't posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share