የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት- Hulbarege worda transport & road office

  • Home
  • Ethiopia
  • Silt'e
  • የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት- Hulbarege worda transport & road office

የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት- Hulbarege worda transport & road office ይህ የሁልባረግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የፌስቡክ ፔጅ ነው

በሁልባራግ ወረዳ በገጠር ተዳራሽ የህብረተሰብ ተሳትፎ የመንገድ ሥራ  ተጠናክሮ ቀጥሎዋል።        ሀምሌ 3/11/2018ዓ/ም                 ኬረቴበወረዳችን በብረሃን ክትክታ ቀበ...
10/07/2026

በሁልባራግ ወረዳ በገጠር ተዳራሽ የህብረተሰብ ተሳትፎ የመንገድ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሎዋል።
ሀምሌ 3/11/2018ዓ/ም
ኬረቴ
በወረዳችን በብረሃን ክትክታ ቀበሌ የዪራፕ መንገድ ከባለሃብት ሙላጌ ቡና ፕሮጀክት በመተባበር የዲችየመቁረጥና የጥገና ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

በወረዳው በ2018 በጀት ዓመት በህብረተሰብ ተሳትፎና በመንግስት ትብብር ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የተሰሩ የመንገድ ስራዎችን የዞን መምሪያ ምዘና ኮሚቴ በተግባር ምልከታ አደረገ።‎ሐምሌ 01/...
08/07/2026

በወረዳው በ2018 በጀት ዓመት በህብረተሰብ ተሳትፎና በመንግስት ትብብር ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የተሰሩ የመንገድ ስራዎችን የዞን መምሪያ ምዘና ኮሚቴ በተግባር ምልከታ አደረገ።

ሐምሌ 01/2018 ሁልባራግ

‎በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ12 ወሩ በወረዳው በህብረተሰብ ተሳትፎና በመንግሥት ትብብር ከ19 ሚሊየን ብር በላይ የተሰሩ የገጠር ተደራሽ መንገዶችን የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኢንስፔክሽን ኮሚቴ የመስክ ምልከታ አካሂዷል።

‎የኢንስፔክሽን ቡድኑ በወረዳው ባካሄደው ምልከታ አጠቃላይ የመንገድ ከፈታና 50% የአፈር ሥራ፣ 100% ቦሮቦር የማልበስ የ17 ኪ.ሜ ኢንሼቲቭ ፣ ርክክብ የተደረጉ የዩራፕ መንገድ ስራዎችን ጥገናና የተለያዩ የስትራክቸር ስራዎች የድልድይና ቱቦ የመቅበርና ሌሎችን የመስክ ምልከታና ልኬት አድርጓል።

በምልከታው በበጀት አመቱ የተሰሩ ስራዎች የሚበረታቱና በተጨባጭ የህብረተሰቡን የመንገድ መሰረተ ልማት ችግር የሚቀርፉ ተግባራት እንደሆኑ የኢንስፔክሽን ቡድኑ ገልጿል።

‎በመርሃ ግብሩ የዞኑ መንገድ ትራንስፖርት መምሪያ የመንገድ ዘርፍ አስተባባሪ አቶ መሀመድ ሙክታር፣ የዞኑ መንገድ ትራንስፖርት መምሪያ የመንገድ ደህንነት አስተባባሪ አቶ ኒውማን ስሩር እንዲሁም የወረዳው መንገድ ትራንስፖርት ባለሙያ አቶ መሀመድ ዙቤር ተገኝተዋል።

ሰኔ 27/2018 ኬራቴበስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ የገጠር ተደራሽ መንገድ በህዝብ ተሳትፎ የመስራት ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።በአንበርቾ አጨሞ ቀበሌ ድኔ ሸንጎ ከዋናው አስፋልት መንገድና ከቀበሌ...
04/07/2026

ሰኔ 27/2018 ኬራቴ
በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ የገጠር ተደራሽ መንገድ በህዝብ ተሳትፎ የመስራት ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በአንበርቾ አጨሞ ቀበሌ ድኔ ሸንጎ ከዋናው አስፋልት መንገድና ከቀበሌው ማዕከል ጋር የሚያገናኘው 3.35 ኪሎ ሜትር የመንገድ ፕሮጀክት በአሁኑ ወቅት የማቴሪያል ዳምፒንግ (Dumping) ሥራ በንቃት እየተከናወነ ይገኛል።

ይህ የመንገድ ግንባታ ለአካባቢው ነዋሪዎች ቀላል መጓጓዣን ከማረጋገጥ ባሻገር የግብርና ምርቶችን ወደ ገበያ ለማድረስ፣ ማህበራዊ አገልግሎቶችን በቀላሉ ለማግኘት እና የገጠር ልማትን ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።

ወረዳውም በህዝብ ተሳትፎ የሚከናወኑ የገጠር ተደራሽ መንገዶችን በተቀናጀ ሁኔታ በማስቀጠል የመሠረተ ልማት ተደራሽነትን ለማሻሻል በትኩረት እየሠራ ይገኛል።

በሁልባራግ ወረዳ ትርፍ እና ታሪፍ እንዲሁም የተሽከርካሪ ቴክኒክ ሁኔታ ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል!!ሰኔ 25/2018 የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ከወረዳው ፖሊስ...
02/07/2026

በሁልባራግ ወረዳ ትርፍ እና ታሪፍ እንዲሁም የተሽከርካሪ ቴክኒክ ሁኔታ ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል!!

ሰኔ 25/2018

የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ከወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት በተሽከርካሪዎች ላይ የትርፍ ጭነት፣ ተጨማሪ ታሪፍ በሚያስከፋሉና የቴክኒክ ብቃት ሁኔታን የሚመለከት ቁጥጥር ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎዋል።

በሁልባራግ ወረዳ ትርፍ እና ታሪፍ እንዲሁም የተሽከርካሪ ቴክኒክ ሁኔታ ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል!!ሰኔ 24/2018 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴየሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ል...
01/07/2026

በሁልባራግ ወረዳ ትርፍ እና ታሪፍ እንዲሁም የተሽከርካሪ ቴክኒክ ሁኔታ ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል!!

ሰኔ 24/2018 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ከወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ጋር በመቀናጀት በተሽከርካሪዎች ላይ የትርፍ ጭነት፣ ተጨማሪ ታሪፍ በሚያስከፋሉና የቴክኒክ ብቃት ሁኔታን የሚመለከት ቁጥጥር እየተካሄደ ይገኛል።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አንዳንድ አሽከርካሪዎች ከተፈቀደው በላይ መንገደኞችን በመጫን፣ ከተደነገገው በላይ ታሪፍ በማስከፈል እንዲሁም የቴክኒክ ችግር ያለባቸውን ተሽከርካሪዎች ወደ ስራ በማሰማራት በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ አደጋ ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ተገልጿል።

በመሆኑም በወረዳው በሚገኙ ሦስቱም ዋና መስመሮች ላይ የትርፍ ጭነት፣ የታሪፍ ተግባራዊነት እና የተሽከርካሪዎች የቴክኒክ ብቃት ፍተሻ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ተቋማቱ አስታውቀዋል።

ተቋማቱ ህብረተሰቡ ከተወሰነው በላይ ታሪፍ የሚያስከፍሉ፣ ትርፍ ጭነት የሚጭኑ ተሽከርካሪዎችን ሲመለከት መረጃ በመስጠት እንዲተባበር አሳስበዋል።

26/06/2026
የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርት ና መንገድ ልማት ጽ/ቤ የ2018ዓ/ም የ4ኛው ሩብ ዓመት የህዝብ ክንፉ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይትና የምዘና መድረክ አካሄዷል  ።        ሰኔ 19/201...
26/06/2026

የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርት ና መንገድ ልማት ጽ/ቤ የ2018ዓ/ም የ4ኛው ሩብ ዓመት የህዝብ ክንፉ ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይትና የምዘና መድረክ አካሄዷል ።
ሰኔ 19/2018ዓ/ም
ኬራቴ
በመድረኩም የ2018ዓ/ም የሴክተሩ የአጠቃላይ ተግባራት ዕቅድ ክንውን ና የመልካም አስተዳደር ቀርቦ በጥንካሬ በጉድለት በሉ ጉዳዮች ለይ ሰፋ የለ ውይይት ተደርጎዋል ።
በተጨማሪም የ2019ዓ/ም የሴክተሩ ዋና ዋና ዕቅዶችና ግቦች ለይ በዜጎች ቸርተር ለይ በአጠቃላይ በሴክተሩ በቀረቡ ሪፖርቶችና ዕቅዶች በጋራ በዝርዝር መወያየት ና የጋራ መግባባት ተደርሷ መድረኩ በሰለም ተጠናቋል ።

በሁልባራግ ወረዳ የገጠር ተደራሽ መንገድ ግንባታ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የወረዳው መንገድ ፅ/ቤት አስታወቀ።ሰኔ 16/2018 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴበስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ የገጠር ተ...
23/06/2026

በሁልባራግ ወረዳ የገጠር ተደራሽ መንገድ ግንባታ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የወረዳው መንገድ ፅ/ቤት አስታወቀ።

ሰኔ 16/2018 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ

በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ የገጠር ተደራሽ መንገድ ግንባታ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የወረዳው መንገድ ፅ/ቤት አስታወቋል።

የመንገድና ትራንንፖርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ እሸቱ ቢረጋ እንደገለፁት የመንገድ ግንባታ ስራው የገጠር አካባቢዎችን ከዋና መንገዶች ጋር በማገናኘት የህብረተሰቡን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ፣ የግብርና ምርቶችን ወደ ገበያ በቀላሉ ለማድረስ እንደሆነ በማንሳት የተሰሩ መንገዶችን ህብረተሰቡ እንዲጠብቃቸው አሳስበዋል።

የመንገድ ልማቱ የገጠር አካባቢዎችን ተደራሽነት በማሻሻል ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር የጠቆመው ፅ/ቤቱ በወረዳው በወራበት ቀበሌ ችሮ ጋፋት አካባቢ መገሮናን ከሻማ ማዘጋጃ የሚያገናኝ 5.3 ኪ.ሜ መንገድ 100% መጠናቀቁን ገልጿል።

በሁልባራግ ወረዳ በገጠር ተዳራሽ የህብረተሰብ ተሳትፎ የመንገድ ሥራ  ተጠናክሮ ቀጥሎዋል።        ሰኔ 15/10/2018ዓ/ም                 ኬረቴበወረዳችን በአንበርቾ ግንባ ቀበ...
22/06/2026

በሁልባራግ ወረዳ በገጠር ተዳራሽ የህብረተሰብ ተሳትፎ የመንገድ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሎዋል።
ሰኔ 15/10/2018ዓ/ም
ኬረቴ
በወረዳችን በአንበርቾ ግንባ ቀበሌ በህብረተሰብ ተሳትፎ የአበሱጆ ሜንቶ ጃዌ የሚያገናኝ መንገድ በወረዳው ማሽነሪዎች በመታገዝ ከ3ኪ/ሜትር በለይ መንገድ በአከባቢ በተመረጠ መቴሪያል/ቦሮ/የማልበስ/ዳንፕ የማድረግ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ።

የመሰረተ ልማቶች ቁንጮ የሆነውን መንገድ መስራት የእድገትና የትልቅነት ምልክት ነው ~~ የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ከድር አብደላ ሰኔ 08/2018 ዓ.ም ሁልባራግ ...
15/06/2026

የመሰረተ ልማቶች ቁንጮ የሆነውን መንገድ መስራት የእድገትና የትልቅነት ምልክት ነው ~~ የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ከድር አብደላ

ሰኔ 08/2018 ዓ.ም ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን - ኬራቴ

በስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ ደመቄና ቢለዋንጃ ቀበሌያት በክልሉ 17 ኪ.ሜ ኢኒሼቲቭ ከ14 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተሰሩ 03 መንገዶች በዛሬው እለት የዞን የወረዳና የቀበሌ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በይፋ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆኗል።

በመንገድ ምረቃው ወቅት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ መምሪያ ኃላፊ አቶ ከድር አብደላ የመሰረተ ልማቶች ቁንጮ የሆነውን መንገድ መስራት የእድገትና የትልቅነት ምልክት መሆኑን በማንሳት መንገድ የገበያ መዳረሻ በመሆኑ አርሶአደሩ ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ አቅርቦት ማምረት መቻል አለበት ብለዋል።

አቶ ከድር አያይዘውም መንገድ መስራት ብቻ ሳይሆን የተሰራውን መንገድ በአግባቡ ማስተዳደር ያስፈልጋል ብለዋል።

የሁልባራግ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽፋ ሀምዳላ በቢለዋንጃና በደመቄ ቀበሌዎች ተሰርተው የተጠናቀቁ 03 መንገዶችን (20.35 ኪሎ ሜትር) መርቀው አገልግሎት እንዲሰጥ ባስጀመሩበት ወቅት የመንገድ አላማው የነፍሰጡር እናቶችን ህይወት ከመታደግ ባለፈ ምርትን ወደ ገበያ ማውጫና መነገጃ መንገድ መሆን ይኖርበታል ያሉ ሲሆን ለዚህም የአርሶአደሩ ምርትና ምርታማነት ማደግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ዋና አስተዳዳሪው አክለውም መንገድን መስራት ብቻ ሳይሆን ተሰርተው የተጠናቀቁ መንገዶችን በጥንቃቄ ሳይበላሹና አደጋ ሳያስከትሉ መጠቀም እንደሚያስፈልግና መንግዶች ላይ የሚለቀቁ ውሃዎችን እንደ አይን ብሌን በመጠበቅና በመከላከል የመንገዶችን ደህንነት ማስጠበቅ ይገባል ብለዋል።

የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እሸቴ ብረጋ በበጀት አመቱ 17 ኪ/ሜ ኢኒሼቲቭ ታቅደው ከተሰሩ መንገዶች 1ኛ) ከጫቂፍ ሌፎ - ዱፈኔ - ቢለዋንጃ መንገድ 10.3 ኪ/ሜ፣ ከደመቄ ማእከል ሲዳሜ መንገድ 5.75 ኪ/ሜ፣ የሄሮ ቢለዋንጃ - ዲጆ መንገድ 4.3 ኪ/ሜ በአጠቃላይ 20.35 ኪ/ሜትር መንገድ ሰርቶ በማጠናቀቅ በዛሬው እለት ማስመረቅ መቻሉን ገልፀዋል።

አቶ እሸቴ ብረጋ በዛሬው እለት የምረቃ አካል በሆኑት በ3ቱም መንገድ ከ14 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበትና የበጀት ምንጩም አረብ ሀገር ካሉ የዲያስፖራ አካላት፣ በባለሀብቶችና በአከባቢው ማህበረሰብ ተሳትፎና የወረዳ ማሽነሪዎችን በመጠቀም የተሰራ የመንገድ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል።

ለመንገድ ፕሮጀክቱ መሳካት ከጅምር እስከ መጨረሻ ድረስ ሲያግዙና ሲያስተባብሩ ለነበሩ አካላት እንደወረዳ የተዘጋጀ የእውቅናና የሽልማት ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በቀበሌ ደረጃ በቢለዋንጃ በጫቂፍ ሌፎ ወጣቶች የተዘጋጀ የእውቅናና የምስጋና ፕሮግራምም ተካሄዷል።

በምረቃ ፕሮግራሙ የስልጤ ዞን ሴቶችና ህጻናት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ኸይሪያ ስርሞሎ፣ የሁልባራግ ወረዳ ምክርቤት አፈጉባዔ አቶ እንዳለ ፍቃዱ፣ የሁልባራግ ወረዳ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ሙላጎ ከይረድን እና ሌሎች የወረዳ አስተባባሪ አካላት፣ የስልጤ ዞን መንገድ መምሪያ ምክትል ሀላፊዎች አቶ ሙሰፋ ሸ/ነስሮ እና አቶ አዩብ ሙስጠፋ፣ የወረዳ አመራሮች፣ የቀበሌ አመራሮች የሶስቱም መንገድ ተጠቃሚ ህብረተሰብ፣ የሀገር ሽማግሌ፣ የሀይማኖት አባቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

Address

Kerate
Silt'e

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሁልባራግ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት- Hulbarege worda transport & road office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share