14/10/2020
#ለጥንቃቄ⤵
አዲስ የታተሙ የብር ኖቶች አይነት እና የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች
~~~~
❶ ተከታታይ ቁጥሮች፦
የገንዘቡ ቁጥሮች በሚያጎላ ማሽን ሲታዩ ከጥቁር ወደ አረንጓዴ ፍሎረሰንት ቀለም ይለወጣሉ፡፡
❷ ማየት ለተሳናቸው እውቅና ምልክት፦
የብሩን ዋጋ የሚገልጽ ማየት የተሳናቸው በእጅ ዳሰሳ ማወቅ የሚችሉበት የደህንነት መጠበቂያ ምልክት፡፡
❸ ጎርባጣ_መስመሮች (PEAK)፦
የባንክ ኖቱ ሲዳሰስ የመጎርበጥ ስሜት እንዲሁም የኖቱ ዋጋ ይታያል፡፡
❹ ደማቅ አንፀባራቂ ምልክት፦
ገንዘቡ ወደላይ ወይም ወደታች ሲዞር የሚንቀሳቀስ ደማቅ የቀለም ፍንጣቂ (SPARK) የደህንነት መጠበቂያ ምልክት፡፡
❺ የደህንነት መጠበቂያ ክር፦
የሚሽከረከር ደማቅ ቀለም ኮከብ አዲስ የደህንንት መጠበቂያ ክር፡፡ በክሩ ውሰጥ NBE፣ ኢብባ እና የገንዘቦቹ አይነት ተጽፎ ይገኛል፡፡
❻ የውሃ ምልክት፦
ገንዘቡ ወደብርሃን አቅጣጫ ተደርጎ ሲታይ በላዩ ላይ ከሚገኘው ምስል ፊት ለፊት ተመሳሳይ ደብዛዛ የውሃ መልክ ያለው ምልከት ይታያል፡፡
❼ ትይዩምልክት፦
የብር ኖቶች ከብርሃን አቅጣጫ ሲታዩ ኳስ መሳይ ምልክት ከገንዘቡ በስተኋላው ካለው ተመሳሳይ ምልክት ጋር በፍጹም ትይዩ ሆነው በአንድ ቦታ ላይ ያርፋሉ፡፡
❽ ፈሎረሰንስ ምልክት፦
አንበሳው ምስል ራስ ላይ አልትራቫዮሌት ጨረር ሲበራበት ወደቢጫነት የሚለወጥ ፈሎረሰንት ምልክት፡፡
👉ያስተውሉ፦
አዲስ የታተሙት የብር ዓይነቶች በአካላቸው ላይ የሚገኙ የደህንነት መጠበቂያ ምልክቶች ያሉባቸው ናቸው፡፡
እነዚህን ያላሟሉ ወይም ተመሳስለው የተዘጋጁ ገንዘቦቸን የያዙ ወይም የሚጠቀሙ ግለሰቦች ካጋጠሙዎት ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ለሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ/ የጸጥታ አካል ያሳወቁ፡፡