Kominikeeshinii Jiillee Dhummuugaa/ ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መ/ኮሚኒኬሽን

  • Home
  • Ethiopia
  • Senbete
  • Kominikeeshinii Jiillee Dhummuugaa/ ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መ/ኮሚኒኬሽን

Kominikeeshinii Jiillee Dhummuugaa/ ጅሌ ጥሙጋ  ወረዳ  መ/ኮሚኒኬሽን 𝗧𝗵𝗶𝘀 𝗶𝘀 𝘁𝗵𝗲 𝗢𝗳𝗳𝗶𝗰𝗶𝗮𝗹 𝗙𝗮𝗰𝗲𝗯𝗼𝗼𝗸 𝗣𝗮𝗴𝗲 𝗼𝗳 𝗝𝗶𝗶𝗹𝗹𝗲𝗲 𝗗𝗵𝘂𝗺𝗺𝘂𝘂𝗴𝗮𝗮 𝗖𝗼𝗺𝗺𝘂𝗻𝗶𝗰𝗮𝘁𝗶𝗼𝗻

የእምርታ ቀንን ምክንያት በማድረግ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ላይ የልምድ ልውውጥ ተካሄደ--------------------------------ሰንበቴ:ጿጉሜ 01/2018 ዓ.ም(ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬ...
06/09/2026

የእምርታ ቀንን ምክንያት በማድረግ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ላይ የልምድ ልውውጥ ተካሄደ
--------------------------------

ሰንበቴ:ጿጉሜ 01/2018 ዓ.ም(ጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን)

​በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መሰዋ ሀደሬ ቀበሌ ሀደሬ ጎጥ ልዮ ቦታ ካሂማ ጳጉሜ 1 አገር አቀፍ የእምርታ ቀንን ምክንያት በማድረግ የሙዝ እና የተለያዮ አትክልት ልማት ላይ ልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተካሄዷል።

​መርሃ ግብሩ በ«ሆርቲላይፍ» (HortiLife) ፕሮግራም ድጋፍ በሞዴል አርሶ አደሮች መሬት ላይ የተካሄደ የሙዝ እና አትክልት ልማት ልምድ ልውውጥ ነው።

​በልምድ ልውውጡ የወረዳ እና ቀበሌ አመራሮች፣ የግብርና ባለሙያዎች እንዲሁም አርሶ አደሮች በመገኘት የሙዝ ልማት የተግባር አፈፃፀም፣ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም እና ምርታማነትን ማሳደጊያ ዘዴዎች ላይ ልምድ እንዲወስዱ ተደርጓል።

በዚህም ​የልምድ ልውውጥ መድረኩ አርሶ አደሮች ከትናንሽ መሬት የተሻለ የኢኮኖሚ ጥቅም ማግኘት እንደሚችሉ እንዲሁም ምርታማነትን ማሳደግ እና የገቢ ምንጫቸውን ማስፋት የሚችሉበትን ዕድል እንዲገነዘቡ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል።

በተያያዘም ከመድረኩ ​የተገኘውን መልካም ልምድ ወደ ሌሎች ቀበሌዎች ማስፋፋት፣ የሙዝ እና የአትክልት ክላስተር ልማትን ማጠናከር እና ቀጣይነት ያለው የቴክኒክ ድጋፍ እና ክትትልን ማጠናከር እንደሚገባ አቅጣጫዎች ተቀምጧል።

Guyyaa Oomishtummaa Qaammee 1 fi Waljijjiirraa Muuxannoo Misooma MuuziiAanaa Jiillee Dhummuugaa, Ganda Maruwwaa Haadaare...
06/09/2026

Guyyaa Oomishtummaa Qaammee 1 fi Waljijjiirraa Muuxannoo Misooma Muuzii

Aanaa Jiillee Dhummuugaa, Ganda Maruwwaa Haadaaree, Gooxii Hadaree, Dirree Kaahimaa keessatti, Guyyaa Oomishtummaa Qaammee 1 sababeeffachuun sagantaan waljijjiirraa muuxannoo misooma muuzii fi kuduraa, gaggeeffame.

Sagantaan kun deeggarsa Sagantaa HortiLife tiin lafa qonnaan bulaa adda duree irratti, misooma muuzii fi kuduraa akka Mana Barumsaa Dirree Qonnaa tajaajilutti qophaa’e irratti gaggeeffame.

Hirmaattota sagantichaa keessaa gaggeessitoonni Aanaa fi Ganda, ogeeyyiin qonnaa akkasumas qonnaan bultoonni argamuun, muuxannoo hojii irra oolmaa misooma muuzii, fayyadama teknooloojiiwwan qonnaa fooyya’oo fi mala omishtummaa guddisuu irratti muuxannoo waljijjiiraniiru.

Sagantaan kun qonnaan bultoonni lafa xiqqaa irraa bu’aa dinagdee fooyya’aa argachuu, omishtummaa guddisuu fi madda galii isaanii babal’isuuf carraa fi mala hojii qabatamaa akka hubatan gumaacha guddaa taasiseera.

Muuxannoo gaarii argame gara gandoota biroo babal’isuu, misooma kilaastaraa muuzii fi fuduraa cimsuu, akkasumas deeggarsa teeknikaa fi hordoffii itti fufiinsa qabu jabeessuun kallattii fuulduraa ta’a.

“Kaleessa irraa haa barannu, har’a haa hojjennu, boru haa ijaarru!”

🌾 “Itoophiyaan Haa Oomishtuu!” 🇪🇹


Qaammeen 1:Guyyaa Oomishtummaa Ol ka'iinsa biyyaatiif!
06/09/2026

Qaammeen 1:Guyyaa Oomishtummaa Ol ka'iinsa biyyaatiif!

ጳጒሜን 1የእምርታ  ቀን
06/09/2026

ጳጒሜን 1
የእምርታ ቀን


Qaammee 1 Guyyaa Oomishtummaa
06/09/2026

Qaammee 1 Guyyaa Oomishtummaa


የክረምት የአዋቂዎች እግር ኳስ ውድድር የዋንጫ ጨዋታ   በአጣዬ ሆስፒታል የእግር ኳስ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።ሰንበቴ፣ነሀሴ 30/2018 ዓ,ም (ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መነግስት ኮምኒኬሽንየክረ...
05/09/2026

የክረምት የአዋቂዎች እግር ኳስ ውድድር የዋንጫ ጨዋታ
በአጣዬ ሆስፒታል የእግር ኳስ ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

ሰንበቴ፣ነሀሴ 30/2018 ዓ,ም (ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መነግስት ኮምኒኬሽን

የክረምት የአዋቂዎች እግር ኳስ ውድድር የዋንጫ ጨዋታ ቢፍቱ የእግር ኳስ ክለብ እና የአጣዬ ሆስፒታል የእግር ኳስ ክለብ በሰንበቴ ሁለገብ እስታዲየም በርካታ ተመልካችና ደገፊ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አካሂደዋል

በዋንጫ ጨዋታው የተሳተፉት ቡድኖች የውድድሩን ዋንጫ ለማሸነፍ በከፍተኛ ትጋት ተፎካክረዋል። የጨዋታውን ሂደት ለመከታተልም በርካታ የስፖርት ወዳጆችና የአካባቢው ነዋሪዎች በሰንበቴ ሁለገብ እስታዲየም ተገኝተዋል።

በመጨረሻም የአጣዬ እግር ኳስ ክለብ ቢፍቱን 4 ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የዋንጫተሸላሚ ሆኗል።

በሚዲያ ይዘት ማበልፀግ ዝግጅትና ስርጭት ቡድን

የክረምት  የአዋቂዎች  የእግር ኳሰ ውድድ  በሰንበቴ ሁለገብ እስታዲየም የዋንጫ ጨዋታ ውድድር  እየተካሄደ ይገኛል ።ሰንበቴ፣ነሀሴ 30/2018 አም( ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን)የ...
05/09/2026

የክረምት የአዋቂዎች የእግር ኳሰ ውድድ በሰንበቴ ሁለገብ እስታዲየም የዋንጫ ጨዋታ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል ።

ሰንበቴ፣ነሀሴ 30/2018 አም( ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን)

የቢፍቱ ና የአጣዬ ሆስፒታል የእግርኳስ ከለብ በሰንበቴ ከተማ ሁለገብ እስታዲየም በርካታ ደጋፊና ተመልካች በተገኙበት ጨዋታው እየተካሄደ ነው

የቢፍቱ ና የአጣዬ ሆስፒታል ክለብ የእግር ኳስ የዋንጫ ውድድር በመጀመሪያ ዙር ጨዋታ አጣዬ ሆስፒታል ቢፍቱ የእግር ኳስ ክለብን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በመምራት ላይ ይገኛል።

በእግርኳስ ውድድሩ ላይ የከተማ አሰተዳር አመራሮችና ማህበረሰብ የተገኙ ሲሆን በአሁኑ ሰአት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸውን አጠናቀዋል።

በሚዲያ ይዘት ማበልፀግ ዝግጅትና ስርጭት ቡድን

“ብዝሃ የወጣቶች እውቀት ለጋራ ትልም” በሚል መሪ ቃል የአለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሰንበቴ ከተማ ተከበረ ።ሰንበቴ፣ነሀሴ 28፣2018 ዓ,ም ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን)“ብዝሃ የ...
03/09/2026

“ብዝሃ የወጣቶች እውቀት ለጋራ ትልም” በሚል መሪ ቃል የአለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሰንበቴ ከተማ ተከበረ ።

ሰንበቴ፣ነሀሴ 28፣2018 ዓ,ም ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መንግስት ኮምኒኬሽን)

“ብዝሃ የወጣቶች እውቀት ለጋራ ትልም” በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ26ኛ ጊዜ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ23ኛ ጊዜ የሚከበረው የአለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ በተለያዩ ማህበራዊ እና በጎ ፈቃድ ተግባራት ተከናውኖ በሰንበቴ ከተማ ተከብሯል።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የህዝብ አደረጃጀት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ወይዘሮ አሚና አልይ መድረኩ ከመጀመሩ በፊት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በመክፈቻቸውም እንደገለፁት ወጣቶችን በልማት፣ በሰላም እና በማህበራዊ ተሳትፎ ዙሪያ ለማበረታታት በተቀናጀ መንገድ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ የወጣቶች ተጠቃሚነት እና የውሳኔ ሂደት ተሳትፎ በቀጣይ የበለጠ እንዲጠናከር ከመቸውም ጊዜ በላይ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ለመድረኩ የተዘጋጀውን ሰነድ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት የወጣት አደረጃጀት ስራ ሂደት አስተባባሪ ለተሳታፊዎቹ ገለፃና ማብራሪያ ከተደረገ በኃላ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ሴቶች ወጣቶች ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ፋጠማ ሰይድ በመድረኩ እንደ ተናገሩት ከሆነ፣ ወጣቶች በሀገር ግንባታ፣ በልማት እና በሰላም ማስፈን የማይተካ ሚና እንዳለቸው ገልጸዋል ።

በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰማሩ የወረዳው ወጣቶች በርካታ ማህበራዊ እና ልማታዊ ተግባራትን በስኬት ማከናወናቸውን ተናግረዋል ።

የበዓሉ ዋና ዓላማ ወጣቶች ለሰላሙ ዘብ በመቆም አንፃራዊ ሰላሙን ዘላቂ ማድረግ፣ ያላቸውን እውቀት፣ አቅምና ጉልበት በመጠቀም የበጎ ፈቃድ ተግባራትን ውጤታማ ማድረግ፣ ብቁና ተወዳዳሪ ውሳኔ ሰጭ ወጣት ማፍራት እንዲሁም ስብዕና የተላበሰ፣ ሀገር ወዳድ እና የሀገሩን ባህልና እሴት የሚያከብር ተተኪ ትውልድ መገንባት መሆኑን ተናግረዋል ።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ወጣት ክንፍ የሆነው ወጣት ኡመር አደም እንደገለፀው ወጣቱ የውሳኔ ባለቤት፣ ተተኪ እና በልማቱ ተሳታፊ በመሆን ተጠቃሚነቱ እንዲረጋገጥ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ።

በመድረኩ የተሳተፉ ወጣቶችም በሰላም ዘብነት ተደራጅተው በመስራት የማህበረሰቡን ሰላም ለማጠናከር ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመንግስት በኩል ቃል የተገባው የወጣት ተጠቃሚነት በተግባር እንዲረጋገጥ አሁንም የሚሰሩ ስራዎች ላይ ክፍተቶች እንዳሉ በመጠቆም የበለጠ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

በጅሌ ጠሙጋ ወረዳ የተከበረው የዘንድሮ የአለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ወጣቶችን በበጎ ፈቃድ፣ በሰላም ግንባታ፣ በልማት እና በማህበራዊ ኃላፊነት ዙሪያ የበለጠ ለማነቃቃት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በሚዲያ ይዘት ማበልፀግ ዝግጅትና ስርጭት ቡድን

03/09/2026

በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የመህር ሰብልን በማስመልከት በአሚኮ የተላለፈ ዜና

03/09/2026

የ2019 ዓ.ም የትምህርት ምዝገባና ቅድመ ዝግጅት ስራዎች በማስመልከት በአሚኮ አፋን ኦሮሞ ፕሮግራም የተላለፈ ዜና

Address

Sanbatee, Aanaa Jiillee Dhummuugaa
Senbete

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kominikeeshinii Jiillee Dhummuugaa/ ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መ/ኮሚኒኬሽን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Kominikeeshinii Jiillee Dhummuugaa/ ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ መ/ኮሚኒኬሽን:

Shortcuts

Share