ተ/ሃ/መ/ጠ ሆስፒታል THMG Hospital

ተ/ሃ/መ/ጠ ሆስፒታል THMG Hospital Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ተ/ሃ/መ/ጠ ሆስፒታል THMG Hospital, Government Organization, Sek'ot'a.

The focus of public relations is to improve health digital technology, community participation and ownership, improve information-based decision-making systems, improve leadership and good governance,

25/08/2026

‎የአንድ ከተማ የስሉጥ መገለጫ የዲጂታላይዜሽን ስራ ነው፥ ባህር ዳር ከተማ በጤና ተቋማት የተሰራው ዲጂታላይዜሽን ለሌሎች ተሞክሮ የሚሆን ነው።

አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ


#አብክመጤናቢሮ

Care Ethiopia ለተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል የግብዓት ድጋፍ አደረገ::ሐምሌ 29/2018ዓ.ም  ሰቆጣ፦ Care Ethiopia የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በዋግኽምራ ብሔረሰ...
06/08/2026

Care Ethiopia ለተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል የግብዓት ድጋፍ አደረገ::

ሐምሌ 29/2018ዓ.ም ሰቆጣ፦ Care Ethiopia የተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ከተማ ለሚገኘው ለተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ሊያቃልሉ የሚችሉ ልዩ ልዩ የመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያ ግብዓቶችን በድጋፍ መልክ አበረከተ።

ሆስፒታሉ ከሰሜኑ ጦርነት ጀምሮ በደረሰበት ከፍተኛ ውድመትና አሁን ላይ ባሉ ወቅታዊ የፀጥታ ችግር እና የበጀት እጥረት ምክንያት በተፈጠረው የመድሃኒት እና የተለያዩ የህክምና የመሳሪያ ግብከቶች እጥረት ምክንያት ችግርን ሊቀርፍ የሚችል ከ18ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ ግብአቶች በCare Ethiopia አማካኝነት ተበርክቶለታል።

በዕለቱ የድጋፍ ቁሳቁሶቹን ሲያስረክቡ የተገኙት የሆስፒታሉ ሚዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ባዩ አስናቀ እንደገለጹት፤ ድርጅቱ ያደረገው ድጋፍ ሆስፒታሉ አሁን ላይ ያለበትን የግብዓት እጥረት ለመቅረፍና ለታካሚዎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ያሉ ሲሆን፦ Care Ethiopia ከዚህ ቀደምም ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን እያደረገልን የመጣ እና አሁንም እየደገፈን ያለ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ነው ካሉ በሗላ ይህ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የሆስፒታሉ ስራአስኪያጅ የሆኑት አቶ ታምሩ ቢምረው እንደገለጹት የተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ዘረፈ ብዙ ችግሮች እንዳሉበት የሚታወቅ ነው ካሉበሗላ የዛሬው የcare Ethiopia ድጋፍ በዚህ አጣበቂኝ ሁኔታ ላይ ባለነበት ወቅት በመሆኑ ከዚህ ቀደሙ ድጋፍ ይለያል ብለዋል።አያይዘውም የሆስፒታሉን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመቅረፍ ልክ እንደ Care Ethiopia ሁሉ ሌሎች ግብረሰናይ ድርጅቶችም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

Care Ethiopian በሆስፒታሉ እና በዋግኽምራ ህዝብ ስም ከልብ እናመሰግናለን!!

ሐምሌ 29/2018ዓ.ም

አባይ ባንክ  ለተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል የገንዘብ ድጋፍ አደረገ አባይ ባንክ  1ሚሊዮን ብር    ለተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል የገቢ ማሰባሰቢያ ድጋፍ አድርጓል።  ...
30/07/2026

አባይ ባንክ ለተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
አባይ ባንክ 1ሚሊዮን ብር ለተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል የገቢ ማሰባሰቢያ ድጋፍ አድርጓል።

ሆስፒታሉ ከልብ እያመሰገነ ሌሎች ባንኮችም የአባይ ባንክን አርአያነት እንዲከተሉ ጥሪ አስተላልፋል።

ሐምሌ 23/2018ዓ.ም

29/07/2026

ርቀትን እንቀንስ፣ ህይወትን እንታደግ!"

28/07/2026

የእርስዎ ዛሬ የሚያደርጉት ድጋፍ፣ የነገውን የሰው ህይወት ይታደጋል።

27/07/2026

ህክምናን ወደ ደጃችን እናቅርብ፤ የሲቲ እስካን ክፍላችንን አብረን እንገንባ!

26/07/2026

የምንገነባው ህንፃ ብቻ አይደለም፤ የሰዎችን ህይወትና ተስፋ ነው

26/07/2026

Address

Sek'ot'a

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ተ/ሃ/መ/ጠ ሆስፒታል THMG Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share