Ethiopian Police University

Ethiopian Police University The Ethiopian Police University Formerly Called Aba Dina Police College is a public institution of

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከመካከለኛ አመራር ወደ ከፍተኛ አመራር የማዕረግ ሽግግር እና በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ያሰለጠናቸውን አመራሮችና አባላትን አስመረቀ፡፡***********...
14/10/2021

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከመካከለኛ አመራር ወደ ከፍተኛ አመራር የማዕረግ ሽግግር እና በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ያሰለጠናቸውን አመራሮችና አባላትን አስመረቀ፡፡
*******************************************************************
ጥቅምት 04/2014ዓ/ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ፤
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በረጃጅምና በአጫጭር ትምህርትና ስልጠናዎች በመስጠት የዜጎችን ሰላምና ደህንነት መጠበቅና ማስጠበቅ የሚችሉ የፖሊስ አመራሮችና አባላትን በማስተመርና በማሰልጠን የ75 ዓመት ዕድሜ ያለው አንጋፋ የትምህርትና ስልጠና ተቋም ነው፡፡ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት የፌደራል ፖሊስ አባላት መተዳደሪያ ደንብ ቁጥር 268/2005ዓ.ም አንቀፅ 13 ንዑስ ቁጥር 2/ለ ከኢንፔክተር ወደ ዋና ኢንስፔክተር የሚደረግ የማዕረግ እድገት በውድድር፣በፈተና እና በስልጠና በሚለው መሰረት በጥር 2012ዓ/ም እና በሐምሌ 2012ዓ/ም የቆይታ ጊዜያቸውን ላጠናቀቁ 117 ኢንስፔክተሮች በዩኒቨርሲቲው ለ 3 ተከታታይ ወራት የተሠጠውን ስልጠና በሚገባ በማጠናቀቃቸው ዋ/ኢ/ር ማዕረግ ያገኙ ሲሆን ከዚህ ባሻ ገር በዩኒቨርሲቲው ለ15 ተከታታይ ቀናት የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ 98 አመራሮችና አባላት ተመርቀዋል፡፡
በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በኢ/ፖ/ዩ የፖሊሳዊ ስልጠና ፣አካል ብቃት፣አጫጭር ስልጠናዎች ም/ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጋሹ አለማየሁ ከአንድ ማዕረግ እርከን ወደ ሌላኛው የማዕረግ እርከን ስትሻገሩ ከፍተኛ ሀላፊነት የተጣለባችሁ በመሆኑ በዛሬው ዕለት ከመካከለኛ አመራር ወደ ከፍተኛ አመራር የተሸጋገራችሁ መኮንኖች ለቀጣይ ተልዕኮ የምትዘጋጁበት በመሆኑ ጠንክራችሁ መስራት አለባችሁ ሲሉ የገለፁ ሲሆን በዚህም አያይዘው በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ሰራ ላይ የተሰማችሁና በዩኒቨርሲቲያችን ገብታችሁ ያገኛችሁትን ዕውቀት በተጨባጭ እንድትተገብሩ ሲሉ አመላክተዋል፡፡
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መስፍን አበበ ስልጠና ለአንድ ተቋም በራሱ ግብ ሳይሆን ከስልጠናው በኋላ የታሰበለትን ዓለማ ሊያሳካ የሚችል የተግባር እና የአስተሳሰብ ለውጥ ማምጣት የሚችል የሰው ሀይል ማፍራት ነው ያሉ ሲሆን ለሁሉም ተመራቂዎች የሥራ መመሪያ ሠጥተዋል፡፡

14ኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተከበረጥቅምት 1/2014 ዓ.ም******************************************************...
11/10/2021

14ኛው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ
ጥቅምት 1/2014 ዓ.ም
**********************************************************************************
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ ሲቪል ሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች ለ14ኛ ጊዜ “በአዲስ ምዕራፍ በተሟላ ሉአላዊነት ለሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ” በሚል መሪ ቃል በመላ ሀገራችን እየተከበረ የሚገኘው ሰንደቅ ዓላማ ቀንን በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞችና ተማሪዎች ደማችን ለሰራዊታችን በሚል መሪ ቃል ሰንዳፋ በሚገኘው  በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ የደም ልገሳ አደረጉ፡፡በደም ልገሳው ወቅት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩ...
07/10/2021

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰራተኞችና ተማሪዎች ደማችን ለሰራዊታችን በሚል መሪ ቃል ሰንዳፋ በሚገኘው በዩኒቨርሲቲው ዋና ግቢ የደም ልገሳ አደረጉ፡፡በደም ልገሳው ወቅት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ተወካይ ዳይሬክተር ኮ/ር አላምረው ከበደ በዛሬው ዕለት የለገስነው ደም ህግ በማስከበር ወቅት ለሚደርሰው ጉዳት እንዲሁም ለጀግናው መከላካያ ሰራዊት እና በዘመቻው እየተሳተፉ ላሉ ለሁሉም የፀጥታ አካላት ደጀን መሆናችንን እና አለኝታችንን ለመግለፅ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

መስከረም 27/2014ዓ/ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንደፋ

05/10/2021
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊስ ሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች እና ሰራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ፡፡*******************************************************...
24/09/2021

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊስ ሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮች እና ሰራተኞች የደም ልገሳ አደረጉ፡፡
******************************************************************
መስከረም 14/2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊስ ሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ ከፍተኛ የፖሊስ አመራሮች፣ አባሎች እና ሲቪል ሰራተኞች የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ህይዎቱንና አካሉን እየሰጠ ለሚገኘው ለመከላከያ ሰራዊት ፣ ለፌደራል ፖሊስ እና አጠቃላይ ለፀጥታ ሀይል የሚሆን የደም ልገሳ አድርገዋል፡፡
የተደረገው የደም ልገሳ በሀገራችን በተለያዩ ምክንያቶች አደጋ የሚደርስባቸው ዜጎች ደም ስለሚያስፈልጋቸው በተለይም በአሁኑ ስዓት በወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታ ህይዎታቸውን አሳልፈው እየሰጡ ለሚገኙት የፀጥታ ሀይሎች ታሳቢ በማድረግ የተደረገ የደም ልገሳ ፕሮግራም መሆኑን በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊስ ሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ የልዩ ልዩ ፖሊስ ሙያ ስልጠና ዲቪዥን ሀላፊ ኮ/ር ዋለልኝ ገስፅ ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊስ ሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ የተቋሙንና ሌሎች አጋር አካላትን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፍላጎት አጠናክሮ ለማስቀጠል የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
በደም ልገሳ ፕሮግራሙ ላይ የፖሊስ ሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር ተስፈዬ ወንድሙን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የኮሌጁ አመራሮች ተገኝተው ደማቸውን ለፀጥታ ሀይል እና በደም አቅርቦት እጥረት አደጋ ውስጥ ለሚገቡ ወገኖች የለገሱ ሲሆን ደም በመስጠታችን የሰው ህይዎት ከማትረፋችን እና ለጤና ከሚሰጠው ጠቀሜታ ያለፈ የሚጎዳን ነገር ባለመኖሩ ሁሉም የኮሌጃችን አመራርና ሰራተኞች ይህን አምነውበት በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የደም ልገሳ ማድረጋቸውን የገለፁት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊስ ሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ የጤና ማስተባበሪያ ሀላፊ የሆኑት ኮ/ር ጤና መኮንን መለሰ ኃይሌ ናቸው፡፡
"ደም መለገስ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ" አንድም የተጎዱ ወገኖችን ህይዎት ለመታደግ በሌላ በኩል ደግሞ ደሙን ለሚለግሰው ግለሰብ ከፍተኛ የሆነ የጤና ጠቀሜታ ስላለው ማንኛውም ደም ለመለገስ የሚያስችሉ መስፈርቶችን የሚያሟላ ዜጋ ሁሉ ደሙን በመለገስ ለሀገር ክብር እና አንድነት እየተዋደቀ ለሚገኘው የፀጥታ ሀይላችን አለኝታነቱን ማሳየት ይገባል ሲሉ በደም ልገሳ ፕሮግራሙ ላይ የተሳተፉ የኮሌጁ ሰራተኞች እና የጤና ባለሙያዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስካውት ማህበር ጋር በመተባበር ከፌደራልና ከክልል ለተውጣጡ  የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡መስከረም 07/2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ...
17/09/2021

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስካውት ማህበር ጋር በመተባበር ከፌደራልና ከክልል ለተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
መስከረም 07/2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ስካውንት ማህበር ጋር በመተባበር ከፌደራልና ከተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ለተውጣጡ የስካውት ማህበር አመራሮች እና ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
ስልጠናው ከመስከረም 06 እስከ 16/ 2014 ዓ.ም ለተከታታይ 10 ቀናት በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ የሚሰጥ ሲሆን ለሀገርና ዓለም አቀፍ መግባባት ወንድማማችነት እና እህታማማችነት፣ ለሰላም መስፈን የሚጥሩ በበጎ ፈቃደኝነት ሀገራቸውንና ህዝባቸውን ለማገልገል ተነሳሽነት ያላቸው፣ በስነ-ምግባር የታነጹ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት ያለመ ስልጠና መሆኑን በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል፡፡
በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማማከር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ረ/ኮሚሽነር ተሻለ ተሾመን ጨምሮ የኢትዮጵያ ስካውት ማህበር ከፍተኛ አመራሮች፣ አሰልጣኞች፣ ባለድርሻ አካላት እና ሰልጣኖች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ የጋራ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡*******************************************************...
08/09/2021

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ የጋራ የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
*********************************************************
ጳጉሜን 03/2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ

በሀገራችን ከሚገኙ የመንግስት የሰላም እና ደህንነት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ቀዳሚ እና አንጋፋው ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እና የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ የስምምነት ሰነድ ጳጉሜን 02/2013 ዓ.ም ተፈራርመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ም/ኮሚሽነር ጀኔራል መስፍን አበበ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው የተደረገው የስምምነት ሰነድ ፊርማ ተቋማቱ በቅንጅት እና በትብብር በመስራት የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ሊያስጠብቁ የሚችሉ በጥናት ላይ የተመሰረተ ስራ ለመስራት የሚያስችል እንዲሁም በቀጣይ ለምንሰራቸው ስራዎች የበለጠ ተልዕኳችንን ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሁለቱ የሰላምና ደህንነት ተቋማት በጋራ በመሆን ለሀገራችን ሰላምና ደህንነት ግብዓት የሚሆኑ ጥናትና ምርምሮችን ማድረግ ፣የውይይት መድረኮችንና ኮንፈረሶችን ማዘጋጀት ፣ በተቋማቱ መካከል መምህራንና ተመራማሪዎችን በማሰማራት ልውውጥ በማድረግ ከፖለቲካ ወገተኝነት ነፃ የሆኑ የደህንነት ተቋማትን በመገንባት ለሀገራቸው ዘላቂ ሰላም እና ደህንነት መረጋገጥ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተፈራርመዋል ፡፡
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እና በኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ዋር ኮሌጅ መካከል የተደረገው ስምምነት ለሀገራችን ብቁ እና ሙያዊ ክህሎት ያላቸውን የፖሊስ እና የመከላከያ አመራር እና መኮንኖችን ለማፍራት የሚያስችል መሆኑን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ.መከላከያ ዋር ኮሌጅ ዋና አዛዥ ሜጀር ጀኔራል ሀብታሙ ጥላሁን ገልፀዋል፡፡
በሌላ በኩል ሁለቱ ተቋማት ያደረጉት አብሮ የመስራት የጋራ ስምምነት ሰነድ የነበረው ሂደት ይፋ ያደረጉበት እንጅ እንደ አዲስ የጀመሩት ባለመሆኑ ባልሰራንባቸው ጉዳዮች ላይ ይበልጥ በመስራት ከሀገራችን አልፎ በምስራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋት መፍጠር የሚችል ሰራዊት ከመገንባት አንፃር ስምምነቱ ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማማከር ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ረ/ኮሚሽነር ተሻለ ተሾመ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ለሚማሩ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡**************************************************************...
30/08/2021

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት ለሚማሩ ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ፡፡
********************************************************************
ነሀሴ 24/2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከሰንዳፋ በኬ ከተማ አስተዳደር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተውጣጥተው የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት ለሚፈልጉ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው መምህራን እንዲማሩ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር እያስተማረ ይገኛል ፡፡ በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው ከትምህርቱ ባሻገር ፆታን መሰረት አድርገው ከሚፈፀሙ ጥቃቶች ተማሪዎቹ የተሻለ አመለካከትና አረዳድ ይኖራቸው ዘንድ በማሰብ ለክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት ለሚማሩ ተማሪዎች የስርዓተ ፆታ እና ፆታዊ ጥቃት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከነሀሴ 23 አስከ 24/2013 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ብዙ የሚያከናውናቸው የትምህርት እና ስልጠና ፕሮግራሞች ያሉት ቢሆንም የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት አንዱ ተግባሩ በመሆኑ ስልጠናው መዘጋጀቱን እና ከስልጠናውም ጥሩ ግንዛቤ እደምታገኙ ይታመናል ሲሉ በስልጠናው መክፈቻ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የዩኒቭርሲቲው የማማከርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር ኮ/ር አላምረው ከበደ ገልፀዋል፡፡
ፆታን መሰረት አድርገው የሚፈፀሙ ጥቃቶችን አስቀድሞ ለመከላከል የስርዓተ ፆታ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በመስጠት ፈፅሞ ማጥፋት ባይቻልም መቀነስ በሚቻልበት ደረጃ ላይ ለማድረስ እና ህብረተሰባችንን በአመካከት የተሻለ ለውጥ እንዲያመጣ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ጊዚያት ለፖሊስ አባላት እንዲሁም ለተለያዩ ማህበረሰብ ክፍሎች ስልጠና በመስጠት እየሰራ እንደሚገኝ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ጉዳይ ዲቪዥን ኃላፊ ኮ/ር አበሪት ተ/አረጋይ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የወንጀል ምርመራ እና ፎረንሲክ ሳይንስ ኮሌጅ ስር አዲስ በሚከፈቱና ክለሳ በተደረገባቸው የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር   ውይይት ...
27/08/2021

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የወንጀል ምርመራ እና ፎረንሲክ ሳይንስ ኮሌጅ ስር አዲስ በሚከፈቱና ክለሳ በተደረገባቸው የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ ፡፡
***************************************************************
ነሀሴ 21/2013 ዓ.ም ኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሰንዳፋ
በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በወንጀል ምርመራ እና ፎረንሲክ ሳይንስ ኮሌጅ በዲፕሎማ፣ በአመራር እና በአጫጭር ስልጠና ሲሰጥ የነበረውን የትምህርትና ስልጠና ፕሮጋራም በደረጃ (LEVEL) እንዲሰጡ ለማድረግ አዲስ በተቀረፁ እና በነባር ስርዓተ- ትምህርቶች ላይ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተካሔደ ፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከአሁን በፊት በዲፕሎማ ፣በመካከለኛ እና በአጫጭር ስልጠና ፕሮግራም ሲሰጡ የነበሩ የጦር መሳሪያ ምርመራ፣ሰነድ ምርመራ ፣ቃጠሎና ፍንዳታ ምርመራ ክለሳ ተደረጎባቸው በደረጃ(LEVEL) መስጠት እንዲቻል የቀረቡ የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ 04 ሙሉ በሙሉ እንደ አዲስ የሚከፈቱ የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ለተሳታፊዎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጣቸው ትምህርትና ስልጠናዎች የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ በመሆናቸው ውይይት የሚደረግባቸው አዲስ የሚከፈቱ እና ክለሳ የተደረገባቸው የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ተግባር ተኮር ለማድረግ እና ብቁ የፎረንሲክ ምርመራ ባለሙያ ለማፍራት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው የዩኒቨርሲቲው የጥናት፣ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ረ/ኮሚሽነር ተሻለ ተሸመ ገልፀዋል፡፡

Address

Sendafa
1503

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Police University posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Police University:

Share